Back

ⓘ የሳይንስ ፍልስፍና. የሳይንስ ፡ ፍልስፍና የሳይንስ መሠረቶችን ፣ ዘዴዎችን እና መዘዞችን በጥልቀት የሚያጠና የፍልስፍና ዘርፍ ነው። ሳይንስን ከሌሎች የ ዕውቀት ዓይነቶች የሚለየው ምንድን ነው? ምን ዓይነት ዕውቀት ሳይንስ ሊባል ይችላል? ምን ዓይነትስ ..
የሳይንስ ፍልስፍና
                                     

ⓘ የሳይንስ ፍልስፍና

የሳይንስ ፡ ፍልስፍና የሳይንስ መሠረቶችን ፣ ዘዴዎችን እና መዘዞችን በጥልቀት የሚያጠና የፍልስፍና ዘርፍ ነው። ሳይንስን ከሌሎች የ ዕውቀት ዓይነቶች የሚለየው ምንድን ነው? ምን ዓይነት ዕውቀት ሳይንስ ሊባል ይችላል? ምን ዓይነትስ አይባልም? የሳይንስ ጽንሰ ሓሳቦች የቱን ያክል አስተማማኝ ናቸው? የዚህ ሁሉ የሳይንስ ዕውቀት የመስተጨረሻ ግብ ምንድን ነው? የሰውን ህይወት ማሻሻል ነው? ወይንስ ስለከባቢ ዓለም ዕውነትን ለማዎቅ ነው? እነዚህ ጥያቄዎች የዚህ ፍልስፍና ዋና ትኩረት ናቸው።

ተጨባጩን ዓለም ለመገንዘብ በተደረጉ ጥረቶች፣ ከጥንት ጀምሮ ብዙ ዓይነት ሐሳቦች ፈልቀዋል። እነዚህ ጥረቶች፣ በአንድ ወይም በሌላ ምክንያት ምናባዊን አለም፣ መናፍስትንና እና ሌሎች ተጨባጭ ያልሆኑ ነገሮችን ያሳተፉ ነበሩ። ሆኖም ቀስ በቀስ፣ አንዳንድ ፈላስፋዎች እነዚህ ለሽህ ዓመታት የተሰራባቸው ሐሳቦች ከባድ ስህተት እንዳለባቸው ፤ ይባስ ብሎም ለቀጣይ የመሻሻል እርምጃ እንቅፋት እንደሆኑ ማሳዎቅ ጀመሩ።

ይህ የተጠራቀመ ትችትና ቅሬታ በአውሮጳ የሳይንስ አብዮትን አስከተለ። የዛሬ አራት መቶ ዓመት አካባቢ የነበሩ ፈላስፎች በውርስ ባገኙት የጥንታዊት ግሪክ ፍልስፍናዎች ላይ አመጽ በማድረግ የዘመናዊውን ሳይንስ መሰረት ጣሉ። የተጨባጩን አለም ለመረዳት ተጨባጩ ዓለም በቂ ነው። ተጨባጩን ዓለም ለመረዳት፣ ከተጨባጩ ዓለም ውጭ መንስዔ መፈለግ አላስፈላጊ መሆኑን በማስረገጥ አዲሱን ሳይንስ መገንባት ጀመሩ።

ይህም እጅግ በጣም የተሳካ ፍልስፍና ስለነበር ሰዎች ስለተፈጥሮ ያላቸው ግንዛቤ በከፍተኛ ፍጥነት እንዲያድግ አድርጓል። ባሁኑ ዘመን ላለው የምዕራባዊው ዓለም የህክምና፣ እርሻ እና ቴክኖሎጂ ውጤቶች መትረፍረፍ ከፍተኛ ፋይዳ ያለው ክስተት ነው።

