Back

ⓘ የኮሞዲቲ ገበያ. ይህ ገጽ በመታደስ እና በመስተካከል ሁኔታ ላይ ነው። በኮሞዲቲ ገበያ ውስጥ ሻጭም ሆነ ገዢ የሚዋዋልበትና የመነጋገጃው ዘዴ ከሌላው ገበያ አይነት ለየት የሚያደርገው ውሉ በኮንትራት ነው። ይህም ማለት መጀመሪያ ለመገበያየት በኮምፒውተር ላ ..
                                               

የብረት ማዕድኖች

ብር ፤ እንግሊዝኛ silver /ሲልቨር/ የተባለው ማዕድን ደግሞ ተፈላጊነቱ በድሮ ጊዜ ለመገበያያነት ቀጥሎም ለተለያዩ የንብረት እቃዎችና የፋብሪካ ውጤቶች አገልግሎቱን የሚሰጥ የማዕድን ብረት ነው። ንፁህ ብር የሚባለው ብዙውን ጊዜ ዘጠና ሁለት ነጥብ አምስት ያክሉን ሲልቨር የሚይዘው ነው። የተቀረው ሰባት ነጥብ አምስት ከመዳብ ኮፕር - ወይንም ከሌላ የብረት ማዕድን ጋር የሚደባለቀው ነው። የአጠቃላይ ስሙም እስተርሊንግ ሲልቨር ይባላል። መደባለቁ የሚጠቅመው የብር ይዘቱን ለማጠንከር ወይንም በቀላሉ ከውስጡ ያሉትን ንጥረ ማዕድኖች በሙቀት ጊዜ ወይንም በቅዝቃዜ መጠናቸው እንዳይለወጥ ነው። በኮሞዲቲ ገበያ ውስጥ በሚሸጥበትና በሚገዛበት ጊዜ በሁለት መመዘኛ መልክ ነው። አንደኛው በአምስት ሺህ ትሮይ አውንስ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በአንድ ሺህ ትሮይ አውንስ ነው። የንግድ መገበያያ ምልክታቸውም- ኤስ አይ SI - ለባለ አምስት ሺህ ትሮይ አውንስ ሲሆን -ዋይ አይ YI- ደግሞ ለባለ አንድ ሺህ ትሮይ አውንስ ነው።

የኮሞዲቲ ገበያ
                                     

ⓘ የኮሞዲቲ ገበያ

ይህ ገጽ በመታደስ እና በመስተካከል ሁኔታ ላይ ነው። በኮሞዲቲ ገበያ ውስጥ ሻጭም ሆነ ገዢ የሚዋዋልበትና የመነጋገጃው ዘዴ ከሌላው ገበያ አይነት ለየት የሚያደርገው ውሉ በኮንትራት ነው። ይህም ማለት መጀመሪያ ለመገበያየት በኮምፒውተር ላይ ፤ አካውንት መክፈት ያስፈልጋል። በአካውንት መክፈቻ ጊዜ የኢንቬስትመንት ባንኩ የሚጠይቀው የመነሻ መጠን አለ። ብዙ ጊዜ ከአምስት ሺህ ዶላር በላይ ነው። ይህ መጠን ለአንድ ኮንትራት በቂ ነው። ለምሳሌ አንድ ኮንትራክት እንደየ ኮሞዲቲው አይነት እስከ ሦስት ሺህ እና ከዚያም በላይ ይደርሳል። በአንድ ቀን ጥዋት ውስጥ ሁሉም ለማጣት ወይንም ሁለት እጥፍ አድርጎ ለማርፈድ ይቻላል። ለዚህ ነው ብዙ ጊዜ የኢንቬስትመንቱ ባንክ ደላላ በቅድሚያ ስለገበያው ሁኔታ ማወቃችሁን ማረጋገጥ የሚፈልገው። ዋናው መሠረቱ ከሚገዛው የኮሞዲቲ ኮንትራት እኩል ስለ ገበያው አካሄድ ሁኔታ ማወቅ ያስፈልጋል። በኮሞዲቲው ዋጋ ላይ የትንሽ ሳንቲሞች ልዩነት በኮንትራቱ ይዘት ላይ ቶሎ ለውጥን ያሳያል። ከመቶዎች ዶላር እስከ ሺህ በላይ በአንድ ኮንትራክት ውስጥ። አብዛኛው ኮሞዲቲ የሚገዛና የሚሸጥ ሰው ፤ ትርፉንም ሆነ ኪሳራውን በቶሎ አውቆ ወይ መሸጥ ወይም መቆየት ይችላል። መጀመሪያ አካውንቱ ውስጥ ካለው ገንዘብ ላይ ኮሞዲቲውን በኮንትራት ይገዛል። ኮንትራቱም የሚለው የዚህ አይነት ኮሞዲቲ ኮንትራክት በዚህ ወር ላይ የሚያልቀውን በዝህ ያክል ዋጋ ገዝቷል ፤ ወይም የዚህ አይነት ኮሞዲቲ በዚህ ወር ላይ ኮንትራቱ የሚያልቀውን በዚህ ያክል ዋጋ ይሸጣል ነው የሚለው። እና ገዢው ወይም ሻጩ ሰው የኮንትራቱ ጊዜ ሳያልቅ በፊት ትርፉን ወይም ኪሳራውን ተገንዝቦ ከኮንትራቱ መውጣት ይገባዋል። ካለበለዚያ ኮንትራቱ ካለቀ በኋላ እዳ ውስጥ ገብቶም ቢሆን መግዛትና ወዳ ቤቱ ለማስጫን በኮንትራቱ ይገደዳል። ነገር ግን በኮሞዲቲ ገበያ ውስጥ ፤ አብዛኛው የገበያ ተዋናኝ ፤ ማለትም ከዘጠና በመቶው በላይ ፤ የኮንትራቱ ቀን እስከሚደርስ ሳይጠብቅ ኪሳራውን አምኖ ወይንም እጥፍ ትርፉን ወስዶ ከኮንትራክቱ ውስጥ ይወጣል። ከዚያም ወደ ሌላ ኮሞዲቲ በመሄድ ግዥ እና ሽያጩን ያካሄዳል። በዚህ አርስት ላይ በተለያይ ጊዜ ጨማምሬ ለመፃፍ እሞክራለሁ። በቶሎ ይሚገባ ሊሆን አይችልም ፤ ቢሆንም ብዙ የማወቅ ልምምድ ያስፈልገዋል ካለበለዚያ ውጤቱ በጣም አክሳሪ ነው የሚሆነው።

                                     
  • ምክንያቱም ዋነኛው የኮሞዲቲ ገበያ ላይ ንግድ እንደማንኛውም የንግድ ዘርፍ ትርፍ በብዛት ለማግኘትና ኪሳራን ለመቀነስ ሲሆን በኮሞዲቲ ንግድ ላይ ደግሞ የወደፊቱ ዋጋ ስንት ሊሆን እንደሚችል ለመገመትና ኪሳራን አስወግዶ አትራፊው ገበያ ይትኛው እንደሚሆን
  • አንድ ነጥብ አስር ግራም ሲባዛ በአንድ መቶ ነው ውጤቱን ወደ ግራምና ወደ ኪሎግራም ለማወቅ ያክል ማግኘት ቢቻልም የኮሞዲቲ መገበያያ መጠኑ በኮንትራት ቁጥር ብዛትና በትሮይ አውንስ ክብደት መለኪያ ነው የወርቅ ኮንትራት የሚሸጡባቸው ቦታዎች