Back

ⓘ የባቢሎን ግንብ. በመጽሐፍ ቅዱስ ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 11 ዘንድ፣ የባቢሎን ግንብ ሰማይን እንዲደርሱ የተባበሩት ሰው ልጆች የሠሩ ግንብ ነበር። ያ ዕቅድ እንዳይከናወንላቸው ለመከልከል፣ እግዚአብሔር እያንዳንዱ በተለየ ቋንቋ እንዲናገርበት ልሳናታቸውን ..
                                               

ራግው

በ ኦሪት ዘፍጥረት 11፡20 ዘንድ፣ የራግው እድሜ 132 ሲሆን ሴሮሕ ተወለዱ፤ ራግውም ከዚያ 207 ዓመታት ኑሮ በጠቅላላ 339 ዓመታት ኖረ ማለት ነው። እነዚህ ቁጥሮች ከግሪኩ ትርጉም 70ው ሊቃውንት እና ከሳምራዊው ትርጉም ጋራ ይስማማሉ። በመደበኛው ዕብራይስጥ ትርጉም ግን፣ ራግው ሴሮሕን የወለደው ዕድሜው 32 ዓመት ነበር፤ ስለዚህ በጠቅላላ 239 ዓመታት መኖሩ ነው። በ መጽሐፈ ኩፋሌ ዘንድ፣ የራግው እናት ስም ሎምና የሰናዖር ልጅ ነበር፤ በ1580 ዓመተ ከዓለም ፍጥረት በኋላ ተወለደ። ይህም የባቢሎን ግንብ የተጀመረበት ወቅት ነበር፤ በኩፋሌ አቆጣጠር ከማየ አይኅ 272 ዓመታት በኋላ ነው። የባቢሎን ግንብ የወደቅበት ዓመት ዕድሜው 59 ዓመታት ሲሆን ነው። በ1681 ዓመተ አለም ሚስቱን ኡራን የኡር ከሰድ ልጅ አገባት። በ1687 ዓ.ዓ. ሴሮሕ ተወለዱ፣ እንግዲህ የራግው እድሜ ያንጊዜ 107 ዓመታት ነበር። በዚያም አመት የከለዳውያን ዑር ተሠራና ከኖኅ የተወለዱት አሕዛብ መጀመርያ ጦርነት ሠሩ። የሞተበት ዓመት አይሠጠም።

                                               

ፋሌቅ

ፋሌቅ በ ኦሪት ዘፍጥረት መሠረት የዔቦር ልጅና የራግው አባት ነበረ። ዘፍጥረት 11፡18-19 ስለ ፋሌቅ እንደሚለው፣ የፋሌቅ ዕድሜ 130 ዓመት ሲሆን ራግውን ወለደ፣ ከዚያም ፋሌቅ 209 ዓመት ኖረ። እነዚህ ቁጥሮች ከግሪኩ ትርጉም ሲገኙ የዕብራይስጥና ሳምራዊው ትርጉም ቁጥሮች ግን ይለያያሉ። በእብራይስጥ ትርጉም በ30 ዓመት ራግውን ወለደ፣ ከዚያም 209 ዓመት ኖረ፤ በሳምራዊውም በ130 ዓመት ራግውን ወለደ፣ ከዚያም 109 ዓመት ኖረ። በተጨማሪ በዘፍጥረት 10፡25 ዘንድ በፋሌቅ ዘመን ምድሪቱ ተከፍላለች። ይህ የሴም፣ ካምና ያፌት ልጆች ኩፋሌ እንደ ሆነ ይታመናል። በ መጽሐፈ ኩፋሌ 8፡40 ፋሌቅ ከአባቱ ኤቦርና ከእናቱ አዙራድ በ1567 አመተ አለም ተወለደ። የምድር አከፋፈል በ1569 አ.አ. ሆነ 9፡1። በ1577 አ.አ. ፋሌቅ ሚስቱን ሎምና አገባ፤ እርሷም የሰናዖር ልጅ ትባላለች። በ1580 አ.አ. አዙራድ ልጁን ራግውን ወለደችለት; የባቢሎን ግንብ በ1596 አ.አ. ተጀመረ ይላል 10፡10-11።

                                               

