Back

ⓘ ታሪክ ነክ መዋቅሮች ..
                                               

20ኛው ምዕተ ዓመት

ኅዳር 19 ቀን፦ አልባኒያ ነጻነቱን ከኦቶማን መንግሥት አወጀ። ኅዳር 18 ቀን፦ ፈረንሳይ የሞሮኮ ስሜናዊና ደቡባዊ ክልሎች ለእስፓንያ ጥብቅ ግዛት እንዲሆኑ መስጠቷን ተዋወለች። የካቲት 6 ቀን፦ ቲበት ነጻነቱን ከቻይና አወጀ። ጳጉሜ 1 ቀን - ታንክ የሚባል የጦርነት መሳርያ ለመጀመርያ ጊዜ በእንግሊዞች ተፈተነ። 1907 - የደቡብ አፍሪካ ጭፍሮች ጀርመን ደቡብ-ምዕራባዊ አፍሪካ ናሚቢያ ወረሩ። 1906 - 1ኛ አለማዊ ጦርነት በአውሮፓ ጀመረ።

                                               

ሊሙ (የአሦር ማዕረግ)

ሊሙ በአሦር መንግሥት የተሾመ የአመት በዓል ሹም ነበር። የሹሙም ስም በአሦራዊ መቆጣጠር የዓመቱ ስም ሆነ። እስከ 1123 ዓክልበ. ድረስ ፣ አሦራዊው የዓመት መቆጣጠሪያ ጨረቃዊ ዓመት ስለ ነበር፣ ዓመቱ 365 ቀኖች ሳይሆን 354 ቀኖች ብቻ ነበሩበት። ከ1187 ዓክልበ. ጀምሮ ደግሞ ሊሙዎቹ በየፀሐያዊ ዓመት ይመረጡ ነበር። ከ1187 አስቀድሞ ሊሙዎቹ የተመረጡት በየጨረቃዊ ዓመቱ በመሆን፣ ከየፀሐያዊው ዓመት ፲፩ ቀኖች ይጠፋሉ። ስለዚህ ከዚያው ዓመት በፊት፣ ለየ፴፪ ዓመታት፣ ፴፫ የሊሙ ስሞች አሉ። ለየመቶውም አመታት ሦስት ተጨማሪ የሊሙ ስሞች አሉ ማለት ነው። ከሥነ ቅርስ የተነሣ፣ የሊሙ ስሞች ዝርዝር በሙሉ ከ918 ዓክልበ. እስከ አሦር ውድቀት እስከ 617 ዓክልበ. ድረስ ታውቋል። እንዲሁም ከ13ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ.አካባቢ፣ አብዛኖቹ የሊሙ ስሞች ሊታወቁ ታቻለ። የማሪ ዜና መዋዕል የሊሙ ስሞችና የዓመቱን ድርጊቶች ከ1781 እስከ 1691 ዓክልበ. ግ. ድረስ ይሰጣል። በቅርብም ጊዜ ውስጥ ተጨማሪ ዝርዝሮች በካነሽ ተገኝተው፣ ከ18 ...

                                               

ልብነ ድንግል

"ዓፄ ልብነ ድንግል" ወዲህ ይመራል። ለቤተ ክርስቲያኑ፣ አጼ ልብነ ድንግል ይዩ። ዓፄ ልብነ ድንግል የዙፋን ስም "አንበሳ ሰገድ" ወይም ዳግማዊ ዳዊት ከነሐሴ ፲ ቀን ፲፬፻፺፱ እስከ ነሐሴ ፴ ቀን ፲፭፻፴፪ ዓ.ም. የነገሱ ሲሆን የተወለዱትም በ1501 እ.ኤ.አ. ነበር። የኢትዮጵያና አዳል ጦርነትም የተጀመረው በኒህ ንጉስ ዘመን በ1528 እ.ኤ.አ. ነበር። ሚስታቸውም ሰብለ ወንጌል ትባል ነበር። ዓፄ ልብነ ድንግል የዓፄ ናዖድ ልጅ የዓፄ በአደ ማርያም የልጅ ልጅ ናቸው። ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብም ቅድመ አያታቸው ናቸው። ዓፄ ናዖድ ፲፫ ዓመት ገዝተው ሲሞቱ በ፲፭፻ ዓ.ም. ዓፄ ልብነ ድንግል ገና የ፲፪ ዓመት ወጣት እያሉ ነገሡ። ስመ መንግሥታቸውም ወናግ ሰገድ ተባለ። ወናግ ማለት በኦጋዴን ሱማሌ ቋንቋ አንበሳ ማለት ነው። የግዕዙን ወይም የአማርኛውን ቋንቋ "አንበሳ ሰገድ" ን ትተው በኦጋዴን ቋንቋ ወናግ ሰገድ የተባሉበት ምክንያት ምናልባት ያን ጊዜ በይፋትና በፈጠጋር ያለውን ግዛት የሚያውኩ ያዳልና የሱማሌ ተወላጆች ስለሆኑ እነሱ በሚያውቁት ...

                                               

ሚሌሲያን

ሚሌሲያን በአይርላንድ አፈ ታሪክ ዘንድ፣ አይርላንድን በጥንት ከወረሩት ነገዶች መጨረሻዎች ነበሩ። ከሚሌሲያን አስቀድሞ አይርላንድን የሠፈሩት ፬ ሕዝቦች - የፓርጦሎን ሕዝብ፣ የነመድ ሕዝብ፣ ፊር ቦልግ፣ እና ቱአጣ ዴ ዳናን - ሁላቸው የማጎግ ዘር ይባላሉ። በተቀራኒ የኚህ ሚሌሲያን ሃረገ ትውልድ ግን ከማጎግ ሳይሆን ከጋሜርና ከፌኒየስ ፋርሳ እንደ ደረሰ ይጻፋል።

                                               

ሚታኒ

ሚታኒ ከ1507 እስከ 1288 ዓክልበ. ግድም በስሜን ሶርያ፣ ስሜን ሜስጶጦምያና ደቡብ አናቶሊያ የቆየ ጥንታዊ መንግሥት ነበረ። ሚታኒ ደግሞ በኬጥኛ ሑሪ ፣ በግብጽኛ መተኒ ወይም ናሐሪን ፣ በአካድኛ ሐኒጋልባት ይባል ነበር። ከጎረቤቶቻቸው ከኬጥያውያን፣ ጥንታዊ ግብጽና አሦር ጋራ ይታገሉ ነበር፤ በመጨረሻ በ1307 ዓክልበ. ግድም ለአሦር መንግሥት ወደቆ ተገዥ ሆነ። የያምኻድና የባቢሎን መንግሥታት በ1508-7 ዓክልበ. ለኬጥያውያን መንግሥት ንጉሥ 1 ሙርሲሊ በወደቁበት ጊዜ ያህል በሑራውያን ብሔሮች መካከል የሚታኒ መንግሥት በኪርታ እንደ ተመሠረተ ይታመናል። ሆኖም የግብጽ ፈርዖን 1 ቱትሞስ ከዚያ ትንሽ በፊት 1512 ዓክልበ. ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ በ "ናሓሪን" ላይ ዘምቶ ነበርና በአንዱ ጽሑፍ "መታኒ" ሲል ከዚህ ዘመቻ እንደ ሆነ ይታመናል፤ ቀደም-ተከትሉ እንዲህ ከሆነ ምናልባት ኪርታና የሚታኒ ባለሥልጣናት ከሙርሲሊ ዘመቻ በፊት በሑራውያን አገር ወይም ሐኒጋልባት ተመሠረቱ። "ናሓሪን" የሚለው ግብጽኛ ስያሜ ደግሞ በእብራይስጥ መጽሐፍ ...

