Back

ⓘ ከጥላቸው እራቅ. ህመምህ እንዳያገረሽብህ ኋላ መጥፎ ነው የሰው ጥላ ብለው ሲሉህ ሰምቼ ለወንድምነትህ ሳስቼ ልመክርህ ተነሳሁ በጥብቅ ከጥላቸው እንድትርቅ 2 መጨበጫም የለው መቼም የኔ ጣጣ በሀገሬም አልኖር ካገሬም አልወጣ እዛ ስሆን እዚ ከዚ እዛ እያሰብ ..
                                               

ቅኔ

ቅኔ ማለት፡ ቀነየ ፡ገዛ፡ ካለው፡ ግስ፡ የተገኘ፡ ጥሬ፡ ዘር፡ ነው። ወይም፡ ቀነየ ፡ገዛ፡ የሚለውን፡ አንቀጽ፡ ያስገኘ፡ ጥሬ፡ ዘር፡ ነው። ፍችውም፡ መገዛት፡ ማለት፡ ነው። ቁሙ፡ እንከ፡ ወኢትሑሩ፡ ዳግመ፡ ውስተ፡ አርዑተ፡ ቅኔ፡ እንዲል፡ ፥ ቅኔ፡ ማለት፡ መገዛት፡ ማለት፡ ከኾነ፥ ይህ፡ ከያንዳንዱ፡ ሰው፡ በየጊዜው፡ የሚመነጨው፡ እንግዳ፡ ድርሰት፡ ስለ፡ ምን፡ ቅኔ፡ ተባለ፡ ቢሉ፥ ፍጡር፡ ዐዲስ፡ ዐዲስ፡ ምስጋና፡ እየደረሰ፡ በማቅረብ፥ ለፈጣሪው፡ መገዛቱን፡ የሚገልጥበት፡ ስለ፡ ኾነ፡ ነው። ለፍጡራን፡ የሚደረሰውም፡ ቅኔ፥ ቅኔው፡ የሚደረስለት፡ ፍጡር፡ ከቅኔ፡ ደራሲው፡ በላይ፡ ክብር፡ ያለው፡ መኾኑን፡ የሚገልጽ ፡ ድርሰት፡ ስለ፡ ኾነ፥ መገዛትን፡ ከማመልከት፡ የራቀ፡ አይደለም። አንድም፥ ሕዋሳተ፡ አፍኣን፣ ሕዋሳተ፡ ውስጥን፡ ለኅሊና፡ አስገዝቶ፥ በተወሰነ፡ ቍርጥ፡ ሐሳብ ፡ የሚታሰብ፡ ስለ፡ ኾነ፥ ቅኔ፡ ተብሏል። ይኸውም፡ ሊታወቅ፥ በቅኔ፡ ምስጢር፡ ልቡ፡ የተነካ፡ ሰው፥ ቅኔ፡ በሚያስብበት፡ ጊዜ፥ እፊቱ፡ የሚደረገውን፡ ነገር፡ እያየ፣ ...

                                     

ⓘ ከጥላቸው እራቅ

ህመምህ እንዳያገረሽብህ ኋላ መጥፎ ነው የሰው ጥላ ብለው ሲሉህ ሰምቼ ለወንድምነትህ ሳስቼ ልመክርህ ተነሳሁ በጥብቅ ከጥላቸው እንድትርቅ

2 መጨበጫም የለው መቼም የኔ ጣጣ

በሀገሬም አልኖር ካገሬም አልወጣ

እዛ ስሆን እዚ ከዚ እዛ እያሰብኩኝ

ማደሪያ የሌለው ከንቱ አሞራ ሆንኩኝ

3

ሳስርና ስፈታ ስስብ ስሸመቅቅ

ብዙ ዘመን ኖርኩኝ ስዘዋወር ስለቅ

ዘንድሮም ደርሶብኝ ይሄው መገላበጥ

ልብስ መሃል ቆሜ መስያለሁ ሸቀጥ

4. የየኔሰው ስንብት ከዋካ

ምነው ፈጣሪ አምላክ? ምነው የዓለም ቤዛ

በድርብ ሰንሰለት፤ እየተገረፍን ስንገዛ

ጠላት እንኳን፤ ባልፈጸመው ጭካኔ

ሲሸነቁጠን ወያኔ

ስቃይ፤ ሞታችንን ለዓለም ነግረን

ሰሚ ጠፍቶ ዝም ሲለን

ምነው አንተስ ጨከንክብን?

