Back

ⓘ ሌብኒትዝ. ጎትፍሪድ ቪልሄልም ሌብኒትዝ 1646 – November 14 1716 እ.ኤ.አ የ17ኛው ክፍለ ዘመን የጀርመን የሒሳብ ሊቅ፣ ሳይንቲስት፣ ፈላስፋ፣ ፍርድ አጥኝና ባጠቃላይ መልኩ ሁለ ገብ ተመራማሪ ነበር። ሌብኒዝ ከኢሳቅ ኒውተን ትይዩ ካልኩለስ የ ..
ሌብኒትዝ
                                     

ⓘ ሌብኒትዝ

ጎትፍሪድ ቪልሄልም ሌብኒትዝ 1646 – November 14 1716 እ.ኤ.አ) የ17ኛው ክፍለ ዘመን የጀርመን የሒሳብ ሊቅ፣ ሳይንቲስት፣ ፈላስፋ፣ ፍርድ አጥኝና ባጠቃላይ መልኩ ሁለ ገብ ተመራማሪ ነበር። ሌብኒዝ ከኢሳቅ ኒውተን ትይዩ ካልኩለስ የተባለውን የዕውቀት ዘርፍ ፈጥሯል። አሁን ድረስ ተማሪወች የሚጠቀሙበት የካልኩለስ የአጻጻፍ ስልት በዚህ ሰው የተፈለሰፈ ነው። ለኮምፒዩተር ስራ እጅግ ወሳኝ የሆነውን የሁለትዮሽ ቁጥር ስርዓት ዘመናዊ ኮምፒዩተሮች ከመሰራታቸው 300 አመት በፊት ፈልስፏል።

በፍልስፍናው ዘርፍም ጠለቅ ያለ አስተዋጽኦ አበርክቷል። የሌብኒዝ ፍልስፍና እንደ ደካርት ፍልስፍና ቀልበኛ ይባላል። "ይህ ዓለም እግዚአብሔር ሊፈጥራቸው ይችላቸው ከነበሩ ዓለማት ሁሉ የተሻለ" ነው የሚለው ድምዳሜው የሌብኒዝን ፍልስፍና ብሩህ ተስፈኛ በሚባል መደብ ስር እንዲታወቅ አድርጎታል። የሌብኒዝ ፍልስፍና የቀደምት አውሮጳውያን የፍልስፍና ዘዴ ተብሎ የሚታወቀውን ስኮላስቲክ ወደ ኋላ የሚመለከትና ወደፊት ደግሞ በ20ኛው ክ/ዘመን ብቅ ያሉን ዘመናዊ ሥነ አምክንዮ እና ትንታኔአዊ ፍልስፍናን የተነበየ ነበር። በርግጥም ከደካርትና ከስፒኖዛ ጋር በመሆን ሌብኒዝ የ17ኛው ክፍለ ዘመን የአውሮጳ ዋና ቀልበኛ ፈላስፋ ነበር ቢባል ማጋነን አይሆንም።

ከዚህ በተጨማሪ ሌብኒዝ ለተፈጥሮ ህግጋት ጥናት እና ቴክኖሎጂ እንዲሁም ሥነ ህይወት ጥናቶች ከፍተኛ አስተዋጾችን አድርጓል። በህክምና፣ መሬት ጥናት፣ እድል ጥናት ፣ ታሪክ፣ ስነ ቋንቋ፣ ሥነ ምግባር፣ ሕግ፣ ፖለቲካ፣ ሥነ አዕምሮ፣ መረጃ ሳይንስ ላይ ህልቁ መሳፍርት ጽሁፎችን አቅርቧል። የሚያሳዝነው ግን እኒህ ሁሉ ጽሁፎቹ በመጽሄቶች ገጽና በደብዳቤውች ተሰባጥረው አንድ ላይ ስላልታተሙ እስካሁን ዘመን ድረስ የዚህ ሰው ስራ ስፋትና ወርዱ በርግጥም አይታወቅም።

ሌብኒዝ ከኒውተን ጋር "ማን ካልኩለስን ቅድሚያ ፈለሰፈ" በሚል ጥን አንስተው በእንግሊዝና በአውሮጳ ሳይንቲስቶች መካከል ከፍተኛ ሽኩቻ ነበር። በአሁኑ ዘመን ሁለቱም ሰወች ካልኩለስን ለየብቻቸው እንዳገኙ ይታመናል። ሌብኒዝ ብዙ ወዳጆች ቢያፈራም በኋለኛ ዘመኑ ብዙ ጠላቶች ስለነበሩት ሲሞት ካለጸሃፊው በስተቀር ለቀብሩ የመጣ አልነበረም። የዚህ ድንቅ ሰው ህይወት እንዲህ መፈጸሙ ብዙ ጸሃፊወችን እስከ አሁኑ ዘመን ሲያሳዝን ይኖራል።

                                     
  • የኒውተን የግስበት ቀመር ካልኩለስ ለተባለውን የሒሳብ ክፍል መጀመር ይህን ክብር ከጀርመናዊው ምሁር ከጎትፍሪድ ሌብኒትዝ ጋር ይጋሩታል ስለ ብርሃንና ስለሚይዛቸው ቀለማት ያገኘው ግኝት ይጠቀሳሉ በተጨማሪም ኒውተን የእንቅስቃሴ ህጎችን
  • ጀርመናዊው ሌብኒትዝ ካልኩለስን ከጥራዝ ነጠቅነት በተላቀቀ መልኩ ወጥ በሆነ ስሌት ማነጽ ጀመረ ሌብኒትዝ በጊዜው ከኒውተን ኮረጀ ተብሎ ቢከሰስም ባሁኑ ዘመን ግን እራሱን ችሎ የካልኩለስን ህጎች እንዳገኘ ይታመናል ሌብኒትዝ ከኒውተን
  • በምክኑያዊነት rationalism ፍልስፍና ታዋቂነትን ያተረፈና ከሱ ፍልስፍና ተነሰተው በማስፋፋት እነ ባሩክ ስፒኖዛ እና ሌብኒትዝ ለምክኑያዊ ፍልስፍና ጥበብ ታላላቅ ድርሻ ሊያበረክቱ ችለዋል በዚህ ተቃራኒ ግን ዳሳሻዊነት empiricism ፍልስፍናን