                                               

ማሪ

ከማሪ ጽላቶች እንዲሁም ከኤብላ ጽላቶች ከተገኘው በርካታ መረጃ የማሪ ነገሥታት ዘመኖች ሊታወቅ ይቻላል። መጀመርያ የሚታወቀው የማሪ ንጉሥ በኡር ንጉሥ መስ-አኔ-ፓዳ ዘመን 2345-2314 ዓክልበ. ግ. የነገሠው ጋንሱድ ይመስላል። ጋንሱድ ከመስ-አኔ-ፓዳ ጋር በዚህ ዘመን ንግድ እንዳካሄደው ይታወቃል። ከዚያ በኋላ የላጋሽ ንጉሥ ኤአናቱም ግዛቱን እስከ ማሪ ድረስ አስፋፋ። በኤአናቱም መሞት 2195 ዓክልበ. ግ. ማሪ እንደገና ነጻ መንግሥት ሆነ። ኢቱፕ-ኢሻር ኢኩን-ሳማጋን ኢኩን-ሳማሽ 2195 ዓክልበ. ግ. ኢሽቂ-ማሪ 2077-2068 ዓክልበ. ግድም ሒዳዓር 2112-2077 ዓክልበ. ግድም - ከ2107-2100 ዓክልበ. ግ. ደግሞ የሱመር ኒፑር ንጉሥ እንደ ሆነ ይመስላል። ኢብሉል-ኢል 2127?-2115 ዓክልበ. ግድም - "የማሪና የአሹር ንጉሥ" ተባለ፤ ከርሱ በኋላ ግን አሦር ነጻ ሆነ። ኒዚ 2115-2114 ዓክልበ. ግድም አኑቡ ኤና-ዳጋን 2114-2112 ዓክልበ. ግድም - የኤብላ ንጉሥ ኢሻር-ዳሙ የሾመ አለቃ ነበረ። ኢኩን-ኢሻር 211 ...

                                               

ማካ ሞንግ ሩዋድ

ማካ ሞንግ ሩዋድ በአየርላንድ አፈ ታሪክ ከ440 እስከ 426 ዓክልበ. ድረስ የአይርላንድ ብቸኛ ከፍተኛ ንግሥት ነበረች። የአይርላንድ ታሪኮች እንዳሉት፣ ከ503 ዓክልበ. ጀምሮ ድሮ አቆጣጠር የማካ አባት አይድ ሩዋድ፣ ዲጦርባ እና ኪምባይጥ በስምምነት እያንዳንዱ ዙፋኑን በየ፯ቱ ዓመታት እንዲፈራርቁ ወሰኑ። እንዲሁም ሦስቱ ነገሥታት እያንዳንዱ ለ፫ ጊዜ የ፯ ዓመታት ዘመኖች ነበሩዋቸው፤ ይህም 63 ዓመታት ፈጀ። በ ሌቦር ጋባላ ኤረን በአንዱ የድሮ ግጥም ያ ከክርስቶስ ልደት 450 ዓመታት በፊተ እ.ኤ.አ. ወይም 458 ዓክልበ. አካባቢ እንደ ነበር ያረጋግጣል። አይድ ሩዋድ ግን ዓርፎ እንደገና ፈንታው በደረሰበት ወቅት በ440 ዓክልበ. ሴት ልጁ ማካ ሞንግ ሩዋድ ስለ ዙፋኑ ይግባኝ አለች። ይች ማካ ዲጦርባን በውግያ ገደለች፣ የተረፈውንም ንጉሥ ኪምባይጥን አገባችው። ከዚያ ኪምባይጥና ማካ አብረው ለ፯ ዓመታት ነገሡ፤ ኪምባይጥም በ433 ዓክልበ. አርፎ ከፍተኛ ንግሥት ማካ ለብቻዋ ሌላ ፯ አመታት ነገሠች። በ426 ዓክልበ. ሬክታይድ ሪግዴርግ ...

                                               

ቀዳማዊ ምኒልክ

የኢትዮጵያ ነገሥታት ቤተ እስራኤላውያን እነማን ናቸው? ታሪኩን ለመረዳት ከጌታችን ልደት በፊት በእስራኤል ላይ ነግሦ የነበረውን የንጉሥ ዳዊት ልጅ የሆነውን የጠቢቡ ሰሎሞንን ታሪክ እና በኢትዮጵያ/በአቢሲኒያ የነገሠችውን የንግሥተ ሳባን ታሪክ ማየት ግድ ይለናል። እንድሁም ታራኩ ከታቦተ ፅዮን አመጣጥ ጋር ቀጥተኛ የሆነ ግንኙነት ያለው ሲሆን በመጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ ምዕራፍ 10 ላይ እና በሌሎች አዋልድ መጻሕፍት ላይ ተፅፎ እናገኜዋለን። ጌታችን በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 12:42 ላይ "ንግሥተ ዓዜብ በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥታ ትፈርድበታለች፤ የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳር መጥታለችና" በማለት የጠቀሳት ንግሥተ ማክዳ ወይም ንግስተ ሳባ በወቅቱ የኢትዮጵያን/የአቢሲኒያን ሕዝብ የምታስተዳድር ንግሥት ነበረች፡፡ እንድሁም በጊዜው በእስራኤል ላይ ነግሦ የነበረውን የሰሎሞንን መንፈሳዊ ጥበብ በነጋደዎች በኩል ትሰማ ነበር። ዕለት ዕለትም የሰማችውን የሰሎሞንን ጥበብ እና ዝና ለማየት ትጓጓ ነበር፡፡ በዚህም የተነሣ የሰሎሞን ...

