Back

ⓘ ኅብረተሰብ - ሱዳን, የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር, ዴሞክራሲ, ክሻትሪያ, የባቢሎን ግንብ, ሐረ ሼይጣን, ሥልጣኔ, ኅብረተሰብ, የባሕል ጥናት, ባሕል, የመረጃ ኅብረተሠብ, ሙአይ ኪባኪ ..
                                               

ሱዳን

ሱዳን በይፋ የሱዳን ሪፑብሊክ ከአፍሪካ በስፋት ሦስተኛ ስትሆን በአህጉሪቱ ሰሜናዊ ምስራቅ ክልል ትገኛለች። ዋና ከተማዋ ካርቱም ነው። ከግብፅ ፣ ከቀይ ባሕር ፣ ከኤርትራ ፣ ከኢትዮጵያ ፣ ከደቡብ ሱዳን፣ ከመካከለኛው የአፍሪካ ሪፑብሊክ ፣ ከቻድ ፣ እና ከሊቢያ ጋር ድንበር ትካለላለች። የአባይ ወንዝ ሀገሪቱዋን ወደ ምሥራቅና ምዕራብ ይከፍላል። የአረብ ባህል ደንበኛ ሲሆን አብዛኛው ሕብዝ የእስልምና ዕምነት ተከታይ ነው። ሱዳን ከግብፅ የተጣመረ ረዥም ታሪክ አላት። የመጀመሪያው የሱዳን እርስ በርስ ጦርነት ከ1955 እስከ 1972 እ.ኤ.አ. ከዚያም ሁለተኛው የሱዳን እርስ በርስ ጦርነት ከ1983 እስከ 2005 እ.ኤ.አ. ተከስቷል። በ1989 እ.ኤ.አ. በሰላማዊ መፈንቅለ መንግሥት ኦማር ሀሳን አህመድ አል-በሽር ሥልጣን ላይ የወጡ ሲሆን እራሳቸውን የሱዳን ፕሬዝዳንት ብለው ሾመዋል። የእርስ በርስ ጦርነቱ በሰላም ውል የቆመ ሲሆን ይህ ውል ያኔ የሀገሪቱዋ ደቡባዊ ክፍል ለነበረው ቦታ ራስን የመምራት መብት ሰጥቷል። በጃኑዋሪ 2011 እ.ኤ. ...

                                               

የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር

የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ፣ በጠላት ወረራ ዘመን የተመሠረተ ድርጅት ሲሆን፤ እስከ አሁን ድረስ ያሉት አዛውንት አባላቱ በዚያው የአምሥት ዓመት ትግል ዘመናት፣ መኳንንቱ፤ የጦር መሪዎቻቸውና ንጉሠ ነገሥቱም ጭምር እነዚያን ወጣት ኢትዮጵያውያን አንጀታቸውን ለረሀብ፤ እግራቸውን ለሾኽ ለጠጠር፤ ግንባራቸውን ለእርሳስ አጋልጠዋቸው በካዷቸው መራር ዘመን፤ ሞትም ቢመጣ እናት አገራችንን አሳልፈን ለጠላት አንሰጥም፤ ነፃነታችንን ለጊዜያዊ ሹመት፣ ሽልማት አንለውጥም ብለው የተጋፈጡ ጀግኖች ናቸው።

                                               

