Back

ⓘ ሚሌሲያን በአይርላንድ አፈ ታሪክ ዘንድ፣ አይርላንድን በጥንት ከወረሩት ነገዶች መጨረሻዎች ነበሩ። ከሚሌሲያን አስቀድሞ አይርላንድን የሠፈሩት ፬ ሕዝቦች - የፓርጦሎን ሕዝብ፣ የነመድ ሕዝብ፣ ፊር ቦልግ፣ እና ቱአጣ ዴ ዳናን - ሁላቸው የማጎግ ዘር ይባላሉ ..
                                               

ሪፋት

ሪፋት በኦሪት ዘፍጥረት 10:3 መሠረት የጋሜር ያፌት ፪ኛ ልጅ ነበር። በ፩ ዜና መዋዕል 1:6 ደግሞ ሲጠቀስ፣ በአንዳንድ ዕብራይስጥ ቅጂ ስሙ በስኅተት ዲፋት ይባላል። ፍላቪዩስ ዮሴፉስ እንዳሰበው፣ ሪፋት የወለዳቸው ብሄር "ሪፋትያውያን፣ አሁንም ጵፍላጎንያውያን የተባሉት" ነበር። ቅዱስ አቡሊደስ ደግሞ ሪፋት የ "ሳውሮማትያውያን" አባት አንደ ሆነ ጻፉ። ሪፋት ብዙ ጊዜ ከሪፋያዊ ተራሮች ጋር ግንኙነት እንዳለው ይታስባል። በጥንታዊ ግሪኮች ታሪክ ጸሐፍት ዘንድ በሪፋያዊ ተራሮች ግርጌ ሪፋያውያን፣ አሪምፋያውያን ወይም አሪማስፒ የተባለ ብሔር ይገኝ ነበር። እነዚህ ተራሮች መታወቂያ ባብዛኛው ጸሐፍት ዘንድ ከዑራል ተራሮች ሰንሰለት በዛሬው ሩስያ ጋር አንድላይ ነው። በመጽሐፈ ኩፋሌ ሰንሰለቱ "ራፋ" ይባላል። በአውጉስት ቪልሄልም ኖበል ሃልዮ ዘንድ፣ ሪፋት ቄልታውያንን ወለዳቸው። በፕሉታርክ መሠረት ቄልታውያን ከራፋ ተራሮች ወደ ስሜን አውሮፓ ተሻግረው ነበርና። በመካከለኛው ዘመን በአይርላንድ አፈታሪክ ደግሞ የአይርላንድና የስኮትላንድ ኗሪዎች ...

ሚሌሲያን
                                     

ⓘ ሚሌሲያን

ሚሌሲያን በአይርላንድ አፈ ታሪክ ዘንድ፣ አይርላንድን በጥንት ከወረሩት ነገዶች መጨረሻዎች ነበሩ።

ከሚሌሲያን አስቀድሞ አይርላንድን የሠፈሩት ፬ ሕዝቦች - የፓርጦሎን ሕዝብ፣ የነመድ ሕዝብ፣ ፊር ቦልግ፣ እና ቱአጣ ዴ ዳናን - ሁላቸው የማጎግ ዘር ይባላሉ። በተቀራኒ የኚህ ሚሌሲያን ሃረገ ትውልድ ግን ከማጎግ ሳይሆን ከጋሜርና ከፌኒየስ ፋርሳ እንደ ደረሰ ይጻፋል።

                                     