መጽሐፈ ኩፋሌ

መጽሐፈ ኩፋሌ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዲዩትሮካኖኒካል መጻሕፍት አንዱ ነው። በሌሎቹ አብያታ ክርስትያናት ግን ዛሬ የማይቀበል መጽሐፍ ወይም ሲውዴፒግራፋ ይባላል። ነገር ግን ለቀድሞው የቤተ ክርስቲያን አበው ታውቆ የጥቅስ ምንጭ ሆነላቸው። የመጽሐፉ ግሪክ ትርጉም የሚታወቀው ከቅዱስ ኤፒፋንዮስ ጥቅሶች ባቻ ሳይሆን እንዲሁም በዩስቲን ሰማዕት፣ በኦሪጄን፣ በዲዮዶሮስ ዘአንጥያክያ፣ በኢሲዶር ዘሰቪላ፣ በአሲዶር ዘእስክንድርያ፣ በዩቲክዮስ ፣ በዮሐንስ ማላላስ፣ በጊዮርጊስ ሱንኬሎስና በቄድሬኖስ ጥቅሶች በከፊል ይታወቃል። ሆኖም መጽሐፉ በአይሁድ ሳንሄድሪን ከ1ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ እንደ ቅዱሳን መጻሕፍት አልተቀበለም ነበር። አንዳንድ ክፍል በቁምራን ዋሻ በ1939 ዓ.ም. እስከተገኘ ድረስ፣ የመጽሐፉ ዕብራይስጥ ትርጉም በሙሉ ጠፍቶ ነበር። ስለዚሁ ሁኔታ የዕብራይስጥ ትርጉም በማጣት መጽሐፉ በኋላ ዘመን በሮማ ቤተ ክርስቲያን አለቆች አልተቀበለም። ሆኖም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ዘንድ እንዲሁም በቤተ እስራኤል አይሁ ...

                                               

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥንታዊነት

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥንታዊነት በጥንት የተቀነባበረ የአይሁዶች ታሪክ መጽሐፍ ነው። አሁን ጽሑፉ የሚታወቀው በሮማይስጥ ትርጉም ብቻ ሲሆን ፣ ከጥንታዊ አይሁዳዊው ፈላስፋ ፊሎ 28 አክልበ 42 ዓም ገደማ ጽሑፎች ጋር አብሮ ተገኝቶ ስለ ደረሰልን፣ ለረጅም ጊዜ ፊሎ እራሱ የጻፈ ድርሰት እንደ ነበር ታሰበ። ዛሬ በፊሎ እንደተጻፈ ስለማይታመን፣ መጽሐፉ "ሲውዶ ፊሎ" Pseudo-Philo ወይም "ሐሣዊ ፊሎ" በመባል ይታወቃል። በጽሁፉ ውስጥ የደራሲው ስም መቸም ስለማይጠቀስ፣ ይዘቱ ሆን ብሎ በሐሠት ተጽፏል ለማለት ሳይሆን፣ ፊሎ በውነት እንዳልጻፈው ብቻ ለማመልከት ነው "ሐሣዊ ፊሎ" የተባለው። ታሪኩ በተጻፈበት ወቅት የአይሁዶች ዋና ቤተ መቅደስ በኢየሩሳሌም ገና እንዳልጠፋ ይመስላል፤ ስለዚህ ብዙዎቹ ሊቃውንት ከ62 ዓም አስቀድሞ እንደ ተቀነባበረ ገመቱ። የተጻፈበት ቋንቋ ዕብራይስጥ ሲሆን ከዚያ ወደ ግሪክኛ፣ ከዚያም ከግሪክኛ ወደ ሮማይስጥ እንደ ተተረጎመ ይታስባል። በዚህ መንገድ በይዘቱ ውስጥ ካሉት ስያሜዎች በሮማይስጥ ሲነበቡ በርካታዎች ከዕው ...

የባቢሎን ግንብ
                                     

ⓘ የባቢሎን ግንብ

በመጽሐፍ ቅዱስ ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 11 ዘንድ፣ የባቢሎን ግንብ ሰማይን እንዲደርሱ የተባበሩት ሰው ልጆች የሠሩ ግንብ ነበር። ያ ዕቅድ እንዳይከናወንላቸው ለመከልከል፣ እግዚአብሔር እያንዳንዱ በተለየ ቋንቋ እንዲናገርበት ልሳናታቸውን አደባለቀ። መግባባት አልተቻላቸውምና ስራው ቆመ። ከዚያ በኋላ፣ ሕዝቦቹ ወደ ልዩ መሬት ክፍሎች ሄዱ። ይህ ታሪክ ብዙ የተለያዩ ዘሮችና ቋንቋዎች መኖሩን ለመግለጽ እንደሚጠቅም ይታስባል።

                                     

