Back

ⓘ ፍልስፍና - የሳይንስ ፍልስፍና, ኅልውነት, ማኅበረሰባዊ ፍልስፍና, ፔሪፓቶስ, የፕላቶ አካዳሚ, ሌብኒትዝ, ዥን-ፖል ሳትራ, ለሴ ፈር, ሳትያግራሃ, በቂና አስፈላጊ, ነፍስ, የብርሃናት ክፍለ ዘመን, የኅሊና ነፃነት, የኅልውና ቀውስ, የኅልውና ድንጋጤ ..
                                               

የሳይንስ ፍልስፍና

የሳይንስ ፡ ፍልስፍና የሳይንስ መሠረቶችን ፣ ዘዴዎችን እና መዘዞችን በጥልቀት የሚያጠና የፍልስፍና ዘርፍ ነው። ሳይንስን ከሌሎች የ ዕውቀት ዓይነቶች የሚለየው ምንድን ነው? ምን ዓይነት ዕውቀት ሳይንስ ሊባል ይችላል? ምን ዓይነትስ አይባልም? የሳይንስ ጽንሰ ሓሳቦች የቱን ያክል አስተማማኝ ናቸው? የዚህ ሁሉ የሳይንስ ዕውቀት የመስተጨረሻ ግብ ምንድን ነው? የሰውን ህይወት ማሻሻል ነው? ወይንስ ስለከባቢ ዓለም ዕውነትን ለማዎቅ ነው? እነዚህ ጥያቄዎች የዚህ ፍልስፍና ዋና ትኩረት ናቸው። ተጨባጩን ዓለም ለመገንዘብ በተደረጉ ጥረቶች፣ ከጥንት ጀምሮ ብዙ ዓይነት ሐሳቦች ፈልቀዋል። እነዚህ ጥረቶች፣ በአንድ ወይም በሌላ ምክንያት ምናባዊን አለም፣ መናፍስትንና እና ሌሎች ተጨባጭ ያልሆኑ ነገሮችን ያሳተፉ ነበሩ። ሆኖም ቀስ በቀስ፣ አንዳንድ ፈላስፋዎች እነዚህ ለሽህ ዓመታት የተሰራባቸው ሐሳቦች ከባድ ስህተት እንዳለባቸው ፤ ይባስ ብሎም ለቀጣይ የመሻሻል እርምጃ እንቅፋት እንደሆኑ ማሳዎቅ ጀመሩ። ይህ የተጠራቀመ ትችትና ቅሬታ በአውሮጳ የሳይን ...

                                               

ኅልውነት

አብዛኞች ሃይማኖቶችና ፍልስፍናወች የሰው ልጅ ኅይወት ትርጉም አለው ብለው ያምናሉ። ስለሆነም ይህን አላማ ወይም ለማስፈጸም ወይም ደግሞ ለማግኘት ሲጥሩ ይታያሉ። ከዚህ በተጻራሪ በ ኅልውነት ፍልስፍና የሰው ልጅ ህይወት ከመፈጠሩ በፊት የተጻፈ ትርጉምም ሆነ አላማ የለውም። ስለሆነም የፍልስፍና አትኩሮት መሆን ያለበት "እያንዳንዱ ግለሰብ ለህይወቱ እንዴት ትርጉምና አላማ መስጠት አለበት?" የሚል ነው። የኅልውነት ፍልስፍና አባት ነው የሚባለው ሶረን ኬርከጋርድ እንዳስቀመጠው "እያንዳንዱ ግለሰብ ለህይወቱ ትርጉም የመስጠት እንዲሁም ይህን ህይወቱን በሃቀኝነትና በሙሉ ስሜት የመምራት ኃላፊነት አለበት።" ይህ ሲሆን ታዲያ ተስፋ መቁረጥ፣ የኅልውና ድንጋጤ፣ ባይተዋርነት፣ ድብርትና መሰረተ ቢስነት የተባሉ የኅልውና ቀውሶች የሰውን ልጅ ይጋረጣሉ፣ እኒህን እንቅፋቶችን የማሸነፍ ዘዴ መቀየስ የኅልውነት ፍልስፍና አይነተኛ አትኩሮት ነው። የሰው ልጅ ህይወት ትርጉም የለሽና አላማውም የማይታወቅ ሲሆን ትርጉም አለው እምንለው እያንዳንዱ ግለሰብ ለህይወ ...

                                               

ማኅበረሰባዊ ፍልስፍና

ማኅበረሰባዊ ፍልስፍና በሰው ልጅን ማኅበራዊ ባህርይ ላይ የሚመራመር የፍልስፍና ዘርፍ ነው። የማሕበራዊ ማንነት፣ የፖለቲካዊ ሥነ ምግባር፣ የተለያዩ ር ዕዮተ ዓለሞችን፣ የሚዎጡ ኅግጋት ፍትሃዊነትን፣ የሥነ ልቡናን ፍልስፍናዊ መሰረቶች፣ እና መሰል የቡድን ጠባያትን የሚያጠና ክፍል ነው። በዚህ የ ዕውቀት ሥር ከሚካለሉ ውስጥ፣ ማኅበራዊ ሥነ ኑባሬ እና ማኅበራዊ ሥነ ዕውቀት እንደ ቅርንጫፍ ሊዎሰዱ ይችላሉ። በማኅበራዊ ሥነ ኑባሬ "ማኅረሰቦች ኑባሬ አላቸውን? አንድ ማኅበረሰብ አለ ከተባለ፣ በውስጡ ካሉት አባላት ግለሰቦች ይለያል? ከተለየስ በምን ዓይነት ሁኔታ?" የሚሉት ጥያቄዎች ይመረመራሉ። በማኅበራዊ ሥነ ዕውቀት "የአንድ ግለሰብ ዕውቀት በማኅበረሰቡ የቱን ያክል ጫና ይደረግበታል? ማኅበራዊ ተቋማት በአንድ ግለሰብና በአጠቃላይ ማኅብረሰቡ ዕውቀትና እምነት ላይ ምን አስተዋጽዖ ያደርልጋሉ?" የሚሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ይሞክራል። ስለሆነም ይህ የፍልስፍና ዘርፍ ከፖለቲካ እና ሥነ ባሕል ጥናቶች ጋር ተነባባሪ ክፍሎች አሉት።