                                               

ቢዛንታይን መንግሥት

የቢዛንታይን መንግሥት ወይም የሚሥራቃዊ ሮሜ መንግሥት ከ387 እስከ 1445 ዓ.ም. ድረስ የቆየ መንግሥት ነበር። በ387 ዓ.ም. የሮሜ መንግሥት ለመጨረሻው ጊዜ ተለይቶ ምሥራቁ ግማሽ ልዩ መንግሥት ሆነ፤ ዋና ከተማው ቁስጥንጥንያ ነበር። ከዚሁ ትንሽ በፊት ክርስትና በሮሜ መንግሥት ውስጥ የመንግሥት ሃይማኖት ሆነ። በ468 ዓ.ም. ሮሜ እራሱና የምዕራባዊ ሮሜ መንግሥት ለኦዶዋከር ወገን ወደቁ። በቁስጥንጥንያ ግን የሮሜ መንግሥት በረታ። እስከ 612 ዓ.ም. ድረስ ይፋዊ ቋንቋ ሮማይስጥ ሆኖ ቀረ፤ በዚያ አመት ግን የሕዝቡ መነጋገሪያ ግሪክኛ ይፋዊ ሆነ። ከ1196 እስከ 1252 ድረስ በመስቀል ጦርነት ምክንያት የቁስጥንጥንያ መንግሥት ለጊዜው ጠፋ። ከዚያ በኋላ ግዛቱ እየደከመ እስከ 1445 ዓ.ም. ድረስ ቀረ። በዚያው አመት የቱርክ ሰዎች ቁስጥንጥንያን ያዙ። ቢዛንታይን የሚለው ስም ከቁስጥንጥንያ ጥንታዊ ስም "ቢዛንቲዮን" መጣ። ሆኖም ይህ ስም በታሪክ መጻሕፍት መጀመርያ በ1549 ታየ። በጊዜው የነበሩት ዜጋዎች ግን ራሳቸውን "ሮማዮይ" አ ...

                                               

ተክለ ሐዋርያት ተክለ ማርያም (ፊታውራሪ)

ፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያት ተክለ ማርያም የኢትዮጵያ የሥነ ጽሑፍና የመንግሥት ሰው ነበሩ። ለጊዜ የጅጅጋ እና የጨርጨር በአገረ ገዥነት ካገለገሉ በኋላ፣ በጅሮንድ በኋላ ፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያት በ1923 ዓም ከኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ደራሲዎች ዋናው ሆኑ። አጼ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በጻፉት ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ ውስጥ አንድ ወሳኝ ምዕራፍ ፴ "የሕገ መንግሥትን ትርጓሜ ስለ ማስረዳት።" በሙሉ ከበጅሮንድ ተክለ ሐዋርያት ቃላት ጠቀሱዋቸው። በዚህም ሰዓት ለጥቂት ወሮች በጅሮንድ ተክለ ሐዋርያት የገንዘብ ሚኒስትር ሆነው አገለገሉ። ለጊዜም የኢትዮጵያ መላክተኛ በብሪታኒያ ሆነዋል። ከ ሕይወቴና ምዕራፍ ፴ ጠቃሚ የሆነ አጭር ጥቅስ ይከተላል፦ "ሰው እንዲጠቀምበት የሚፈቀድለት ነገር ሁሉ የጥቅም መብት ተብሏል። ይኸውም የጥቅም መብት በሁለት ዋና ክፍል ይለያያል። ፩ኛ ፡ የግል ጥቅም ለያንዳንዱ ሰው በነፍስ ወከፍነት ለየራሱ የሚሆን ነው። ፪ኛ ፡ የመተባበር ጥቅም ለሕዝቡ ሁሉ በሙሉ ለኢትዮጵያም ለአንድነትዋ የሚሆን ነው። የግልም የመተባበርም አ ...

                                               

ቴምፕላርስ

ቴምፕላር ወይም በሙሉ ስማቸው የክርሰቶስ እና የሰለሞን መቅደስ ምስኪን ወታደሮች የሚባሉት በጣም ታላቅ እና ሃይለኛ ከነበሩት ክርስቲያናዊ ወታደራዊ ስርአቶች ውስጥ ዋነኞቹ ናቸው። ይህ ስርዓት በ1088 ዓ.ም. ከተካሄደው አንደኛው የመስቀል ጦርነት በኋላ ማለትም በ1110 ዓ.ም. አዲስ የተቋቋመውን የእየሩሳሌም መንግስት ከእስላሞች ለመከላከልና ወደ ከአውሮፓ ወደ እየሩሳሌም የሚጎርፉትን ተሳላሚዎች ደህንነት ለመጠበቅ የተመሰረተ ነው።

                                               

ቶማስ ጄፈርሰን

ቶማስ ጄፈርሰን ከየካቲት 26 ቀን 1793 እስከ የካቲት 25 ቀን 1801 ዓ.ም. ድረስ የአሜሪካ 3ኛ ፕሬዝዳንት ነበሩ። ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ቨርጂኚያን ያቋቋሙት ጄፈርሰንም ነበሩ። ቶማስ ጄፈርሰን ከአባቱ ከፒተር ጄፈርስን እና ከእናቱ ጄን ራንዶልፍ ተወለዱ። ቶማስ በአሜሪካ አብዮት ጊዜ በ1768 ዓ.ም. ከእንግሊዝ ንጉሥ የአሜሪካ ነጻነት ዐዋጅ ጻፉ። በኋላ ፕሬዚዳንት ሲሆኑ የመርከብ ሃያላት ወደ አልጀርስ ላኩ፣ ከናፖሌዎን ደግሞ ሰፊ መሬት በሚሲሲፒ ወንዝ አቅራቢያ የሉዊዚያና አቅራቢያ የተባለው ገዝተው ነበር። ይህ ድርጊት የአሜሪካ ስፋት በሁለት እጅ አስፋፋ። "እኛ እነዚህን እውነቶች ለራስ ግልጽ እንደ ሆኑ እንቆጠራለን፤ ሰዎች ሁሉ እኩል ሆነው ተፈጥረዋል፤ አንዳንድ የማይቋረጡ መብቶች በፈጣሪያቸው ተሰጥተዋል፤ ከነዚህም መካከል ሕይወት፣ አርነትና የደስታ ፍለጋ አሉ።" -- የአሜሪካ ነጻነት ዐዋጅ

                                               

ነነዌ

ነነዌ የአሦር ጥንታዊ ከተማ ነበረ። ፍርስራሹ በጤግሮስ ወንዝ ምሥራቅ ዳርቻ በሞሱል ዙሪያ አሁን አለ። በ ኦሪት ዘፍጥረት 10፡11 መሠረት የሴም ልጅ አሦር ከሰናዖር ወጥቶ ነነዌንና ሌሎችን ከተሞች ሠራ። አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ግን ከፊተኛው ቁጥር ከ10፡10 በመውሰድ አድራጊው እንደ ናምሩድ ቆጥረውት፣ ናምሩድ እራሱ ወደ አሦር ወደ ሀገሩ ወጥቶ እኚህን ከተሞች እንደ ሠራ ይላሉ። በጥንታዊ የግሪክ ታሪክ ጸሃፊዎች ዘንድ ኒኑስ የነነዌ መስራችና የአሦር መጀመርያ ንጉስ ነበረ። ነነዌ ከጥንት ጀምሮ ከአሹር ከተማ-አገር ይገዛ ነበር። እንደ አሹር ከ1440 እስከ 1366 ዓክልበ. ድረስ በሚታኒ ይቆጣጠር ነበር። ትልቅ ከተማ ነበረ። በ775 ዓክልበ. አካባቢ ነቢዩ ዮናስ ወደ ነነዌ ሂዶ የአሦር ሰዎች ወደ ንሥሐ እንዳመጣቸው በ መጽሐፈ ዮናስ ይገለጻል። የዮናስ መቃብር የሚባለው የተቀደሠ መስጊድ በነነዌ የአሁኑ ሞሱል አካባቢ ይገኝ ነበር፤ በሐምሌ 2006 ዓ.ም. የኢስላማዊ ተዋጊዎች ከ "ኢስላም ግዛት በኢራቅና ሶርያ" ወገን የዮናስን ...