1.1. ከዕብራይስጥ ብሉይ ኪዳን የባቢሎን ግንብ ዘፍ. 11፡1-9

ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች። ከምሥራቅም ተነሥተው በሄዱ ጊዜ በሰናዖር ምድር አንድ ሜዳ አገኙ፤ በዚያም ተቀመጡ። እርስ በርሳቸውም፦ ኑ፣ ጡብ እንሥራ፣ በእሳትም እንተኲሰው ተባባሉ። ጡቡም እንደ ድንጋይ ሆነላቸው፤ የምድርም ዝፍት እንደ ጭቃ ሆነችላቸው። እንዲህም፦ ኑ ለእኛ ከተማና ራሱ ወደ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ፤ በምድር ላይ ሳንበተንም ስማችንን እናስጠራው አሉ። እግዚአብሔርም የአዳም ልጆች የሠሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ። እግዚአብሔርም አለ፡ - እነሆ፣ እነርሱ አንድ ወገን ናቸው፣ ለሁሉም አንድ ቋንቋ አላቸው፤ ይህንም ለማድረግ ጀመሩ፤ አሁንም ያሰቡትን ሁሉ ለመሥራት አይከለከሉም። ኑ፣ እንውረድ፤ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው። እግዚአብሔርም ከዚያ በምድር ሁሉ ላይ በተናቸው፤ ከተማይቱንም መሥራት ተዉ። ስለዚህም ስምዋ ባቢሎን ተባለ፣ እግዚአብሔር በዚያ የምድርን ቋንቋ ሁሉ ደባልቋልና፤ ከዚያም እግዚአብሔር በምድር ሁሉ ላይ እነርሱን በትኖአቸዋል።
                                     

1.2. ከዕብራይስጥ ብሉይ ኪዳን በትንተና

የሰው ልጆች ሁሉ አንድ ኅብረተሰብ ሆነው የሠፈሩባት አገር ሰናዖር ለኤፍራጥስ ወንዝ ቅርብ ነበረች። ባቢሎን በጥንታዊ አካድኛ ምንጭ በተገኘ ባቢሉ ባብ-ኢሉ ማለት "የአማልክት በር" ለማለት ነው። በዕብራይስጥ ትርጉም ግን የ "ባቤል" ስም "መደባለቅ" ለማለት ለሚለው ቃል ይመስላል። ከውድቀቱ በፊት የተናገረው ቋንቋ አንዳንዴ "የአዳም ቋንቋ" መሆኑ ይባላል። በታሪክ አንዳንድ ሰው በግምት ያም ሆነ ይህ ቋንቋ መጀመርያው ቋንቋ እንደ ነበር የሚለው ክርክር አቅርቧል። ለምሳሌ ቋንቋው ዕብራይስጥ፣ አራማይስጥ፣ ግዕዝ ወይም ባስክኛ ቢሆንም እንደ ነበር በልዩ ልዩ አስተያየቶች ዘንድ ተብልዋል።

በኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 10 ባቢሎን ከተማ የናምሩድ ግዛት መጀመርያ እንደ ነበር ይላል።

                                     

2.1. ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ያለው አፈ ታሪክ ታሪክ

በሱመር ሳንጋር አፈ ታሪክ ተመሳሳይ ተረት አለ። በ ኤንመርካርና የአራታ ንጉስ የኡሩክ ኦሬክ ንጉስ ኤንመርካር አንድ ታላቅ መቅደስ በኤሪዱ ሲሠራ ለግንቡ የወርቅና የዕንቁ ግብር ከአራታ ያስገድዳል። አንድ ጊዜ ኤንኪ የተባለውን አምላክ ኗሪ ያለባቸው አገሮች ሁሉ ወደ አንድ ቋንቋ እንዲመልሳቸው ይለምናል። በሌላ ትርጉም ግን ኤንኪ የአገሮች ቋንቋ እንዲያደባለቅ ይላል። እነዚህ አገሮች ስሞች ሹባር፣ ሐማዚ፣ ሱመር፣ ኡሪ-ኪ የአካድ ዙሪያ እና የማርቱ አገር ይባላሉ።

በአንድ ዘመናዊ አስተሳሰብ መሠረት፣ የኤንመርካር መታወቂያ የብሉይ ኪዳን ናምሩድ አንድ ነው በመገመት የባቢሎን ግንብ ፍርስራሽ በውኑ ኤሪዱ በሚባል ከተማ ውስጥ ይገኛል ይላል። በዚህ ሀሳብ ኤሪዱ መጀመርያይቱ "ባቤል" እንደ ነበረች ማስረጃ ያቀርባል።

447 ከክርስቶስ በፊት የግሪክ ታሪክ መምህር ሄሮዶቱስ በባቢሎን ከተማ ስለተገኘ ታላቅ ግንብ ጻፈ። ይህ ምናልባት ሜሮዳክ የተባለው ጣኦት ቤተ መቅደስ ነበር፤ አንዳንድ ሊቅ ይህ መቅደስ የባቢሎን ግንብ ታሪክ ምንጭ እንደ ነበር የሚል እምነት አለው።

