Back

ⓘ የኮርያ ጦርነት በኮርያ ከሰኔ 18 1942 እስከ ኃምሌ 20 1945 የተዋገ ጦርነት ነበር። የኮሪያ ዘማቾች ትውስታ ሬሳ እንኳ አልተማረከብንም” አለመማረክ የጀግንነት ጉዳይ አይደለም” በአምስት ዙር ኮርያ ከዘመቱት 6037 ኢትዮጵያውያን መካከል 122ቱ በ ..
የኮርያ ጦርነት
                                     

ⓘ የኮርያ ጦርነት

የኮርያ ጦርነት በኮርያ ከሰኔ 18 1942 እስከ ኃምሌ 20 1945 የተዋገ ጦርነት ነበር። የኮሪያ ዘማቾች ትውስታ ሬሳ እንኳ አልተማረከብንም”" አለመማረክ የጀግንነት ጉዳይ አይደለም” በአምስት ዙር ኮርያ ከዘመቱት 6037 ኢትዮጵያውያን መካከል 122ቱ በጦርነቱ ሞተዋል፡፡ አንዳቸውም አልተማረኩም ሳይማረኩ ግዳጃቸውን ፈጽመው ከተመለሱት 350ው የዛሬ 20 ዓመት የኢትዮጵያ ኮርያ ዘማቾች ማህበርን መስርተው ሰሞኑን የዘመቻውን 61ኛ ዓመት አክብረዋል፡፡ የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ መልካሙ ተክሌ ከአስር አለቃ ዘነበወርቅ በላይነህ እና ከየኢትዮጵያ ኮሪያ ዘማቾች ማህበር ፕሬዝደንት ኮሎኔል መለሰ ተሰማ ጋር አጭር ቃለምልልስ አድርጓል፡፡ ለኮሪያ ዘመቻ እንዴት ነው የተመረጡት? በመሠረቱ የገበሬ ልጅ ነኝ፡፡ ለኮሪያ ዘመቻ ተብዬ አይደለም ወደ ወታደራዊ ዘመቻ የገባሁት፡፡ በጣልያን ወረራ ወቅት በሕፃንነቴ ከአባቴ ጋር ለጫካ ተንከራትቻለሁ፡፡ በ1939 ዓ.ም ወታደርነት ተቀጠርኩ፡፡ የተወለድኩት በ1922 ዓ.ም ነው፡፡ ወታደር በሆንኩ በአምስት ወይ በስድስት ዓመት ኮርያ ዘመትኩ፡፡ እውነቱን ለመናገር ስዘምት ማንበብና መፃፍ አልችልም ነበር፡፡ አሁንም ድረስ? አይደለም፡፡ እዚያው ኮርያ እያለሁ ዘመድ ደብዳቤ ፃፈልኝ፡፡ ሃምሳ አለቃ ንጉሤ ወልደሚካኤል የሚባል ጓደኛዬን ፃፍልኝ ስለው ሂድ አልጽፍም አለኝ፡፡ ንዴት ያዘኝና ወንጌሌ ቆስጣ ለሚባሉ አለቃዬ ጋዜጣ ስጡኝና ፊደል ልማርበት አልኳቸው፡፡ ፊደል ጭምር ሰጡኝ፡፡ በዚያው በጓደኞቼ አጋዥነት ተለማምጄ ስሜን መፃፍ ቻልኩ፡፡ በሦስት ወር ደብዳቤ ለቤተሰብ ጽፌ ደብዳቤዬ እንደደረሳቸው ቤተሰቦቼ ሌላ ደብዳቤ ላኩልኝ፡፡ ጥሩ አለቆች ስለነበሩኝም እዚህ ስመለስ ጫካ ወስደው ጥቁር ሰሌዳ በማሸከም ያስተምሩን ነበር፡፡ የ...