Back

ⓘ እንግሊዝኛ የምዕራብ-ጀርመናዊ ቋንቋዎች ቤተሠብ ቋንቋ ነው። በዓለም ላይ በብዙ አገራት ውስጥ ይነገራል። የመጀመሪያ ተናጋሪዎቹ ቁጥር 380 ሚሊዮን ያሕል ሲሆን በብዛት የምድር 3ኛው ቋንቋ ነው። ከዚህ በላይ እስከ 1 ቢሊዮን ሰዎች እንደ ሁለተኛ ቋንቋ ይ ..
                                               

የ2010 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ዲ

የ2010 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ዲ ከሰኔ ፮ እስከ ሰኔ ፲፮ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. ተካሄዷል። በዚህ ምድብ ውስጥ የጀርመን፣ ጋና፣ አውስትራልያ እና ሰርቢያ ቡድኖች ነበሩ። ሁሉም ሰዓታት በደቡብ አፍሪቃ ሰዓት UTC+2 ናቸው።

                                               

ኦስካር

የአካዳሚ ሽልማት ወይም ኦስካር ኢንዱስትሪ ተሳታፊዎች ሽልማት ነው። ይህ ሽልማት የሚሰጠው በአመት አንድ ጊዜ የሚካሄድ የምርጥ ፊልሞች መሸለሚያ ዝግጅት ላይ ነው። ይህ የሽልማት ዘርፍ በአለማችን ሚዲያ እድሜ ጠገቡ ነው። ሌሎች እንደ ግራሚ አዋርድስ፣ ኤሚ አዋርድስ፣ ጎልደን ግሎብ አዋርድስ እና ሌሎች የሚዲያ ዘርፍ ሽልማቶች ከዚሁ ሽልማት የተቀዱ ናቸው። ኦስካር በአለማችን ትልቁ የፊልም ሽልማት መድረክ ነው።

                                               

ዘ ቢተልስ

ዘ ቢትልስ በሊቨርፑል፣ እንግሊዝ የተመሠረተ እጅግ ስመ ጥሩ የሆነ የሮክ ሙዚቃ ቡድን ነበረ። ዘፋኞቹ ጆርጅ ሀሪሰን፣ ጆን ሌኖን፣ ፖል መካርትኒ ፣ አና ርንጎ ስታር ነበሩ። ደግሞ ይዩ፡ ብጫ ሱማራ - የቢተልስ 1968 እ.ኤ.አ. ሳይከደሊክ ካርቶን ፊልም

                                               

ኢንች

አንድ ኢንች የፊትfeet አንድ አስራ ሁለተኛ1 12 {\textstyle {\frac {1}{12}}} ያህል ነው። እንግሊዝኛው ኢንች የሚል ስያሜ ያገኘው ከዚህ ጋር በተያያዘ ነው፣ አንድ አስራ ሁለተኛ በላቲን አንቺያ ይባል ነበረና። በድሮ እንግሊዝኛ ይንች ይባልም ነበር። በአማርኛም ልክ እንዳሁኑ እንግሊዝኛ ኢንች ተብሎ ይጠራል።

                                               

ሲያትል የህዝብ ቤተ መጻሕፍት

ሲያትል የህዝብ ቤተ መጻሕፍት በአሜሪካ ዋሽንግተን ክፍላገር የሲያትል ከተማን የሚያገለግል የህዝብ ቤተ መጻሕፍት ሥርዓት ነው። ቤተ መጻሕፍቱ በ1890 እ.ኤ.አ. የተቋቋመ ሲሆን ከማዕከላዊ ቤተ መጻሕፍትና ተንቀሳቃሽ ቤተ መጻሕፍት በተጨማሪ ፳፮ ቅርንጫፎች አሉት።

                                               

ኮርትኒ ቼትዊንድ

ኮርትኒ ቼትዊንድ በደራሲው ዲጀይ መክሄይል ልቦለድ ፔንድራጎን ውስጥ አንዲት ወጣት ሴት ልጅ ናት። ኮርትኒ ቼትዊንድ ናት የከንፍር ወዳጅ ለቦቢ ፔንድራጎን፣ የቀዳሚነቱ መንገደኛ በፐንድራጎኑ ልቦለድ ናት። በአንደኛው መፅሐፉ ልቦለድ ሻጩ የሞት ኮርትኒ የዐሥራ አራት ዓመት አሮጊት ናት፣ በሰባተኛ መፅሐፍ የኲለኑ ጨዋታዎች ዐሥራ ሰባት ናት።