                                               

ነጋሽ

አህመድ ነጋሽ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በ610 እ.ኤ.አ.፣ አመተ ሂጅራ ነብዩ ሙሀመድ ዘመን፣ የሀበሻ ንጉስ ነበር፤ ኢትዮጵያ በዛን ሰአት አቢሲኒያ ወይንም ሀበሻ ትባል ነበር። ነበር። ነብዩ ሙሀመድ ሰ.አ.ወ እባልደረቦቻቸው ላይ የሚፈጸመውን ጥቃት ሊከላከሉ እንደማይችሉ ሲገነዘቡ ወደ ሃበሻ ምድር እንዲሰደዱ መከርዋቸው። እንደዚህም አልዋቸው። ወደ ሀበሻ ተሰደዱ በርስዋ አንድ ንጉስ አሉ፡ ከርሱ ፊት ማንም ተበዳይ አይሆንም ፤ ስለዚህ ተሰደዱ "አላህ ካላችሁበት ሁኔታ አውጥቶ ድል እስኪጎናጸፉ ድረስ." በዚህም መሰረት ነብዩ ሙሀመድ ሰ.አ.ወ ትእዛዝ ተቀብለው በአምስተኛው የነብይነት አመት በረጀብ ወር 615 እ.ኤ.አ. የመጀመርያውን ስደት ሂጅራ ወደ ሀበሻ አደረጉ አስራ ሁለት ሁነው ነበር የተሰደዱት። በጀልባ ለአንድ ሰው ግማሽ ዲናር ከፍለው ወደ ሃበሻ ተጎዙ። ከስደተኞቹ መካከል የነብዩ ሙሀመድ ሰ.አ.ወ ሴት ልጅ ሩቅያ ቢንት ሙሀመድ እና ባለቤትዋ ቡሃላ ላይ ሶስተኛ ኸሊፋ ወይንም የሳዑዲ ንጉስ የሆኑት። ኡስማን ቢን አፋን ይገኙበታል። በዚ ...

                                               

አሻንቲ መንግሥት

አሻንቲ መንግሥት ከ1662 እስከ 1949 ዓም ድረስ በዛሬው ጋና አካባቢ የነበረ ግዛት ነው። ከአካን ብሔር ግዛቶች አንዱ ነበር። የብሔሩ ስም በአካንኛ በትክክል "አሳንቴ" ፣ የአገሩም ስም "አሳንቴማን" ተብሎ ይጠራል። ይህም ከአካንኛ "አሳ" እና "-ንቴ" ወይም "ስለ ጦር" ለማለት ነው። "አሻንቲ" የሚለው አጠራር ከእንግሊዝኛው አጻጻፍ የተነሳ አጠራር ሲሆን፣ በአሁኑ ዘመን በጋና ውስጥ ተቀባይነት አለው። አካን የተባሉት ብሔሮች ከጥንቱ ጋና መንግሥት በዛሬው ማሊና ሞሪታኒያ ከ1068 ዓም በኋላ እንደ ፈለሱ ይነገራል። በዚያን ጊዜ መጀመርያውን አካን ግዛት ቦኖማን መንግሥት መሠረቱ። አገራቸው የወርቅ ማዕድን በብዛት የተገኘበት በመሆኑ በንግዱ ምክንያት ይበልጸግ ነበር። ከ1500 ዓም በኋላ የተለያዩ ተወዳዳሪ ግዛቶች ነበሩ፤ ዋነኛውም እስከ 1692 ዓም ያህል ድረስ የደንክዪራ መንግሥት ሆኖ ነበር። በዚያው ዓመት የአሻንቲ ንጉሥ ኦሰይ ቱቱ ደንክዪራን በማሸንፍ ዋናው ላዕላይ ግዛት ሆነ። የአሻንቲ ንጉሥ ማዕረግ አሳንቴሄኔ ይባል ነበር። ...

                                               

አንጥያኮስ አፊፋኖስ

፬ኛ አንጥያኮስ አፊፋኖስ ከ183 እስከ 172 ዓክልበ. ድረስ የሴሌውቅያ መንግሥት ንጉሥ ነበር። "ኤፒፋኔስ" ማለት በትዕቢቱ እንደ ተመካ "የአምላክ ክሥተት" ማለት ነው። እንደ ወፋፌ እና ጨካኝ ንጉሥ ይታወሳል። አፊፋኖስ የአይሁድናን ሃይማኖት ያሳደደ ንጉሥ ነበር። ከአይሁዶቹ አያሌዎች "ግሪካዊ-አይሁዶች" ሲባሉ እነኚህ የአይሁድ ሃይማኖትና ባህል ንቀው የግሪክ ባህልና ቋንቋ ደጋፊዎች ነበሩ። ሌሎች የአይሁድ ወገኖች እንደ መቃብያን በአይሁድና ባህል ቀሩ። አፊፋኖስ አይሁድናን ለማጥፋት ከግሪካዊ-አይሁዶች ጋራ ተባብሮ ነበር። ከመቃብያን ወገን ጋር ብሔራዊ ጦርነት ሆነ፣ ብዙ አይሁዶችም ተገደሉ። ይህም ንጉሥ በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ውስጥ የግሪኮች ጣኦታት አስገባ። በግሪኩ መጻሕፍተ መቀባውያን አፊፋኖስን ይተርካል፣ በመጨረሻ የሞተው አንጀቱ ከሥፍራው ሲወድቅ ነበር። በኢትዮጵያ ያሉ መጻሕፍተ መቃብያን ደግሞ ጺሩጻይዳን ብለውት እንደ ጠቀሱት ይታመናል። በብዙ መሐለቅ ላይ ከምስሉ አጠገብ የታተመባቸው ከተሞች "ጺር ቲሮስ ኡ እና ጻይዳን ሲዶና ...

