Back

ⓘ እሳት ብርሃንንና ሙቀት የሚሰጥ የጥንተ ንጥሮች አፀግብሮት ነው፣ የውክሰዳ ምሳሌ ነው። የሚነካቸውን ነዳጅ ነገሮች ሁሉን ይበላል፣ ጢስንም ያወጣል፣ አመድ ወይም ቀላጭ ይተርፋል። አስፈላጊ የሆኑት ነገሮች ኦክሲጅን፣ ነዳጅና ሙቀት በሚፈለገው መጠን አንድላይ ..
                                               

የማርያም ቅዳሴ ገፅ ፰

፵፭ ፤ ከአባቱ አጠገብ ሳይለይ ቃል ወዳንቺ መጣ ሳይወሰን ፀነስሽው በላይ ሳይጎድል በታችም ሳይጨምር በመኀፀንሽ ተወሰነ ። ፵፮ ፤ መጠንና መመርመር የሌለበት እሳተ መለኮት በሆድሽ አደረ በምድራዊ እሳት እንመሰለው ዘንድ አይገባንም ለእሳትስ መጠን አለው ልክም አለው መለኮት ግን ይህን ያህላል ይህንንም ይመስላል ሊባል አይችልም ። ፵፯ ፤ ለመለኮት እንደ ፀሐይና እንደ ጨረቃ ክበብ እንደ ሰውም መጠን ያለው አይደለም ። ድንቅ ነው እንጂ የሰው ኅሊና የመላዕክትም አእምሮ በማይደርስበት በአርያም የሚኖር ነው እንጂ ። ፵፰ ፤ ለመለኮት ወርድና ቁመት ላይና ታች ቀኝና ግራ ያለው አይደለም በሁሉ የመላ ነው እንጂ ። ፵፱ ፤ ለመለኮት የሚዘረጋበት የሚሰበሰብበት ያለው አይደለም ። ግዛቱ ባገር ሁሉ ነው እንጂ ። ፶ ፤ ለመለኮት በላይ ጠፈር በታችም መሠረት ያለው አይደለም ጠፈሩ እርሱ መሠረቱም እርሱ ነው እንጂ ። ፶፩ ፤ ለመለኮት ከምድር ከውስጥዋ የሆነውን ያነሳ ዘንድ ማጎንበስ ራስንም ዝቅ ማድረግ ያለበት አይደለም ለጴጥሮስ እንዳሳየው ሁሉ በእ ...

እሳት
                                     

ⓘ እሳት

እሳት ብርሃንንና ሙቀት የሚሰጥ የጥንተ ንጥሮች አፀግብሮት ነው፣ የውክሰዳ ምሳሌ ነው። የሚነካቸውን ነዳጅ ነገሮች ሁሉን ይበላል፣ ጢስንም ያወጣል፣ አመድ ወይም ቀላጭ ይተርፋል። አስፈላጊ የሆኑት ነገሮች ኦክሲጅን፣ ነዳጅና ሙቀት በሚፈለገው መጠን አንድላይ ሲጋጥሙ፣ እሳት ይከሠታል። የራሱን ሙቀት ከዚያ ይፈጥራል፣ ኦክሲጅን ወይም ነዳጅ እስከሚያልቅ ድረስ ይቃጠላል።