Back

ⓘ ሱዳን በይፋ የሱዳን ሪፑብሊክ ከአፍሪካ በስፋት ሦስተኛ ስትሆን በአህጉሪቱ ሰሜናዊ ምስራቅ ክልል ትገኛለች። ዋና ከተማዋ ካርቱም ነው። ከግብፅ ፣ ከቀይ ባሕር ፣ ከኤርትራ ፣ ከኢትዮጵያ ፣ ከደቡብ ሱዳን፣ ከመካከለኛው የአፍሪካ ሪፑብሊክ ፣ ከቻድ ፣ እና ..
                                               

ኑርኛ

ኑዌርኛ በደቡብ ሱዳን እንዲሁም በኢትዮጵያ የሚነገርሲሆን በስሩ ሌሎች ዳየሌቶታችም አሉ ።ኑዌርኛ ናይሎ ሳህራዊ ተብሎ በሚታወቀው የቋንቋ መደብ ውስጥ ይጠቃለላል።በኢትዮጵያ የሚነገረው ኑዌርኛ በዋናነት በጋምቤላ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ በስፋት ይነገራል። በትምህርት ቋንቋነትም እንደ አንድ የትምህርት አይነት ይሰጣል።

                                               

ጌታቸው ወልዩ

ጌታቸው ወልዩ ተወልዶ ያደገው አዲስ አበባ ነው።የተለያዩ ትምህርቶችን በከፍተኛ ትምህርት ተቁዋማት ገብቶ ተከታትሉዋል። በፍልስፍና፤ ፔዳጎጂ፤ ሳይኮሎጂ፤ ስነ-ጽሁፍ፤ጋዜጠኝነት፤ ኮሙኒኬሽን፤ ማርኬቲንግ፤ ታሪክ፤ ኣለም አቀፍ ጉዳዮችና ጂኦ ፖለቲክስ ላይ ሰፊ እውቀትና ልምድ ያለው ባለሙያ ነው፡፡በዓባይ ወንዝ ዙሪያ የኣባይ መዘዝ፤የዓባይ ጉዳይነ ያልተዘጋው ዶሴ የሚሉ ሶስት መጽሐፍትን ከዓመታት በፊት አዘጋጅቱዋል።በዓባይ ላይ ሶስት የአማርኛ መጽሃፍትን በመጻፍና በቀዳሚነት በማዘጋጀት የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ነው።በዓባይ ላይ ጥናት ለመስራት በመርከብ፤በአውሮፕላንና ሔሊኮፕተር፤በእግርና ጋማ ከብት፤ በመኪናና ባቡር ፈታኝ ጉዞ ያደረገ ዓባይ አስታዋሽ ባጣበት ዘመን የደከመ ጋዜጠኛና ደራሲ ነው።ከዓባይ መነሻ ጮቄና ግሽ ዓባይ ተነስቶ ጣናና ባህርዳርን ፤ጢስ ዓባይን አልፎ እስከ ወለጋ ደቡብ ሱዳንና ካርቱም አልሞርጋን፤እንዲሁም ናይልን እስከ ደቡባዊ ግብጽ ድረስ ያካለለ፤ ተከዜን ከላሊበላ ከፍተኛ ስፍራዎች አንስቶ እስከ ሱዳን አትባራ፤ባሮን ከምዕራብ ...

                                               

አገው ምድር

አገው ምድር በሀገሪቱ ስርዓት አዊ ብሄ/አሰ/ዞን እየተባለ የሚጠራው አካባቢ ሰው ያልነበረበት ፣ጥቅጥቅ ያለ ጫካ በዱር አራዊት የተሞላ ፣ ንፁህ የአየር ንብረት ለም አፈር ፣በቂ ውሃ ምቹ መልካአ ምድራዊ አቀማመጥ፣ የጫካ ማር ያለበት ጠፍ እንደነበረ አፋአዊ መረጃዎች ይጠቁማሉ ፡፡ ይሁን እንጂ የዚህ ቦታ ስያሜ የተሠጠው በአካባቢው በቀዳሚነት በሰፈሩት ሰባቱ አገው ወንድማማቾች መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ አገው ምድር እየተባለ የሚጠራው ቦታ በመጀመሪያዎቹ ነዋሪዎች ሲሰየም ክልሉ መኖራቸው ለብሄ/አስ/ዞን ወስንና ስፋት ዋነኛ እማኞች ለምሳሌ፡- ድኩል ካን ፣ዳድ ዩሃንስ ቢዝራ ካኒ ፃና የሚባሉት ተጠቃሽ ናቸው ሰባት ቤት አገው የተጠናከረና የተደራጀ መረጀ ባይኖርም በአፈ ታሪክ ደረጃ ከተለያዩ አባቶችና ታሪክ አዋቂዎች የተገኙ መረጃዎች እንደሚጠቁመን የእስራኤል ደም ወገን የሆነው ንጉስ ሰለሞን የልጅ ኩሳ ከቀዳማዊ ሚኒሊክ ጋር ታቦተ ፅዮንን ከእየሩሳሌም ይዘው ከመጡ በኋላ ንጉስ ኩሳ ሰቆጣ አካባቢ ትዳር መስርቶ በመኖር አዲልን ወለዱ ፣አዲ ...