                                               

አካድ

አካድ በመስጴጦምያ የተገኘ ጥንታዊ ከተማ ነበረ። ቦታው በኤፍራጥስ ወንዝ ላይ ከሲፓርና ከኪሽ መካከል እንደ ነበር ቢታሠብም ፍርስራሹ ግን እስካሁን ድረስ አልተገኘም። ዙሪያው በሱመርኛ ኡሪ-ኪ ወይም ኪ-ኡሪ ተባለ። በሱመራውያን ነገሥታት ዝርዝር መሠረት አካድ አጋደ የገነባው ታላቁ ሳርጎን ነበረ። ሆኖም ከተማው ከሳርጎን ቀድሞ በኡሩክ ንጉሦች ኤንሻኩሻና እና ሉጋል-ዛገሢ ዘመናት እንደተገኘ ከጽሕፈቶች ይታወቃል። በመጽሐፍ ቅዱስም ዘፍ. 10፡10 ዘንድ ናምሩድ ከሠሩት ከተሞች 1ዱ መሆኑ ይቆጠራል። ከዚህ በላይ ኤንመርካርና የአራታ ንጉስ በተባለው ሱመራዊ አፈ ታሪክ፣ ልሣናት የተደባለቁባቸው አገሮች ሹባር፣ ሐማዚ፣ ሱመር፣ ኡሪ-ኪ የአካድ ዙሪያ እና የማርቱ አገር በመባላቸው፤ ይህም የአካድን ጥንታዊነት ይመሰክራል። እንደገና በብዙ ጥንታዊ መዝገቦች፣ ከሰናዖር ሱመር ዙሪያ ሌሎቹ 4 ሩቦች ሲዘረዘሩ እነርሱ ማርቱ አሞራውያን፣ ሹባር አሦር?፣ ኤላምና ኡሪ-ኪ አካድ ናቸው። ከአካድ ንጉሥ ከሳርጎን ዘመን ጀምሮ የአካዳዊ መንግሥት ዋና ከተማ ሆኖ ከ ...

                                               

አዳል

የ አዳል ሱልጣኔት ተብሎ ይታወቅ የነበረው ግዛት በመካከለኛው ዘመን የነበረ የብዙ እስልምና ተከታይ ጎሳወች ድብልቅ የነበረ ግዛት ነው። አንዳንድ ተመራማሪወች አብዛኛው አዳል የአፋር ጎሳወች ተዋጾ ነበረበት ሲሉ አንዳንዶች ደግሞ ባብዛኛው ከዲር እና ዳሩድ የሶማሌ ነገዶች የተውጣጣ ነበር ይላሉ። የአዳልን ሱልጣኔት አብዛኛ ጎሳ ስብጥር ክርክር ይውደቅ እንጂ በርግጥም ሱልጥኔቱ የብዙ ጎሳወች ስብስብ እንደነበር ግን ክርክር የለም።. . ስለ አዳል ሱልጣኔት በትንሹ ከ1415- 1577 ዓ.ል. በአብዱ እንድሪስ ከሚሴ አስራ ሁለተኛው የኢትዮጵያ ሰለሞናዊ ነጋሲ የነበረው ወጣቱ አጼ ዳዊት በ1413 ዓ.ል. በአጠገቡ በነበረው የኢፋት ሱልጣኔት ላይ ሀይለኛ ጥቃት ከፈተ። የሱልጣኔቱ ገዠ የነበረውን ሱልጣን ሰዓደዲንን በዜይላ ከተማ ከገደለው በኋላም ኢፋትን ከአጼው ግዛተ መንግስት ጋር ቀላቀለው። ሆኖም አጼ ዳዊት በቁጥጥር ስር ካዋለው የኢፋት ግዛት በሙሉ ሀይሉ ለመግዛት የቻለው ከአዋሽ ወንዝ በስተምዕራብ ያለውን ብቻ ነው። ከወንዙ በስተ-ምስራቅ ያለ ...

                                               

ኡራርቱ

ኡራርቱ በጥንት የነበረ መንግሥት ሲሆን በደብረ አራራት ዙሪያ ተገኘ። ስያሜው "ኡራርቱ" አሦርኛ ሲሆን ከደብረ አራራት ስም ጋር እንደ ተዛመደ ይታሥባል። በአሦርኛ ሰነዶች "ኡራርቱ" ና "ናይሪ" የሚሉት ስሞች ለዙሪያው ከ1300 ዓክልበ. አካባቢ ጀምሮ ተዘግበዋል። በተጨማሪ በሱመር አፈ ታሪክ "አራታ" የተባለ ሀገር ምናልባት 2450-2350 ዓክልበ. ይታወቅ ነበር፣ እሱም ከአሶርኛው "ኡራርቱ" ጋር ዝምድና እንዳለው የሚያስቡ አሉ። በትንቢተ ኤርምያስ ብሉይ ኪዳን 600 ዓክልበ. አካባቢ ደግሞ በ51:27 የአራራት፣ የሚኒ እና የአስከናዝ መንግሥታት ሲጠቅስ፣ ይህ "አራራት መንግሥት" ማለት በዚያን ጊዜ የነበረው የኡራርቱን መንግሥት ይገልጻል። በኡራርትኛ የመንግሥቱ ስም "ቢያይኒሊ" ተባለ። ከአሦርኛ መዝገቦች እንደምናውቅ፣ ከ1300 እስከ 868 ዓክልበ. ድረስ እነዚህ "ናይሪ" ወይም "ኡሯትሪ" ብሔሮች በተለያዩ ነገዶች ይኖሩ ነበር፤ በ868 ዓክልበ. የናይሪ ሕዝቦች በንጉሥ አራሙ ተባብረው የኡራርቱ ቢያይኒሊ መንግሥት ፈጠሩ። በቋንቋ ረገ ...

                                               

ከነዓን (ጥንታዊ አገር)

የዕብራውያን ወረራ በከነዓን በተለይ በመጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ ይገለጻል። መጀመርያ ኢያሪኮንና ጋይን ያዙ፣ ከዚያም ገባዖን ተገዛላቸው። አምስት የአሞራውያን ነገሥታት፦ የኢየሩሳሌም ንጉስ አዶኒጼዴቅ፣ የኬብሮን ንጉሥ ሆሃም፣ የየርሙት ንጉሥ ጲርአም፣ የለኪሶ ንጉሥ ያፊዓ፣ የኦዶላም ንጉሥ ዳቤር ለመቃወም ተሰብስበው ኢያሱ አጠፋቸውና ደቡቡን ከነዓን ሁሉ ያዘ። ትልቅ ተዓምራት እንደ ተደረጉ ይጻፋል። ካሌብ ኬብሮን የተሰጠው ከጸአት 45 ዓመት በኋላ ኢያሱ 14:10 ወይም በ1616 ዓክልበ. ነበር። ከዚያ የአሶር ሐጾር ንጉስ ኢያቢስና የማዶን ንጉሥ ዮባብ በስሜን ተቃወሙት፣ ኢያሱም አሸነፋቸውና ሐጾርን አቃጠለ። ከኢያሱ ዘመቻዎች በኋላ የከነዓን ሰዎች በአንዳንድ ቦታዎች በተለይ በፍልስጥኤምና በፊንቄ አካባቢ ቀሩ። ወደ ስሜኑ በሶርያ የያምኻድ ንጉሥ እርካብቱም 1587-1575 ከ "ሃቢሩ ወገን አለቃ "ሰሙማ" ስምምነት እንዳደረገ ይዘገባል። ከዚህ ጀምሮ "ሃቢሩ / አፒሩ" የተባለው ወገን በከነዓን ምድር ሃይለኛ ወገን እንደ ነበሩ በብዙ መዝገቦች ...