                                               

ፔሪፓቶስ

ፔሪፓቶስ በአቴና፣ ግሪክ አገር በአሪስጣጣሊስ የተመሠረተ ጥንታዊ የከፍተኛ ትምህርት ቤት ተቋም ነበር። ከ343 እስከ 94 ዓክልበ. ድረስ ቆየ። መገናኛ ቦታው በአረመኔ ጣኦት በአፖሎ ቤተ መቅደስ ሊሲየም ነበረ። አሪስጣጣሊስ ከ375 እስከ 355 ዓክልበ. በፕላቶ አካዳሚ አባል ነበረ፣ ከዚያ የራሱን ትምህርት ቤት በሊሲየም ጀመረ። እንደ ዘመናዊ ትምህርት ቤት አስተማሪና ተማሮች ተለይተው ሳይሆን፣ እንደ አካዳሚ ግን ከፍተኛ እና ታቸኛ አባላት ነበሩ። ትምህርቱ በጥያቄና መልስ ይካሄድ ነበር። በተቋሙ ውስጥ ከተማሩት ጥናቶች መካከል በተለይ ፍልስፍና፣ የተፈጥሮ ሕግጋት ጥናትና ሌላ የታወቀ ሳይንስ ዕውቀት ነበሩ። አሪስጣጣሊስ በ330 አክልበ. አረፈና እስከ 296 ዓክልበ. ድረስ የነበሩት አስተዳዳሪዎች ከአሪስጣጣሊስ ፍልስፍና በላይ ምንም ይፋዊ ርዕዮተ አለም አላስተማሩም። ይህም ማናቸውንም ፍልስፍና ወይም ዕውቀት ለመሰብሰብ ነበረ። በ296-277 ዓክልበ. የተቋሙ ሦስተኛ መሪ የሆነው ስትራቶ ዘላምፕሳኮስ ያስተማረው ርዕዮተ አለም የአምላክ ሚና ...

                                               

የፕላቶ አካዳሚ

የፕላቶ አካዳሚ በአቴና፣ ግሪክ አገር በፕላቶ የተመሠረተ ጥንታዊ የከፍተኛ ትምህርት ቤት ተቋም ነበር። ከ395 እስከ 94 ዓክልበ. እና እንደገና ከ402-521 ዓም ቆየ። ቦታው በአቴና ከተማ በቅዱስ የወይራ ደን አጠገብ ነበረ። ግሪካዊ ፈላስፎች በፕላቶ መኖሪያ ይሰብስቡ ጀመር። እንደ ዘመናዊ ትምህርት ቤት አስተማሪና ተማሮች ተለይተው ሳይሆን፣ ከፍተኛ እና ታቸኛ አባላት ነበሩ። ሴቶች አባላትም ነበሩ። ትምህርቱ በጥያቄና መልስ ይካሄድ ነበር። በተቋሙ ውስጥ ከተማሩት ጥናቶች መካከል በተለይ ፍልስፍና፣ ሥነ ቁጥር፣ ሥነ ፈለክ ነበሩ። በመግቢያ ላይ "ከጂዎሜትሪ ተመራማሪዎች በቀር ማንም አይግባ" የሚል መፈክር እንደ ተለጠፈ ተብሏል። አሪስጣጣሊስ ከ375 እስከ 355 ዓክልበ. በዚያ አባል ነበረ፣ ከዚያ የራሱን ትምህርት ቤት ፔሪፓቶስን በሊሲየም ጀመረ። ፕላቶ በ355 አክልበ. አረፈና እስከ 274 ዓክልበ. ድረስ የነበሩት አስተዳዳሪዎች ከፕላቶ ፍልስፍና በላይ ምንም ይፋዊ ርዕዮተ አለም አላስተማሩም። በ274 ዓክልበ. አርቄሲላዎስ ዋና አስተ ...

                                               

ሌብኒትዝ

ጎትፍሪድ ቪልሄልም ሌብኒትዝ 1646 – November 14 1716 እ.ኤ.አ) የ17ኛው ክፍለ ዘመን የጀርመን የሒሳብ ሊቅ፣ ሳይንቲስት፣ ፈላስፋ፣ ፍርድ አጥኝና ባጠቃላይ መልኩ ሁለ ገብ ተመራማሪ ነበር። ሌብኒዝ ከኢሳቅ ኒውተን ትይዩ ካልኩለስ የተባለውን የዕውቀት ዘርፍ ፈጥሯል። አሁን ድረስ ተማሪወች የሚጠቀሙበት የካልኩለስ የአጻጻፍ ስልት በዚህ ሰው የተፈለሰፈ ነው። ለኮምፒዩተር ስራ እጅግ ወሳኝ የሆነውን የሁለትዮሽ ቁጥር ስርዓት ዘመናዊ ኮምፒዩተሮች ከመሰራታቸው 300 አመት በፊት ፈልስፏል። በፍልስፍናው ዘርፍም ጠለቅ ያለ አስተዋጽኦ አበርክቷል። የሌብኒዝ ፍልስፍና እንደ ደካርት ፍልስፍና ቀልበኛ ይባላል። "ይህ ዓለም እግዚአብሔር ሊፈጥራቸው ይችላቸው ከነበሩ ዓለማት ሁሉ የተሻለ" ነው የሚለው ድምዳሜው የሌብኒዝን ፍልስፍና ብሩህ ተስፈኛ በሚባል መደብ ስር እንዲታወቅ አድርጎታል። የሌብኒዝ ፍልስፍና የቀደምት አውሮጳውያን የፍልስፍና ዘዴ ተብሎ የሚታወቀውን ስኮላስቲክ ወደ ኋላ የሚመለከትና ወደፊት ደግሞ በ20ኛው ክ/ዘመን ብቅ ያሉን ዘ ...