570 ከክርስቶስ በፊት የባቢሎን ንጉስ ናቡከደነጾር እንዲህ ብሎ ጻፈ፦

የዱሮ ንጉስ "የምድር ሰባት ብርሃናት" ቤተ መቅደስ አገነባ፤ ነገር ግን ራሱን አልጨረሰም። ከጥንት ጀምሮ ሰዎች ያለ ስርዓት ቃላቸውን ሳይገልጹ ትተውት ነበር። ከዚያ በኋላ መንቀጥቀጥና መብራቅ ደረቁን ሸክላ በትነውት ነበር፤ ጡቦቹ ተሰንጥቀው የውስጡ መሬት በክምር ተበትኖ ነበር። ትልቁ ጌታ ሜሮዳክ ሕንፃውን ለመጠገን አእምሮዬን አስነሣ። ሥፍራውን አላዛወርኩም፤ ዱሮ እንደነበር መሠረቱን አልወሰድኩም። እንግዲህ እኔ መሰረትኩት፤ ሠራሁት፤ በጥንት እንደነበር፣ ጫፉን እንዲህ ከፍ አደረግኩት።


                                     

2.2. ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ያለው አፈ ታሪክ በአይሁድና በዲዩተሮካኖኒካል ሥነ ጽሁፍ

በኦሪተ ዘፍጥረት እግዚአብሔር ግንቡን እንዳጠፋው ወይም ሥራውን ዝም ብሎ እንዳቆመ ምንም አይለንም። መጽሐፈ ኩፋሌ ግን በታላቅ ንፋስ ግንቡን እንዳገለበጠ ይመሰክራል። የድሮ ታሪክ ጸሐፊዎች አብዴንስ፥ ቆርኔሌዎስ አሌክስንድሮስ እና ዮሴፉስ እንዲሁም የሲቢሊን ራዕዮች ሁላቸው ግንቡ በንፋሶች እንደ ተገለበጠ ጻፉ፡

                                     

2.3. ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ያለው አፈ ታሪክ መጽሐፈ ኩፋሌ

መጽሐፈ ኩፋሌ ስለ ግንቡ ብዙ ይላል።

.በአራተኛው ሱባዔ ጡቡን ሠርተው በእሳት ተኰሱ። ጡቡም እንደ ድንጋይ ሆነላቸው፤ የሚመርጉበት ጭቃውም ከባሕር በሰናዖር አገርም ከውኃዎች ምንጭ የሚወጣ የባሕር አረፋን ሆነላቸው። በአርባ ሦስት ዓመት ሠሩት። ፍጹም ጡብ አድርገው ሲሠሩት ኖሩ። ወርዱ ሦስት ክንድ፣ ቁመቱ አሥር ክንድ፣ አንድ ወገን የሚሆን አቈልቋዩ ሦስት ክንድ ነው። ቁመቱ አምስት ሺህ ከአራት መቶ ከሠላሳ ሦስት ክንድ ከሁለት ስንዝር ወደ ሰማይ ወጣ። አቈልቋዩ አሥራ ሦስት ምዕራፍ ነው.
                                     

2.4. ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ያለው አፈ ታሪክ የአይሁድ ሚድራሽ

የአይሁድ ረቢዎች ሥነ ጽሑፍ ስለ ባቢሎን ግንብ ማገንባት ምክንያቶች የተለያዩ አስተያየቶች ያቀርባሉ። በእግዚአብሔር ላይ አመጽ እንደ ማድረግ ሚሽና ይቈጥረዋል።

የግንቡ ሰሪዎች በአንዳንድ አይሁዳዊ ምንጭ ደግሞ "የመነጣጠል ትውልድ" ይባላሉ። እነሱ፦ "እግዚአብሔር ላየኛውን አለም ለራሱ ለመምረጥ ታቸኛውንም ለኛ ለመልቀቅ መብት የለውም፣ ስለዚህ ግንብ እንስራ፣ በጫፉም ሰይፍ የያዘ ጣኦት ይኑር፤ ከእግዚአብሔር ጋራ መዋጋት የምናስብ እንዲታይ" እንዳሉ ሚድራሽ ደግሞ ይጽፋል።

አንዳንድ ጽህፈት ደግሞ አብርሃም አስጠነቀቃቸውና ሰሪዎቹም የተቃወሙ አብሪሃም ነበር ይላል። ከዚያ በላይ በየ1656 አመታት ወሃ በምድር አፍስሶ ሰማይ ስለሚንገዳገድ እንግዲህ ማየ አይህ እንዳይዳግምብን በዓምዶች እንደግፈው ማለታቸው በአይሁዶች ታሪክ ማንበብ ይቻላል። እንኳን ተልሙድ በተባለ አይሁዳዊ መጽሐፍ ስለ ግንቡ ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር መዋጋት እንደ ፈለጉ ይመዝገባል። ፍላጻ ወደ ሰማይ ልከው በደም ተቀብቶ ሲመለስ ተበረታቱ ይላል። ጆሲፉስና አንድ ሚድራሽ ናምሩድ የስራ እቅዱ መሪ እንደ ነበር ይጽፋሉ።

                                     