                                               

ኮናይረ ሞር

ኮናይረ ሞር በአይርላንድ አፈ ታሪክ ከ22 እስከ 36 ዓም ድረስ የአየርላንድ ከፍተኛ ነጉሥ ነበር። የላውድ አቆጣጠሮች 1014 ዓም ተቀነባብሮ ዘንድ፣ የኮናይረ ዘመን ለ14 ዓመታት ቆየ፣ የኢየሱስም ስቅለት በኮናይረ ፬ኛው ዓመት ደረሰ። በዚያን ጊዜ በአውሮጳውያን አቆጣጠር ስቅለት በ34 እ.ኤ.አ. 26 ዓም እንደ ሆነ ይታመን ነበር። የቲገርናቅ ዜና መዋዕል 1080 ዓም ተቀነባብሮ ዘንድ፣ ኮናይረ በ36 ዓም = 44 እ.ኤ.አ. ዓረፈ። ፕሮፌሰር ዲ ፒ ማካርጢ እንዳስረዳው፣ ከ11ኛው ክፍለ ዘመን ዓም የተረፉት ቅድመኞቹ ምንጮች በአቆጣጠር ረገድ እርስ በርስ ይስማማሉ። በዚያው አቆጣጠር፣ የክርስቶስ ልደት 1 እ.ኤ.አ. እንደ ታሠበ ወይም በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር 8 ዓክልበ. በዮኩ ፈይድሌክ ዘመን 11 እስከ 1 ዓክልበ. ፫ኛው ዓመት ደረሰ። በኋላ የተጻፉት ዝርዝሮች ግን ኮናይረ ለ70 ዓመታት ሙሉ እንደ ገዛ ይላሉ። ማካርጢም እንዳስረዳው፣ ከ12ኛው ክፍለ ዘመን ዓም ጀምሮ ምንጮቹ በአይርላንድ ነገሥታት አቆጣጠር ስለ ክርስቶስ ልደት ዓመት ...

                                               

ዓፄ ተክለ ሃይማኖት

ቀዳማዊ ተክለ ሃይማኖት ፣ ዙፋን ስም ለዓለ ሰገድ ፣ ከ1698 እስከ 1700 ዓም ድረስ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ነበሩ። የቀዳማዊ ዓፄ ኢያሱና የንግሥት መለኮታዊት ልጅ ነበሩ። አፄ ኢያሱ ቁባታቸው ቅድሥተ ክርስቶስ አርፈው በጣና ሃይቅ ውስጥ ወዳለ ደሴት ቆይተው ነበር። በንግሥቲቱ መለኮታዊት ድጋፍ፣ ከመኳንንት ወገን አያሌዎች ኢያሱ እንደ ጥንቱ አክሱም ንጉሥ ካሌብ ማዕረቁን እንደ ተዉ ተከራከሩና ልጅ ተክለ ሃይማኖት በጎንደር እንደ ንጉሠ ነገሥት ሆነው ዘውድ ጫኑባቸው። ይሄው ድርጊት በመላው ግዛት ስላልተቀበለ በተነሣው ሁከት ውስጥ ተክለ ሃይማኖት አባታቸውን ኢያሱን አስገደሏቸው። በዚህ ሥራ ስማቸውን "እርጉም ተክለሃይማኖት" አግኝተዋል። በመስከረም ወር 1700 ዓም አንድ የጎጃም አመጸኛ እራሱን ንጉስ "ዓምደ ጽዮን አድርጎ አዋጀ። ወደ ዋና ከተማው በጎንደር ደርሶ ዘውድም ተጫነ። አጼ ተክለ ሃይማኖት ክረምት ቢሆንም ቶሎ ወደ ጎንደር ተመለሱ፤ ነጣቂውንም አባረሩት። ከትንሽ በኋላ ዓምደ ጽዮን በማይጻ በውግያ ተገደለ። ሆኖም ግን የተወደ ...

                                               

ዓፄ ቴዎፍሎስ

ቴዎፍሎስ ፣ ዙፋን ስም ወልደ አምበሳ ፣ ከ1700 እስከ 1704 ዓም ድረስ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ነበሩ። የቀዳማዊ ዓፄ ኢያሱ ወንድም ነበሩ። የአጼ ኢያሱ ልጅ ዓፄ ተክለ ሃይማኖት ከተገደሉ በኋላ፣ ቴዎፍሎስን ከደብረ ወህኒ አምጥተዋቸው ንጉሠ ነገሥት ተደረጉ። የተክለ ሃይማኖት ወንድ ልጅ አራት ዓመት ሕጻን ሲሆን የፈረስ አለቃ ዮሐንስና የኢያሱ ንግሥት መለኮታዊት ድጋፍ ነበረለት። ቴዎፍሎስ ግን ቶሎ ብለው ዮሐንስ በአጸ ተክለሃይማኖት ላይ ሤራ ውስጥ ነበር ብለው ከሠውት አሰሩትና ከአገሩ ሰደዱት።. በአቶ ጄምስ ብሩስ ዘንድ፣ በመጀመርያው የወንድማቸውን የኢያሱ ቂም እንደማይበቅሉ ቢመስልም፣ ይህ ማታለል ነበርና ያው ወገን ከተዝናና በኋላ እርምጃ ወሰዱባቸው። የአረፉት አጼ ተክለ ሃይማኖት አባታቸውን በመግደላቸው ረገሙዋቸው፤ ከዚያም ጀምሮ ነው "እርጉም ተክለሃይማኖት" የተባሉት። ንግሥት መለኮታዊት ስለ ሚናቸውና ሁለት ወንድሞቻቸው ደግሞ ተገደሉ። በብሩስ መሠረት በአንድ ቀን 37 ሰዎች ይሙት በቃ አገኙ። ቴዎፍሎስም የወንድማቸውን የኢያሱ ...

