Back

ⓘ የብረት ዘመን በ ሦስቱ ዘመናት አስተሳሰብ ከናስ ዘመን ቀጥሎ የነበረው ዘመን ነው። በአጠቃላይ እንደ ተለመደ ከ1200 ዓክልበ. ያህል ጀምሮ ያለው ዘመን ያመልክታል። በዚህ ዘመን አብዛኞቹ መሣርያዎችና እቃዎች የተሠሩ ከብረት ነበር። የብረት ዶቃዎች በጥን ..
                                     

ⓘ የብረት ዘመን

የብረት ዘመን በ "ሦስቱ ዘመናት" አስተሳሰብ ከናስ ዘመን ቀጥሎ የነበረው ዘመን ነው። በአጠቃላይ እንደ ተለመደ ከ1200 ዓክልበ. ያህል ጀምሮ ያለው ዘመን ያመልክታል። በዚህ ዘመን አብዛኞቹ መሣርያዎችና እቃዎች የተሠሩ ከብረት ነበር።

የብረት ዶቃዎች በጥንታዊ ግብጽ ጥንታዊ መንግሥት 3000 ዓክልበ ያህል ተገኝተዋል፤ እነዚህ ከተፈጥሮ በረቅ ብረት ተደቀደቁ እንጂ አቃላጮቻቸው ለብረት ቀለጣ በቂ ሙቀት አያሞቁም ነበር። የናስ ቀለጣ ግን መዳብና ቆርቆሮ ያውቁ ነበር።

የብረት ቀለጣ ምናልባት ከ1880 ዓክልበ. ግድም ጀምሮ በሐቲ አገር ይታወቅ ነበር ካሩም ይዩ። ዳሩ ግን የብረት መሣርዮች በጅምላ ተሥረው የነሐስ እቃዎች የተኩ ከ1200 ዓክልበ. በፊት አልሆነም። ከ1200 ዓክልበ. በኋላ "የብረት ዘመን" ሊባል ይችላል። የብረት ጥቅም ደግሞ በአውሮፓ፣ በእስያና በአፍሪካ በሙሉ ከ400 ዓክልበ. በፊት ተስፋፋ። ዓረብ ብረት የሚባሉት ጠንካራ ብረት ውሁድ አይነቶች ከ300 ዓክልበ. ግድም ጀምሮ ከሕንድ አገር ታውቀዋል። ይህም ዓረብ ብረት በ1 ዓም ግድም በታንዛኒያ ይሠራ ጀመር፤ በአውሮጳ ግን ዓረብ ብረት ከ900 ዓም ያህል በፊት አልተሠራም።

የ "ሦስቱ ዘመናት" አስተሳሰብ በመጀመርያ በጥንት በተደረጀው ወቅት፣ "አሁን በብረት ዘመን ውስጥ ነን" የሚል አስተሳሰብ ነበር። ስለዚህ የብረት ዘመን ልክ መቼ እንደ ተጨረሰ አልተወሰነምና ልዩ ሀሣቦች አሉ።

 • 1 ዓም ጨረሰ፣
 • መቸም አልጨረሰም፣ እቃዎች እስካሁን በብረት እየተሠሩ ነውና።
 • እስከ የኢንዱስትሪ አብዮት አዲስ ቴክኖሎጂ፣ 1750 ዓም. ግድም ድረስ ቆየ፣ ወይም
 • 1000 ዓም ጨረሰ፣
                                     