ዴሞክራሲ

ዴሞክራሲ በተጠነሰሰበት ጥንታዊት ግሪክ ፣ ሰዎች ይኖሩ የነበረበት መሠረታዊ የፖለቲካ አሃድ ዩኒት ፣ ከተማዊ መንግስት ይባላል። ይህ በአሁን ዘመን ካለው አገር ወይንም ብሔራዊ መንግስት ይለያል። ከተማዊ መንግስታት፣ ለምሳሌ አቴና እንደ ከተማ አስተዳደርነቱ ፣ በቆዳ ስፋት አንስተኛ ስለነበር የዘመኑ ዲሞክራሲ በቀጥተኛ ተሳትፎ በስብሰባ ላይ የተመሰረተ ነበር። ነገር ግን ይህ ዓይነት አሰራር ከ፲፯ኛው ክፍለ ዘመን በኋላ ለተነሱት በንፅፅር ግዙፍ ለሆኑት ብሔረ መንግስታት እማይቻል ስለነበር ማለት ከአገሪቱ ግዙፍ የቆዳ ስፋት አንጻር ሁሉን ዜጋ በየሳምንቱ ለስብሰባ መጥራት ስለማይቻል በእንግሊዝ አገር ፓርላማ የተባለ አዲስ ሥርዓት ተፈጠረ። ይህም ማለት ሕዝቡ ተወካዮቹን የፓርላማ ዓባላትን ይመርጣል፤ ተመራጮችም መንግሥትን ይመሠርታሉ። ይህ ዓይነት ሥርዓት ቀጥተኛ ያልሆነ ዴሞክራሲ በመባል ይታዎቃል። በአሁኑ ሰአት አብዛሃኛዎቹ የአለም ሃገራት የሚጠቀሙበት የመንግስት መዋቅር ነው።

                                               

ክሻትሪያ

ክሻትሪያ የህንዳውያን ኅብረተሠብ በተለያዩ 4 መደባት የሚከፋፈልበት አንዱ የህብረተሰባዊ ክፍል ነው። በዚህ አከፋፈል ዘዴ የወታደሮችና የገዢዎች ክፍል እሱ ነው። ክሻትሪያ ከብራህሚን በታችና ከቫይስያ እንዲሁም ከሹድራ በላይ ሆኖ ይቆጠራል። በመጀመርያ በጥንት ይህ ደረጃ በሰው ችሎታ፣ ተግባርና ጸባይ ምክንያት ሊገኝ የቻላ ሲሆን፣ በዘመናት ላይ ግን የተወረሰ ማዕረግ በዘር የሚዛወር ብቻ ሆነ። በአንዳንድ ወቅት ደግሞ የክሻትሪያ መኳንንት ክፍል ከብራህሚኖች ቄሳውንት ክፍል ይልቅ ላየኛነቱን ይይዝ ነበር። ብራህሚኖችም በኋላ የበለጡት ከትግል በኋላ እንደ ሆነ ይታመናል። የቃሉ ሥር በሕንዳዊ-ኢራናዊ ቋንቋዎች ቤተሠብ "*ክሺ" መግዛት ሲሆን ለዚሁ ብዙ የተዛመዱ ቃሎች እንደ ሳንስክሪት "ክሻትራ" ግዛት ይኖራሉ። በጥንታዊ ፋርስኛ በኩል "ሕሻጥራ" ማለት ሃይል፣ መንግሥት ነበረ፤ የ "ሕሻያጢያ" ትርጉም የፋርስ ንጉሠ ነገስት ሆኖ ከዚህ በዘመናዊ ፋርስኛ ንጉሥ ሻህ ይባላል። በአማርኛ፣ ቼዝ ሰንጠረዥ የሚባል ጨዋታ ስም ከዚህ የመጣ ነው። በተጨማሪ ...

                                               

የባቢሎን ግንብ

በመጽሐፍ ቅዱስ ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 11 ዘንድ፣ የባቢሎን ግንብ ሰማይን እንዲደርሱ የተባበሩት ሰው ልጆች የሠሩ ግንብ ነበር። ያ ዕቅድ እንዳይከናወንላቸው ለመከልከል፣ እግዚአብሔር እያንዳንዱ በተለየ ቋንቋ እንዲናገርበት ልሳናታቸውን አደባለቀ። መግባባት አልተቻላቸውምና ስራው ቆመ። ከዚያ በኋላ፣ ሕዝቦቹ ወደ ልዩ መሬት ክፍሎች ሄዱ። ይህ ታሪክ ብዙ የተለያዩ ዘሮችና ቋንቋዎች መኖሩን ለመግለጽ እንደሚጠቅም ይታስባል።

                                               

