Back

ⓘ የጂኦፖሊመር ሲሚንቶ በክፍል ውስጥ የሙቀት እና ቅዝቃዜ መጠን ለማጠንከር የሚያገለግል የማያያዣ ስርዓት ነው፡፡ ይህም ለፖርትላንድ ሲሚንቶ በአማራጭነት የቀረበ ከአካባቢ ጋር ጥሩ ግንኙነት ያለው ምርት ነው፡፡ በብዙ የሂንዱ ቤተመቅደሶች ውስጥ በአገልግሎት ..
የጂኦፖሊመር ሲሚንቶ
                                     

ⓘ የጂኦፖሊመር ሲሚንቶ

የጂኦፖሊመር ሲሚንቶ በክፍል ውስጥ የሙቀት እና ቅዝቃዜ መጠን ለማጠንከር የሚያገለግል የማያያዣ ስርዓት ነው፡፡ ይህም ለፖርትላንድ ሲሚንቶ በአማራጭነት የቀረበ ከአካባቢ ጋር ጥሩ ግንኙነት ያለው ምርት ነው፡፡ በብዙ የሂንዱ ቤተመቅደሶች ውስጥ በአገልግሎት ላይ ውሎ የነበረ ሲሆን እነዚህም ከሺህ አመታት በላይ እድሜ ያላቸው ናቸው ከፍተኛ የካርቦን ምልክት ያላቸውን የሲሚንቶ ምርት ለመቀነስ በተፈጥሮ ካሉት የአፈር አይነቶች ወይም ከኢንዱስትሪ ተረፈ ምርቶች የሚሰራ ሲሆን በብዙ የአርማታ የቆይታ ጊዜ ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ ተከላካይ ሆኖ የሚያገለግል ነው፡፡

የጂኦፖሊመር ሲሚንቶዎች ከፖርትላንድ ሲሚንቶ በላይ የሚገኙ እና የሚያገለግሉ ናቸው፡፡

                                     

1. አመራረት

የፖሊመር ሲሚንቶ ምርት አሉሚኒዮ ሲሊኬትን ለመፍጠር የሚያስፈልጉ እንደ ሜታ ፖሊን ወይም የአፈር ብናኝ የሚያስፈልግ ሲሆን እነዚህም ተጠቃሚ የሚገለገልባቸው እና ጉዳት የማያደርሱ የአልካላይን ሪኤጀንት ናቸው /ለምሳሌ የሶዲየም ወይም ፖታሺየም የሚሟሟ ሲሊኬት ከሞላር ሬሽዎ MR SiO 2: M 2 O > 1.65 M ሶዲየም ወይም ፖታሺየም የሆነ ኤም/ እንዲሁም ውሃ ከዚህ በታች ያለውን ተጠቃሚ የሚገለገልበት እና ጉዳት የማያደርስ ሪኤጀንት ፍቺ ይመልከቱ ፡፡ የክፍል ሙቀት እና ቅዝቃዜ ማጠናከሪያ የካልሺየም ካታዮኖችን በመጨመር ይህም የማቅለጫ ሀይል በመጨመር የሚሳካ ነው፡፡

የጂኦፖሊመር ሲሚንቶዎች ከፖርትላንድ ሲሚንቶዎች በፍጥነት ለማዳን የተሰሩ ናቸው፡፡ የተወሰኑት ውህዶች በ24 ሰዓታት ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ጥንካሬያቸውን ያገኛሉ፡፡ ይሁን እንጂ በመቀላቀያ ፋብሪካ ውስጥ መቀላቀል እንዲችሉ በዝግታ መሰራት አለባቸው፡፡ ይህም ለስራውም ሆነ ወይም በአርማታ ማቀላቀያው ለማቅረብ ነው፡፡ የጂኦፖሊመር ሲሚንቶ በስሊኬት አለት ላይ ከተመሰረቱት ኮረቶች ጋር ጠንካራ የኬሚካል ቦንድ የመፍጠር ችሎታ አለው፡፡ በመጋቢት 2010 በዩኤስ የፌዴራል ትራንስፖርት የፍጥነት መንገድ አስተዳደር መምሪያ ጂኦፖሊመር አርማታ የተሰኘውን ቴክ ብሪፍ ለቅቆ የነበረ ሲሆን ይህም እንዲህ ይላል፡፡