 • ተሥረው የነሐስ እቃዎች የተኩ ከ1200 ዓክልበ. በፊት አልሆነም ከ1200 ዓክልበ. በኋላ የብረት ዘመን ሊባል ይችላል የብረት ጥቅም ደግሞ በአውሮፓ በእስያና በአፍሪካ በሙሉ ከ400 ዓክልበ. በፊት ተስፋፋ የናስ ቀለጣም በደቡብ
 • የታሪክ መጀመርያ ደግሞ ይባላል እንግዲህ የ ድንጋይ ዘመን እና የ ቅድመ - ታሪክ ትርጉም አንድላይ ሊሆን ይችላል የዚህ አከፋፈል ዋጋ አጠያያቂ ነው በብዙ ቦታዎች የናስና የብረት ዕውቀት የገቡት በአንድ ጊዜ ነበረ ለምሳሌ በስሜን አሜሪካ
 • የምናውቀው በኋላ በተዘገቡት ጽሑፎች ብቻ ሲሆን የዚያ ዘመን ታሪክ አፈ ታሪክ ሊባል ይችላል ድንጋይ ዘመን ናስ ዘመን የብረት ዘመን መካከለኛ ዘመን ዘመነ ህዳሴ የብርሃናት ክፍለ ዘመን የኢንዱስትሪ አብዮት የመረጃ ኅብረተሠብ የፈጠራዎች ታሪክ
 • ያህል መካከል የተከሠተው ለውጦች ዘመን ነው በነዚህ አመታት ለውጦቹም የአዲስ ፈጠራዎችና ቴክኖሎጂዎች ፈጣን መስፋፋት ነበሩ ከታላቅ ብሪታንያ ጀምሮ ተስፋፋ የእጅ ሥራ ዘዴዎች በፋብሪካዎች ተተኩ ብዙ የብረት ክፍሎች የነበሯቸው ውስብስብ መኪናነቶች
 • በፍልስጤም ጀመረ ፲፱፻፴፮ ዓ ም - የጀርመን ሃያላት ሙሶሊኒን ከእስር በት እንዲያመልጥ ነጻ አወጡት ፲፱፻፹፪ ዓ ም - የብረት መጋረጃ በኰሙኒስት ሃንጋሪና በኦስትሪያ መሃል ተከፍቶ ወዲያው ብዙ ሺህ የቀድሞው የምሥራቅ ጀርመን ዜጋዎች ወደ ምዕራብ
 • ጀርመን ሲቆዩ ኦሲሪስና ሚስቱ እኅቱ ኢሲስ የብረት ሥራ ግብርና ማዳበር የመድኃኒት ዕፅዋት ጥቅም እና ቢራ ከገብስ መጠመቅ ሁሉ እንዳስተማሩ ይባላል አበንስበርግ በባየርን በአፒስም በዚሁ ዘመን እንደ ተሠራ ይለናል በመጨረሻ የጊጋንቴስ
 • በኪንግስተን ጃማይካ በሌቦች ተገደለ 1981 - ቮየጀር የተባለ ሰው ሰራሽ መንኮራኩር በኔፕቱን ፈልክ አለፈ 1982 - የብረት መጋረጃ በኰሙኒስት ሃንጋሪና በኦስትሪያ መሃል ተከፍቶ ወዲያው ብዙ ሺህ ጀርመኖች ወደ ምእራብ ፈለሱ ነሐሴ 22 ቀን
 • የተንጋደደው የፒሳ ግንብ ላይ በመውጣት የተለያዩ ክብደት ያላቸውን የብረት ኳሶች ወደመሬት በመልቀቅ ሁሉም በዕኩል ሰዓት መሬትን እንደሚመቱ አረጋግጧል ከዚህ በመነሳት እስከሱ ዘመን ይሰራበት የነበረውን የአሪስቶትል አስተሳሰብ ከባድ ነገሮች
 • ናቡከደነጾር እራሱ የባቢሎን ንጉስ የምስሉ ወርቃማ ራስ ነው ከባቢሎን በኋላ ሌላ የሚያንስ መንግሥት ይመጣል ይህም የብረት ደረትና እጆች መሳይ ይሆናል ከሱ ተከትሎ ሦስተኛ የናስ መንግስት ይነሣል ከዚያም አራተኛው መንግሥት እንደሚጨምቅ
 • ከዚያ በፊት ከጥንት ጀምሮ ወርቅና ብር በክብደት ሰቀል ለሸቀጥ ቢጠቅምም ለምሳሌ በካሩም ብዙ ጊዜ ከሌሎች የብረት አይነቶች ጋር ተቀላቅሎ ነበር አሁን የልድያ ንጉሥ ማሕተም የጥረቱ ማረጋገጫ ሆነ በዚህም አዲስ የመሐለቅ ገበያ መጀመርያ