Back

ⓘ መላከ ህይዎት ነቃ ጥበብ እሸቱ. መላከ ህይዎት ነቃጥበብ እሸቱ ከአባታቸው ከአቶ አሸቱ ይመር እና ክእናታቸው ከወሮ አየናለም በ ፩፱፳፮ በደቡብ ወሎ ዞን በወልደያ ከተማ ተወለዱ። እድሜያቸው ለትምህርት እስኪደረስ ድረስ ልክ እንደማንኛውም ህጻን ቤተሰቦቻቸ ..
                                     

ⓘ መላከ ህይዎት ነቃ ጥበብ እሸቱ

መላከ ህይዎት ነቃጥበብ እሸቱ ከአባታቸው ከአቶ አሸቱ ይመር እና ክእናታቸው ከወ/ሮ አየናለም በ ፩፱፳፮ በደቡብ ወሎ ዞን በወልደያ ከተማ ተወለዱ። እድሜያቸው ለትምህርት እስኪደረስ ድረስ ልክ እንደማንኛውም ህጻን ቤተሰቦቻቸውን በተለያዩ ስራዎች ሲረዱ ከቀዩ በኃላ ፯ ዓመት ሲሞላቸው ወደ ደቡብ ጎንደር ምስራቅ እስቴ ወረዳ በመሄድ ከወረዳው ዋና ከተማ ፲ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ቁት አረጋዊ ቤተ ክረሰቲያን የመንፈሳዊ ትምህርታቸውን ጀመሩ። ገና ከህጻንነታቸው ጀምሮ በትምህርት አቀባበላቸው መምህራኖቻቸውን በማስደነቃቸው ከሌሎች ተማሪዎች የተለየ ትምርት እንዲማሩ ይደረግ ነበር። ከላይ ከፍ ሲል ከተገለጸው የማዕረግ ስም በፊት የመጠረያ ስማቸው መኳንንት ነበር። ትምህርታቸውንም በአጭር ጊዜ ከዳዊት ደገማ አስከ ከፍተኛ ንባብ ፣ ከውዳሴ ማርያም እስከ ጸዋትወ ዜማ ትምህርታቸውን በማጠነቀቅ መምህሮቻቸውን አስደመሙ።