Back

ⓘ የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የኢትዮጵያ ዋና ካሌንደር ነው። አዲስ ዓመት በጁሊያን ካሌንደር አቆጣጠር በኦገስት 29 ወይም 30 የሚጀምር ሲሆን በግሪጎሪያን ካሌንደር ደግሞ ከ1901 እ.ኤ.አ. እስከ 2099 እ.ኤ.አ. ድረስ በሴፕቴምበር 11 ወይም 12 ይጀ ..
                                               

ካም

ካም የተወለደው ከማየ አይኅ አስቀድሞ እንደ ነበር ይታመናል። ኦሪት ዘፍጥረት 5፡32 እንደሚለን፣ "ኖኅም የአምስት መቶ አመት ሰው ነበረ፤ ኖኅም ሴምን ካምን ያፌትንም ወለደ።" በመጽሐፈ ኩፋሌ አቆጣጠር፣ ኖህ በዓመተ ዓለም 707 ተወልዶ፣ ሴምን በ1207 ዓ.ዓ. ወለደ፤ በ1209 ዓ.ዓ. ካምንም፣ በ1212 ዓ.ዓ. ያፌትንም ወለዳቸው። በዚህ አቆጣጠር በ1308 ዓ.ዓ. ማየ አይኅ ወይም የጥፋት ውኃ በደረሰበት ዓመት የካም ዕድሜ 99 ዓመት ያህል ነበር። በዚያ ዘመን የአበው ዕድሜ እስከ ሺ ድረስ ሊሆን ስለሚችል ይህ እንደ ወጣት መቆጠሩ ማለት ነው። የሚስቱ ስም በዘፍጥረት ባይጻፍም በኩፋሌ ግን ስሟ ናኤልታማኡክ ወይም ኔኤላታማኡክ፣ አኤልታማኡክ እንደ ነበር ይተረካል። በሌላ ጥንታዊ ምንጮች ዘንድ ስሟ ናሐላጥ፣ ኖኤላ፣ ናሕላብ፣ ወዘተ. የሚመስል ነበር። እነዚህ ሁለቱ ከውኃው በኖህ መርከብ ያመለጠው የ8 ሰዎች ቤተሠብ መካከል ነበሩ።

                                               

ፍቼ ጫምባላላ በዓል በዩኔስኮ የሰው ልጆች ወካይ የማይዳሰስ ባሕላዊ ቅርስ ዝርዝር ላይ በዩኔስኮ ተመዘገ

DECEMBER 4, 2015ARCCHPRLEAVE A COMMENT የማይዳሰሱ ኢንታንጀብል ባህላዊ ቅርሶችን የሚመለከተው የዩኔስኮ አካል በይነ መንግሥታዊው ኮሚቴ Intergovernmental Committee 10ኛ ስብሰባውን ከኅዳር 20 እስከ ኅዳር 24 ቀን 2008 ዓ.ም. በናሚቢያ መዲና ዊንድሆክ በተደረገው 10ኛ የዩኔስኮ ጉባዔ ለውሳኔ ከቀረቡት 35 ሠላሳ አምስት ባሕላዊ ቅርሶች መካከል የሲዳማ ብሔር የአዲስ ዓመት ዘመን መለወጫ የሆነው ፍቼ ጫምባላላ በዓል በሰው ልጆች ወካይ ቅርስ ዝርዝር ውስጥ Representative List of Intangible Cultural Heritage of Humanity የ2003 የኢንታጀብል ባህላዊ ቅርሶች ጥበቃ ዓለም አቀፍ ስምምነት መስፈርቶችን አሟልቶ በመገኘቱ አባል አገሮች ውይይት ካደረጉበት በኋላ ፍቼ ጫምባላላ ተመዝግቧል፡፡ ይህም ከመስቀል በዓል ቀጥሎ የኢትዮጵያ ሁለተኛው የማይዳሰስ ዓለም አቀፍ የሰው ልጆች ወካይ ቅርስ ሆኖ ሕዳር 22 ቀን 2008 ዓ.ም በአገሩ ሰዓት አቆጣጠር 9፡40 በፋይል ቁጥር ...