ሐረ ሼይጣን

ሐረ ሸይጣን ከአዲስ አበባ ወደ ደቡባዊው ኢትዮጵያ ክፍል ፻፵፫ ኪሎ ሜትር ከተጓዙ በኋላ የሚያገኙት ሐይቅ ሐረ ሸይጣን ይባላል፡፡ የሚገኘውም በደቡብ ክልል ስልጤ ዞን ርእሰ ከተማ ወራቤ በስተሰሜን አቅጣጫ ፴ ኪሎ ሜትር ተጉዘውም ያገኙታል፡፡ ሐይቁ ከኢትዮጵያ ተፈጥሯዊ የቱሪስት መስህቦች አንዱ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ የሐይቁ ይዘት አስገራሚ ሁኔታዎች አሉበት፡- ሐይቁ የሚገኘው ከመሬት ንጣፍ በታች ሲሆን፣ የተለያዩ ተፈጥሯዊ ሀብቶችና ገጽታዎች እንዲሁም ክስተቶችን የያዘ ሐይቅ ነው፡፡ በመሆኑም የገበቴ ቅርጽ ያለውን ሐይቅ ከጉድጓዱ አፋፍ አንስቶ ቁልቁል ውኃው እስካለበት ለመድረስ በአማካይ የ ፪፻፷ ሜትር ርቀት ጉዞ ይጠይቃል፡፡ በሌላ አገላለጽ ከአፋፉ እስከ ውኃው ያለው አምዳዊ ርቀት አማካይ ከፍታ ፻፱ ሜትር ነው፡፡ ከዳገቱ አፋፍ በመነሳት ድንጋይ ወርውሮ ለማስገባት ፪፻፴፯ ሜትር የጎንዮሽ የመወርወር አቅምን ይጠይቃል ማለት ነው፡፡ ድንጋይ ሲወረወር ወደ ውኃ የማይዘልቅበት ዋናው ምክንያት ለዚህ ሳይሆን አይቀርም፡፡ የሐረ ሸይጣን ሐይቅ የውኃ ...

                                               

ሥልጣኔ

ሥልጣኔ ማለት የሠለጠነ ባህል ወይም ኅብረተሠብ ነው። ይህም ምን ማለት እንደ ሆነ ለመግለጽ በታሪክ ልዩ ሀሣቦች ቀርበዋል። ባጠቃላይ የሠለጠነ ትርጉም በአማርኛ በጥበብ፣ በባለሙያነት ወይም በዕውቀት የተመጠነ የተለመደ ማለት ነው። የስልጣኔ ተቃራኒ አንትረቢ፣ አውሬነት ወይም ነውር ተብሏል። አልቤርት ሽቫይፀር በ1915 ዓም በጻፈው "የሥልጣኔ ፍልስፍና" ዘ ፊሎሶፊ ኦቭ ሲቪላይዜሽን፦ "በያንዳንዱ ሙያ፣ ከያንዳንዱም አስተያየት፣ በሰው ልጅ የተደረገው እርምጃ ሁሉ ድምር ነው፣ ድምሩ የእርምጃ ሁሉ እርምጃ ሆኖ ወደ ግለሠቡ መንፈሳዊ ፍጻሜ እስከሚረዳው ድረስ።" በማለት "ስልጣኔ" ን አስተርጒሟል። በአጭሩ፣ ወደ መንፈሳዊ ፍጻሜ የሚመራው የሰው ልጅ እርምጃ ሁሉ ድምሩ ሥልጣኔ ሊባል ይችላል። ላለፉት ጊዜዎች እርምጃ፣ ብዙ ጊዜ "ስልጣኔ" እንደ "ባህል" ወይም "ኅብረተሠብ" በመለዋወጥ ለማናቸውም ሊወከል ይችላል፤ ለምሳሌ "የማልታ-ቡረት ሥልጣኔ" በቅድመ ታሪክ በሳይቤሪያ ተገኘ፤ ወይም የማያ ሥልጣኔ ከ2000 ዓክልበ. እስከ 1690 ዓም ድረስ በ ...