ለምን ፊትህን አዞርክብን?

እንግዲያውስ ፈጣሪዬ፤ የማሪያም ልጅ

ልመናዬ መራር ሆኖ ላንተም ባይበጅ

በቃላቸው እንዳልረታ

በገንዘባቸው እንዳልገታ

አካሌ በችግር ደክሞ

ሆዴ በጉርሻ ተስለምልሞ

በፍቅረ ነዋይ ልቤ እንዳይደለል

መንፈሴ ጽናት አጥቶ እንዳይዋልል

ተደናቅፌ እንዳልቀር ሃገሬን እንዳልከዳ

ሞቴን አትንሳኝ፤ አታድርገኝ የሀገር እዳ

ፍቀድልኝ እንድጨክን

ለሀገሬ ቤዛ እንድሆን

ርሃቤ አስመርሮኝ

እርዛቴ አስነውሮኝ

በእጃቸው እንዳልወድቅ ሰጋሁ

ነፃነትን እንዳልደፈጥጣት ፈራሁ

ገና በልጅነት ከሀገር ሀገር ዞሬ

ተምሬ ፍደል ቆጥሬ

የበኩሌን የዕውቀት አዝርዕት

በተማሪዎቼ ላይ ላሸት

ድንቁርናን ላጠፋ" ሀ” በሉ ልል

ከራሴ ጋር ተስማምቼ ገብቼ ውል

ተስፋ በጠፋበት ስፍራ

ተስፋ ዘርቼ ላፈራ

ምኞት ሀሳብ ነበረኝ

ይሄው ቀረ ሳይሆንልኝ

እናም" የኔ ሰው” የሚባል ኖሮ

ካልጠቀማት ለዳውሮ

ኢትዮጵያም ከተደፈቅሽበት ፍዳ

ማውጣት አቅቶኝ ከምሆንሽ እዳ

ኖሬ ሳይሆን ሞቼ ከሆነ የምጠቅምሽ

ከበሽታሽ የማድንሽ

ከስቃይሽ የማወጣሽ

በስጋዬ ታጠኝበት ፈውስ ይሁንሽ

መንፈሴ ግን በወገኖቼ ላይ አድሮ

ነፃ ትውጣ ኢትዮጵያ፤ ብርሃን ታግኝ ዳውሮ

የስጋዬ ጭስ አይጥፋ፤ ሰማየ ሰማያት ይንካ

የሚጠቅማት፤ የሚረዳት፤ ከሆነላት ትዳን ዋካ

አለዛም ጌታዬ ታምር አውርድ

በጥፋተኞች ላይ ፍረድ

እኔንም አድነኝ ከመንደድ

ሆኖም እኩልነትን ረግጨ

ፍርድን አብሬአቸው ደፍጥጨ

ሰብዓዊ መብትን ከምገድላት

ዲሞክራሲን ከማፍናት

ስጋዬን ሳይሆን ነፍሴንም አትማራት

በአላማዬ አጽናኝ

ለሀገሬ ቤዛ አድርገኝ

ዋካን እንዳላሳፍር፤ ዳውሮን አንገት እንዳላስደፋ

ነፍሴን ነጥቄ እንዳጠፋ

እርዳታህ አይለየኝ

ፍራቻዬን ግፈፍልኝ

ዳግም በሞቴ ማንም አያልቅሰ

እልል ይበል ይልቅስ

የሚለቀስለት ለቆመው ነው

እንባ ለሱ ነው የሚአስፈልገው

ለኢትዮጵያ ነው ኡኡታ ለሷ ነው ለቅሶ

አንገቷ ከላይ ተበጥሶ

አጥንቷ ድረስ እየተጋጠች

የስቃይ ቀኗን እየቆጠረች

ላለችው ነው ለቅሶ የሚአስፈልጋት

የገዛ ልጆቿ በመከራ ለደፈቋት

እንግዲህ ኢትዮጵያ፤ ኖሬ ሳይሆን ሞቼ ከሆነ የምጠቅምሽ