ሁለገብ የሆነ፣ ወጪ ቆጣቢ የሆኑ እና እንደ ፖርትላንድ ሲሚንቶ መቀላቀል እና ማጠንከር የሚችሉ የጂኦፖሊመር ሲሚንቶዎች የትራንስፖርት መሰረተ ልማት እና የግንባታ ኢንዱስትሪውን የግንባታ ደረጃ ማሻሻያ፣ ለውጥ እና ማሳደጊያ ሆኖ ሊወክል ችሏል፡፡

                                     

2. የጂኦፖሊመር አርማታ

አጂኦፖሊመር ሲሚንቶ በሚለው እና ጂኦፖሊመር አርማታ በሚሉት ቃላት መካከል ሁልጊዜም ውዝግብ አለ፡፡ ሲሚንቶው መያዣ ሲሆን አርማታ ግን ሲሚንቶውን ከውሃ ጋር በመቀላቀል እና በማጠናከር የሚገኝ የቅልቅል ምርት ውጤት ነው፡፡ ወይም በጂኦፖሊመር ሲሚንቶ አገላለጽ የአልካላይን እንዲሁም የድንጋይ ኮረት ውህድ ነው፡፡ የሁለቱ ምርቶች ጂኦፖሊመር ሲሚንቶ እና ጂኦፖሊመር አርማታ መሳሪያዎች በተለያዩ በአለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙ ገበያዎች ውስጥ ይገኛሉ

                                     

3. ኬሚስትሪ፡ የፖርትላንድ ሲሚንቶ እና የጂኦፖሊመር ሲሚንቶ

ግራ፡ የፖርትላንድ ሲሚንቶ ፒሲ የካልሲየም ስልኬትን ወደ ካልሲየም ስልኬት ሀይድሬት ሲ-ኤስ-ኤች እና ፖርትላንዳይት፣ Ca OH 2 በመቀየር ማጠናከር, CaOH 2 ፡፡

ቀኝ፡ የፖሊመር ሲሚንቶውን ጂፒ ፖታሺየም አሊጐ ሴሊየት ሲሎክሶ የተባለውን የፖሊ ማቀዝቀዣ እና ማጠንከሪያ ወደ ፖታሺየም ፖሊ ሲሊየት ሲሎክሶ በመቀየር በተገናኘ ትስስር በኩል ማጠናከር ነው፡፡

የጂኦፖሊመር ሲሚንቶ ውህዱ ሙቀት የሚፈልግ ከሆነ የጂኦፖሊመር ሲሚንቶ የሚባል ሳይሆን የጂኦፖሊመር መያዣ ይባላል፡፡ ሁለቱ አይነቶች በአርማዎቻቸው ይታወቃሉ፡፡

ሰንጠረዡ የተወሰኑ የአካላይን ኬሚካሎችን እና የደህንነት መጠበቂያ ደረጃቸውን አስቀምጧል፡፡ የሚያዝጉ ምርቶች በጓንት፣ በመስታወት እና በጭምብል በመጠቀም የምንገለገልባቸው ናቸው፡፡ እነዚህም ተጠቃሚውን ሊጐዱ የሚችሉ እና ትክከለኛ የደህንነት መጠበቂያ ሕጐችን ሳንከተል በብዛት ልንተገብራቸው የማንችላቸው ናቸው በሁለተኛው ምድብ የፖርትላንድ ሲሚንቶ ወይም ሀድሬትድ ላየን የተባሉ አይነተኛ ከፍተኛ ምርቶች ይገኛሉ፡፡ የጂኦፖሊመራዊ አልካላየን ሪኤጀንቶች የተባሉ እና በዚህ ምድብ የሚገኙት ምርቶች ተጠቃሚን የማይጐዱ ተብለው ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ እነዚህም የሚገነፍል ተፈጥሮ ያላቸው የአልካላይን ምርቶች ሲሆኑ የምርቶቻቸውን ዱቄቶች በአየር ወደ ውስጥ እንዳይገቡ ምርጫ እና ትክክለኛ የግል ደህንነት መጠበቂያ መሳሪያ መልበስን የሚጠይቅ ሲሆን ይህም በማንኛውም ሁኔታ ኬሚካሎች ወይም ዱቄቶች በሚያዙበት አያያዝ መፈፀም ይገባል፡፡