                                               

የሞንጎላውያን መንግሥት

የሞንጎላውያን መንግሥት ከ1198 እስከ 1286 ዓም. ድረስ የተባበረ መንግሥት ነበረ። በ1198 ዓም መጀመርያው ንጉሥ ቺንግስ ካን የሞንጎላውያን ብሔሮች በሞንጎልያ በአንድ መንግሥት አዋሃዳቸው። በዚህም ዘመን ያህል በቻይና የእጅ መድፍ እየተደረጀ ነበር። ሞንጎላውያን ይህን ቴክኖሎጂ አገኝተው በዚያው ምክንያት ሥራዊታቸው ባሩድ ባልታወቀባቸው አገራት ወርረው እንዳልተሸነፉ ይሆናል። መንግሥታቸው በፍጥነት ከአውሮፓ እስከ ቬትናም ድረስ ይስፋፋ ቻለ። ችንግስ የአረመኔነት ተከታይ ቢሆንም፣ በሞንጎላውያን በኩል ሃይማኖቶች ሁሉ - በተለይም ክርስትና፣ ቡዲስም፣ እስልምና - ይገኙ ነበርና ይከብሩ ነበር። ዳሩ ግን ሞንጎሎች ለእስላም ወይም ለአይሁድ የራሳቸውን በግ እንዲያርዱ ወይም የራሳቸውን ምግብ አልፈቀዱላቸውም ነበር፤ ሰው ሁሉ እንደ ሞንጎላውያን እንዲመገቡ አስገደዳቸው። ይህም እንስሳው የሚታርደው በጉሮሮ በመቋረጥ ሳይሆን በአረመኔ መንገድ ልቡ በሕይወት ሳለ በእጅ መጨመቅ ነበር። ቺንግስ ደግሞ የዳዊስም አለቃ ጪው ቹጂ ለመንግሥቱ ሁሉ ሃይማኖ ...

                                               

የቬትናም ጦርነት

የቬትናም ጦርነት ከ1948 ዓ.ም. እስከ 1967 ዓ.ም. ድረስ በቬትናም የነበረ ጦርነት ነበር። ይህ ጦርነት እንደ ኮሪያ ጦርነት ሳይሆን ከተመድ ምንም በረከት ያላገኘ ሥራ ነበር። ከ1946 ዓም የጀኔቭ ጉባኤ በኋላ የፈረንሳይ ቅኝ አገር የነበረችው የፈረንሳይ ኢንዶቻይና በላዎስ፣ ካምቦዲያ፣ ስሜን ቬትናምና ደቡብ ቬትናም ተከፋፈለች። በቅርቡ ግን ከስሜን ቬትናም በሶቪዬት ሕብረትና በቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ ድጋፍ እና ከደቡብ ቬትናም በዩናይትድ እስቴትስ ድጋፍ መካከል፣ ኹኔታው ወደ እርስ-በርስ ጦርነት መራ። በአሜሪካዊው ፕሬዚዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ ዘመን በየወገኑ የቻይና ወይም የአሜሪካ ሚለታሪ አማካሪዎች በቬትናም ተገኙ። ባጠቃላይ አሜሪካውያን ግን ስለ ቬትናም ባሕል ወይም ታሪክ ያወቁት እምባዛም ነበር። በተለይ ኬኔዲ በጥይት ተገድሎ ምትኩ ፕሬዚዳንቱ ሊንደን ጆንሰን በኅዳር 1956 ዓም ፕሬዚዳንት ከሆነ በኋላ፣ ሰበብ አድርጎ ቬትናም ትልቅ የአሜሪካ ጦርነት እንዲሆን አሰበ። በነሐሴ ወር 1956 ዓም ስሜኑን በቦምብ መደብደብ ጀመረ፣ ይህ ...

                                               

የአድዋ ጦርነት

የአድዋ ጦርነት በየካቲት ፳፫ ቀን ፲፰፻፹፰ ዓ.ም. በኢትዮጵያና ኢጣሊያ መካከል የተካሄደ ውጊያ ሲሆን የአንደኛው የኢትዮጵያና ጣሊያን ጦርነት ክፍል ነው። በ ኢትዮጵያ አሸናፊነት የጣልያን የቀኝ ግዛት ማስፋፋት ተኮላሸ። ምኒሊክ ተወልዶ ባያነሣ ጋሻ ግብሩ እንቀላል ነበር ይሄን ጊዜ አበሻ፤ *** ገበየሁ ቢሞት ተተካ ባልቻ መድፍ አገላባጭ ብቻለብቻ፤ *** የአድዋ ሥላሴን ጠላት አረከሰው ገበየሁ በሞቴ ግባና ቀድሰው፤ የአድዋ ድል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ክብር ማኅተም፤ የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተጋድሎ ቀንዲል ነው፡፡ የመላው ዓለም ተፈጥሮአዊ ግብር እና ሰብአዊ ክብር የታደሠው፤ በእውነትና በፍትህ ህልውናና ምልዓት ላይ የተሰካ ትልቅ ጥርስ የተነቀለው … በአድዋ የታላቅ ህዝቦች ታላቅ ድል ነው፡፡ ከአዲስ አበባ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ስንሄድ 1066 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ታላቁ ጦርነት የተደረገበትና ታላቁ ድል የተገኘበት ሥፍራ አድዋ ከተማና የከተማው ግድም ገመገሞች ይገኛሉ፡፡ በኢትዮጵያውያን አቡሻኽር Julian calendar የካቲት 23 ቀን ...

                                               

የኦርኾን ጽሑፎች

የኦርኾን ጽሑፎች በ724 ዓም በአሁኑ ሞንጎሊያ በኦርኾን ወንዝ ሸለቆ በጥንታዊ ቱርክኛና በቻይንኛ በጎክቱርክ መንግሥት አለቆች የተቀረጹ ሐውልቶች ናቸው። ያስቀረጹዋቸው መሪዎች ቢልጌ ቃጋንና ወንድሙ ኩል ቲጊን ነበሩ። ጥንታዊ ቱርክኛ እና ቅድመ-ቱርክኛ ከዘመናዊ ቱርክኛ በጣም አይለዩም። እነዚህ ጽሑፎች በማንኛውም የቱርኪክ ቋንቋዎች ቤተሠብ ከሁሉ ቅድመኛ የታወቁት ናሙናዎች ናቸው። የተጻፈበት የኦርኾን ጽሕፈት በተባለው ጥንታዊ ቱርክኛ አልፋቤት ነበረ። ጽሕፈቶቹ የቱርኮች ታሪክ ይናገራሉ፤ የተንግሪስም እምነት ተከታዮች መሆናቸውን ይገልጻሉ። ጥንታዊ ቱርኮች ዘላኖችና ወራሪዎች ሲሆኑ፣ ቅዱስ ዋና ከተማቸው "ኦቱከን" በኦርኾን ወንዝ ሸለቆ በአሁኑ ሞንጎሊያ እንደ ተገኘ ይገልጻሉ። "ኦቱከን ከእርሱ አገራት ሊገዙ የሚቻልበት ቦታ ነው. ሁልጊዜ ከኦቱክን ብትገዙ ከዚያም ቅፍለቶችን ብትልኩ ምንም ችግር አይኖርህም." በጽሑፎቹም ደግሞ መሪያቸው ቃጋናቸው ቢልጌ እንደሚተርከው፣ ቅድም-አያቶቹ ወደ አራት አቅጣጮቹ ዘምተው ጎረቤቶቻቸውን ሁሉ ይገዙ ነበር ...