                                               

ጴንጤ

Pentay አንድ መጀመሪያ ነው Amharic - ትግርኛ ለ ቋንቋ ቃል የጴንጤቆስጤ እና ሌሎች የምስራቅ-ተኮር የፕሮቴስታንት ክርስቲያኖች ውስጥ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ, እና የኢትዮጵያ እና የኤርትራ የዲያስፖራ. ዛሬ ቃሉ የሚያመለክተው በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ማኅበረሰቦች ውስጥ የሚገኙ ሁሉንም የወንጌላውያን ክርስቲያን ቤተ እምነቶች እና ድርጅቶች የኢትዮጵያ-ኤርትራዊ ወንጌላዊነት ወይም የኢትዮጵያ-ኤርትራዊ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያንን ነው ፡ አንዳንድ ጊዜ ቤተ እምነቶች እና ድርጅቶች ወኒግላው በመባል ይታወቃሉ ፡ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ወንጌላውያን ክርስቲያኖች በአሜሪካ እና በአውሮፓውያን የፕሮቴስታንት የወንጌል ተልእኮ ምክንያት ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርስቲያናት በተውጣጡ ሥነ-መለኮታዊ ልዩነቶች ምክንያት በወጡ ወጣቶች ላይ እና በኋላም በእነሱ ላይ ስደት በተስፋፋባቸው ወጣቶች መካከል ነው ፡ Pentay ክርስቲያኖች schismed የ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናት, ሌላ ቅርንጫፎች ክርስትና, ወይም ወደ የፕሮቴስታንት ሚስዮ ...

                                               

ብርሃኑ ሰሙ/ birhanu semu

ተወዳጅ ሚድያና ኮሚኒኬሽን በስነ-ጽሁፍ፣ በፊልም ፣ በቴአትር፣ በሬድዮ ድራማ ፤ በማስታወቂያ ዘርፍ ፤ በሚድያ ዘርፍ ከ1990ዎቹ ጀምሮ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ባለሙያዎችን ታሪክ በፌስ ቡክ ፤ በዊኪፒዲያ እንዲሁም በሌሎች የማህበራዊ ሚድያዎች እናስተዋውቃለን፡፡ ብዙዎቹ በወጣትነት አንዳንዶቹም በጉልምስና እድሜ ላይ የሚገኙ ሲሆኑ የዛሬ ጎልማሳ የነገ የሀገር ባለውለታ ነውና ታሪካቸውን እየሰነድን ለትውልድ እናስቀምጣለን፡፡ ለወደፊቱም ምርምር ለሚያደርጉ እና ወይም የስራ ፕሮጀክቶቻቸውን ለሚደግፉ ሰዎች ይጠቅማል ብለን እናምናለን፡፡ በ6 ዘርፎች ትልቅ ስራ ሰርተዋል ብለን ያመንባቸውን ሰዎች ታሪክ እናቀርባለን፡፡ ይህ የማስተዋወቅ ስራ ውድድር ሳይሆን በሙያው የተለየ ሚና ያበረከተ ማንኛውም ሰው ታሪኩ የሚሰነድበት ነው፡፡ ከድርሰት እና ስነጽሁፍ ዘርፍ ታሪኩ የሚቀርብለት ሰው ብርሀኑ ሰሙ ይሆናል፡፡ ትውልድና ልጅነት ሴት አያቱ የአባቱ እናት እና ወላጅ እናቱ ‹‹የተወለድከው በፍልሰታ ፆም ሰሞን ነው›› ስላሉት፣ ‹‹ወልደመድኅን›› የሚል ስም አወ ...