2.5. ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ያለው አፈ ታሪክ 3 ባሮክ

ክግሪክና ከስላቮኒክ ቅጂ ብቻ የሚታወቀው 3 ባሮክ ስለ ግንብ ሲያውራ ለአይሁዳዊው ልማድ ሊስማማ ይችላል። ባሮክ በራእይ መጀመርያ የነፍሶች እረፍት ቦታ ለማየት የወሰዳል። እነዚህ በእግዚአብሔር ላይ የሁከት ግንብ የሰሩ ይባላሉ። ከዚያ በኋላ ሌላ ቦታ ያያል፣ እዚያም በውሻ መልክ፣

ግንቡን ለመስራት የመከሩ ናቸው፣ የምታያቸው ብዙ ወንድንና ሴት ጡብ ለመስራት ነዱአቸውና፤ ክነዚህም አንዲት ጡብ የምትሰራ ሴት በመውለድዋ ሰዓት ልትፈታ አልተፈቀደችም፤ ነገር ግን ጡብ እየሰራች ወለደች፤ ልጅዋንም በሽርጥዋ ውስጥ ተሸከመች፤ ጡብንም መስራትዋን አላቋረጠችም። ገታም ታያቸው ንግግራቸውንም ደባለቀ፤ ይህም ግንቡ ለ463 ክንድ ቁመት በሰሩት ጊዜ ሆነ። መሠርሠርያንም ይዘው ሰማይን ለመውጋት አሰቡ፣ እንዲህ ሲሉ፦ ሰማይ ሸክላ ወይም ነሃስ ወይም ብረት መሆኑን እናውቅ። እግዜር ይህንን አይቶ አልፈቀደላቸውም፤ ነገር ግን አሳወራቸው ንግግራችውንም ደባለቀ፤ አንተም እንደምታያቸው አደረጋቸው።
                                     

2.6. ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ያለው አፈ ታሪክ በቁርዓንና በእስልምና

በስም ባይታወቅም፣ የባቢሎንን ግንብ የሚመስል ንባብ በቁርዓን ውስጥ ይገኛል። በሱራ 28፡38 እና 40፡36-37 እንደሚለው፣ ፈርዖን ወደ ሰማይ ወጥቶ የሙሴን አምላክ እንዲቃወም ሐማንን የሸክላ ግንብ እንዲሰራለት ጠየቀው።

በሱራ 2:96 ደግሞ የባቢል ስም ቢገኝም ብዙ ተጨማሪ ዝርዝር አያቀርብም ። ይሁንና በያቁጥ አል ሃርናዊ ጽሕፈት እና ልሳን ኤል አራብ በተባለ መጽሐፍ ዘንድ ስለ ግንብ ምንም ባይጻፍም የሰው ልጆች ባቢል ወደሚባል ሜዳ በንፋሶች ሃይል ተወስደው እዚያ አላህ ለየወገናቸው ልዩ ቋንቋ እንደ መደባቸውና ንፋሶች ከዚያ ሜዳ እንደ በተናቸው ይተረታል።

በ9ኛ መቶ ዘመን የነቢያትና የነገሥታት ታሪክ የጻፉት የእስላም ታሪከኛ ሙሐመድ እብን ጃሪር አል-ታባሪ ይህን የመሰለ ተረት ያቀርባል ። በዚህ መሠረት ናምሩድ ግንቡን አስገንቦ አላህ አጠፋውና የሰው ልጅ ቋንቋ ከዚያ ቀድሞ የሶርያ አራማያ ሲሆን የዛኔ ወደ 72 ልሣናት ይደባለቃል።

ከዚያ በላይ ደግሞ በ13ኛ መቶ ዘመን የጻፉት ሌላ የእስላም ታሪከኛ አቡ አል-ፊዳ ይህን መሰል ታሪክ ሲያወራ የአብርሃም ቅድመ-አያት ዔቦር ግንቡን ለመሥራት እምቢ ስላለ የፊተኛው ቋንቋ ዕብራይስጥ እንዲቀርለት ተፈቀደ ብሎ ይጽፋል።

                                     

2.7. ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ያለው አፈ ታሪክ መጽሐፈ ሞርሞን

የሞርሞኖች መጽሐፍ መጽሐፈ ሞርሞን ስለ ግንቡ ካለበት መረጃ አብዛኛው ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ይስማማል። በተጨማሪም በ መጽሐፈ ኤጠር ዘንድ የያሮዳውያን ወገን ቋንቋቸው ሳይደባለቅ ወጥተው በስሜን አሜሪካ ሠፈሩ። ነገር ግን እነኚህ "ያሮዳውያን" የሚባል ሕዝብ እስከ ዛሬ በተገኘ ከሞርሞን በተቀር በምንም ሌላ እምነት ጽሁፍ አልታወቁም።

                                     

2.8. ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ያለው አፈ ታሪክ በሌሎች ባህሎች አፈታሪክ