                                               

ዥን-ፖል ሳትራ

ሳትራ ፓሪስ ፈረንሳይ ሲወለድ፣ እዚያው ተምሮ 1928ዓ.ም. ላይ ከዩኒቨርሲቲ በፍልስፍና ዶክትሬት ተመርቋል። ቀጥሎም ለ2 አመት የፈረንሳይን ጦር ተደባልቆ በውትድርና አገልግሏል። በ1938 በደረሰው ልቦለድ፣ ሳትራ የኅልውነትን ፍልስፍና ነጥቦች በሚያሳይ መልኩ ስለ ሰው ልጅ ነጻነት ዘግቧል። በ1939 ሳትራ የፈረንሳይን ሰራዊት ተቀላቅሎ የጀርመንን ናዚ ሰራዊት ሲዋጋ በ1940 ዓ.፣ም. ተማረከ። ለሚቀጥሉት 9 ወራት በእስር አሳለፈ። ከእስር ከተለቀቀ በኋላ በአስተማሪነት ስራው ቀጠለ። በ1943 ኅልውነትና ምንምነት የተሰኘውን መጽሐፉን አሳተመ። በመጽሐፉ የሰው ልጆች ለሚኖሩበት አገር ወይንም ማህበረሰብ ደንቦች በጣም ተገዥ ከሆኑ፣ የራሳቸውን ውሳኔ ማሳለፍ ያቅታቸዋል የሚል ነጥብን ለአንባቢወቹ ለማሳየት ይሞክራል። በ1945 ዘመናዊ ጊዜ የተሰኘውን ጋዜጣ በማቋቋም ስለ ፖለቲካ፣ ኪነት እና ሥነ ፅሑፍ ብዙ ጽሑፎችን ያቀርብ ነበር። በ1946 ኅልውነት ሰውነት ነው የተሰኘውን መጽሐፉን በማሳተም የኅልውነትን ፍልስፍና ለማብራራት ሞክሯል። ኅልውነ ...

                                               

ለሴ ፈር

ለሴ ፈር ማለት ባለሥልጣናት በግለሠቦች መገበያየት ጥልቅ ሳይገቡ ቀርተው የሚታገሡበት የምጣኔ ሀብት ዘዴ ነው። በፈረንሳይኛ ዘይቤው "ለሴ ፈር" ከ1671 ዓም ጀምሮ እንዲታወቅ ይታመናል። ፍልስፍናው ከፈረንሳይ ይልቅ በታላቁ ብሪታን እንዲሁም በአውሮፓና በአሜሪካ ውስጥ ዘመናዊ ሆነ። በጥንቱ ቻይና ደግሞ ተመሳሳይ የአገዛዝ ፍልስፍና "ዉ ወይ" "ያለመሥራት" ይታወቅ ነበር። በለሴ ፈር ምክንያት የአውሮፓና የአሜሪካ ምጣኔ ሀብትና ንግድ ድርጅቶች ሊያብቡ እንደ ቻሉ፣ በፋብሪካ አብዮት በኩል ኑሮ ዘዴ እንዲለወጥና እንዲቀለል፣ አዳዲስ መጓጓዣና መገናኛ ፈጠራዎች እንዲገኙ ያስቻለው ሁሉ ይታመናል። የፈጠራዎች ታሪክ ስንመለከት፣ ከ200 ዓክልበ. እስከ 1200 ዓም ያህል አብዛኞቹ አዳዲስ ፈጠራዎች የተደረጁ ከቻይና ነበረ፤ ወይም እስከ ሞንጎሎች ግዛት ድረስ። እንዲሁም ከ1500 እስከ 1940 ዓም ያሕል አብዛኞቹ አዳዲስ ፈጠራዎች የተደረጁ በምዕራባውያን አለም ነበረ። በተቀራኒ በጀርመን ፈላስፋ ካርል ማርክስ ፍልስፍና ዘንድ ማንም ሕዝብ እንዳይበልጽ ...

                                               

ሳትያግራሃ

ሳትያግራሃ ማለት ማህተማ ጋንዲ የጀመሩት የሰላማዊ መቃወም ዘዴ ነው። ጋንዲ በሕንድ ነጻነት እንቅስቃሴ እንዲሁም ከዚህ ቀድሞ በደቡብ አፍሪካ ትግል ይጠቀማቸው ነበር። ከዚህ በላይ የሳትያግራሃ ፍሬ ሂሳብ ለኔልሰን ማንዴላ፣ ለማርቲን ሉተር ኪንግና ለሌሎች ትግል መሪዎች ከፍተኛ ተጽእኖ አሳድሯል። ሳትያግራሃ የሚፈጽመው ሰው ሳትያግራሂ ይባላል።

                                               

በቂና አስፈላጊ

በስነ አምክንዮ "በቂ" እና "አስፈላጊ" የሚሉት ቃላቶች በጣም የጠራ ትጓሜና አጠቃቀም አላቸው። ṾưựưḀḀḀḀ’ ₵¤v‰”ℳm³m³m³m³m³== አስፈላጊ ሁኔታ == መጀመሪያ ምሳሌዎችን እንይ፡rterg ለማየት አይን አስፈላጊ ነው -- 575676645ሲተረጎም፣ ለማየት የአይን መኖር መሟላት አለበት። በሌላ አነጋገር አይን ከሌለ ማየት አይቻልም። አባት ለመሆን ወንደ መሆኑ አስፈ45ty456ላtፋል፡ r> P), ትርጉሙም P የ"Q መዘዝ ነው ማለት ነው። ወይም በሌላ አነጋገር Q እውን ሲሆን Pን ያመላክታል ማለት ነው። ምሳሌ፡ እይታ => አይን መኖር ፤ እይታ መፈጠሩ አይን መኖርን ያመላክታል። ወይም ደግሞ አይን መኖር የእይታ መዘዝ ነው። yt5ytert34trm45tmewmtmrymrtmum56y4576ʶ645