                                               

አስናቀዉ ሲሳይ ተገኘ-Asnakew Sisay Tegegne

የማይዘነጉ ባለውለታ----- አስናቀዉ ሲሳይ ተገኘ-Asnakew Sisay Tegegne ‹‹የማይዘነጉ ባለውለታዎች›› ለወጣቱ ትውልድ አርአያ እና መንገድ አመላካች ናቸው የአፍሪካ መጽሀፍ ደራሲ የዚህ ታሪክ አሰባሳቢ፣ ተወዳጅ ሚድያና ኮሚኒኬሽን በስነ-ጽሁፍ፣ በስነ-ስእል፣ በፊልም ፣ በቴአትር፣ በሬድዮ ድራማ ፤ በማስታወቂያ ዘርፍ ፤ በሚድያ ዘርፍ ከ1970ዎቹ ጀምሮ አስተዋጽኦ ያበረከቱና አሁንም በስራ ላይ ያሉ ባለሙያዎችን ታሪክ በፌስ ቡክ ፤ በዊኪፒዲያ እንዲሁም በሌሎች የማህበራዊ ሚድያዎች እያስተዋወቀ እንዳለ ይታወቃል፡፡ ውድ ይህን ሀሳብ የምትደግፉ መስፈርቱን ያሟላሉ የምትሏቸው ሰዎች ጠቁሙን ፤ እርስዎም ታሪኬ መሰነድ አለበት ካሉ ይላኩልን፡፡ ከተቀመጠው መስፈርት አንጻር አይተን ታሪክዎን እናወጣለን፡፡ በ tewedajemedia gmail.com ግለ-ታሪክዎን ይላኩ፡፡ ጥቅምት 14 2014 የ1000 ሰዎች ታሪክ ሲሞላ ድንቅ ታሪካዊ ምረቃ ይኖራል፡፡ ይህ አጭር ግለ-ታሪክ ለወደፊቱም ምርምር ለሚያደርጉ እና ወይም የስራ ፕሮጀክቶቻቸውን ...

ሱዳን
                                     

ⓘ ሱዳን

ሱዳን በይፋ የሱዳን ሪፑብሊክ ከአፍሪካ በስፋት ሦስተኛ ስትሆን በአህጉሪቱ ሰሜናዊ ምስራቅ ክልል ትገኛለች። ዋና ከተማዋ ካርቱም ነው። ከግብፅ ፣ ከቀይ ባሕር ፣ ከኤርትራ ፣ ከኢትዮጵያ ፣ ከደቡብ ሱዳን፣ ከመካከለኛው የአፍሪካ ሪፑብሊክ ፣ ከቻድ ፣ እና ከሊቢያ ጋር ድንበር ትካለላለች። የአባይ ወንዝ ሀገሪቱዋን ወደ ምሥራቅና ምዕራብ ይከፍላል። የአረብ ባህል ደንበኛ ሲሆን አብዛኛው ሕብዝ የእስልምና ዕምነት ተከታይ ነው።

ሱዳን ከግብፅ የተጣመረ ረዥም ታሪክ አላት። የመጀመሪያው የሱዳን እርስ በርስ ጦርነት ከ1955 እስከ 1972 እ.ኤ.አ. ከዚያም ሁለተኛው የሱዳን እርስ በርስ ጦርነት ከ1983 እስከ 2005 እ.ኤ.አ. ተከስቷል። በ1989 እ.ኤ.አ. በሰላማዊ መፈንቅለ መንግሥት ኦማር ሀሳን አህመድ አል-በሽር ሥልጣን ላይ የወጡ ሲሆን እራሳቸውን የሱዳን ፕሬዝዳንት ብለው ሾመዋል። የእርስ በርስ ጦርነቱ በሰላም ውል የቆመ ሲሆን ይህ ውል ያኔ የሀገሪቱዋ ደቡባዊ ክፍል ለነበረው ቦታ ራስን የመምራት መብት ሰጥቷል። በጃኑዋሪ 2011 እ.ኤ.አ. በተካሄደው ውሳኔ ሕዝብ referendum መሠረት በሱዳን ፈቃድ ደቡብ ሱዳን ሐምሌ ፪ ቀን ፳፻፫ ዓ.ም. ሉዓላዊ ሀገር ሆነች።

