Back

ⓘ ደጋ እስጢፋኖስ በጣና ሃይቅ ውስጥ በሚገኘው ደጋ ደሴት ውስጥ የሚገኝ ቤክርስቲያን ሲሆን ወደ200 የሚጠጉ መነኮሳትን ያስተዳድራል። ቤክርስቲያኑ የተቆረቆረው በ13ኛው ክፍለ ዘመን፣ በአጼ ይኩኖ አምላክ የወንድም ልጅ በሂሩተ አምላክ ነበር። ሂሩተ አምላክ ..
                                     

ⓘ ደጋ እስጢፋኖስ

ደጋ እስጢፋኖስ በጣና ሃይቅ ውስጥ በሚገኘው ደጋ ደሴት ውስጥ የሚገኝ ቤ/ክርስቲያን ሲሆን ወደ200 የሚጠጉ መነኮሳትን ያስተዳድራል። ቤ/ክርስቲያኑ የተቆረቆረው በ13ኛው ክፍለ ዘመን፣ በአጼ ይኩኖ አምላክ የወንድም ልጅ በሂሩተ አምላክ ነበር። ሂሩተ አምላክ ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት ጋር በወሎ በሚገኘው ሃይቅ እስጢፋኖስ በአስተማሪያቸው እየሱስ ሞዓ የተማሩ የአንድ ክፍል ሰወች ናቸው።

ቀደምቱ ደጋ እስጢፋንኖስ በ19ኛው ክፍለ ዘመን በእሳት ሲቃጠል አሁን የቆመው ቤ/ክርስቲያን በምትኩ ተሰርቷል። በዚህ ምክንያት ከታሪክ አንጻር የቤ/ክርስቲያኑ ዋና መስዕብ ሆኖ የሚቀርበው ሳይቃጠል የተረፈው ቤተ-መዘክሩ ነው። በዚህ መዘክር የይኩኖ አምላክ፣ ቀዳማዊ ዳዊት፣ ዘርአ ያዕቆብ፣ ዘድንግል፣ ፋሲለደስና ባካፋ የደረቁ ቅሬቶች ይገኛሉ። አጼ ሃይለ ስላሴ በ1951 ደሴቲቱን ከጎበኙ በኋላ የነገስታቱ እሬሳ በመስታውት ሳጥን እንዲቀመጥ አደረጉ። የፋሲለደስ ቅሪት ከሌሎቹ ነገስታት በበለጠ መልኩ እስካሁን ብዙ ሳይበላሽ በመቆየቱ የፊቱን መልክ ከቅሪቱ መገንዘብ ይቻላል።

                                     
  • ደጋ ደሴት ጣና ሃይቅ ውስጥ ከደቅ ደሴት በስተ ደቡብ ምስራቅ ትገኛለች የደጋ እስጢፋኖስ ቤ ክርስቲያንም የሚገኘውም በዚህ ደሴት ሲሆን ይኩኖ አምላክ ቀዳማዊ ዳዊት ዘርአ ያዕቆብ ዘድንግል ፋሲለደስና ባካፋ የተሰኙት ነገሥታት ከእንጨት
  • ቤ ክርስቲያን ያሰሩ እኒሁ ንጉስ ናቸው ባረፉ ጊዜ የተቀበሩትም ደጋ ደሴት ተብላ በምትታወቀው የጣና ሃይቅ ደሴት ውስጥ የወንድማቸው ልጅ ሂሩተ አምላክ ባሰራው ደጋ እስጢፋኖስ ነው In the Ethiopian calendar, 10 Sené
  • መድሃኒአለም ማርያም ግምብ ጎርጎራ ግምብ ጎርጎራ ገሊላ ዘካሪያስ ናርጋ ስላሴ አርሲማ ሰማዕታት ደጋ እስጢፋኖስ ደቅ ደሴት ደጋ ደሴት መትራሃ ባርየ ግምብ ሚካኤል አብርሐ አጽብሐ ግምብ እንፍራዝ ቆጋ ልደታ ጋርኖ ወንዝ ድልድይ
  • እንደቀበሩት ያትትታል ከ10 አመት በኋላም ወደጁ የነበረው የአጎቱ ልጅ ሱሰንዮስ ሬሳው ተቆፍሮ ወጥቶ በደጋ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ደጋ ደሴት ጣና ሃይቅ ከሌሎች ቀደምት ነገሥታት ጎን እንዲያርፍ አድርጓል James Bruce, Travels
  • ኖሮት ሞትን የማያይ ማን ሰው አለ? አስከሬናቸውም የአገሪቱ መላ ህዝብ ባዘነበት ሁኔታ በቅዱስ እስጢፋኖስ ገዳም ጣና ሃይቅ ውስጥ ደጋ ደሴት ተብላ በምትታወቀው ደሴት የዘላለም እረፍት አገኘ መቃብራቸውም ውስጥ ያንድ ትንሽ ህፃን አስክሬን
  • ደሴ ወይም ላኮመልዛ በወሎ ክፍለ ሃገር የሚገኝ ከተማ ሲሆን በድሮ አጠራሩ ወይራ አምባ ይሰኝ ነበር የወይና ደጋ አየር ጸባይ ያለው ይህ ከተማ በከተማነት ታዋቂ እየሆነ የመጣው በዓፄ ዮሐንስ ፬ኛ ዘመን እንደሆነ ይጠቀሳል የአካባቢው መሬት