                                               

ነፍስ

ነፍስ የአንድ ሰው ምንነት ማለት ሲሆን በብዙ ሃይማኖቶች ዘንድ ይህ ምንነት አንድ ሰው ከሞተ በኋላ እንኳ የማይጠፋ ነው። ስለሆነም ነፍስ ከአዕምሮ ጋር በብዙ ፍልስፍናዎችና ሃይማኖቶች ዘንድ የተቆራኙ ናቸው። ነፍስና መንፈስ በተለምዶ አንድ ተደርገው ቢታዩም ሁለቱ ይለያያሉ። ነፍስ፣ የአንድ ሰው ምንነት እንደመሆኑ መጠን የራሱ የሆነ መለያ ጠባዮች አሉት ስለሆነም ከሌሎች ነፍሶች ጋር አንድ ላይ ሆኖ ሊቀናጅ አይችልም። መንፈስ ባንጻሩ አለም አቀፍ እንደመሆኑ መጠን ብዙ ነፍሶች የሚጋሩት ነው። ነፍስ ከ "እኔነት" ጋር ምንም ልዩነት የለውም። አንድ ሰው "እኔ ህልው ነኝ" ወይም "በርግጥ እኔ አለሁ" ሲል "እኔ" የሚለው ቃል የሰውየውን ነፍስ ያጠቅሳል። አንድ ሰው ህልው መሆኑን ማረጋገጥ የሚችለው ለነፍሱ ብቻና ለነፍሱ ብቻ ስለሆነ ሰውነቱ የነፍሱ ንብረት እንጂ ነፍሱ እራሱ አይደለም። ይህ አስተሳሰብ ቀልበኝነት የሚባል ፍልስፍና አካል ነው። ደግሞ ይዩ፦ ደመነፍስ

                                               

የብርሃናት ክፍለ ዘመን

የብርሃናት ክፍለ ዘመን በተለይ በ18ኛው ክፍለ ዘመን የተከሠተው፣ ከ17ኛው ክፍለ ዘመን "ሳይንሳዊ አብዮት" የተከተለ የዘመናዊ ፍልስፍና እንቅስቃሴ ነበረ። "የፍልስፍና ክፍለ ዘመን" ወይም "የምክንያት ዘመን" ተብሏል። እንቅስቃሴው የተጀመረው በፈረንሳይ ሲሆን፣ በተለምዶ ከ1707 እስከ 1781 ዓም ድረስ እንደ ቆየ ይቆጥሩታል። ከፈረንሳይ የ "ማብራራት" ሀሣቦች በተለይ ወደ እስፓንያ፣ ጀርመን፣ ፖላንድ፣ ሩስያ፣ ግሪክ፣ ስኮትላንድና አሜሪካ ተስፋፉ። በሌሎች አገራት ግን ለምሳሌ በእንግላንድ ወይም በጣልያን፣ "ማብራራቱ" አነስተኛ ሚና አጫወተ። በዚህ ወቅት ዘመናዊ ከነበሩት ሃሣቦች መሃል፦ የሳይንስ ፍልስፍና ሃይማኖታዊ መታገሥ ዴሞክራሲ ጥቅማዊነት ብሔራዊ መብቶች ለሴ ፈር እኩላዊነት ምክኑያዊነት እንዲሁም በዚህ ወቅት የምጣኔ ሀብት፣ የሕገ መንግሥት፣ የአርነት፣ የትምህርት ፍልስፍናዎች እየተደረጁ ነበር። መደበኛ የክርክር ማህበር ሥርዓትና ቡና ቤት ቡና የሚጠጣበት ሰዎችም የሚወያዩበት ዘመናዊ ሆኑ። እንዲሁም የንጉሥ ወይም የፓፓ ሥልጣና ...

                                               

የኅሊና ነፃነት

የኅሊና ነጻነት ለሰዎች ለመከልከል ቢሞከር ኖሮ ይህ የሰው ልጆች መሠረታዊ መብት ሰው ለራሱ ለማሰብ እንደ መከልከል ይቆጠራል። የኅሊና ነጻነት ፍሬ ነገር እያንዳንዱ ግለሠብ ለራሱ የቱን እምነት ለመምረጥ ስለሚሰጥ፣ የሃይማኖት ነጻነት ጽንሰ ሐሳብ ከዚህ ጋር ተያይዟል። በአንዳንድ ህብረተሠብ ወይም መንግሥት በተግባር የሃይማኖት ነጻነት ወይም የእምነት ነጻነት ባይከበርም፣ በሌሎች ህብረተሠብ ወይም ሕገ መንግሥታት ግን በተለይ በምእራቡ አለም ይህ ነጻነት በታሪክ እጅግ ተከብሯል። ለምሳሌ በአሜሪካ ሕገ መንግሥት 1ኛ ማሻሻያ አንቀጽ መሠረት ሃይማኖት ወይም ንግግር የሚከለክል ሕግ እንደማይጸና ይረጋገጣል። ዛሬ በአለም ዙሪያ ደግሞ አብዛኛው ሕገ መንግሥታት የእምነት ነጻነት የሚያረጋግጡ ናቸው። በ1948 ዓ.ም. በኢትዮጵያ የወጣ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 40 አባባል እንዲህ ነው፦ "የሕዝቡን መልካም ጠባይ ወይም ፀጥታን ወይም በፖለቲካ ረገድ የሚያውክ ካልሆነ በቀር በንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት ግዛት የሚኖሩ ሰዎች በሕግ መሠረት የሃይማኖታቸውን ሥርዓት ...

