Back

ⓘ ኣጠፋሪስ ወይም አስተናግርት ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ነው። ስሙ ኣጠፋሪስ ከ እጸ ፋርስ ጋር የተዛመደ ይሆናል፣ አሁን ግን እጸ ፋርስ በተለመደ ለCannabis sativa ያጠቆማል። ሌላም ዝርያ Nicandra physalodes ደግሞ አጠፋሪስ ተብሏል ..
ኣጠፋሪስ
                                     

ⓘ ኣጠፋሪስ

ኣጠፋሪስ ወይም አስተናግርት ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ነው።

ስሙ ኣጠፋሪስ ከ "እጸ ፋርስ" ጋር የተዛመደ ይሆናል፣ አሁን ግን "እጸ ፋርስ" በተለመደ ለCannabis sativa ያጠቆማል።

ሌላም ዝርያ Nicandra physalodes ደግሞ "አጠፋሪስ" ተብሏል።

                                     

1. የተክሉ ጥቅም

ዘሮቹም ቅጠሎቹም እንደ መድኃኒት ይጠቀማሉ።

የተደረቁ የተደቀቁ ቅጠሎች ከቅቤ ጋራ ተቀላቅለው እንደ ፀረ-ሻገቶ ለፎረፎር/የአናት ልክፈት፣ ወይም አንዳንዴም በመልክ ላይ ይጠቀማሉ። ቅጠሎቹ ተደቅቀው ለጥፍ ተደርገው የጭነት ከብት ቁስል፣ ወይም የሰው ቁስል ወይም ጭርት ያክማል።

የተፈሉ ዘሮች ፍልፋይ ወይም ቅጠሎች እንፋሎት የጥርስ ሕመም ለማስታገስ ይናፈሳል።

ጥቁር ዘሮቹ በጣም ገዳይ መርዛም ናቸው። በጣም ጥቃቅን መጠን ማሳበድ ይችላል። ተክሉ በሙሉ መርዛም ይቆጠራል፣ አይበላም።