በሜክሲኮ እና በማዕከል አሜሪካ አፈታሪክ ውስጥ ለባቢሎን ግንብ በጣም ተመሳሳይ ተረቶች አሉ። ለምሳሌ በአንድ ተረት ዘንድ፣ ሸልኋ ከማየ አይህ ያመለጡ 7 ራጃጅሞች አንዱ ሲሆን፣ ሰማይን ለመውረር ታላቅ ፒራሚድ በቾሉላ ሠራ። አማልክት ግን በእሳት አጥፈውት የሠሪዎቹን ቋንቋ አደናገሩ። የስፓንያዊው መነኩሴ ዲየጎ ዱራን 1529-1580 የኖሩ ሜክሲኮ ከተወረረ በኋላ ይህንን ተረት ከባለ መቶ አመት ቄስ ሰምተው ጻፉበት።

እንዲሁም ጥንታዊ ቶልቴክ ሕዝብ ሌላ ትውፊት እንደ ነበራቸው ኗሪው የታሪክ ሊቅ ዶን ፈርዲናንድ ዳልቫ እሽትልሾችትል 1557-1640 ይጠቅሳል። በዚህ ተረት ከታላቅ ጎርፍ በኋላ የሰው ልጆች በዝተው ሌላ ጎርፍ እንዳይዳግምባቸው አንድ ረጅም ግንብ ሠሩ ይላል። ነገር ግን ልሳናታቸው ተደባልቀው ወደ ተለያዩ አገሮች ተጓዙ።

እንደገና ሌላ ትውፊት በአሪዞና ቀይ ኢንዲያኖች ጎሣ በቶሆኖ ኦኦዳም ብሔር መካከል ይገኛል። በዚህ መሠረት ሞንተዙማ የሚባል ሃያል ከታልቅ ጎርፍ ከማምለጡ በኋላ እጅግ ክፉ ሆነና እስከ ሰማይ ድረስ የሚረዝም ቤት ለመሥራት ቢሞክር ታላቁ መንፈስ በመብራቅ አጠፋው።

ከዚያ በላይ በታዋቂው መርማሪ ዶክቶር ሊቪንግስተን ዘንድ በ1871 ዓ.ም. በንጋሚ ሀይቅ አፍሪቃ ተመሳሳይ ተረት አገኙ። በዚህ ትርጉም ግንቡ ሲወድቅ የሠሪዎቹ ራሶች ተሰባበሩ። ጸሐፊው ጄምስ ጆርጅ ፍሬዘር ደግሞ የሊቪንግስተን ወሬ በሎዚ ጎሣ አፈ ታሪክ ከሚገኝ ተረት ጋር ግንኙነቱን አጠቁሟል። በዚህ ተረት ዘንድ፣ ፈጣሪ አምላካቸው ኛምቤ ወደ ሰማይ በሸረሪት ድር ሸሽቶ ክፉ ሰዎች እንዲያሳድዱት ከተራዳዎች ግንብ ቢሠሩም ተራዳዎቹ ግን ሲወድቁ ሰዎቹ ይጠፋሉ። በተጨማሪ በአሻንቲ ጎሣ እንዲህ መሰል ተረት ሲያገኝ በተራዳዎቹ ፈንታ ግን ግንቡ የተሠራ ከአጥሚት ዘነዘናዎች ክምር ነው። ፍሬዘር ደግሞ እንደነዚህ ያሉ ትውፊቶች በኮንጎ ሕዝብ እና በታንዛኒያ ጠቅሶአል፤ በነዚህ ትውፊቶች ሰዎቹ ወደ ጨረቃ ለመድረስ ሲሞክሩ ተራዳዎች ወይም ዛፎች ይከምራሉ።.

ይህን የመሠለ ታሪክ ደግሞ በጣሩ ሕዝብ እንዲሁም በካርቢና በኩኪ ብሔሮች በስሜን ሕንድ ተገኝቷል። ከዚህ በላይ በምየንማ የሚኖረው ካሬን ሕዝብ ያላቸው ልማድ ይህን አይነት ተጽእኖ ያሳያል። በዚያ ልማድ መሠረት፣ ከአዳም 30 ትውልዶች በኋላ በካሬን-ኒ አገር ታላቅ ግንብ በተተወበት ቋንቋዎችም በተደባለቀበት ጊዜ የካሬን ቅድማያቶች ከካሬን-ኒ ተለይተው ወደ አገራቸው እንደ ፈለሱ ይባላል። እንደገና በአድሚራልቲ ደሴቶች ሌላ አፈታሪክ ሰዎች እስከ ሰማይ ድረስ ታላቅ ቤቶች ለማድረስ ሞክረው ከወደቁ በኋላ ልሳናታቸው ተደባለቁ ይላል።                                     

