Back

ⓘ ቅድመ-ታሪክ ማለት ከታሪክ ወይም መዝገቦች ከተጻፉ በፊት ያለፈው ጊዜ ነው። በአለም ደረጃ መጀመርያው የታወቁት የጽሑፍ ቅርሶች ከ3125 ዓክልበ. ያሕል ሲሆኑ ከጥንታዊ ግብጽ ሥነ ቅርስ ታውቀዋል። ለምሳሌ የመንደሮቹ መኳያ ሰሌዳ እና የጊንጥ ዱላ ከዚህ ዘ ..
ቅድመ-ታሪክ
                                     

ⓘ ቅድመ-ታሪክ

ቅድመ-ታሪክ ማለት ከታሪክ ወይም መዝገቦች ከተጻፉ በፊት ያለፈው ጊዜ ነው።

በአለም ደረጃ መጀመርያው የታወቁት የጽሑፍ ቅርሶች ከ3125 ዓክልበ. ያሕል ሲሆኑ ከጥንታዊ ግብጽ ሥነ ቅርስ ታውቀዋል። ለምሳሌ የመንደሮቹ መኳያ ሰሌዳ እና የጊንጥ ዱላ ከዚህ ዘመን ናቸው። ስለዚህ ከ3125 ዓክልበ. በፊት ያለፈው ሁሉ የአለም "ቅድመ-ታሪክ" ነው። ከ3125 ዓክልበ. በፊት ደግሞ የድንጋይ ዘመን እየሆነ ከዚያ ወቅት ጀምሮ የናስ ዘመን ሆነ።

ከግብጽ ውጭ፣ በሌሎች አገራት የቅድመ-ታሪክ መጨረሻና የታሪክ መጀመርያ የሚወሰንበት ጊዜ መዝገቦች ለመጻፍ የጽሕፈት ችሎታ በዙሪያው እንደ ታወቀ ይለያያል። ለምሳሌ በመስጴጦምያ ዙሪያ ታሪክ በ2400 ዓክልበ. ግድም ይጀምራል፤ ከዚያ በፊትም ቅድመ-ታሪክ ሊባል ይችላል። በአውሮጳ ግን ከሁሉ ቀድሞ ማንበብ የምንችልበት ጽሑፎች በ "ሚውኬናይ ጽሕፈት" ግሪክ አገር ከ1400 ዓክልበ. ግድም ናቸው። በአሜሪካዎችም በሜክሲኮ ዙሪያ ጽሕፈቶች ቢያንስ ከ900 ዓክልበ. ጀምሮ እንደ ታወቁ ቢመስልም፣ ከ300 ዓክልበ. በፊት የሆኑት ቅርሶች ግን ማንበብ ገና አልተቻለም። በአውስትራሊያ ከ1780 ዓም አስቀድሞ ምንም ጽሕፈት ወይም መዝገብ ባለመገኘቱ የአውስትራሊያ ቅድመ-ታሪክ እስከ 1780 ዓም እንግሊዞች እስከ መጡ ድረስ ቆየ ይባላል።

የብሔሮችና የሰዎች ስሞች ሊነበቡባቸው የሚችሉ መዝገቦች ሳይኖሩ ቢሆንም፣ ከሥነ ቅርስ ስለ ቅድመ-ታሪክ ሌሎች መረጆች ሊታወቁ ይቻላል። ለምሳሌ በስሜን አውርስያ እስከ 2000 ዓክልበ. ያሕል ድረስ የድሮ ዝሆን ወይም "ቀንደ መሬት" በአዳኞች እንደ ተገደለ ይታወቃል። በሳይቤሪያ ለሥነ-ቅርስ የታወቀው የማልታ-ቡረት ሥልጣኔ የነዚህን አዳኞች አኗርኗር ይገልጻል።

በስሞችና በተወሰኑ ጊዜ አሀዶች ጉድለት፣ እንዲሁም በልዩ ልዩ ሃይማኖት ትምህርቶች ወይንም በአፈ ታሪክ ብዛት፣ ብዙ ጊዜ ስለ ቅድመ-ታሪክ በትክክል ምን እንዳለፈ ወይም መቼ በርካታ ተቃራኒ አስተሳስቦች አሉ። አንዳንዴም የቅድመ-ታሪክ መጨረሻ ለመወሰን ይከብዳል። በአይርላንድ ልማዳዊ ታሪክ መጻሕፍት ውስጥ የአይርላንድ ነገሥታት ዝርዝር እና የአይርላንድ ታሪክ ከ2300 ዓክልበ. ጀምሮ ይዘግባል፣ ዳሩ ግን ከ370 ዓም ያህል በፊት ለነበረው ሁሉ ምንም ሌላ ማስረጃ ስላልተገኘ፣ ያው ሁሉ ከ370 ዓም በፊት የአይርላንድ "አፈ ታሪክ" እንዲሁም "ቅድመ-ታሪክ" ተብሏል። ከዚህም በላይ የግሪክ ተጓዥ ፒጤያስ ዘማሢሊያ በ325 ዓክልበ. ግድም አይርላንድን "ኢየርኔ" ሲለው እንደጎበኘው ይታወቃል፤ የአይርላንድ ታሪክ ከነዚህ መዝገቦች ጀምሮ እንደ ተከፈተ ሊከራከር ይቻላል። በቻይናም እንደዚህ ነው፣ የተጻፉት ቅርሶች ከ1200 ዓክልበ. ቢገኙም የታሪክ መዝገቦች ከ2400 ዓክልበ. አካባቢ ጀምሮ ላለፈው "አፈታሪካዊ ዘመን" ብዙ መረጃ ያቀርባሉ።