በአልካላየን የሚሰሩ ሲሚንቶች ወይም በአልካላይን የሚሰሩ ፖሊመሮች በተወሳኑት አካላት በኋላ ላይ ትክክለኛ ያልሆነ ቃል መሆናቸውን አውቀዋል፡፡ እንዲሁም የተወሰኑ ባለሙያዎች በስነ ጽሑፉ ውስጥ እና በኢንተርኔት የተገኙ የተለያዩ አዘጋጃጀቶች በተለይም በብናኝ ላይ የተመሰረቱ የአልካላይን ስልኬቶችን ከሞላር ሬሽዎች SiO 2: M 2 O ከ1.20 በታች ከሆነው ጋር ወይም በንፁህ የኤንኤኦኤች 8M ወይም 12M ሲስተሞች ላይ ተመስርቶ የሚያገለግል ሆኖ ተገኝቷል፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች ለማንኛውም ሰው አገልግሎት ለማዋል በተጠቃሚው ላይ ጉዳት የማያደርሱ አይደሉም፡፡ ስለዚህ በዚህ የስራ መስክ ላይ ከተቀጠሩ ከፍተኛ ጥንቃቄ እና የግል የአደጋ መከላከያ መሳሪያ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ በእርግጥ የወጡ ሕጐች እና ደንቦች እንዲሁም መመሪያዎች ለሰራተኞች የደህንነት እና የጤና አጠባበቅ እንዲሁም ፕሮቶኮላቸውን ለማስፈፀም የወጡ ናቸው፡፡

ከዚህ በተቃራኒ በመስክ ላይ የተሰማሩ የጂኦፖሊመር ሲሚንቶ አዘገጃጀት ሰራተኞች የአልሪላይን ውህድ ያላቸውን ስልኬቶች ከማስጀመሪያ የሞላር ሬሾ መጠኑ 1.45 እስከ 1.95 ከሆነው ጋር ያካትታሉ፡፡ በተለይም ከ1.60 እስከ 1.85 በሚያህለው በማካተት የሚፈጽሙ ሲሆን ይህም ተጠቃሚውን በማይጐዱ ሁኔታዎች የሚያገለግል ነው፡፡ ለምርምር አላማ የተወሰኑ የላብራቶሪ አዘገጃጀቶች ከ1.20 እስከ 1.45 የሚሆኑ የሞላር ሬሾዎች ያላቸው ናቸው፡፡                                     

4. የጂኦፖሊመር ሲሚንቶ ምድቦች

የጂኦፖሊመር ሲሚንቶ ምድቦች

 • በዝቃጭ ላይ የተመሰረተ የጂኦፖሊመር ሲሚንቶ፡፡
 • በብናኝ አፈር ላይ የተመሰረተ የጂኦፖሊመር ሲሚንቶ
 • በአለት ላይ የተመሰረተ የጂኦፖሊመር ሲሚንቶ፡፡
 • አይነት 2፡ በዝቃጭ/በብናኝ አፈር ላይ የተመሰረተ የጂኦፖሊመር ሲሚንቶ፡፡
 • አይነት 1፡ በአልካላይ የሚሰራ የብናኝ አፈር የጂኦፖሊመር ሲሚንቶ፡፡
 • የፌሮ ሴሊየት ላይ የተመሰረተ የጂኦፖሊመር ሲሚንቶ፡፡
                                     

4.1. የጂኦፖሊመር ሲሚንቶ ምድቦች በዝቃጭ ላይ የተመሰረተ የጂኦፖሊመር ሲሚንቶ

የተሰራባቸው ዝርዝሮች፡ ሜታ ኮሊን MK-750 + የብረት ማቅለጫ ዝቃጭ + አልካላይ ስልኬት ተገልጋይ የሚጠቀምባቸው እና የማይጐዳ፡፡ የጂኦፖሊመር ስሪት፡ Si:Al = 2 በእርግጥ የኤስአይ፡ ኤኤል = 1 ጠጣር ውህድ ነው፣ Si:Al=1 ዳይ-ስልኬት የአኖርታይት አይነት + Si:Al =3–5 Na,K- ፖሊ ሲያሌት - ዳይሲሎክሶ ኦርቶ ክላስ አይነት እና ሲ-ኤስ-ኤች ካልሺየም C-S-H Ca-- ሲሊኬት ሀይድሬት፡፡
                                     

