Back

ⓘ ተማረ ባምላኩ. Banks, J የህብረ ባህላዊ አመለካከትን ማዳበር ስለሚያስገኘው ጠቀሜታ በሚከተለው መልኩ ገልፆታል፡፡ በባህላችን አማካኝነት ያዳበርናቸው እሴቶችና እይታዎች እንዴት ዓለምን የምንተረጉምበትን መንገድ እንደሚመሩና እይታችንም ላይ ድርሻ እንዳ ..
                                     

ⓘ ተማረ ባምላኩ

Banks, J የህብረ ባህላዊ አመለካከትን ማዳበር ስለሚያስገኘው ጠቀሜታ በሚከተለው መልኩ ገልፆታል፡፡ በባህላችን አማካኝነት ያዳበርናቸው እሴቶችና እይታዎች እንዴት /ዓለምን የምንተረጉምበትን መንገድ/ እንደሚመሩና እይታችንም ላይ ድርሻ እንዳላቸው እንድናስተውል የሚረዳ አቅም ይፈጥርልናል፡፡ ጎልቶ የሚታየው ባህል እንዴት በሌሎች ባህሎች አባላት ግምት ላይ ጫና ሊፈጥር እንደሚችል ያሳውቃል፡፡ አገልግሎት ሰጭዎችና ባለሙያዎች ከሌሎች የባህል አባላት ጋር እንዴት ተግባብቶ ማድረግ እንደሚገባቸው ግንዛቤ ይፈጥርልናል፡፡ ለሁሉም ባህሎች፣ ብሔረሰቦችና የእምነት ተከታዮች እኩል የሆነ አዎንታዊ እይታ እንድናዳብር የሚያስችል አቅም ይፈጥርልናል፡፡ ተረስተው እና ትኩረት አጥተነው የነበሩ ህዝቦች በባህላቸው፣ በብሔረሰባቸውና በሚከተሉት እምነት ሳይሸማቀቁ በዜግነታቸው የሚኮሩበትን ስነልቦናዊ አቅም ያዳብርላቸዋል፡፡ በአጠቃላይ ህብርባህላዊ አመለካከት ማዳበር ራሳችንን የምንገነዘብበትን መንገድ ያጎለብትልናል፡፡