Back

ⓘ የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ውስጥ የሥነምግባር መከታተያ ኮሚሽን ነው። የኮሚሽኑ ተጠሪነት በቀጥታ ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ነው። የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ክቡር አቶ ዓሊ ሱለይማን ሲሆኑ ምኮሚሽነሩ ደግሞ ክቡር አ ..
የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን
                                     

ⓘ የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን

የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ውስጥ የሥነምግባር መከታተያ ኮሚሽን ነው። የኮሚሽኑ ተጠሪነት በቀጥታ ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ነው። የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ክቡር አቶ ዓሊ ሱለይማን ሲሆኑ ም/ኮሚሽነሩ ደግሞ ክቡር አቶ ወዶ አጦ ናቸው። ኮሚሽኑ "ሥነምግባር" የተባለ በዓመት አራት ጊዜ የሚታተም መፅሄት እና "መስታወት" የተባለ በዓመት ሁለት ጊዜ የሚወጣ ኒውስሌተር አለው።

                                     

1. አመሠራረት

እ.ኤ.አ. በ1996 በብሔራዊ ደረጃ የተጀመረው የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ፕሮግራም የሥነምግባር ንዑስ ፕሮግራምን በውስጡ የያዘ ነበር። የስነምግባር ንዑስ ፕሮግራም አንድ ፕሮጀክት ኮሚሽኑን ማቋቋም ነበር። የፕሮጀክቱም ስም የስነምግባር መከታተያና ማዕከላዊ አካል ማቋቋሚያ ፕሮጀክት የሚል ነበር። በዚህም መሰረት የፌደራል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ግንቦት ፲፮ ቀን ፲፱፻፺፫ ዓ.ም. በአዋጅ ተቋቋመ።

                                     

2. መዋቅር

ኮሚሽኑ ዘጠኝ ዳይሬክቶሬቶችና ሁለት አገልግሎቶች አሉት። በተጨማሪም የኮሚሽኑን ውስጣዊ አሠራርን የሚከታተል የሥነምግባር መከታተያ ጽ/ቤት አለ። ይህም ጽህፈት ቤት በአቶ ሃረጎት አብርሃ ይመራል። የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን እስከ መጋቢት ፴ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. ድረስ 315 ሠራተኞች ያሉት ሲሆን ከዚህ ውስጥ 101 ሴቶች ናቸው።

የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ዋና መስሪያ ቤት አዲስ አበባ ይገኛል። በድሬዳዋ ከተማ የሚገኘው የኮሚሽኑ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተመረቀው በመጋቢት ፲፩ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. ሲሆን በአሁኑ ወቅት 21 ሠራተኞች አሉት።

                                     

3. በጀት

ኮሚሽኑ ከመንግስት በ፳፻፪ ዓ.ም. 16.23 ሚሊዮን ብር፣ በ፳፻፫ ዓ.ም. 26 ሚሊዮን 93 ሺህ 930 ብር፣ በ፳፻፬ ዓ.ም. ደግሞ 34 ሚሊዮን 840 ሺህ ብር የተመደበለት ሲሆን ከሌሎች አለም አቀፍ ተቋማት በየዓመቱ የሚያገኘው ገንዘብም አለ።