                                     
  • ፍልስፍና ሥነ አምክንዮ ሥነ ምግባር ሥነ ዕውቀት የሳይንስ ፍልስፍና ቀልበኝነት ሐሳባዊነት ቁሳ አካላዊነት መዋቅራዊነት ኅልውነት ፋሺዝም ሶሻሊዝም ኮሚኒዝም ታዖይዝም
  • ቤከን Francis Bacon 1553 - 1618 ዓም. የኢንግላንድ ፈላስፋና ሳይንቲስት ነበር የሳይንስ ፍልስፍና እና የልማዳዊነት ፍልስፍና መሥራች ተብሏል ይህ ስለ ሰው ሕይወት የሆነ ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው እርስዎ ሊያስፋፉት
  • አጋጣሚ ዕውነት ተቃራኒ ዕውነት ሊሆን ይችል ስለነበር ስለሆነም የሳይንስ አረፍተነገሮች ከተጨባጩ አለም አንጻር መፈተን ይገባቸዋል ከአለም ጋር አብረው እሚሄዱ የሳይንስ ዕውቀቶች ቀስ ብለው ኅልዮት በኋላም የተፈጥሮ ኅግጋት ለመባል ይበቃሉ
  • ምስስል በየሳይንስ ፍልስፍና ውስጥ የአንድ አመክንዮአዊ ዓረፍተ ነገርን እውነትነት እና ውሸትነት መካከል ያለውን ልዩነት መለያ ዘዴ ነው መነሻው ሃሳብም ማናቸው የሳይንስ ኅልዮቶች በአጠቃላይ መልኩ ውሸት ቢሆኑም ዳሩ ግን አንዳቸው ከሌላው
  • ወይም በጣልያን ማብራራቱ አነስተኛ ሚና አጫወተ በዚህ ወቅት ዘመናዊ ከነበሩት ሃሣቦች መሃል ምክኑያዊነት የሳይንስ ፍልስፍና ጥቅማዊነት ለሴ ፈር ዴሞክራሲ እኩላዊነት ብሔራዊ መብቶች ሃይማኖታዊ መታገሥ እንዲሁም በዚህ ወቅት የምጣኔ ሀብት
  • ሳይንስ ከሌሎች የዕውቀት ዘርፎች ለምሳሌ ፍልስፍና ወይም ሂሳብ ወይም ስነ ሃይማኖት የሚለይበት ዋናው ቁም ነገር የሳይንስ ዘዴን በመጠቀሙ ነው እርግጥ ነው ሳይንሳዊ ዘዴ ተብሎ የሚታወቀው ስርዓት ብዙ ጊዜ በዝርዝር ድረጃ በድረጃ በሚከተለው
  • ዘመን ሳይንስ ማለት ዕውቀት ማለት አይደለም ሳይንስ የዕውቀት ዘርፍ ነው እንጂ ሁሉ ዕውቀት ሳይንስ አይደለም ፍልስፍና ለምሳሌ ሳይንስ አይደለም ምንም እንኳ ዕውቀት ቢሆንም ሂሳብ ለምሳሌ ሳይንስ አይደለም ዕውቀት ይሁን እንጂ ሳይንስ
  • በዘመኑ የሳይንስ አብዮት በአውሮጳ እንዲፈነዳ ጉልህ አስተዋጾ አድርጓል ዴካርት በ17ኛው ክፍለ ዘመን ግዙፍ ስም ያገኘ ፈላስፋ ሲሆን በተለይ በአውሮጳ አህጉር በምክኑያዊነት rationalism ፍልስፍና ታዋቂነትን ያተረፈና ከሱ ፍልስፍና ተነሰተው
  • በቀድሞው ወቅት ሳይንስ ሳይራቀቅ ቴክኖሎጂም ዓለምን በፍጥነት ከመቀየሩ በፊት የነበሩት የጥንት ፈላስፎች ለአሁኑ ዘመን የሳይንስ እድገት የራሳቸውን አሻር አሳርፈዋል ታዲያ የጥንት ፈላስፎች ሲነሱ የአንበሳውን ድርሻ የሚወስዱት የግሪክ ፈላስፎች