                                               

የኅልውና ቀውስ

የኅልውና ቀውስ የምንለው አንድ ግለሰብ በህይወት ጎዳናው ላይ በድንገት ቆም ብሎ በአጠቃላይ የህይወቱ መሰረቶች ላይ ጥያቄ ሲያቀርብ ነው፡- ለምሳሌ ህይወቴ ትርጉም፣ ዋጋ ወይም አላማ አለው ወይ?" ብሎ ሲጠይቅ። ይህ ጉዳይ በኅልውነት ፍልስፍና ከፍተኛ ቦት ተሰጥቶት የሚጠና ነው። የኅልውና ቀውስ ብዙ ጊዜ የሚነሳው ባንድ ግለሰብ ህይወት ውስጥ ክፍተኛ ግምት የሚሰጣቸው ክንውኖች ሲፈጸሙ ነው፣ ለምሳሌ ያልን እንደሆን በአለም ውስጥ ብቻየን ነኝ ብሎ ከማሰብ አንድ ሰው ሙሉ ነጻነት እንዳለው ሲረዳ፣ ሃላፊነቱንም በዛው ልክ ሲቀበል ወይም ሲክድ አንድ ግለሰብ በርግጥም መሞቱ የማይቀር መሆኑን በርግጥ ሲረዳ በጋብቻ ወቀት፣ በፍቺ፣ መለያየት፣ የሚወዱት ሰው መሞት፣ አዲስ ፍቅረኛ፣ ልጆች አድገው ቤት ሲለቁ፣ 30 ወይም 40 ዓመት ሲሞላ፣ ወዘተ. እጅግ አስደሳች ወይም እጅግ ጎጂ የሆነ ጉዳይ በግለሰብ ላይ ሲደርስ አንድ ሰው ህይወቱ ትርጉም ሆነ አላማ እንደሌለው ሲገነዘብ እንግዲህ ይህን ቀውስ ከሌሎች ለየት የሚያደርገው ጉዳይ አለ። አንድ ግለሰብ የ ...

                                               

የኅልውና ድንጋጤ

የኅልውና ድንጋጤ በኅልውነት ፍልስፍና እያንዳንዱ ግለሰብ ባለው የኅልውና ነጻነት ምክንያት የሚሰማው መሰረታዊ የመንፈስ አለመረጋጋት ነው። ለምሳሌ አንድ ሰው ከገደል ጫፍ ላይ ቢቆም ሁለት ድንጋጤወች ይጋፈጡታል፣ አንደኛው "ወድቄ ብከሰከስስ" የሚል ሲሆን ሁለተኛውና ለምንነጋገርበት ርዕስ ጠቃሚ የሆነው ደግሞ "ምናልባት እራሴን ብወረውርስ" የሚል ፍርሃቻ ናቸው ። በዚህ አጣብቂኝ ግለሰቡ "ምንም የሚይዘኝ ነገር የለም" ወይም ደግም "በተፈጥሮየ እራሴን እንዳልወረውር የሚጠብቀኝ እንዲሁ በተቃራኒው እራሴን እንድወረወር የሚገፋፋኝ እድል እጣ ፈንታ የለኝም፣ ሁለቱም እራሴ በማደርገው ምርጫ የሚወሰን ነው" የሚለውን መሰረታዊ የሰው ልጅ ነጻነት ይረዳል። ይህ የመመረጥ ሙሉ ነጻነትና የሚያስከተለው ሙሉ ሃላፊነት በሰው ልጅ ላይ ድንጋጤን ይፈጥራል። የኅልውና ድንጋጤ እንደሌሎች የፍራቻ አይነቶች ሳይሆን አብሮ ከሰው ልጅ ሙሉ የመምረጥ ነጻነት ጋር ምንጊዜም የሚገኝ ነው።

                                               

የዞራስተር ፍካሬ

የዞራስተር ፍካሬ: ወደ ሁሉምና ወደ ማንም በፍሬድሪች ዊልሄልም ኒሺ የተደረሰ የፍልስፍና ልቦለድ* ነው። መጽሐፉ በ1883 እና 1885 መካከል በ4 ክፍል የተደረሰ ሲሆን በጊዜው ይሰራበት ከነበረው የአስተሳሰብ ዘዴ ለየት ባለ መልኩ የፍልስፍናን እና የግብረገብን ጥናቶች መርምሯል። የመጽሃፉ አትኩሮቶች፡- የዘላለማዊ ምልልስ፣ ኃይልን መፍቀድ ፣ የአምላክ በጊዜው በነበሩ አውሮጳውያን ልብ ውስጥ መሞት፣ ስለዚህም የአዳዲስ ዋጋ ወይም ህግጋት አስፈላጊነት፣የበላይ ሰው መምጣት ትምህርቶች ነበሩ። ጽሁፉ የመጽሐፍ ቅዱስ አጻጻፍ ስልት ይከተል እንጂ የውስጡ ፍሬ ነገር ግን የክርስትናና አይሁድ ሃይማኖቶችን መሰረታዊ እምነቶች የሚጻረር ነበር። ኒሺ ይህን መጽሐፍ ከሰዎችና ከጊዜ 6000 ጫማ" እርቆ እንደጻፈ ይናገራል፣ ማለቱም የመጽሃፉን ሃሳቦች በተራራ ላይ እያለ እንዳገኛቸው ለማስገንዘብ ነበር። ኒሺ "የዞራስተር ፍካሬ" ብሎ የሰየመውን መጽሃፍ "ስርዓት አልባ"ጥራዝ ነጠቅ በሆነ ዘዴ ስለጻፈው ለተመራማሪወች እጅግ አስቸጋሪ ሆነ። ይሁንና ተመራማሪወች ...