3. የግንቡ ቁመት

ኦሪት ዘፍጥረት ስለ ግንቡ ቁመት ከፍታ ምንም ባይነግረንም፣ በሌላ ምንጭ ግን ልዩ መልስ ሊገኝ ይቻላል። መጽሐፈ ኩፋሌ 5.433 ክንድ እንደ ደረሰ ሲል ይህ ከዛሬ ሕንጻዎች እንኳ በእጥፍ የሚልቅ ነው። እንዲሁም በ3ኛ ባሮክ መሠረት እስከ 463 ክንድ 212 ሜትር ድረስ መሆኑን ሲነግረን ይህ ቁመት እስከ ዘመናዊው 1881 ዓ.ም. አይፈል ግንብ ድረስ አልተበለጠም። ናቡከደነጾር ክ.በ. 570 አካባቢ ያሠራው ግንብ 100 ሜትር ገደማ ከፍ እንዳለ ይታመናል።

በሌሎች ምንጭ ዘንድ፦

  • በ1292 ዓ.ም. - ጣልያናዊው ጸሐፊው ጆቫኒ ቪላኒ እንዳለው፣ የግንቡ ከፍታ እስከ 4000 ፔስ = 1 ሜትር ያሕል ድረስ ዘረጋ፣ ደግሞ ዙሪያው 80 ማይል ነበር።
  • የ14ኛ ክፍለ ዘመን ጉዞኛ ጆን ማንደቪል ደግሞ ስለ ግንቡ ሲገልጽ ቁመቱ 64 ፉርሎንግ 8 ማይል ያሕል ደረሰ ብሎ ጻፈ።
  • የ17ኛ ክፍለ ዘመን ታሪከኛ ፈርስቴገን ስለ ከፍታው 5164 ፔስ 7.6 ማይል ይላል። ከዚህ በላይ ወደ ላይ የሚወስደው ጠምዛዛ መንገድ በይበልጥ ሰፊ በመሆኑ ለሠራተኞችም ሆነ ለእንስሶች ማደሪያ ለመስራት እንኳ የመኖ እርሻ ለመብቀል በቂ እንደ ነበር ይጽፋል።
  • በ586 ዓ.ም. አካባቢ የጻፉት ታሪከኛ የቱር ጎርጎርዮስ የቀድሞውን ታሪከኛ ኦሮስዮስን 409 ዓ.ም. አካባቢ ሲጠቅሱ፣ ስለ ግንቡ ቁመት 200 ክንድ ይሰጣል።
                                     

4. የተበተኑት ልሳናት አቆጣጠር

ከመካከለኛው ዘመን ጽነ ጽሁፍ መካከል በባቢሎን ግንብ የተበተኑትን ልሳናት ለመቆጠር የሚሞክሩ ታሪኮች ብዙ ናቸው። በኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 10 ውስጥ የኖህ ተወላጆች ስሞች ሁሉ ሲቆጠሩ ለያፌት ልጆች 15፣ ለካም ልጆች 30፣ ለሴም ልጆች 27 ስሞች ይሠጣል። እነዚህም ቁጥሮች ከባቤል ባቢሎን መደባለቅ የወጡት 72ቱ ልሣናት ሆነው ተመሠረቱ፤ ሆኖም የቋንቋዎች መታወቂያ በጊዜ ላይ ይለያይ ነበር። የዕብራይስጥ ትርጉም ግን የይልሳና የቃይንም ስሞች ስለሌለው አይሁዳዊ ምንጮች እንደ ሚሽና ስለ 70 ልሳናት ይናገራሉ። 72 ወይም 73 ልሳናት የሚሉ ጥንታዊ ምንጮች ክርስቲያናዊው ጸሐፊዎች የእስክንድርያ ቄሌምንጦስና አቡሊደስ 2ኛ ክፍለ ዘመን እንዲሁም በ350 ዓ.ም. ገዳማ የተጻፈው በዓተ መዛግብት ፤ በ365 ዓ.ም. ገደማ ፓናሪዮን የጻፉት የሳላሚስ ኤጲፋንዮስና በ404 ዓ.ም. ገደማ የግዜር ከተማ የጻፉት ቅዱስ አውግስጢኖስ ናቸው።

የሴቪሌ ኢሲዶሬ 625 አካባቢ ስለ 72 ቋንቋዎች ቢያወራ ከኦሪት ስሞቹን ሲዘረዝር ግን የዮቅጣን ልጆች ቀርተው የአብርሃምና የሎጥ ልጆች ተተኩ፤ ስለዚህ 56 ስሞች ብቻ አሉ። ከዚያ በራሱ ዘመን ከታወቁት ወገኖች እንደ ላንጎባርዶችና ፍራንኮች ይዘረዝራል። ከዚሁ ሂሳብ ተጽእኖ የተነሣ በኋለኞቹ ታሪኮች ለምሳሌ በአይርላንድ መንኩሳዊ መጻሕፍት አውራከፕት ና ኔከሽ ና የ11ኛ ክፍለ ዘመን ሌቦር ጋባላ ኤረን እንዲሁም በአይሁዳዊው ሚድራሽ መጽሐፈ ያሸር ፤ ሎምባርዶችና ፍራንኮች እራሳቸው የያፌት ልጅ ልጆች ስሞች ሆኑ።

