Back

ⓘ ኣያና ብሩ. ኢንጂነር ኣያና ብሩ የአማርኛ የጽሕፈት መሣሪያንና በመሣሪያው የኣከታተቡን ዘዴ የፈጠሩ ኢትዮጵያዊ ሊቅ ናቸው። ከኣድዋ ድል በኋላ ኢትዮጵያውያን የእንግሊዝኛውን የታይፕራይተር ወይም የጽሕፈት መሣሪያ ኣጠቃቀም ከተረዱ ወዲህ መሣሪያውን ለኣማርኛ ..
                                     

ⓘ ኣያና ብሩ

ኢንጂነር ኣያና ብሩ የአማርኛ የጽሕፈት መሣሪያንና በመሣሪያው የኣከታተቡን ዘዴ የፈጠሩ ኢትዮጵያዊ ሊቅ ናቸው።

ከኣድዋ ድል በኋላ ኢትዮጵያውያን የእንግሊዝኛውን የታይፕራይተር ወይም የጽሕፈት መሣሪያ ኣጠቃቀም ከተረዱ ወዲህ መሣሪያውን ለኣማርኛ ቀለሞች እንዲያገለግል ለ85 ዓመታት ግድም ቢታገሉም ሳይሳካ ቀርቷል። በመካከሉ ከተደረጉት የተለያዩ ሙከራዎች መካከል የኢንጂነር ኣያና ሥራ ኣንዱ ነበር። ዋናውም ችግር የመሣሪያው መርገጫዎች በኣማርኛ ፊደላት መብዛት የተነሳ በቂ ስለኣልነበሩ ፊደላቱን ከተለያዩ መርገጫዎች በመሰብሰብ በመቀጣጠል የሚያስከትብ ዘዴ ወደ ፲፱፻፳፭ ዓ.ም. ግድም ኣቀረቡ። በእዚህ ዘዴ" ሀ” ከኣንድ መርገጫ ከተከተበ በኋላ" ሁ” ፊደል የሚከተበው" ሀ” ጎን የመቀነስ ምልክትን ወይም" -” በማስቀመጥ ነበር። ይኸንኑ የመቀነስ ምልክት" ለ”፣" ሐ”፣" መ” እና የመሳሰሉት ጎን በማስቀመጥ" ሁ”፣" ሉ”፣" ሑ”፣" ሙ” ስለሚመስሉ ኣንዱኑ መቀጠያ ለተለያዩ የፈጠራ ቁርጥራጮች እንዲሆን ተደረገ። እንደነ" ሹ” የመሳስሉትን በቅጥልጥል ለመክተብ ከ" ሰ” እና የመቀነስ ምልክት የተሠራውን" ሱ” ፊደል በሌላ መርገጫ ቀደም ብሎ ወይም ወደኋላ መልሶ ሌላ ረዥም መሰመር ከሌላ መርገጫ ከ" ሰ” ኣናት ላይ በማስቀመጥ ነበር የሚሠራው።

ይህ የቅጥልጥል ፊደል ኣሠራርና መኖር ዓማርኛ ባልሆነ ነገር ቀለሞቹን በመሰሉ ነገሮች የቢሮ ሥራ መሥራት ስለተቻለ ኣያና ብሩ ለኢትዮጵያ ታላቅ ባለውለታ ናቸው። የኣያና መሣሪያ ባይኖር ኖሮ የቢሮ ጽሑፎችን በእጅ ጽሑፍ ተጠቅሞ መቀጠል ማዛለቁ ስለሚያጠራጥር ኢንጂነር ኣያና ለዓማርኛ እድገት ክፍተኛ ኣስተዋጽዖ ኣድርገዋል። እንዲህም ሆኖ ትክክለኛውን የግዕዝ ቀለሞች የኢትዮጵያ ማተሚያ ቤቶች ቀደም ብለው ሲጠቀሙባቸው ስለነበርና በኋላም ሲጠቀሙበት ስለነበረ የታይፕ ፊደል ከማተሚያ ቤቶቹ ጋር ግንኙንት ኣልነበረውም። የኣያና የጽሕፈት መኪና ቀለሞችም የዓማርኛ ፊደላት ኣልነበሩም፤ ሊሆኑም ኣይችሉም። ይህ ልዩነት ያልገባቸውና ከመቶ ያነሱ መርገጫዎች ላይ የተበተኑትን የታይፕ ቁርጥራቾጭ ከ፪፻ በላይ የሆኑት የዓማርኛ ቀለሞች ኣንድ የሚመስሏቸው ዛሬም ኣሉ።

የኢንጂነሩ የጽሕፈት መኪና ፊደል እንደ እንግሊዝኛው ወደ ኮምፕዩተር መግባት ነበረበት የሚሉ ቢኖሩም የእንግሊዝኛው ቅጥልጥል ስላልሆነና ትክክለኛዎቹን ቀለሞች ስለከተበ ነው ወደ ኮምፕዩተር የተሻሻለው። የዓማርኛው መሣሪያ ግን ዓማርኛ ስላልከተበ ወደ ኮምፕዩተር መግባት የለበትም ብለው በጽሑፍ ተከራክረው ያስቀሩት ዶ/ር ኣበራ ሞላ ናቸው።