1. ሌቦር ጋባላ ኤረን

በ ሌቦር ጋባላ ኤረን ዘንድ የሚሌሲያን ወላጆች አለቆች ከጋሜር እንዲህ ነው፦

 • አግኖማይን - ኖሚየስን ገድሎ እስኩቴስን ገዛ።
 • አግኒ
 • ኑዋዱ
 • ኔል - ወንድሙን ነኑዋልን ገድሎ ወደ ግብጽ ሸሸ፤ የፈርዖንን ሴት ልጅ ስኮታ አገባት። ይህ በኒኑስ ዘመን እንደ ሆነ ይባላል።
 • ፌኒየስ ፋርሳ - ለ፵ ዓመታት የእስኩቴስ ንጉሥ
 • ኤበር ስኮት - እስኩቴስን ከኑኑዋል ልጆች ያዘ።
 • ብራጥ - ከጥቁር ባሕር አጠገብ ተነስተው በክሬታና በሲኪልያ በኩል ወደ እስፓንያ ደረሱ። 140 ሰዎች
 • ኢባጥ ሪፋት
 • ቧማይን - በነኑዋል ልጅ ኖሚየስ ዕጅ ተገደለ።
 • ኢጥ - አይርላንድን ከእስፓንያ አይቶ ወደዚያ ተጓዘ፤ ይህም በቱዋጣ ዴ ዳናን ነገሥታት ማክ ኲል፣ ማክ ኬክትና ማክ ግሬን ዘመን ነበር፤ ኢጥ በአይርላንድ ሲጎበኝ ስለ ተገደለ፣ ቂሙን ለማብቀል የብሬውጋን ልጆች አሁን 1.500 ሰዎች አይርላንድን ወረሩ።
 • ላምፊንድ
 • ዴጥ
 • ፪ አግሞናይን - ሬፍሎይርን ገድሎ ሕዝቡ ወደ ጥቁር ባሕር አጠገብ ሸሹ 180 ሰዎች፣ ብሔሩም በዚያ ፫ መቶ ዓመታት ቀሩ።
 • ጋሜር - የያፌት ልጅ
 • ስሩ - ሕዝቡ ከግብጽ ወደ እስኩቴስ ተመለሱ 204 ሰዎች። ይህ ሚሌሲያን ወደ አይርላንድ ሳይገቡ 440 ዓመታት በፊት እንደ ሆነ ይባላል።
 • ኤስሩ
 • ኤርቃ
 • ኤበር ግሉንፊንድ
 • በዓጥ
 • ጋይድል ግላስ - ጎይደልኛ ፈጠረ የአይርላንድኛና የስኮትላንድ ጋይሊክኛ ወላጅ።
 • አሎት
 • ታት - የኖሚየስ ልጅ ሬፊልን ገድሎ እስኩቴስን ገዛ፤ በሬፊል ልጅ ሬፍሎይር ዕጅ ተገደለ።
 • ፌብሪ ግላስ
 • ነኑዋል
 • ብሬውጋን - ብሪጋንቲያ ከተማ በእስፓንያ ሠራ።

"ሚሌሲያን" የሚለው ስያሜ ከብሬውጋን ሌላ ልጅ ቢሌ ልጅ ጋላም መጠሪያ "ሚል ኤስፓኝ" ነው። በሮማይስጥ የተጻፈው ሂስቶሪያ ብሪቶኑም የብሪታንያውያን ታሪክ "ሚሌስ ሂስፓኒያይ" የእስፓንያ ወታደር ስላለው ነው። እንዲያውም የብሔሩ ስም በትክክል "ጋይደሎች" ተባለ፤ ከዚያ አይርላንድን ከገዙት ከፍተኛ ነገሥታት አብዛኖቹ ከዚያው ሚል ጋላም ዘር ስለ ተወለዱ "ሚሌሲያን" ይባላሉ። የጋይደሎች አለቃ የ "ሚል" ጋላም ልጅ አመርጊን ሲሆን ቱዋጣ ዴ ከተሸነፉ በኋላ ከፍተኛ ንጉሥነቱን ለወንድሞቹ ለኤቤር ፊን በደቡብ እና ለኤሪሞን በስሜን አካፈለ።

                                     

2. የሚሌሲያን ወረራ ጊዜ በልዩ ልዩ አቆጣጠሮች

በ ሌቦር ጋባላ አቆጣጠር ዘንድ በኋለኞቹ ቅጂዎች ጋይደሎች አይርላንድን የወረሩት በታላቁ አሌክሳንድር ዘመን በ336 ዓክልበ. ሆነ። ከዚህ ጋር በሚሔደው ነገሥታት ዝርዝር መሠረት ግን፣ ጋይደሎች አይርላንድን የገቡ በእስራእል ንጉሥ ዳዊት ዘመን ወይም 1000 ዓክልበ. ግድም ሆነ። የአራት ሊቃውንት ዜና መዋዕሎች በተባለው ታሪክ መሠረት ግን አይርላንድን ከቱዋጣ ዴ ዳናን የያዙት በ1708 ዓክልበ. ሆነ። የአይርላንድ ታሪክ ባለው አቆጣጠር ደግሞ ይህ ወረራ በ1295 ዓክልበ. ሆነ። ከሁሉ ጥንታዊ የሆነውም ምንጭ ሂስቶሪያ ብሪቶኑም እንዳለው ወረራው በሮሜ መጀመርያ ቆንስላ ሉክዩስ ዩንዩስ ብሩቱስ ዓመት 517 ዓክልበ. ሆነ።

በአይርላንድ ዝርዝሮች መካከል ከሁሉ ቀድሞ የተቀነባበረው የላውድ አቆጣጠሮች 1012 ዓም ሲሆን በዚህ በኩል የሚሌሲያን ወረራ በዳዊት ልጅ ሰሎሞን ዘመን ነበር 950 ዓክልበ. ሲል፣ በውስጡ ያሉት የነገስታት ዘመናት በጥንቃቄ ሲደመሩ ወረራው በ1305 ዓክልበ. ያሕል እንደ ሆነ ይመስላል።

በተጨማሪ የእስፓንያ ነገሥታት ዝርዝር 773-744 ዓክልበ. ግድም "ሚሌሲያን" በኢቤሪያ እንደ ገዙ ይላል።

 • የአይርላንድ ነገሥታት ዝርዝር