Back

ⓘ ዶሮ ወጥ. አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች 1 ዶሮ 1 መካከለኛ ጭልፋ የተገረደፈ ባሮ ሽንኩርት 2 መካከለኛ ጭልፋ የተገረደፈ ካሮት 2 መካከለኛ ጭልፋ የተገረደፈ ቀይ ሽንኩርት 6 የሾርባ ማንኪያ ዘይት 1 የሻይ ማንኪያ ጨው 1 ዝንጣፊ ሮዝሜሪ የጥብስ ቅጠል 1 የሻ ..
ዶሮ ወጥ
                                     

ⓘ ዶሮ ወጥ

አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች 1 ዶሮ 1 መካከለኛ ጭልፋ የተገረደፈ ባሮ ሽንኩርት 2 መካከለኛ ጭልፋ የተገረደፈ ካሮት 2 መካከለኛ ጭልፋ የተገረደፈ ቀይ ሽንኩርት 6 የሾርባ ማንኪያ ዘይት 1 የሻይ ማንኪያ ጨው

1 ዝንጣፊ ሮዝሜሪ የጥብስ ቅጠል

1 የሻይ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ

1 ሊትር ቺክን ስቶክ ከዶሮ የተሠራ መረቅ

                                     

1. አዘገጃጀት ቁጥር 1

1. ዶሮውን መበለትና ማጽዳት 2. ቀይ ሽንኩርቱን በዘይት ማቁላላትና ካሮቱን እና ባሮውን ጨምሮ ማቁላላት 3. ቺክን ስቶኩን ጨምሮ ማንተክተክ፣ ከዚያም ሮዝሜሪውን መጨመር 4. የዶሮውን ሥጋ መጥበሻ ላይ በነጩ ጠብሶ በድስቱ ውስጥ ጨምሮ ማብሰል፣ 5. ጨውና ቁንዶ በርበሬ ጨምሮ ማውጣት 6. ለገበታ ሲፈለግ መረቅ በሥጋው ላይ እያፈሰሱ ማቅረብ

                                     

2. አዘገጃጀት ቁጥር 2

መጀምሪያ ስንኩርት ደቆ ይከተፋል ዶሮ ብልት ከወጣለት በሕዋላ በደንብ ይታጠባል ዘይት ቂበ በርበሬ መከለሳ ቅመም ያስፈልጋል

ሽንኩርቱ ዘይት ሳይገባበት በደንብ ይቁላል፤ ከዛ በርበሬ አብሮ ከሽንኩርቱ ጋር እንደገና በደንብ ይታስል፤ ከዛ ዘይት ይገባና ትንሽ ከሽንኩርቱና ከበርበሬው ጋር ከተቁላላ በሕዋላ ዶሮው ይገባል በመቀጠል መከለሳ ቅመሙና በመጠኑ ውሃ ጨምሮ የዶሮው ስጋ ሲበስል ከሳት ላይ ማውጣት