4.2. የጂኦፖሊመር ሲሚንቶ ምድቦች በብናኝ አፈር ላይ የተመሰረቱ የጂኦፖሊመር ሲሚንቶዎች

በኋላም በ1997 በዝቃጭ ላይ በተመሰረተው የጂኦፖሊመር ሲሚንቶዎች ላይ በተካሄዱ ስራዎች በሌላው በኩል በመገንባት እና እንዲሁም ደግሞ በአንዱ በኩል ከዚኦላይትስ ስሪት በተገኙ በአፈር ብናኝ ላይ በመገንባት እነ ሲሊቨር ስትሪም እና ቫን ጃርስቬልድ እንዲሁም ቫንዴቨንተር በብናኝ አፈር ላይ የተመሰረቱትን የጂኦፖሊመሪክ ሲሚንቶዎችን ለመፍጠር ችሏል፡፡ እነ ሲልቨርስትሪም 5.601.643 የዩኤስ የፈጠራ ባለቤትነት ፍላይ አሽ ሴሜንቲሺየስ ማቴሪያል እና የምርት አሰራር ዘዴ በሚል የተመዘገበ ነው፡፡

በአሁኑ ጊዜ ሁለት አይነት በሲሊከስ EN 197 ወይም በደረጃ Class F ASTM C618 የብናኝ አፈር አይነቶች ላይ የተመሰረቱ ምርቶች አሉ፡፡

 • ዓይነት 1: alkali-ስለጀመሩ ቅድሚያ በቀዳሚ geopolymer የተጠቃሚ-ባለጋራ፡፡
በብዙ ሁኔታዎች የማሞቂያ ደረጃው ከ60-80 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ላይ ነው፣ እንደ ሲሚንቶ ተለያይቶ የሚመረት ሳይሆን ልክ እንደ ብናኝ አፈር አርማታ በቀጥታ የሚመረት ነው፡፡ ናይትሮጂን ሀይድሬት በተጠቃሚው ላይ ጉዳት የሚኖረው + ብናኝ አፈር፡ በከፊል የተዋሀዱ የብናኝ አፈር ሆኖ በአሉሚኖ- ሲሊኬት ጄል የተያያዙ እና ኤስአይ፡ ኤኤል = 1 እስከ 2፣ ከዞሊን አይነት ቻባዛይት- ናይትሮጂን እና ሶዳላይት መዋቅሮች ጋር የተያያዘ ነው፡፡
 • አይነት 2፡ የዝጋጭ/የብናኝ አፈር ላይ የተመሰረተ የጂኦፖሊመር ሲሚንቶ ለተጠቃሚው ጉዳት የሌለው፡፡
በክፍል ሙቀት እና ቅዝቃዜ መጠን የማጠንከር ስራ ለተጠቃሚው ጉዳት የሌለው የስልኬት ውህድ + የብረት ማቅለጫ + ብናኝ አፈር፡ በጂኦፖሊመሪክ ማትሪክስ የተካተቱ የብናኝ አፈር ከ Si:Al= 2 ካልሺየም፣ ፖታሺየም - ፖሊ ሲሊየት - ሲሎክሶ


                                     

4.3. የጂኦፖሊመር ሲሚንቶ ምድቦች በፌሮ - ሲሊየት ላይ የተመሰረተ የጂኦፖሊመር ሲሚንቶ

የማምረቻ ዝርዝሮቹ በአለት ላይ ከተመሰረተው የጂኦፖሊመር ሲሚንቶ ጋር ተመሳሳይነት ያለው ሆኖ ነገር ግን በከፍተኛ ደረጃ የኦክሲጅን ይዘት ባለው አይረን የጂኦለጂካል ኤሌመንቶችን ያካተተ ነው፡፡ የጂኦፖሊመር ስሪት አይነት የፖሊ ፌሮ - ሲሊየት ካልሺየም፣ ፖታሺየም – አይረን - ኦክሳይድ – ሲልከን - ኦክስጅን - አሉሙኒየም - ኦክስጂን ናቸው፡፡ ይህ በተጠቃሚው ላይ ጉዳት የሌለው የጂኦፖሊመር ሲሚንቶ በመመረት እና ለንግድ በማቅረብ ምዕራፍ ላይ ይገኛል፡፡