ኅብረተሰብ
                                               

ኅብረተሰብ

ኅብረተሰብ ማለት በጠቅላላ የሰው ልጆች ማህበረሰቦችና ግንኙነቶች ወይም የአንዱ ማህበረሰብ መቧደኖች የሚገልጽ ቃል ነው። ቃሉ ከግዕዝ ሲሆን ትርጉሙ "የሰው" "ትብብር" ሊሆን ይችላል። অওঁ! ደግሞ ይዩ፦ የባሕል ጥናት π`♠"২২`

የባሕል ጥናት
                                               

የባሕል ጥናት

የባህል ጥናት ፣ ሥነ ኅብረተሠብ ወይን ሥነ ማኅበረሰብ ሌላ ስሙ ሶሲዮሎጂ የሰው ልጆች በቡድንና በተናጥል ያላቸውን ባሕል፣ ጠባይና አደረጃጀት የሚያጠና ክፍል ነው። በዚህም ውስጥ አንትሮፖሎጂ ወይም የሰው ልጅ ጥናት አለ። ሶሲዮሎጂ ፈረንሳይኛ፦ sociologie /ሶሲዮሎዢ/ የሚለው ቃል በፈረንሳያዊው ጸሐፊ ኤማኑወል-ዦሰፍ ሲዬ በ1772 ዓ.ም. ከሮማይስጥ socius /ሶኪውስ/ ባልንጀራ፣ ጓደኛ እና ከግሪክ λóγος /ሎጎስ/ ቃል ወይም ጥናት በማጋጠም ተፈጠረ። የፈረንሳይ ፈላስፋ ኦጉስት ኮምፕት ከ1830 ዓ.ም. ጀምሮ በሰፊ ጠቀመው። የኅብረተሰብ ጥናት ሲሆን የኅብረተሰብ ጽንሰ ሀሣብ በሮማይስጥ ትርጉም societas /ሶኪየታስ/ ወይም የባልንጀሮች ግንኙነት ያመልከታል።

ባሕል
                                               

ባሕል

ባሕል ማለት የሰው ልጅ ጥናት ውስጥ የአንድ ኅብረተሠብ አኑዋርኑዋር ነው። በዚህም ውስጥ "ባሕል" የኅብረተሠቡ ቋንቋ፣ ሥነ ጥበብ፣ ሥነ ጽሑፍ፣ ሙዚቃ፣ ጭፈራ፣ ሃይማኖት፣ ቴክኖሎጂ፣ አበሳሰል፣ አለባበስ፣ ስነ ሕንጻ፣ ሕግ፣ አስተያየት፣ ፍልስፍና፣ አፈ ታሪክ እና ብዙ ሌሎች ረገዶች ያጠቅልላል። የባሕል ጥናት ደግሞ "ሥነ ኅብረተሠብ" ወይም "ሥነ ማኅበረሰብ" ሌላ ስሙም "ሶሲዮሎጂ" ነው።

                                               

የመረጃ ኅብረተሠብ

የመረጃ ኅብረተሠብ ማለት ዘመናዊ የመረጃና የመገናኛ ቴክኖዎሎጂ አይነተኛ ሚና የሚጫወትበት ኅብረተሠብ ነው። በዚሁ ኅብረተሠብ ውስጥ በምጣኔ ሀብት ረገድ የተነገደው ሸቀጣሸቀጥ ወይም የሚዛወረው ዋና ጥቅም ተጨባጭ ዕቃ ሳይሆን የመረጃና ዕውቀት ማሠራጨት እራሱ ይሆናል። ብዙ ጊዜ የአሁኑ ዓለም "የመረጃ ኅብረተሠብ" ከ18ኛው ክፍለ ዘመን ጀመሮ የተካሔደው የኢንዱስትሪ አብዮት ተከታይ እንደ ሆነ ይቆጠራል።

ሙአይ ኪባኪ
                                               

ሙአይ ኪባኪ

ሙአይ ኪባኪ ከ2002 እ.ኤ.አ. እስከ 2013 እ.ኤ.አ. ድረስ 3ኛው የኬንያ ፕሬዚዳንት ነበሩ። ፕሬዚዳንት ከመሆናቸው በፊት ምክትል ፕሬዚዳንት ፣ የፋይናንስ ሚኒስትር ፣ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር እና የጤና ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል።