Back

ⓘ የኢትዮጵያ ሥነ-ጽሁፍ ..
                                               

ልብወለድ ታሪክ ጦቢያ

ጦቢያ ወይም ልብወለድ ታሪክ ጦቢያ በአፈወርቅ ገብረ እየሱስ በ፲፱፻ ዓ.ም. በሮማ የታተመ ሲሆን 90 ገጾች አሉት። በኢትዮጵያ የሥነ ፅሑፍ ታሪክ የመጀመሪያ ልብወለድ መፅሐፍ ለመሆኑ የሚነገርለት ይህ መጽሐፍ በወቅቱ ተነስቶ የነበረውን የአረማውያንንና የክርስቲያኖችን ጦርነት ይተርካል። ደራሲው በመፅሐፉ ውስጥ ስለተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ማለትም ስለደግነትና ክፋት፣ ስለሀይማኖትና ፍቅር በሰፊው ያትታሉ። መፅሐፉ በተለይ የፍቅርን ሀያልነት ለማሳየትና የሀይማኖት ልዩነት ስላልበገረው ታላቅ ፍቅር በሰፊው ይተርካል። በተጨማሪም ደራሲው በጽሑፉ ውስጥ ሊያስተላልፉ የሞከሩት መልዕክት የሰው ልጅ በባዕድ አምልኮ ተሸብቦ ከመኖር ይልቅ ፈተናና ችግር ቢገጥሙት እንኳን ለእነዚህ ሳይበገር በአንድ አምላክ አምኖ ከጸና ድል ሊያደርግ እንደሚችል ነው። ጦቢያን ወደ እንግሊዝኛ ለመተርጎም ጥረቱ ተጀምሯል። ከዚህ በፊት የመጀመሪያውን የትግርኛ ልብወለድ መጽሐፍ ወደ እንግሊዝኛ የተረጎመው ግርማይ ነጋሽ በሚቀጥሉት ጊዚያት ጦቢያን ለመተርጎም ወደደቡብ አፍሪካ እን ...

                                               

መንግሥትና የሕዝብ አስተዳደር

መንግሥትና የሕዝብ አስተዳደር በቢትወደድ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ ተጽፎ በ፲፱፻፲፮ ዓ.ም. የታተመ መጽሐፍ ነው። ይህ መጽሐፍ ከመስራት የተነሳ የሰው ልጅ እንዴት ከተፈጥሮ ጥገኝነት ተላቅቆ ከኋላ ቀር አኗኗር ወደ ተሻለ ሕይወት እንደሚለወጥ የሚያስረዳ ሲሆን የዓለም ሕዝቦች የዕውቀታቸውና የሀብታቸው ደረጃ ከፍና ዝቅ ያለ መሆኑ ምክንያቱ ከጦርነት የተነሳ ነው ይላል። ጦርነቱንም የሚነሱ ነገሥታትና አለቆቹ ሁሉ ልባቸው ሀብት እንደፈለጉ አይገልፅም። ነገር ግን ስም ለመፈለግና ለማግኘት ወይም ሀይማኖቱን ለማስፋፋት ወይም የተጠቃውን ለመርዳት አስመስለው ይነሳሉ። የጦርነት ሁሉ ፍፃሜ ምኞት ግን መዝረፍና ማስገበር ነው። ይህንንም ሲሉ ዕውቀታቸው የሰፋ ነገሥታትም ቢሆኑ መዝረፍን አይተዉም። አዘራረፋቸው ግን የዕውቀት አዘራረፍ ነው እያለ በሰፊው ያወሳል። በአክሱም ዘመነ መንግሥት የእስራኤልና የአህዛብ ወገን ተብሎ የሁለት ዓመት ጦርነት በመፍጀቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከፍ ወዳለው ደረጃ እንዳይደርስ ዋና መሰናክል ሆኗል። ዋጋ ማለት የስራ መለኪያ ነው። ...

                                               

ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት

ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ታኅሣሥ ፳፫ ቀን ፲፱፻፲፯ ዓ/ም በአንዲት" ብርሃንና ሰላም” በተሰኘች አነስተኛ ጋዜጣ ሕትመት ሥራውን ጀመረ። በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው መጻሕፍት ፣ ጋዜጦች ፣ መጽሔቶችና የምስጢራዊ ሕትመት ሥራዎች በተለያዩ ቋንቋዎች እያተመ ይገኛል። ማተሚያ ቤቱ በርካታ የመንግሥት እና የግል ጋዜጦችን የሚያትም ሲሆን ፥ በተጨማሪም በየዓመቱ በርካታ የፈተና ሥራዎችን በማተም ይታወቃል።

                                               

አዲስ ዘመን (ጋዜጣ)

አዲስ ዘመን ጋዜጣ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ሥር የምተዳደር ነዉ ፣ በየዕለቱ የሚታተም ብሔራዊ ጋዜጣ ነው። አዲስ ዘመን በአሁኑ ጊዜ ከ ፵ በላይ ጋዜጠኞች ያሉት ሲሆን የጋዜጣው መጠን ‘መካከለኛ’ /በርሊነር) ሆኖ የፊትና ጀርባ ገፆችን በሙሉ ቀለም ያቀርባል። ይህ ጋዜጣ የአገሪቱ ብቸኛው ዕለታዊ ጋዜጣ ሲሆን የመንግሥትን አቋም የሚያንፀባርቅ እና በየዕለቱ የተለያዩ ልማታዊ ዜናዎችን ይዞ ይወጣል።

                                               

እንደወጣች ቀረች

"እንደወጣች ቀረች" 189 ገጾች ያሉትና በ፲፱፻፵፮ ዓ.ም. የተፃፈ ሲሆን በውስጡም ከ፲፱፻፳፰ እስከ ፲፱፻፴፫ ዓ.ም. በኢትዮጵያ ላይ የተፈፀመው የኢጣልያ ወረራና በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ያመጣው አያሌ ቀውሶች በሰፊው ያትታል። በተለይም በህዝቡ መንፈስ ላይ፣ በአገሪቱ ልማድና የኑሮ ባህል ላይ በአጠቃላይ በማህበራዊ ህይወቱ ላይ ታላቅ ቀውስን ያስከተለ መሆኑንም ያብራራል። የነበረውን የጦርነት አስከፊነት መጽሐፉ ሲያትት ኢጣሊያኖች እጅግ ጨካኞች ነበሩ። በተለይም ከሀገሬው ተወላጆች በልዮ ልዩ ምክንያት በዘመኑ በእስር ላይ የነበሩትን በመፍታት ለራሳቸው ባንዳ አድርገው ከመለመሏቸው በኋላ ከአርበኞች ጋር ያዋጓቸው ነበር። ሀገሬውን እርስ በርሱ በማዋጋት ህዝቡን ጨርሶ ሀገሪቷን ለመውረስ ከፍተኛ እቅድ ነበራቸው። አርበኞች ግን የምግብ ችግር፣ የክረምቱ መጫንና የበረሀው ኑሮ ሳያግዳቸው ቤት ሀገር ነው ሀገር ከሌለ ቤት የለም በማለት ለባዕድ መገዛት አሻፈረኝ ብለው ለነፃነታቸው በየዱሩ እንደተዋጉም ያወሳል። ፀሀፊው በመጽሐፉ በሰፊው ሊያሳይ የሞከረ ...

                                               

የኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር

የኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር ፋሺስት ኢጣሊያ በ፲፱፻፳፱ ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ያደረገውን ጭፍጨፋ ፳፫ኛው ዓመት በሚታሰብበት የካቲት ፲፪ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ.ም.፤ የሀገር ፍቅር ቴአትር አዳራሽ በነበረው ኪነ-ጥበባዊ መሰናዶ ተመሠረተ።

                                               

የዓመፅ ኑዛዜ

የዓመፅ ኑዛዜ በደራሲ አቤ ጉበኛ በ፲፱፻፶፭ ዓ.ም. የተፃፈ ሲሆን 85 ገጾች አሉት። በመፅሐፉም የተገለፀው ታሪክ ሰፊ ሆኖ ደራሲው ባጭሩ ለመግለፅ ቀላልና አጭር በሆነ ዘዴ የፃፈው ነው። ታሪኩም አንድ ራሱን ወዳድ ሰው ታሪክ በኑዛዜ መልክ የሚገለፅበት ሲሆን፣ በአንድ የገጠር መንደር ውስጥ ጥሩ ኑሮ አላቸው ከሚባሉ ቤተሰቦች ውስጥ የወጣው ባለታሪክ ቤተሰቦቹን በድንገተኛ ህመምወያጣል። በድንገትም ያልተጠበቀ የቤተሰብ መበታተን ይደርሳል። በአጎቱ ሚስት ይፈፀምበት በነበረው ድርጊት ተማሮ ወደ ከተማ የኮበለለው ወጣት ባገኘው የትምሀርት ዕድል ተጠቅሞ አገሩንና ወገኖቹን መርዳትና መንከባከብ ሲገባው በተለያዩ ክፉ ነገሮች ተጠምዶ ይልቁንም በአልጠግብ ባይነት ከሚገባው በላይ ሃብት በማግበስበስና የወገኖቹንም ድርሻ ጭምር በመስበሰብ ለአገሩም ሆነ ለወገኖቹ የተጣለበትን ተስፋ ሳይፈፅም በሞት አፋፍ ላይ ሳለ የሚሰማውን ፀፀትና እሱን አይተው ሌሎች እንደ እርሱ ከመሆን እንዲቆጠቡ የሚናገርበት ሲሆን በተጨማሪም የርሱ ህይወት ትምህርት እንዲሆናቸው በመጨ ...

                                               

ዴርቶጋዳ

ዴርቶጋዳ በ ፪፼፩ዓ.ም.በደራሲ ይስማዕከ ወርቁ የቀረበ ልብ-ወለድ ሲሆን ሳይንሳዊ ዘዉግ ያለዉ የኢትዮጵያን አንድነት የሚስብክ መጽሀፍ ነዉ።መጽሀፉ ለዶ/ር ኢ/ር ቅጣዉ እጅጉ ማስታወሻነት ተበርክቷል።ከብዙ በጥቂቱ ገፀ-ባህሪያቱ ሻጊዝ እጅጉ፣ሚራዥ፣ሲፓራ፣ሜሮዳ፣ዣንጊዳ፣ጌራ፣አባ ፊንህሰ፣አባ ዠንበሩ.። ዴርቶጋዳን የኢትዮጵያን ስነ-ጽሁፍ አንድ እርምጃ ወደፊት ያራመደ ብለዉ ብዙ የኢትዮጵያ ሙህራን ጽፈዋል.ይስማዕከ የዴርቶጋዳን ቀጣይ ክፍል ዴርቶጋዳ ፪ለህትመት ዴርቶጋዳን በጻፈ በአመቱ ፪፼፪ አብቅቷል። ይህ ያለዉን ችሎታ ያሳየናል።አንዳንድ ጥራዝ ንጠቅ ሀያሲያን ይስማዕከን ሲተቹ ይስማዕከ የሰጠዉ መልስ "ትችቶች ምንም መጥፎ ቢሆኑ ይበልጥ እንድሰራ ያደርጉኛል"።ቢሆንም ቅሉ ይስማዕከ በስራዎቹ በኢትዮጵያዊያን ልብ ዉስጥ ለዘላለም ይኖራል።ይስማዕከ በመጽሀፉ ብዙ ነገሮችን ለመጥቀስ ሞክሯል ስለ መልካም አስተዳደር እጦት በኢትዮጵያ፣ስለ ጥንት ኢትዮጵያዊያን ጀግንነትና ተጋድሎ፣ስለ ፍቅር፤ስለ ኢትዮጵያዊያን ሙህሮች. በአሁኑ ሰዓት ይስማዕከ ዴርቶጋዳ ...

                                               

አልወለድም

"አልወለድም" በደራሲ አቤ ጉበኛ ብዕር ተከሽኖ የቀረበና በ፲፱፻፶፭ ዓ.ም. ለሕትመት የበቃ ልብ ወለድ መጽሐፍ ነው። በ ፲፱፻፷፮ ዓ/ም ዳግም ለኅትመት የበቃው እና አብዮቱ በሀገሪቱ ሲቀጣጠል በኅብረተሰቡ ዘንድ በከፍተኛ ሁኔታ የተነበበው ‘አልወለድም’ ማንንም ሰው ከእናቱ ማሕጸን ጀምሮ ምኞትና ጥንቃቄ ሊለየው እንደማይገባ የሚያትት ሲሆን በመታየት ላይ ያለው እውነታ ግን አዳጋች የሆነና የሰው ዘር በድህነት ተወልዶ፣ አድጎ እና ኑሮው በድህነት እንደሚያልፍ ያሳያል። እንዲህ ያለው ሁኔታ አግባብ አለመሆኑንም ይቃወማል። መጽሐፉ የሰው ልጅ የሚደርስበትን መከራ በመቃወም ይሞግታል። የሰው ልጅ መብት በአግባቡ መጠበቅ እንዳለበት ያስረዳል።

                                               

አርሙኝ

"አርሙኝ" በቢትወደድ መኮንን እንዳልካቸው ተጽፎ በ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. ለህትመት የበቃ መጽሐፍ ነው። የፀሐፊውን የሕይወት ታሪክ ባጭሩ እንዲሁም በተለያየ ጊዜ ፀሐፊው የሠሩዋቸውን ልብ ወለድ ስብስቦችን፣ ስለ ማይጨው ጦርነት እና የዓለም ፖለቲካን በማካተት የጻፉትን ጠቅልሎ የያዘ ነው።

                                               

አዲስ አድማስ

አዲስ አድማስ በኢትዮጵያ የሚታተም ሳምንታዊ ጋዜጣ ነው። ጋዜጣው የሚታተው በአድማስ አድቨርታይዚንግ ኃ.የተ.የግ.ማ. ሲሆን የተመሰረተው በታኅሣሥ ፳፱ ቀን ፲፱፻፺፪ ዓ.ም. ነው። በአሁኑ ጊዜ የጋዜጣው ሥራ አስኪያጅ ገነት ጎሳዬ ስትሆን ዋና አዘጋጅ ደግሞ ነቢይ መኮንን ነው።

                                               

ከልደት እስከ ሞት

ከልደት እስከ ሞት ከደጃዝማች ኪዳኔ ወልደመድኅን የተደረሰ መንፈሳዊና ፍልስፍና መጽሐፍ ሲሆን፤ ግንቦት 17 ቀን 1964 ዓመት ምህረት በትንሳኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት ታተመ።

                                               

ወዳጄ ልቤ

ወዳጄ ልቤ በብላታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ ተጽፎ በ፲፱፻፲፭ ዓ.ም. የታተመ መጽሐፍ ነው። ይህ መጽሐፍ ዓለማዊ ሃይማኖትን ማስተማሪያ ሲሆን፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ ምሣሌዎችን በመጥቀስ ክፋት የሰው ልጆች አጥፊና መጨረሻው የማያምር መሆኑን ያስረዳል። ከቀድሞው የሃይማኖት ትምህርት ለየት ባለ ልብ ወለድ መልክ የቀረበ በመሆኑ ብዙ አንባቢዎችን እንደ አረካና ጥሩ የጊዜ ማሳለፊያ እንደነበር ይታወቃል።

ወዳጄ ልቤና ሌሎች
                                               

ወዳጄ ልቤና ሌሎች

ወዳጄ ልቤና ሌሎች በብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ የተደረሱ 5 መጻህፍትን አንድ ላይ የያዘ መጽሐፍ ነው። እኒህ ድርሰቶች እንዲህ ይዘረዘራሉ፦ የልብ አሳብ፣ የብርሃኔና የጽዮን ሞገሳ ጋብቻ -- 1923 ታተመ ስሓርና ወተት፣ የልጆች ማሳደጊያ -- 1922 ታተመ ወዳጄ ልቤ፣ የሰውን ጠባይና ኑሮ በምሳሌ የሚገልጽ -- 1915 ታተመ ለልጅ ምክር፣ ለአባት መታሰቢያ-- ለመጀመሪያ ጊዜ 1910ዓ.ም. የታተመ አዲስ አለም፣ የቅኖችና የደግ አድራጊዎች መኖሪያ -- 1925 ታተመ

                                               

የልም እዣት

የልም እዣት በ 1980 በደራሲ ሀዲስ አለማየሁ ስለ ማህበራዊ ጉዳዮችና ስለ ጣሊያን ውርስ የሚዳስሰ ለንባብ የበቃ ልብ ወለድ ነው።መፀሐፉምፈ እጅግ ብዙ ማህበራዊ ህይቶችን ይዳስሳል የልጅ አስተዳደግ፡ እናትነት፡ ፍቅር፡ ጀግንነት. አስወርዱን

                                               

የሾህ አክሊል

"የሾህ አክሊል" በዕውቁ ባለቅኔና ደራሲ ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድኅን በ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. የተደረሰ ተውኔት ሲሆን በመኳንንት ቤት ያደገ አንድ ወጣት የመኳንንት ሴት ልጅ ለትዳር መፈለጉንና እሱ ግን አቻ ቤተሰብ ባለመሆኑ ለጋብቻው ብቁ ሳይሆን እንደቀረ ያሳያል። ይኸውም አንድ ሰው ማንነቱ የሚረጋገጠው በእሱ በራሱ ሳይሆን በቤተሰቡና በወገኑ እንደነበር የሚያመለክት ነው።