                                     

5. በማምረት ወቅት የሚኖሩ የካርቦን ዳይኦክሳይድ ልቀቶች

እንደ አውስትራሊያዊው የአርማታ ባለሙያ ቢ. ቪ. ራንጋን ከሆነ እያደገ ያለው አለም ሁሉም የጂኦፖሊመር ሲሚንቶ አይነቶችን ለማምረት ያለው የአርማታ ፍላጐት ከፍተኛ እድል ነው፡፡ ምክንያቱም በሚመረቱበት ወቅት ዝቅተኛ የካርቦንዳይኦክሳይድ መጠን ስለሚለቁ ነው፡፡

                                     

5.1. በማምረት ወቅት የሚኖሩ የካርቦን ዳይኦክሳይድ ልቀቶች የካርቦንዳይኦክሳይድ ልቀት ንጽጽር

የፖርትላንድ ሲሚንቶ ማምረቻው በሚከተሉት ውህዶችclinker መሰረት የካልሺየም ካርቦኔትን ወደ አመድነት የመቀየር አሰራርን አካትቷል፡፡

3CaCO 3 + SiO 2 → Ca 3 SiO 5 + 3CO 2 2CaCO 3 + SiO 2 → Ca 2 SiO 4 + 2CO 2

የአሉሚናን የሚያካትቱ ውህዶች የምርቱን የአሉሚኔት እና ፌሪት ይዘቶች ወደ መፍጠር የሚያመሩ ናቸው፡፡

አንድ ቶን የፖርትላንድ ክሊንከርን ማምረት በግምት 0.55 ቶን የሚያህሉ የካርቦንዳይኦክሳይድ ኬሚካልን በቀጥታ ያወጣል፡፡ ይህም የዚህ ምርት ውህዶች ሆኖ የሚወጣ ሲሆን ስለዚህ ደግሞ ተጨማሪ የ0.40 ቶን ካርቦንዳይኦክሳይድ ምርት ለማምረት የካርቦን ምርት ያለውን ነዳጅ መቀላቀል ያስፈልጋል፡፡ ይህንንም የስራውን ሂደት ብቃት በማግኘት እና ቆሻሻዎችን እንደ ነዳጅ በመጠቀም መቀነስ ይቻላል፡፡ ይሁን እንጂ በአጠቃላይ 1 ቶን የፖርትላንድ ሲሚንቶ ከ0.8 እስከ 1.0 ቶን ካርቦንዳይኦክሳይድ የሚለቅ ይሆናል፡፡

በንጽጽር ሲታይ የጂኦፖሊመር ሲሚንቶዎች እንደ ቁልፍ ጥሬ እቃ በካልሺየም ካርቦኔት ላይ አይመሰረቱም እንዲሁም በማምረቻ ወቅት ያነሰ የካርቦንዳይኦክሳይድ ልቀት የሚያወጡ ሲሆን ይህም ከ40 በመቶ እስከ 80-90 በመቶ መጠን ያለውን የሚቀንስ ነው፡፡ ጆሴፍ ዴቭዶቪትስJoseph Davidovits በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ በመጋቢት 13/1993 የመጀመሪያ ጽሑፉን ያቀረበ ሲሆን ይህም በአሜሪካ ሲሚንቶ ማህበር በቺካጐ ኢሊኖይስ በተዘጋጀ ሲምፖዚየም ላይ ነው፡፡