                                               

የፕላቶ ሪፐብሊክ

የፕላቶ ሪፐብሊክ በፈላስፋው ፕላቶ ፣ በ390 ዓ.ዓ. የተጻፈ የፍልስፍና መጽሐፍ ሲሆን የሚያተኩረውም የፍትሕን ጽንሰ ሐሳብ በመተርጎምና የ ፍትሐዊ አገር እና ፍትሐዊ ሰው ባህሪዮች ምን ይመስላሉ የሚለውን ጥያቄ በመመለስ ነው። በዚህ ታዋቂ መጽሐፍ ውስጥ ፕላቶ ሁለት ጥያቄዎችን ያነሳል፣ እነርሱም "ሰዎች ለምን ሰናይ ጥሩ ነገር መስራት አለባቸው?" የሚልና "ሰዎች ዕኩይ መጥፎ ነገርን ቢሰሩ ሽልማት ያገኙበታል ወይ?" የሚሉ ናቸው። ፕላቶ ሲመልስ፣ ሰዎች መጥፎ ነገርን መስራት የለባቸውም ምክንያቱም መጥፎ ነገር በሰሩ ቁጥር ደስተኛ የመሆናቼው መጠን ይቀንሳል። በተቃራኒው ጥሩ የሚሰሩ ሰዎች ደስተኛ ይሆናሉ። በተመሳሳይ ሁኔታ፣ ዕኩይ ሰዎች የአንድ ማህብረሰብ ባለስልጣኖች በሆኑ ጊዜ ያ ህብረተሰብ ደስተኛ እንዳይሆን ያደርጋል። በፕላቶ አስተያየት፣ በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ ሰናይ ምግባርን ሊከውኑ የሚችሉ ፈላስፎች ናቸው። ስለሆነም ደስተኛ ለመሆን ይሚፈልግ ህብረተሰብ ባለስልጣኖቹ ፈላስፎች መሆን አለባቸው ይላል። ፈላስፋ ያልሆኑ የህብረተሰብ ክ ...

                                               

ዳው ዴ ጂንግ

ዳው ዴ ጂንግ በ540 ዓክልበ. ገደማ በቻይናው ፈላስፋ ላው ድዙ የተጻፈ የእምነትና የፍልስፍና ጽሑፍ ነው። ይህ መጽሐፍ የዳዊስም ሃይማኖት መሠረት ሆኗል። የጽሑፉ መጀመርያ ዓረፍተ ነገሮች በተለይ ዝነኛ ናቸው፦ 道可道,非恆道;名可名,非恆名。 በጥንታዊ ቻይንኛ እንደሚታሰብ፦ "ክሉሕ ኻሕ ሉሕ ፑዊ ገንግ ክሉሕ። መንግ ኻሕ መንግ ፑዊ ገንግ መንግ።" ትርጉም፦ "የዘላለሙ መንገድ ሊነገር የሚችል መንገድ አይደለም። የዘላለሙ ስም ሊሰየም የሚችል ስም አይደለም።" በፑቶንግኋ ዘመናዊ ቻይንኛ፦ "ዳው ኬ ዳው ፈይቻንግ ዳው። ሚንግ ኬ ሚንግ ፈይቻንግ ሚንግ።" በተረፈ የጽሑፉ ሌላ ታዋቂ ፍሬ ነገር ምዕራፍ 67 እንዲህ ይላል፦ "ሦስት ውድ ሀብቶች በውስጤ ምንጊዜም አሉኝ። መጀመርያው ምኅረት፣ ሁለተኛው ቁጠባ፣ ሦስተኛውም የዓለም ቀዳሚ ለመሆን አለመድፈር ትሕትና።" ተመሳሳይ ትምህርት አስቀድሞ ለእስራኤል ነቢይ ሚክያስ 700 ዓክልበ. ግድም በትንቢተ ሚክያስ 6:8 ተሰጠ፤ "እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድ ...

                                               

ዳያሌክቲክ

ዳያሌክቲክ በፍልስፍና ውስጥ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠው ያስተሳሰብ አይነት ነው። ይህ ዘዴ በጥንቱ ግሪክ ሲሰራበት ቆይቶ በፈላስፋው ፕላቶ ለፅሁፍ በቅቷል። መሰረቱም፣ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የተለያዩ አስተያየት ያላቸው ሰወች እርስ በርሳቸው በመነጋገር ለመተማመን ከሚያደርጉት ጥረት የሚነሳ ነው። ይህ ከሬቶሪክ ይለያል፤ ምክንያቱም በሬቶሪክ አንድ ግለሰብ ብቻ ብዙ ጊዜ የወሰደ ንግግር በማድረግ የራሱን ሃሳብ ለሌሎች ማሳመኛነት ሲያቀርብ ስለሆነ ነው። እንግዲህ በዘመናት ሂደት የተለያዩ አይነት ዲያሌክቲ ዘዴወች ተነስተዋል። ከብዙ በጥቂቱ የማርክስ፣ ሄግል፣ ፕላቶ፣ ሶቅራጥስና የህንዶቹን ፍልስፍናወች ይጠቀልላል።

                                               