እንቺ ስጋዬ ይጭስልሽ

አጥንቴ አሮ ይቡነንልሽ

እድሌ ካንቺ ጋር ይተሳሰር

እንዳሳረሩሽ ልረር

እንዳነደዱሽ ነድጄ

ነፍሴን ስነጥቃት በጄ

የናቴን በደል ስጋራ

በእልልታ አጅቡኝ በጭፈራ

አዎን ሀገሬ መንደዴ ነው የሚአዋጣሽ

የደም የደምማ ያፈሰሰስ፤ የሚአፈስ መች አሳጣሽ

ልጅ ሆኔ በጎልማሳነት ወራት

በተራሮችሽ ግርጌ፤ በሜዳሽ ላይ ስጫውት

ገና ምኑም ሳገባኝ

ፍቅርሽ ልቤ ገብቶ ተጣብቶኝ

አንጀቴ ውስጥ ተቀምጠሽ

ከነፍሴ ጋር ተሳስረሽ

የመውድውዴን ጽናት እንደያዝኩ

ሀዘንሽን፤ ደስታሽንም ስካፈል ኖርኩ

ያም ሆኖ ኖሬ ካልጠቀምኩሽ

ላገረጡት ጥቁር ፊትሽ

እንቺ አካሌ ወዝ ይሁንሽ

ዋካም ብርሃን አግኚ

በመስዋዕትነቴ ዳኚ

ዳውሮም ይርገፍ ጭጋግሽ

ተገላገይ ከመከራሽ

እኔማ እናቴ ስሜን ስታወጣ

ገብቷት ኖሮ የህይወቴ የኋላ እጣ

የኔ ሰው” አለችኝ የኔ ሰውነትን ትታ

ለሷ እንደማልሆናት አውቃው የሀገር ልጅነቴን ገምታ

ያቺ እናቴ ስህተት አላት

ቆሜ ላገር ምን ጠቀምኳት

ትል ይመስል ስፍረውባት

ወስጥ አካሏን ሲቦጭቋት

ለዚህ ጊዜ ካልሆንኩላት

ልጅነቴ ምን ሊበጃት

መሞቴ ነው የሚሻላት።

ለምን ሞተ የሚል ደግሞ ተራ ይዞ

የኔን መንፈስ ተመርኩዞ

ነጻነትን እንዲያመጣ

በበደሉ እንዲቆጣ

ቤዛ ልሁን እኔን አጽናኝ

ሞቴን ከእጄ አትንፈገኝ

ልመናዬ ያወቃችሁ

የእኔ ሚስጥር የገባችሁ

በእፎይታ እንድጠለል

በነፃነት እንድቃጠል

አደራችሁ እንዳትነኩኝ

ለምትቀብሩት አታስቀርኝ

ይልቅስ በእኔ ገናችሁ ተነሱ

አገር ዙርያውን በትግላችሁ ለኩሱ

እሳቱን አቀጣጥሉት አንድዱት

በዕንባችሁ አታርጥቡት

እንባ አይደለም የሚበጀኝ

ባንድነታችሁ አጽድቁኝ

በትግላችሁ አድምቁኝ

የኔሰውን በቃ ተዉት

በልባችሁ ማህደር ጻፉት

ለነገው ሰው ነው ማሰብ፤ ለኔማ ሀዘን ምን ያደርጋል

አቀጣጥሉት፤ አፋፍሙት፤ ትግሉ ይጋል

እናም ሐገሬ ኢትዮጵያ፤ ዳውሮ ዙርያ ገጠም

የማወርስሽ፤ የምሰጥሽ፤ የለኝም ደም

ያም ሆኖ ንፉግ አልምሰልሽ

ለገረጣው ጥቁር ፊትሽ

መድሃኒት ካረገልሽ

እንቺ አካሌ ወዝ ይሁንሽ።

ወለላዬ ከስዊድን welelaye2 yahoo.com