የፖርትላንድ ሲሚንቶ ኢንዱስትሪ የሕግ ተቋማትን በማግባባት በስሙ የሚከራከሩ ሲሆን ይህም የሚለቁት የካርቦንዳይኦክሳይድ ልቀት ቁጥር ከካልሺየም ካርቦኔት ብስባሴ ጋር የተገናኘውን ክፍል የማያካትት ሲሆን ነገር ግን በውህደቱ ልቀት ላይ ብቻ ትኩረት የሚያደርጉ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ ኒው ሳይንቲስት በተባለ ሳይንሳዊ መጽሔት ውስጥ የተፃፈው የ1997 አንቀጽ እንዲህ ይላል …ከሲሚንቶ ማምረቻ የሚለኩ የካርቦንዳይኦክሳይድ ልቀት ግምቶች በቀድሞ ምንጭ የነዳጅ ቅልቅል ላይ ብቻ ትኩረት ያደረጉ ናቸው፡፡ በመንግስታት መካከል የተደረገው እና በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የተካሄደው የዩኤን ፓነል ውይይት አጠቃላይ ኢንዱስትሪው የሚለውቀው የካርቦንዳይኦክሳይድ መጠን 2.4 በመቶ መሆኑን እንዲሁም በታናሴ የኦክሪጅ ብሔራዊ ላብራቶሪ ውስጥ የተገኘው የካርቦንዳይኦክሳይድ መረጃ ትንተና ማዕከሉ መጠን 2.6 ካርቦንዳይኦክሳይድ መሆኑን ይገልፃል፡፡ አሁን የጂኦፖሊመር ሲሚንቶ ተቋሙ ጆሴፍ ዶቪዶቪትስ Joseph Davidovits ለመጀመሪያ ጊዜ በሁለቱም ምንጮች ምልክታዎችን አድርጓል፡፡ እርሱም እንዳሰላው ከሆነ በአመት የሚመረተው 1.4 ቢሊየን ቶን የአለም ኤለመንት አሁን ያለው የካርቦንዳይኦክሳይድ ልቀት /በአለም/ 7 በመቶ ያህል ያመርታል፡፡ ከ15 አመታት በኋላ /2012/ ሁኔታው በፖርትላንድ ሲሚንቶ የካርቦንዳይኦክሳይድ ይህም በአመት 3 ቢሊየን የሚሆን በመሆኑ የከፋ ሆኗል፡፡

የፖርትላንድ ሲሚንቶ ምርት ከዚህ የበለጠውን ካርቦንዳይኦክሳይድ የሚያወጣ ሲሆን ይህም ወደ አመድነት በሚቀየርበት ጊዜ አገልግሎቱ እና የመቆየት መጠኑ አገልግሎት ላይ በሚውለበት ጊዜ ማለት ነው፡ ስለዚህ የጂኦፖሊመሮች በንጽጽሩ 40 በመቶ ወይም ከዚህ በታች ልቀቶች ሊኖራቸው የሚገባ ሲሆን ይህም ያለቀላቸው ምርቶች ሲታዩ ተመራጭ እንዲሆኑ ማለት ነው፡፡ መሰረት ለፖርትላንድ ሲሚንቶ የሚያስፈልገን የሀይል መጠን በአማካይ 4700 ኤምጄ/ቶን ነው፡፡ በአለት ላይ የተመሰረተው የጂኦፖሊመር ሲሚንቶ ስሌት በሚከተሉት ልኬቶች ላይ ተመስርቶ የተሰራ ነው፡፡

- የብረት ማቅለጫ ዝቃጩ ከብረታ ብረት ኢንዱስትሪ በተረፈ ምርት መልክ የሚገኝ ነው ምንም አይነት ተጨማሪ ሀይል አያስፈልገውም፡፡ - ወይም መመረት አለበት ደቃቃ ካልሆነው ዝቃጭ ወይም ከጂኦሎጂካዊ ሀብቶች በድጋሚ የቀለጠ፡፡

በጣም ተመራጭ በሆነው ሁኔታ - በተረፈ ምርትነት መልክ የሚገኝ ዝቃጭ - በአለት ላይ የተመሰረተውን የፖሊመር ሲሚንቶ ማምረት ከፖርትላንድ ሲሚንቶ ጋር ሲነፃፀር የሚያስፈልገው የሀይል መጠን 59 በመቶ ይቀንሳል፡፡ ዝቅተኛ ተመራጭነት ባለው ሁኔታ ደግሞ የዝቃጭ ማምረቻው - ቅነሳው 43 በመቶ ይደርሳል፡፡.