ጥቅማዊነት

ጥቅማዊነት በፍልስፍና ስለ ድርጊት ትክክለኛነት የሚሰፍን ግብረ-ገባዊ ኅልዮ ነው። ከሁሉ የሚሻለው ድርጊት ለአብዛኛዎቹ ደስታ ወይም ጥቅም የሚያመጣው ያው ነው የሚለው ፍልስፍና ነው። ጽንሰ ሃሣቡ በግሪኩ ፈላስፋ በኤጲቁሮስ ጽሑፍ ይገኛል። መርኁ ከጥንት ጀምሮ ቢታወቅም፣ በቅርቡ ዘመን ስለ ጥቅማዊነት በተለይ የጻፉት ፈላስፎች እንግሊዞች ጄርሚ ቤንታም እና ጆን ስቱዋርት ሚል ነበሩ። ቤንታም እንደ ጻፈው የተሻለው ሥራ ለብዛቱ በጎ የሚሆነው ነው። በሱ ፍልስፍና አስተያየት ሰዎች ሁሉ ለ2 ጌቶች እነርሱም ለደስታና ለሀዘን ሲገዙ ይኖራሉ። ስለዚህ ለሰዎች በጎ የሆነ ሥራ ማለት ደስታን ማምጣትና ማብዛት እንደ ሆነ ገመተ። አንዱ ድርጊት ለጥቂቶች ደስ ቢያስን፣ ሁለተኛውም ለብዙዎች ደስ ቢያሰኝ፣ ሁለተኛው ይመረጣል ማለት ነው። ወይም እንደገና አንዱ ድርጊት ለ10 ሰዎች፣ ሁለተኛውም ለ5 ሰዎች ብቻ ደስታ ወይም ጥቅም ካመጣ፣ መጀመርያው የበለጠው ግብረገብ ነው ብሎአል። የቤንታም ደቀ መዝሙር ጆን ስቱዋርት ሚል ዩቲሊቴሪያኒዝም በሚል መጽሐፍ ለፍልስፍ ...

                                               

ፈቃድ

ፈቃድ ማለት ከአንድ ሰው ውስጣዊ ግፊት የሚመነጭ ድርጊት ነው። ውስጣዊ ግፊት ማለት ግለሰቡ በራሱ አዕምሮ ሙሉ ቁጥጥር የጠነሰሰው ማለት ነው። ለምሳሌ አበበ ሳያስበው ድንገት መኪና ቢገጨው ይህ ድርጊት የአበበ ፈቃድ ነው አይባልም። ሆኖም ግን አበበ ስራየ ብሎ በመኪና ቢገጭ፣ ያ እንግዲህ የአበበ ፈቃድ ነው ይባላል። ፈቃድ የፍላጎት አይነት ሲሆን ልዩነታቸው ፈቃድ በሙሉ በአንድ ግለሰብ አዕምሮ የሚጠነሰስና በድርጊትም የሚገለጽ ሲሆን፣ ፍላጎት አልፎ በውጭ ተፅዕኖ የሚፈጠር መሆኑና የግዴት በድርጊት አለመገለጹ ነው።

                                               

ፍቅር

"ፍቅር እንደ ሞት የበረታች ናት" - መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን 8፡6 በአይሁድም በክርስትናም በአንዳንድም ሌሎች ሃይማኖቶች በሚከብረው በብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ ፍቅረ ቢጽ በ ኦሪት ዘሌዋውያን 19፡18 ይታዘዛል፦ "ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ". እንደገና ዘዳግም 10፡19፦ "እናንተ በግብፅ አገር ስደተኞች ነበራችሁና ስለዚህ ስደተኛውን ውደዱ።" በመጽሐፈ ምሳሌ ደግሞ፦ "የጎመን ወጥ በፍቅር መብላት የሰባ ፍሪዳን ጥል ባለበት ዘንድ ከመብላት ይሻላል።" - 15፡17 እናም ፍቅር ወሳኝ ነው

                                               

ፍካሬ ዞራሳተር

ፍካሬ ዞራስተር: ወደ ሁሉምና ወደ ማንም በፍሬድሪች ዊልሄልም ኒሺ የተደረሰ የፍልስፍና ልቦለድ* ነው። መጽሐፉ በ1883 እና 1885 መካከል በ4 ክፍል የተደርሰ ሲሆን በጊዜው ይሰራበት ከነበረው የአስተሳሰብ ዘዴ ለየት ባለ መልኩ የፍልስፍናን እና የግብረገብን ጥናቶች መርምሯል። የመጽሃፉ አትኩሮቶች፡ የዘላለማዊ ምልልስ፣ ኃይልን መፍቀድ ፣ የአዳዲስ ዋጋ ወይም ህግጋት አስፈላጊነት፣ የአምላክ በጊዜው በነበሩ አውሮጳውያን ልብ ውስጥ መሞት፣ የበላይ ሰው መምጣት ትምቢቶች ነበሩ። ጽሁፉ የመጽሐፍ ቅዱስ አጻጻፍ ስልት ይከተል እንጂ የውስጡ ፍሬ ነገር ግን የክርስትናና አይሁድ ሃይማኖቶችን መሰረታዊ እምነቶች የሚጻረር ነበር። ኒሺ ይህን መጽሐፍ ከሰወችና ከጊዜ 6000 ጫማ" እርቆ እንደጻፈ ይናገራል፣ ማለቱም የመጽሃፉን ሃሳቦች በተራራ ላይ እያለ እንዳገኛቸው ለማስገንዘብ ነበር። ኒሺ ይህን "ፍካሬ ዞራስተር" ብሎ የሰየመውን መጽሃፍ "ስርዓት አልባ"ጥራዝ ነጠቅ ወይም ስርዓት ይለሽ በሆነ ዘዴ ስለጻፈው ለተመራማሪወች እጅግ አስቸጋሪ ሆነ። ይሁንና ...