                                               

ቅድስት በላይ-kidist Belay

ቅድስት በላይ-kidist Belay የዚህ ታሪክ አሰባሳቢ፣ ተወዳጅ ሚድያና ኮሚኒኬሽን በስነ-ጽሁፍ፣ በስነ-ስእል፣ በፊልም ፣ በቴአትር፣ በሬድዮ ድራማ ፤ በማስታወቂያ ዘርፍ ፤ በሚድያ ዘርፍ ከ1990ዎቹ ጀምሮ አስተዋጽኦ ያበረከቱና አሁንም በስራ ላይ ያሉ ባለሙያዎችን ታሪክ በፌስ ቡክ ፤ በዊኪፒዲያ እንዲሁም በሌሎች የማህበራዊ ሚድያዎች እያስተዋወቀ እንዳለ ይታወቃል፡፡ ውድ ይህን ሀሳብ የምትደግፉ መስፈርቱን ያሟላሉ የምትሏቸው ሰዎች ጠቁሙን ፤ እርስዎም ታሪኬ መሰነድ አለበት ካሉ ይላኩልን፡፡ ከተቀመጠው መስፈርት አንጻር አይተን ታሪክዎን እናወጣለን፡፡ በ tewedajemedia gmail.com ግለ-ታሪክዎን ይላኩ፡፡ ጥቅምት 14 2014 የ1000 ሰዎች ታሪክ ሲሞላ ድንቅ ታሪካዊ ምረቃ ይኖራል፡፡ ታሪካቸው አሁን የሚሰራላቸው፤ ብዙዎቹ በወጣትነት አንዳንዶቹም በጉልምስና እድሜ ላይ የሚገኙ ሲሆኑ የዛሬ ጎልማሳ የነገ የሀገር ባለውለታ ነውና ታሪካቸውን እየሰነድን ለትውልድ እናስቀምጣለን፡፡ ለወደፊቱም ምርምር ለሚያደርጉ እና ወይም የስራ ፕሮ ...

                                     

ⓘ የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር

የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የኢትዮጵያ ዋና ካሌንደር ነው። አዲስ ዓመት በጁሊያን ካሌንደር አቆጣጠር በኦገስት 29 ወይም 30 የሚጀምር ሲሆን በግሪጎሪያን ካሌንደር ደግሞ ከ1901 እ.ኤ.አ. እስከ 2099 እ.ኤ.አ. ድረስ በሴፕቴምበር 11 ወይም 12 ይጀምራል። በየአራት ዓመቱ አንድ ቀን ይጨመራል። በአንድ ዓመት ውስጥ አስራ-ሁለት ባለሠላሣ ቀናት እና አንድ ባለ አምስት ቀናት ያሉባቸው ወራት አሉ።

በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ዓመታት ሁሉ በአራት መደባት ይዞራሉ፤ እነሱም ስለ ሐዋርያት ስሞች ዘመነ ማቴዎስ፣ ዘመነ ማርቆስ፣ ዘመነ ሉቃስ ተጨማሪ የጳጉሜ ቀን የሚቀበለው እና ዘመነ ዮሐንስ ይባላሉ።

የአመተ ምህረት ዘመናት ከጎርጎርዮስ አኖ ዶሚኒ በ7 ወይም 8 አመታት የሚለይበት ምክንያት፣ ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት 400 አመት ያህል በኋላ አኒያኖስ እስክንድራዊ ዘመኑን ሲቆጥረው ትስብዕቱ በመጋቢት 29 1 ዓ.ም. እንደ ሆነ ስለ ገመተ ይህ በ ትስብዕት ዘመን 1ኛ አመት ሆኗል። ይህ አቆጣጠር በምሥራቅ ክርስቲያን አገራት ከተቀበለ በኋላም በ443 ዓ.ም. ከሮማ ፓፓና ከምሥራቅ አቡናዎች መካከል ልዩነት ደርሶባቸው፤ በ517 ሌላ መነኩሴ ዲዮኒሲዮስ ኤክሲጉዎስ ሌላ አቆጣጠር አኖ ዶሚኒ አቀረበ። በሱ ግምት ትስብዕቱ የተከሠተበት ቀን ከአኒያኖስ ግምት በፊት በ8 አመታት አስቀደመው። የ አኖ ዶሚኒ አቆጣጠር በምዕራብ አውሮፓ ላይኛነት በማግኘቱ የትስብእት ዘመን 1 አመተ ምህረት በ አኖ ዶሚኒ 9 እ.ኤ.አ. ሆነ።

የኢትዮጵያ ዘመን ኣቆጣጠር የጁልያን ዘመን ኣቆጣጠር ኣይደለም። በኣሁኑ ጊዜ በጁልያና በጎርጎርዮስ ካለንደሮች መካከል ያለው የ13 ቀናት ልዩነት ሲሆን የዓመታቱ ቍጥሮች ልዩ ኣይደሉም።

