Back

ⓘ ፈርዖን ማለት የጥንታዊ ግብጽ ንጉሥ ነው። ይህ ከግብጽኛ ፐር-ዓ ከ ፐር እና ዓ ወይም ታላቁ ቤት ደረሰ። ፐር-ዓ መጀመርያ ቤተ መንግሥት ለማመልከት ሲሆን፣ ከ1400 ዓክልበ. በኋላ ንጉሡን ፐር-ዓ ይሉት ጀመር። ስለዚህ ከዚያ በፊትም የነገሡት ግብጻዊ ን ..
                                               

ሃትሸፕሱት

ሃትሸፕሱት በጥንታዊ የግብጽ አዲስ መንግሥትና የ18ኛው ሥርወ መንግሥት ፈርዖን ስትሆን ምናልባት 1487-1466 ዓክልበ. የገዛች ነበረች። ከዚያ በፊት የ2 ቱትሞስ ንግሥት እና ያባቱ 1 ቱትሞስ ልጅ ነበረች። የ2 ቱትሞስ ቁባት ንግሥት ኢሰት ተባለች፣ እርሷም የተከታዩ 3 ቱትሞስ እናት ሆነች። የ፪ ቱትሞስ ተከታይ በይፋ ልጁ ፫ ቱትሞስ ሲሆን፣ እሱ ግን ገና የ 2 ዓመት ሕጻን ልጅ ሆኖ የቱትሞስ ንግሥት ሃትሸፕሱት ባለሙሉ ሥልጣን እንደራሴው፣ በቅርብም ጊዜ ውስጥ በራስዋ መብት ፈርዖን ተባለች። በ22ኛ ዓመትዋ 1466 ዓክልበ. ግ. ዓርፋ ያንጊዜ ፫ ቱትሞስ ለብቻው ፈርዖን ሆነ። 22 አመት ገዛች የሚታሠበው ከሺህ በላይ አመት በኋላ በኖረው በማኔጦን ምስክር ነው። በርሱ ዝርዝር በዚህ ሥፍራ አመንሲስ ወይም አሜሲስ የተባለች ንግሥት ለ22 ዓመት እንደ አፍሪካኑስ ቅጂ ወይም ለ21 ዓመት 9 ወር እንደ ዮሴፉስ ገዛች ይላልና። በ3 ቱትሞስ 22ኛው ዓመት በሶርያ እንደ ዘመተ እንሰማለን፣ ስለዚህ እንደሚታስበው የሃትሸፕሱት 22ኛ አመት በይፋ ደ ...

ፈርዖን
                                     

ⓘ ፈርዖን

ፈርዖን ማለት የጥንታዊ ግብጽ ንጉሥ ነው። ይህ ከግብጽኛ "ፐር-ዓ" ከ "ፐር" እና "ዓ" ወይም "ታላቁ ቤት" ደረሰ። ፐር-ዓ መጀመርያ ቤተ መንግሥት ለማመልከት ሲሆን፣ ከ1400 ዓክልበ. በኋላ ንጉሡን ፐር-ዓ ይሉት ጀመር። ስለዚህ ከዚያ በፊትም የነገሡት ግብጻዊ ንገሥታት ለምሳሌ በኦሪት ዘፍጥረት በአብርሐም፣ በዮሴፍ ወይም በሙሴ ዘመን የነበሩት ነገሥታት ደግሞ "ፈርዖን" ተብለዋል። ነገር ግን በታሪክ ላይ ፈርዖን የሚለው ማዕረግ ጥቅም ላይ የዋለው በጥንቱ የግብጽ መንግሥት ከ 2691-2625 ሳይሆን አሊያም በመካከለኛው የግብጽ መንግሥት ከ 2050-1710 ሳይሆን በአዲሱ የግብጽ መንግሥት በ 1570 ነው። ቁርኣንም ፈርዖን ማለት የጀመረበት በአዲሱ የግብፅ መንግሥት በሙሴ ዘመን ነው።

  • ደግሞ ይዩ፦ የፈርዖኖች ዝርዝር