በማምረት ወቅት የሚኖር የካርቦን ልቀት መጠን

በጣም ተመራጭ በሆነው ሁኔታ - በተረፈ ምርትነት መልክ የሚገኝ ዝቃጭ - በአለት ላይ የተመሰረተውን የፖሊመር ሲሚንቶ ማምረት ከፖርትላንድ ሲሚንቶ ጋር ሲነፃፀር የሚያስፈልገው የሀይል መጠን 80 በመቶ ይቀንሳል፡፡ ዝቅተኛ ተመራጭነት ባለው ሁኔታ ደግሞ የዝቃጭ ማምረቻው - ቅነሳው 70 በመቶ ይደርሳል፡፡

በብናኝ አፈር ላይ የተመሰረቱ ደረጃ ኤፍ የሆኑ ሲሚንቶዎች

እነርሱ ምንም አይነት ተጨማሪ ሙቀት አያስፈልጋቸውም፡፡ ስለዚህም ስሌቱ ቀላል ነው፡፡ ይህም በብናኝ አፈር ላይ ለተመሰረተው የአንድ ቶን ሲሚንቶ የሚለቀው የካርቦንዳይኦክሳይድ መጠን ከ0.09 እስከ 0.25 ቶን ሲሆን ይህም ማለት የካርቦንዳይኦክሳይድ ልቀቱን ከ75 እስከ 90 በመቶ በሚያክል መቶን ይቀንሳል ማለት ነው፡፡

                                     

6. በአለት ላይ ለተመሰረቱ ለጂኦፖሊመር ሲሚንቶ የሚያስፈልጉ ግብአቶች ካሊሺም፣ ፖታሺየም – ፖሊ ሲያሌት-ዳይሲሎክሶ

ይህንን ይመልከቱ

 • ንጽጽራዊ ጥንካሬ አንድ አክሰስ፡ በ28 ቀናት ከ90 MPa በላይ ለከፍተኛ የጥንካሬ ስራ፣ ከ4 ሰዓታት በኋላ 20 MPa፡፡
 • በሚሰራበት ጊዜ ያለው የመሸብሸብ መጠን፡ ከ0.05 በመቶ በታች፣ አልተለካም፡፡
 • የማቀዝቀዣ - ታው፡ የክብደት መቀነስ ከ0.1 በመቶ በታች ASTM D4842፣ የጥንካሬ መቀነስ ከ5 በመቶ በታች ከ180 ኡደቶች በኋላ፡፡
 • የጉብጠት/ልምጠት ጥንካሬ፡ በ28 ቀናት ከ10 እስከ 15 MPa ለከፍተኛ የጥንካሬ ስራ፣ ከ24 ሰዓታት በኋላ 10 MPa ፡፡
 • የያንግ ሞጁልስ፡ ከ2GPa በላይ፡፡
 • የውሃ ማሳለፍ መጠን፡ -10 ሜትር በሰከንድ
 • የውሃ መምጠጥ መጠን፡ ከ3 በመቶ በታች፣ ከውሃ ማሳለፍ አቅም ጋር የተገናኘ አይደለም
 • በውሃ ውስጥ የመለየት መጠኑ፣ ከ180 ቀናት በኋላ፡ K 2 O ከ0.015 በመቶ በታች
 • የእርጥብ - ደረቅ ፡ የክብደት መቀነስ ከ 0.1 በመቶ በታች ASTM D4843
 • የአልካላይ እና የኮረት ውህድ፡ ከ250 ቀናት በኋላ ምንም የተስፋፋ ነገር የለም ሲቀነስ 0.01 በመቶ በምስሉ ላይ እንደተመለከተው ከፖርትላንድ ሲሚንቶ ኤኤስቲኤም ሲ227 ጋር ሲነፃፀር፡፡ እነዚህ ውጤቶች በ1993 የታተሙ ናቸው፡፡ የጂኦፖሊመር ሲሚንቶዎች እና መያዣዎች ከአልካላይ ይዘቶች ጋር እስከ 10 በመቶ ድረስ ከፍተኛ ሲሆኑ ለመደበኛ ውህደት ከኮረት ጋር ሲጠቀሙ ምንም አይነት የአልካላይ እና የኮረት ውህደት አደገኛነት አያስከትሉም ፡፡
 • ሰልፈሪክ አሲድ፣ 10 በመቶ፡ የክብደት መቀነስ 0.1 በመቶ በቀን
 • የአሞኒያ ውህድ፡ የክብደት መቀነሱ አልታየም
 • የሰልፌት ውህድ፡ በ28 ቀናት ውስጥ 0.02 በመቶ ተሸብሽቧል
 • KOH 50 በመቶ፡ የክብደት መቀነስ በቀን 0.02 በመቶ
 • ሀይድሮክሎሪክ አሲድ፣ 5 በመቶ፡ የክብደት መቀነስ በቀን 1 በመቶ


                                     