                                               

ምክኑያዊነት

ምክኑያዊነት ዕውቀት የሚገኘው በመሪ ሐሳቦች እና በምክንያት ነው የሚል የሐሳባዊ ዓይነት ፍልስፍና ነው። በጥሩ አመክንዮ ሊደረስባቸው የማይችሉ ዕውቀቶችን፣ ለምሳሌ ሥሜታዊነትን፣ ሃይማኖታዊ ተዓምራትን፣ ከሕዋሳት የሚፈልቁ ግንዛቤዎችን፣ ባጠቃላይ መልኩ አይቀበልም። አንድ አውሮፕላን፣ መሬት ላይ እያለ ግዙፍ ቢመስልም፣ አየር ላይ ሲዎጣ ጥንጥ ይመስላል። ነገር ግን ማንም እንደሚገነዘብ የአውሮፕላኑ ግዝፈት ምንጊዜም እኩል ነው። ይህን የአለመቀያየር ሁኔታ እምናውቀው በሚዋሸን የሥሜት ሕዋሳታችን ዓይናችን ሳይሆን በአዕምሮ ውስጥ ባለን የተፈጥሮ የአስተሳሰብ መርህ ነው ያላል ምክኑያዊነት። ከዚህ የፍልስፍና ዓይነት ትይይዩ የሚቆመው ፍልስፍና፣ ዳሳሻዊነት ሲባል፣ ስለ ዓለም እምናውቀው ዓለምን በሕዋሶቻችን በመመርመር እንጅ ውስጣዊ መሪሃሳቦችን በምክንየት በማያያዝ አይደለም ያላል።

                                               

1994

1994 አመተ ምኅረት ጳጉሜ 5 ቀን - ገለልተኛ አገር የሆነ ስዊስ በመጨረሻ የተባበሩት መንግስታት አባል ሆነ። መስከረም 1 ቀን - አራት አውሮፕላኖች በአረብ ተዋጊዎች ተሰርቀው በአለም ንግድ ሕንጻና በፔንታጎን ተጋጭተው 3000 ያህል ሰዎች ተገደሉ። ነሐሴ 20 ቀን - የምድር ጉባኤ ስብሰባ በጆሃነስበርግ ደቡብ አፍሪቃ ጀመረ። ሐምሌ 2 ቀን - የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት ተፈትቶ በአፍሪካ ኅብረት ተተካ። ነሐሴ 4 ቀን - የሳምንት ቀኖችና የወር ስሞች ሁሉ በቱርክመንኛ እንደ ቱርክመኒስታን መሪ አቶ ሳፓርሙራት ኒያዞቭ "ሩህናማ" የሚባል ይፋዊ መጽሐፍ ፍልስፍና በአዋጅ ተቀየሩ።

ህሊና
                                               

ህሊና

ህሊና ጥሩና መጥፎን መለየት የሚችል የአዕምሮ ክፍል ነው። አንድ ሰው ለአንድ ድርጊት ከሚሰጠው ዋጋ አንጻር ይመጣል። ይህ ማለት አንድ ግለሰብ ያለውንና ያመነበትን የሥነ ምግባር ዋጋ ጥሶ በተቃራኒ ሲሄድ የራሱ አዕምሮ እንዲወቅሰው የሚያደርገው የዚያ ሰው ህሊና ነው ይባላል። ደግሞ ይዩ፦ የኅሊና ነፃነት

ሒስ
                                               

ሒስ

ሒስ ማለት የአንዱን ነገር ወይም አካሄድ ዋጋ ወይም ጉድለት መተቸት ወይም ማመልከት ነው። ሓያሲ በእንግሊዝኛው አጠራር "ክሪቲክ" critic በመባል የሚታወቀው ሐሳብ ገባሪውንም ያመለክታል። በአማርኛ ሒስ የግብሩ፣ ሐያሲ ደግሞ የገባሪው መጠሪያ ሆኖ ያገለግላል ። ግብሩ ግምገማ፣ ግምት፣ ፍርድ፤ ገባሪው ደግሞ ገምጋሚ፣ ገማች፣ ፈራጅ ማለት ነው።

                                               

ቁሳዊነት

ቁሳዊነት ዓለም በሙሉ አካላዊ ናት፣ ከዚህ ውጭ ምንም ነገር በዓለም የለም የሚል የፍልስፍና ዓይነት ነው። ይህ አስተሳሰብ ከቁስ አካላዊነት ጋር በጣም የተቀራረበ ሲሆን ትንሽ የሚለየው አቅምን እና የተፈጥሮ ኅግጋትንም ከቁስ አካላት ጋር አብሮ ስለሚቀበል ነው።

ንቃተ ህሊና
                                               

ንቃተ ህሊና

ንቃተ ህሊና ማለት "የሚገነዘብ"፣ "ስሜትን የሚረዳ" ፣ "እኔነትን በውል የሚለይ"፣ ወይም ደግሞ ሙሉ አዕምሮን የሚቆጣጠር የሚሉ ብዙ ትርጓሜወች አሉት። ስለሆነም ንቃተ ህሊና ብዙ የአዕምሮ ተግባራትን በጃንጥላው ስር የሚያስተናግድ ክፍል ነው።

ካይዘን
                                               

ካይዘን

ካይዘን የአመራር ፍልስፍና ነው። ከጦርነቱ በኋላ በጃፓን ድርጅቶች ተለማ። በአንዳንድ ኢንዱስትሪ በተለይም በአንዳንድ መኪና ፋብሪኮች በተግባር ውሏል። የካይዘን ፍልስፍና ዘዴ በአጭሩ "ማቀድ -> ማድረግ -> ማመልከት -> መገሰብ/ማስተካከል" ይባላል። በተጨማሪ ማናቸውም ዕንቅፋት በደረሰ ጊዜ የሥሩን ጠንቅ ለማወቅ አምስት ጊዜ "ለምን" መጠይቅን ያስተምራል። እያንዳንዱ ምክንያት ላይኛ ምክንያት እንዳለው በማሠብ። እንዲህ ሲደረግ አንድ የሚታወስ መርኅ "የሚጎደለው ሂደቱ እንጂ ሰዎቹ አይደሉም" ነው ይባላል። የ "ካይዘን" ትርጉም ከጃፓንኛ እንዲያውም "ማሻሻል" ሲሆን፣ ብዙ ጊዜ ፅንሰ ሀሣቡ እንደ "ምንጊዜም ማሻሻል" ይተረጎማል።