                                     
 • ታሪክ በትክክል እንደሚሰፈን ከተጻፉት መዝገቦች አንስቶ ይጀምራል ከዚያ አስቀድሞ ምንም የተጻፉት መዝገቦች ሳይኖሩ የነበረው ወቅት ቅድመ - ታሪክ ይባላል በአለም ደረጃ መጀመርያው የታወቁት የጽሑፍ ቅርሶች ከ3125 ዓክልበ. ያሕል ሲሆኑ ከጥንታዊ
 • አጼ ቅድመ አሰገድ የአጼ ይግባ ጽዮን ልጅ የአጼይኩኖ አምላክ የልጅ ልጅ ሲሆኑ ከ1296 - 1297 ለአንድ አመት የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ነበሩ ታሪክ ጻህፍት እንደሚሉት አባታቸው ይግባ ጽዮን 5 ወንድ ልጆች ስለነበሩዋቸውና የትኛው ንጉስ
 • በ2008 እ.ኤ.አ. የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ቅድመ ምርጫ ተወዳድረው በሌላኛው ዴሞክራቲክ ተመራጭ ባለጋራቸው ተሸንፈው ወጥተዋል ይሁን እንጂ ከ17 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ስለመረጣቸው በአሜሪካ ቅድመ ምርጫ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ሕዝብ ብዛት ተብሎላቸዋል
 • ሺንሺ ወይም ፔዳል በኮርያ ልማዳዊ አፈ ታሪክ መጽሐፍ ኋንዳንጎጊ ዘንድ በኮርያ ቅድመ - ታሪክ የነበረ መንግሥት ነበረ 2331 - 2108 ዓክልበ. ግድም ቺ ዮው በሺንሺ ነገሥታት ዝርዝር 14ኛው ሲሆን ስሙ ጃውጂ ኋኑንግ ይባላል ከዚያስ
 • ኬልሃይም ጀርመንኛ Kelheim በዳኑብ ወንዝ ላይ በጀርመን አገር የሚገኝ ከተማ ነው በዚህ አካባቢ በጥንት ቅድመ - ታሪክ በሰፊና ታላቅ ግቢ ውስጥ የነበረ ከተማና አምባ እስካሁን በፍርስርሽ ይታያል ኬልቶች በኋላ አርኪሞይኒስ ወይም አልኪሞይኒስ
 • በአለም ላይ የጽሑፍ መጀመርያ ወቅት ስለነበር የታሪክ መጀመርያ ደግሞ ይባላል እንግዲህ የ ድንጋይ ዘመን እና የ ቅድመ - ታሪክ ትርጉም አንድላይ ሊሆን ይችላል የዚህ አከፋፈል ዋጋ አጠያያቂ ነው በብዙ ቦታዎች የናስና የብረት ዕውቀት የገቡት
 • ቫይኪንግ የሚባሉት ነገዶች በአሁኑ ዘመን ኖርዌይ ስዊድን ዴንማርክ አይስላንድ እንዲሁም በአንዳንድ አውሮፓውያን አገሮች የሚኖሩ ህዝቦች ቅድመ አያቶች ናቸው ይህ ታሪክ ነክ ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው እርስዎ ሊያስፋፉት ይችላሉ
 • ሁርኛ ናዋር አሁንም አረብኛ ተል ብራክ በጥንት ከቅድመ - ታሪክ ጀምሮ በስሜን መስጴጦምያ አሁን ሶርያ የተገኘ ከተማ ነበር በብዙ ሥነ ቅርስ ሊቃውንት ዘንድ የቦታው ቅድመ - ታሪክ እስከ 5000 ዓክልበ. ድረስ ይዘረጋል መመሠረቱ ከተጻፉ
 • ግን ለግብጽ ታሪክ ቀድም - ተከትል ትልቅ ሚና አጫወተ ከዚህ በታች ዘመናዊ ምሁራን እንደሚያስቡት እስከሚቻል ድረስ የዝርዝሩን ይዞታ ያሳያል ሌሎችም መፍትሄዎች ሊገኙ ይቻላል መጀመርያ 2.5 ዓምዶች የአፈታሪካዊ ወይም ቅድመ - ታሪካዊ አለቆች
 • ወንጌል ትባል ነበር ዓፄ ልብነ ድንግል የዓፄ ናዖድ ልጅ የዓፄ በአደ ማርያም የልጅ ልጅ ናቸው ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብም ቅድመ አያታቸው ናቸው ዓፄ ናዖድ ፲፫ ዓመት ገዝተው ሲሞቱ በ፲፭፻ ዓ.ም. ዓፄ ልብነ ድንግል ገና የ፲፪ ዓመት ወጣት እያሉ
 • ያህል ጀምሮ ቢታወቅም ከዚያ በፊት ከ1450 እስከ 1100 ዓክልበ. ድረስ ባለው ጊዜ በሚውኬናይ ጽሕፈት የተጻፉ ቅድመ - ግሪክኛ መዝገቦች ከሥነ ቅርስ ተገኝተዋል ይህ ቋንቋ ነክ ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው እርስዎ ሊያስፋፉት ይችላሉ