በ525 ዓ.ም. ዲኖስዮስ ኤክሲጅዮስ Dionysius Exiguus የሚባል የሩስያ መነኩሴ የሮማው ጳጳስ መልዕክተኛም በመሆን የፋሲካን በዓል ኣወሳሰን ከግብጻውያን እንዲማር ተልኮ ነበር። እንደሚመስለኝና ኣንዳንድ ፀሓፊዎችም እንደሚሉት ኤክሲጅዮስ በ525 ዓ.ም. 532 ዓመትን ሳይጠቀም ኣልቀረም ይላሉ ዶክተር ኣበራ ሞላ።

                                     
  • 1656 አመተ ምኅረት የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር አመት ነበር በጎርጎርያን ካሌንዳር የ1663 እ.ኤ.አ. መጨረሻና የ1664 እ.ኤ.አ. መጀመርያ ይቆጠራል በዚሁ ዓመት እንግሊዞች ኒው አምስተርዳም አዲስ አምስተርዳም አሜሪካዊ ቅኝ አገር
  • የኢየሱስ ተከታይ ሐዋርያው የዮሐንስ ወንጌል - ሐዋርያው የጻፉት ወንጌል በአዲስ ኪዳን ዘመነ ዮሐንስ - በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ዓመታት ሁሉ በአራት መደባት ይዞራሉ እነሱም ስለ ሐዋርያት ስሞች ዘመነ ማቴዎስ ማርቆስ ሉቃስ ተጨማሪ የጳጉሜ
  • በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፻፳፭ ኛው ዕለት ነው ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ዮሐንስ ፪፻፵፩ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ማቴዎስ ማርቆስ እና ሉቃስ ደግሞ ፪፻፵ ዕለታት ይቀራሉ ፲፰፻፹፰ ዓ ም የኢትዮጵያ ንጉሠ
  • መጋቢት ፭ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፻፹፭ ኛው ቀን ሲሆን ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፹፩ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፹ ቀናት ይቀራሉ ፲፭፻፺፱
  • ሚያዝያ ፳፰ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፴፰ኛው ዕለት ሲሆን የፀደይ በልግ ወቅት ፴፫ኛው ቀን ነው ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፳፰ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ
  • ታኅሣሥ ፳፬ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፻፲፬ተኛው እና የመፀው ወቅት ፹፱ተኛው ቀን ነው ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በ ዘመነ ሉቃስ ፪፻፶፪ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ በ ዘመነ ማቴዎስ እና በ ዘመነ ማርቆስ
  • ከጣኦት ስም ሑት - ሔሩ መጣ በጎርጎርዮስ አቆጣጠር የኖቬምበር መጨረሻና የዲሴምበር መጀመርያ ነው በኅዳር ወር ፲፱፻፲፩ ዓ ም የቸነፈር ግሪፕ በሽታ በአዲስ አበባ እና በሌላውም የኢትዮጵያ ግዛት ላይ ተነስቶ በመዲናው ብቻ ከዓሥር ሺ
  • የሚገኝ ከአስራ ሦስቱ ኢትዮጵያ የወራት አቆጣጠር ውስጥ የመጨረሻው እና አሥራ ሦስተኛው ፲፫ ኛው የወር ስም ነው ጳጉሜ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ዘመነ ዮሐንስ ሥግር ዓመት በጎርጎርያዊ አቆጣጠር leap year በመሆኑ ስድስት ፮
  • በኅዳር ወር መሀከል የሚገኝ ከአስራ ሦስቱ ኢትዮጵያ የወራት አቆጣጠር ውስጥ ሁለተኛው የወር ስም ነው ጥቅምት ከግዕዙ ጠቀመ ከሚለው ግስ የተባዛ ነው በቅብጢ አቆጣጠር የዚህ ወር ስም ፓውፔ ነው ይህም በጥንታዊ ግብጽ አረመኔ ሃይማኖት
  • የኢየሱስ ተከታይ ሐዋርያው የዮሐንስ ወንጌል - ሐዋርያው የጻፉት ወንጌል በአዲስ ኪዳን ዘመነ ዮሐንስ - በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ዓመታት ሁሉ በአራት መደባት ይዞራሉ እነሱም ስለ ሐዋርያት ስሞች ዘመነ ማቴዎስ ማርቆስ ሉቃስ ተጨማሪ የጳጉሜ