ከነዚህ ሌሎች ከባቤል ስለተበተኑት ስለ 72 ወይም 70 ልሣናት የሚናገሩት ምንጮች ብዙ ናቸው። ከነሱም፡ የነቢያትና የነገሥታት ታሪክ ከእስላማዊው መሐመድ እብን ጃሪር አል-ታባሪ 9ኛ ክፍለ ዘመን፤ የጥንታዊ እንግሊዝኛ ግጥም ሰሎሞንና ሳቱርን ፤ አይሁዳዊው ካባላ ጽሑፍ ባሒር 1166 ዓ.ም.፤ የአይስላንዳዊው ስኖሪ ስቱርሉሶን ንዑስ ኤዳ 1190 ዓ.ም. አካባቢ፤ በጽርዕ የተጻፈው መጽሐፈ ንቡ 1214 ዓ.ም.፤ ጌስታ ሁኖሩም ኤት ሁንጋሮሩም 1276 ዓ.ም.፤ የጆቫኒ ቪላኒ ታሪክ 1300 ዓ.ም.፤ እና አይሁዳዊው ሚድራሽ ሃ-ጋዶል 14ኛ ክ.ዘ. ናቸው። በቪላኒ ትርጉምም ግንቡ "ከማየ አይህ በኋላ 700 አመት ተጀምሮ ከአለሙ ፍጥረት እስከ ባቢሎን ግንብ መደባለቅ ድረስ 2354 አመቶች ነበሩ። በስራ ላይ ለ107 አመታት እንደ ቆዩም እናገኛለን፤ ሰዎች በዛኛ ዘመን ለረጅም ዕድሜ ይኖሩ ነበርና።" በ ጌስታ ሁኖሩም ኤት ሁንጋሮሩም መሠረት ግን ሥራ እቅዱን ከማየ አይህ በኋላ 200 አመት ብቻ ጀመሩ።

የ72ቱ ቋንቋዎች ልማድ እስከ ኋለኛ ዘመን ድረስ ቆየ። ስፓንያዊው ሆዜ ዴ አኮስታ በ1568 ዓ.ም. ከዚህ ቁጥር አብልጦ በፔሩ ብቻ ስንት መቶ እርስ በርስ የማይግባቡ ቋንቋዎች እንዳገኘ ተገረመ፤ ከመቶ አመት በኋላ እንደገና ፖርቱጊዙ አንቶኒዮ ቪዬራ ስለ ብራዚል ቋንቋዎች ብዛት ተመሳሳይ አስተያየት አቀረበ።                                     

5. ዘመናዊ ባሕል

የባቢሎን ግንብ በዘመናዊ ልብ ወለድ ታሪክ፣ ፊልሞችና ጨዋታዎች ሚና ተጫውቷል። ለምሳሌ ባንድ ደራሲ ኒል ስቲቨንሶን ልብ ወልደ ታሪክ ስኖ ክራሽ፣ የግንቡ ትርጉም ሰዎች ወደ ሰማይ በመንኮራኩር የመድረስ ሙከራ ምሳሌ ነው። እንደገና በሌላ ልብ ወለድ፣ የዳግላስ አዳምስ ዘ ሂችሃይከርስ ጋይድ ቱ ዘ ጋላክሲ፣ የባቤል ዓሣ በጆሮ ውስጥ ሲገባ ማንኛውንም ቋንቋ ለማስተርጉም ችሎታ አለው።

በ1920 ፊልሙ ሜትሮፖሊስ፣ የባቢሎን ግንብ በአለማዊ መንግሥት ሁለተኛ ይሰራል።

ከዚሁ በላይ የባቢሎን ግንብ በበርካታ የኮምፒዩተርና የቪዴዮ ጨዋታዎች ውስጥ ይታያል። እነሱም ዚኖጊርስ፣ ፋይናል ፋንታሲ 4፣ ዱም፣ ፕሪንስ ኦፍ ፐርዝያ፡ ዘ ቱ ስሮንስ፣ ዶሺን ዘ ጃየንት፣ ሲሪየስ ሳም፡ ሰከንድ እንካውንተር፣ ፍሪስፔስ 2፣ ፔንኪለር፣ ኢሉዠን ኦቭ ጋያ፣ እና ክሩሴድር ኦቭ ሰንቲ የሚባሉ የቪዴዮ ጨዋታዎች ናቸው። እንዲሁም ሻዶው ኦቭ ዘ ኮሎሰስ፣ ሲቪላይዜሸን 3፣ ዴቪል መይ ክራይ 3፣ እና ሜጋ ማን ኤክስ፡ ኮማንድ ሚሸን በሚባሉ ጨዋታዎች የባቢሎን ግንብ ምሳሌዎች ሊታዩ ይችላሉ።