ዋና ከተማዋ ካርቱም የሱዳን የፖለቲካ፣ ባህል እና ንግድ ማዕከል ናት። የሀገሪቱዋ መንግሥት በይፋ ፌዴራላዊ ፕሬዝዳንታዊ ሪፐብሊክ ቢሆንም ስልጣን ላይ ያለው ብሔራዊ ኮንግረስ ፓርቲ National Congress Party በሁሉም የመንግሥት አካላት ላይ ባለው ጥብቅ ቁጥጥር ምክንያት በብዙ የዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ ዘንድ መንግሥቱ አምባገነናዊ ተብሎ ይቆጠራል።

                                     
  • ደቡብ ሱዳን በ2003 ዓ.ም. ከሱዳን የተገነጠለ አዲስ ሀገር ነው ዋና ከተማው ጁባ ነው ከ፷ በላይ ኗሪ ቋንቋዎች እያሉ መደበኛው ቋንቋ ግን እንግሊዝኛ ነው አሁን ከሀገሩ 8 ሚሊዮን ኗሪዎች ምናልባት ስልሳ ከመቶ ክርስቲያኖች ናቸው
  • 1948 አመተ ምኅረት ታኅሣሥ 22 ቀን - ሱዳን ነጻነት ከእንግሊዝ አገኘ መጋቢት 11 ቀን - ቱኒዚያ ነጻነት ከፈረንሣይ አገኘ የካቲት 23 ቀን - ሞሮኮ ነጻነት ከፈረንሣይ አገኘ
  • ድርጅት በኢራን ኢራቅ ኩወይት ሳዑዲ አረቢያና ቬኔዝዌላ መካከል ተመሠረተ መስከረም 12 ቀን - ቀድሞ የፈረንሣይ ሱዳን የተባለው ቅኝ አገር የማሊ ሬፑብሊክ ተብሎ ነጻነቱን አዋጀ መስከረም 21 ቀን - ናይጄሪያ ነጻነቱን ከእንግሊዝ አገኘ
  • 1951 አመተ ምኅረት መስከረም 22 ቀን - ጊኔ ከፈረንሣይ ነጻ ወጣ ኅዳር 16 ቀን - ፈረንሳያዊ ሱዳን ዛሬ ማሊ በፈረንሳያዊ ማሕበረሠብ ውስጥ ራስ - ገዥ ሁኔታ አገኝታለች መጋቢት 26 ቀን - ማሊ ከሴኔጋል ጋር አንድላይ የማሊ
  • የጥቁር አባይ ወንዝ ደግሞ ግዮን ከእንግሊዝኛም ብሉ ናይል ከጣና ሐይቅ ይመነጫል ካርቱም ሱዳን ሲደርስ ከነጭ አባይ ጋር ተገናኝቶ ከዚያ አባይ ወንዝ ናይል በግብጽ በኩል ወደ ሜድትራኒያን ባሕር ይፈሳል ይህ አጭር መልክዐ ምድር
  • ሊቢያ በሰሜን አፍሪካ የምትገኝ ሀገር ስትሆን ከሜድትራኒያን ባሕር ግብፅ ሱዳን ቻድ ኒጄር አልጄሪያ እና ቱኒዚያ ጋር ድንበር አላት ሀገሪቱ ሕገ መንግስት የላትም የምተመራው በእስላም ሕጎች ነው ለ42 አመታት እስከ
  • ዩጋንዳ ሪፐብሊክ ወይም ዑጋንዳ በምስራቅ አፍሪካ የሚገኝ ሀገር ነው በኬንያ ደቡብ ሱዳን ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ ሩዋንዳ እና ታንዛኒያ ይዋሰናል የዩጋንዳ ሰም የመጣው ከቡጋንዳ መንግሥት ነው ከአረቦችና አውሮፓውያን በ1800ቹ
  • የኩሽ ስሜናዊ ጠረፍ ነበረ የአስዋን ግድብ ከዚህ በላይ በ1960ዎቹ ተሠርቶ የናሠር ሃይቅ ፈጠረ ሁለተኛው ሙላት በስሜን ሱዳን ነበር አሁንም ከናሠር ሃይቅ በታች ተሠመጠ ሦስተኛው እስከ ስድስተኛው ሙላቶች ደግሞ በስሜን ሱዳን ይገኛሉ
  • ፉንግ ወይንም ዳር ፉንግ በምስራቅ ሱዳን የሚገኝ ብሔረሰብ ነው የህብረተሰቡ አነሳስ ጠርቶ ባይታዎቅም ነገር ግን በ15ኛው ክፍለ ዘመን ማብቂያ ከደቡብ ሱዳን ወደ ኑቢያ ፈልሰው እንደመጡ ግንዛቤ አለ ከነሱ ወደ አካባቢው መምጣት በፊት