እንግሊዝኛ
                                     

ⓘ እንግሊዝኛ

እንግሊዝኛ የምዕራብ-ጀርመናዊ ቋንቋዎች ቤተሠብ ቋንቋ ነው። በዓለም ላይ በብዙ አገራት ውስጥ ይነገራል። የመጀመሪያ ተናጋሪዎቹ ቁጥር 380 ሚሊዮን ያሕል ሲሆን በብዛት የምድር 3ኛው ቋንቋ ነው። ከዚህ በላይ እስከ 1 ቢሊዮን ሰዎች እንደ ሁለተኛ ቋንቋ ይችሉታል።

እንግሊዝኛ በእንግሊዝ አገር ጀመረ። አንግል እና ሴያክስ የተባሉ ጀርመናዊ ጐሣዎች መጀመርያ የተናገሩት ጥንታዊ እንግሊዝኛ ይባላል። ነገር ግን ይህ እንደ ዛሬው እንግሊዝኛ በጣም አልመሰለም። በ441 አ.ም. ጀምረው እነዚህ ጐሣዎች ከጀርመን ወጥተው በብሪታኒያ ደሴት ሰፈሩ። ቋንቋቸውም የተጻፈበት "ሩን" በተባለው ጽሕፈት ነበር። በ7ኛ መቶ ዘመን ክርስትና ከተቀበሉ በኋላ ግን ቋንቋው በላቲን ፊደል ሊጻፍ ጀመረ።

ከ9ኛ መቶ ዘመን ጀምሮ ብዙ ሠራዊት ከዴንማርክና ከኖርዌ ወደ እንግሊዝ ስለ መጡ ተመሳሳይ ቋንቋ ስለነበራቸው ያን ጊዜ እንግሊዝኛ ከጥንታዊ ኖርስ አያሌ ቃሎች ተበደረ።

በ1058 ዓ.ም. ዊሊያም 1 "አሸናፊ" ከነሠራዊቱ እንግሊዝ አገርን ወርሮ ንጉስ ከሆነ በኋላ አዲስ መንግሥት ለማቆም መኳንንቶቹን ከፈረንሳይ ከሱ ጋራ አመጣ። የእንግሊዝ መንግሥት ቋንቋ ፈረንሳይኛ ሲሆን ለረጅም ጊዜ 300 አመቶች እንግሊዝኛ ከትምህርት ቤቶች ተከለክሎ ቋንቋው ለጽሑፍ ሳይሆን እንደ መነጋገርያ ብቻ ስለ ቀረ በዚያን ጊዜ ጠባዩ ብዙ ተለወጠ። እንግሊዝኛ በዚሁ ዘመን እጅግ ብዙ ቃላት ከፈረንሳይኛ ስለተበደረ በፍጹም ሌላ መልክ ይዞ አሁን መካከለኛ እንግሊዝኛ ይባላል። ቻውሰር የተባለው አንድ ስመ ጥሩ የመካከለኛ እንግሊዝኛ ጸሐፊ ነበር።

በ15ኛ መቶ ዘመን "ታላቅ የአናባቢ መፈራረቅ" በሚባለው ለውጥ ምክንያት፡ አናባቢዎቹ ተለውጠው የቋንቋው ድምጽ እንደገና ሌላ መልክ ያዘና ከዊሊያም ሼክስፒር ዘመን ጀምሮ "ዘመናዊ እንግሊዝኛ" ተብሏል።

እንግሊዝኛ ከሌሎቹ ልሣናት ለምሳሌ ከቻይንኛ፥ ከህንዲ፥ ከጃፓንኛ እና ከእስፓንኛ አንዳንድ አዲስ ቃላት ከመውሰድ አላቋረጠም። ከተለያዩ አገሮች የነበሩት ሊቃውንት እርስ በርስ ለመነጋገር የቻሉ የጋራ ካወቁት ልሳናት ከሮማይስጥና ከግሪክ የጥናቶቻቸውን ቃሎች በመምረጥ ነበር። እነዚያ የተክኖሎጂ ቃሎች ደግሞ ወደ እንግሊዝኛ ገቡ፤ ለምሳሌ፣ photograph ፎቶግራፍ ከግሪክ photo- ፎቶ ብርሀን እና -graph ግራፍ ሰዕል፤ ወይም telephone ተለፎን ስልክ። ስለዚህ እንግሊዝኛ ከብዙ ቋንቋዎች ይሠራል ሊባል ይችላል።

                                     