7. የ ደረጃዎች አስፈላጊነት

በሰኔ 2/2012 እ.ኤ.አ ኤኤስቲኤም ኢንተርናሽናል Aየተባለው ተቋም የቀድሞው የአሜሪካ የምርመራ እና የአፈር፣ ኤኤስቲኤም ማህበር በጂኦፖሊመር መያዣ ሲስተሞች ላይ ሲምፖዚየም አዘጋጅቶ ነበር የሲምፖዚየሙ መግቢያ እንዲህ ይላል፡ ለፖርትላንድ ሲሚንቶ የአፈፃፀም ማብራሪያዎች ሲፃፉ ፖርትላንድ ያልሆኑ መያዣዎች የሚታወቁ አልነበሩም፡፡ እንደ ጂኦፖሊመሮች የመሳሰሉ አዳዲስ መያዣዎች በከፍተኛ ደረጃ ምርምር ተካሂዶባቸው እንደ ልዩ ምርቶች በገበያ ላይ ውሎ በመዋቅራዊ አርማታ ላይ አገልግሎት ላይ ውሏል፡፡ ይህ ሲምፖዚየም የኤኤስቲኤም ተቋም ያሉትን የሲሚንቶ ደረጃዎች አቅርቦት ከግምት እንዲያስገባ ይህም በአንዱ መንገድ ተጨማሪ የጂኦፖሊመር መያዣዎችን ለማግኘት ውጤታማ ስራ እንዲሰራ እንዲሁም በሌላ መንገድ እነዚህን ምርቶች ለሚጠቀሙ አካላት አስተማማኝ ጥበቃ ለማቅረብ እድል እንዲሰጠው ታስቦ የተካሄደ ነው፡፡

ያሉት የፖርትላንድ ሲሚንቶ ደረጃዎች ከጂኦፖሊመር ሲሚንቶ ጋር የሚሄዱ አይደሉም፡፡ በልዩ ኮሚቴ ሊፈጠሩ ይገባል፡፡ ነገር ግን ይህንን ለማድረግ ደረጃቸውን የጠበቁ የጂኦፖሊመር ሲሚንቶዎች መገኘት አለባቸው፡፡ በአሁኑ ጊዜ እያንዳንዱ ባለሙያ በሀገር ውስጥ ሕግ ላይ በመመስረት የራሱን አሰራር ዘዴ ማቅረብ ያለበት ሲሆን ይህም በምርቶቹ ቆሻሻዎች፣ ተረፈ ምርቶች ወይም የተጣሉ ምርቶች ላይ በመመስረት ነው፡፡ ትክክለኛ የጂኦፖሊመር ሲንቶን ምድብ ለመምረጥ የሚያስፈልግ ነገር አለ የ2012 የጂኦፖሊመር ስቴት ጥናትና ምርምር. ሁለት ስሞቻቸው ከዚህ በታች የተጠቀሱ ምድቦችን እንደ ሀሳብ አቅርበዋል፡፡

 • የአይነት 2 ዝቃጭ/ በብናኝ አፈር ላይ የተፈሰረተ የጂኦፖሊመር ሲሚንቶ፡ የብናኝ አፈር የሚገኙት በዋናነት እያደጉ ባሉ ሀገራት ውስጥ ነው፡፡
እና
 • በፌሮ - ሲሊየት ላይ የተመሰረተ የጂኦፖሊመር ሲሚንቶ፡ ይህ በገፀ ምድር አይረን የበለፀገው ጥሬ እቃ በአለም አቀፍ ደረጃ በሁሉም ሀገራት ውስጥ የሚገኝ ነው፡፡
እና
 • ትክክለኛ ተጠቃሚን የማይጐዳ የጂኦፖሊመር ሪኤጀንት
                                     

8. Bibliography

 • Geopolymer Chemistry and Applications, Joseph Davidovits, Institut Géopolymère, Saint-Quentin, France, 2008, መለጠፊያ:ISBN 4th ed., 2015. In Chinese: National Defense Industry Press, Beijing, መለጠፊያ:ISBN, 2012.
 • Geopolymers Structure, processing, properties and industrial applications, John L. Provis and Jannie S. J. van Deventer, Woodhead Publishing, 2009, መለጠፊያ:ISBN.
 • Geopolymer ተቋም
 • Geopolymer አሊያንስ