1. ትንትና

ከሷዴሽ ዝርዝር 207 ዘመናዊ እንግሊዝኛ ቃላት፣ 161 ወይም 78% በቀጥታ ከጥንታዊ እንግሊዝኛ ቃላት ተደረጁ።

ከተረፉትም 46 ቃላት መኃል፤

 • 11 ወይም 5% ከፈረንሳይኛ መጡ እንዲያውም "because" ከጥንታዊ እንግሊዝኛ bi + ፈረንሳይኛ cause የሚገኝ ውሁድ ነው።
 • 2 ቃላት ወይም 1% ከሮማይስጥ መጡ vomit, correct
 • 10 ወይም 5% ከኖርስኛ መጡ
 • 2 ቃላት ወይም 1% ከሆላንድኛ መጡ split, rub

የተረፉት 21 ቃላት ወይም 10% የመጡ ከጥንታዊ እንግሊዝና ሲሆን፣ ከጥንታዊ እንግሊዝኛ አዲስ ትርጉም ተሰጡ።

                                     
 • ሕዝብ የተናገሩበት ሲሆን የዘመናዊ እንግሊዝኛ ቀድሞ አይነት ነው ሆኖም በቃላትም ሆነ በስዋሰው ከዘመናዊ እንግሊዝኛ በጣም ይለያል ቅርብ ዘመዶቹ ጥንታዊ ፍሪዝኛ እና ጥንታዊ ሴክስኛ ናቸው ጥንታዊ እንግሊዝኛ በርካታ ተመሳሳይ ቀበሌኞች ነበሩት
 • በቄሱ ቻርለስ ዊሊየም ኢዘንበርግ በለንደን እንግሊዝ የታተመው የአማርኛና እንግሊዝኛ መዝገበ ቃላት ከጎን ይታያል መጽሐፉ በመጀመሪያ ክፍሉ አማርኛን ወደ እንግሊዝኛ ሲተረጉም በሁለተኛ ክፍሉ መልሶ እንግሊዝኛን ወደ አማርኛ ይተረጉማል
 • እንግሊዝኛ አማርኛ መዝገበ ቃላት 1972 በወፍ ልሳል የተደረሰ ከእንግሊዝኛ ወደ አማርኛ መዝገበ ቃላት ሲሆን ባጠቃላይ 1503 ገጾችን ይዟል መጽሐፉ ከሌሎች መዝገበ ቃላት ለየት የሚለው ቃላትን በቃላት ሳይሆን የሚተረጉመው በአገባባቸው
 • ዲሴምበር እንግሊዝኛ December በጎርጎርያን ካሌንዳር ውስጥ 12ኛው ወር ነው በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ይህ ወር የኅዳር መጨረቫና የታኅሣሥ መጀመርያ ነው
 • በ1859 ዓ.ም. በቤንጋል ህንድ የታተመው የአማርኛ ኡርዱና እንግሊዝኛ መዝገበ ቃላት ከጎን ይታያል
 • ሰፕቴምበር እንግሊዝኛ September በጎርጎርያን ካሌንዳር ውስጥ 9ኛው ወር ነው በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ይህ ወር የነሐሴ መጨረቫ ጳጉሜና የመስከረም መጀመርያ ነው
 • አዳምስ ከ1838 - 1918 እንግሊዝኛ Democracy: An American Novel ሄንሪ ጄምስ ከ1843 - 1916 እንግሊዝኛ Washington Square ጄኔፈር ሃይ ትውልድ 1968 እንግሊዝኛ Mrs. Kimble ጀሲካ ሃግዶርን
 • ጃንዩዌሪ እንግሊዝኛ January በጎርጎርያን ካሌንዳር ውስጥ መጀመርያው ወር ነው በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ይህ ወር የታኅሣሥ መጨረቫና የጥር መጀመርያ ነው ወሩ 31 ቀኖች አሉት ጃንዩዌሪ የወሩ ስም በእንግሊዝኛ አጠራር ሲሆን
 • ኦገስት እንግሊዝኛ August በጎርጎርያን ካሌንዳር ውስጥ 8ኛው ወር ነው በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ይህ ወር የሐምሌ መጨረቫና የነሐሴ መጀመርያ ነው ይህ ወር ስሙን ያገኘው ከአውግስጦስ ቄሳር Augustus Caesar ነው
ክርስታደልፍያን
                                               

ክርስታደልፍያን

ክርስታደልፍያን በ1848 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ በሥላሴ የማያምን ቤተ ክርስቲያን ነው። መለጠፊያ:EN መጽሔት "Glad Tidings" እንግሊዝኛ መጽሔት "The Christadelphian" መምሪያ - አማርኛ Bible Basics in Amharic