                                               

የኩሽ መንግሥት

የኩሽ መንግሥት በላይኛ አባይ ወንዝ በጥንት የተመሠረተ አፍሪካዊ መንግሥት ነበረ። በኢትዮጵያ ታሪክ ጸሓፊዎች ዘንድ የኩሽ መንግሥት በካምና በልጁ ኩሽ ተመሠረተ። ይህ የኩሽ ወይም የኩሳ ሥርወ መንግሥት ግዛት እስከ ደጋ ድረስ ሲዘረጋ አንዳንድ ጎሣ ከውጭ አገር በተለይ ከከነዓን በዚያ ይሠፈር ነበር። "ኩሽ" የሚለው ስም መጀመርያ በግብጽ መዝገቦች የታየው በ2 መንቱሆተፕ ዘመን ነው። ያው ፈርዖን በ2092 እና 2090 ዓክልበ. ግድም ከ2ኛው ፏፏቴ ወደ ደቡብ በኩሽ ላይ ዘመተ። ከ16ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. እስከ 11ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. ድረስ ኩሽ በዛሬው ሱዳን ለግብጽ አዲስ መንግሥት ተገዥ ነበር። ከዚያ እንደገና ነጻ ሆነ፣ በ8ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. የኩሽ ነገሥታት ደግሞ በግብጽ የ25ኛው ሥርወ መንግሥት ፈርዖኖች ሆኑ፤ እስከ ሶርያም ድረስ አገሩን አቀኑ።

                                               

የኮርያ ነገሥታት ዝርዝር

ማስታወሻ፦ ከ200 ዓክልበ. አስቀድሞ የነበሩት የኮርያ ነገሥታት በታሪክ ሊቃውንት ዘንድ ከአፈ ታሪካዊ ሁኔታ በላይ የላቸውም። በአፈ ታሪክ የቻይና ንጉሥ ዦው ዉ በ1134 አክልበ. ግድም ጊጃን በጎጆሰን ዙፋን አስቀመጠው። ይህ ታሪክ ቀድሞ በቻይናም ሆነ በኮርያ ሊቃውንት የተቀበለ ሲሆን፣ አሁን ግን የቻይና ሊቃውንት ሲቀበሉት ብዙ የኮርያ ሊቃውንት አይቀበሉትም፤ የፊተኛው 47 ነገሥታት እስከ 203 ዓክልበ. ድረስ እንደ ነገሡ ያደርጋሉ እንጂ። የውንገውል 527–511 ህዮጆንግ ቻንጉክ 769–756 ሱሰውንግ 568–527 ሙንሙ 1008–980 ኡያንግ 904–851 ሳምህዮ 323–298 ሰውንህየ 933–904 ኊያንግ 623–602 ሰውንግደክ 801–786 ቸውንጉክ 473–440 ህውንግፕየውንግ 965–951 ጀሰ 494–473 ሙሰውንግ 756–730 ቸውንህዮ 666–642 ሙንሰውንግ ጊጃ 1134 – 1090 ዓክልበ. ሰውልሙን 377–369 ግየውንግህዮ 1065–1038 ቦንጊል 602–586 ጎንግጀውንግ 1038–1008 ጀውንግየውንግ 730–711 ዶሄ 786– ...

                                               

የኮርያ ጦርነት

የኮርያ ጦርነት በኮርያ ከሰኔ 18 1942 እስከ ኃምሌ 20 1945 የተዋገ ጦርነት ነበር። የኮሪያ ዘማቾች ትውስታ ሬሳ እንኳ አልተማረከብንም”" አለመማረክ የጀግንነት ጉዳይ አይደለም” በአምስት ዙር ኮርያ ከዘመቱት 6037 ኢትዮጵያውያን መካከል 122ቱ በጦርነቱ ሞተዋል፡፡ አንዳቸውም አልተማረኩም ሳይማረኩ ግዳጃቸውን ፈጽመው ከተመለሱት 350ው የዛሬ 20 ዓመት የኢትዮጵያ ኮርያ ዘማቾች ማህበርን መስርተው ሰሞኑን የዘመቻውን 61ኛ ዓመት አክብረዋል፡፡ የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ መልካሙ ተክሌ ከአስር አለቃ ዘነበወርቅ በላይነህ እና ከየኢትዮጵያ ኮሪያ ዘማቾች ማህበር ፕሬዝደንት ኮሎኔል መለሰ ተሰማ ጋር አጭር ቃለምልልስ አድርጓል፡፡ ለኮሪያ ዘመቻ እንዴት ነው የተመረጡት? በመሠረቱ የገበሬ ልጅ ነኝ፡፡ ለኮሪያ ዘመቻ ተብዬ አይደለም ወደ ወታደራዊ ዘመቻ የገባሁት፡፡ በጣልያን ወረራ ወቅት በሕፃንነቴ ከአባቴ ጋር ለጫካ ተንከራትቻለሁ፡፡ በ1939 ዓ.ም ወታደርነት ተቀጠርኩ፡፡ የተወለድኩት በ1922 ዓ.ም ነው፡፡ ወታደር በሆንኩ በአምስት ወይ በስ ...

                                               

የፈረንሳይ አብዮት

የፈረንሳይ አብዮት በፈረንሳይ አገር ታሪክ ከ1781 እስከ 1791 ዓ.ም. ድረስ የተካሄደ ሲሆን በዚህ አብዮት የፈረንሳይ ሕዝብ ከጥንት ዘመን ጀምሮ የነበረውን የዘውድ አገዛዝ እና ተያያዥ የፊውዳል ሥርዓትን በመገርሰስ፣ አገራቸውን በአዲስ መልክ በሪፐብሊክ ያዋቀሩበት ሂደት ነው። የአብዮቱ አነሳስ ብዙና በአንድ ጊዜ የተከማቹ ምክንያቶች ነበሩት። አንደኛው ምክንያት የፈረንሳይ ሕዝብ ቁጥር ማደግ ነበር። ከሕዝቡ ቁጥር ጋር አብሮ እየጨመረ የሄደው በትውልድ ሳይሆን በጥረት ባለሃብት የሆነውለምሳሌ፣ ነጋዴ፣ አምራች፣ ሐኪም፣ ወዘተ. ባጠቃላይ በፈረንሳይኛ ቡርዧ መደብ፣ የፖለቲካ ስልጣን እንደ ባላባቶች ለመያዝ መፈለጉ አንዱ የአብዮቱ መነሻ ነበር። የገበሬው መደብ አባላት በአንጻሩ አብዛኞቹ የራሳቸው መሬት ባለቤት እየሆኑ ስለመጡ፣ በፊውዳል ሥርዓቱ ላይ ከንቀት ጋር የተቀላቀለ ጥላቻ ነበራቸው። ሊያጠፉትም ይፈልጉ ነበር። በዚህ መሃል፣ የብርሃናት ክፍለ ዘመን የተባለው ከፍተኛ የውይይት፣ ክርክር እና የዕውቀት ስርጭት በፈረንሳይ አገር ይካሄድ ነ ...

                                               

የፈርዖኖች ዝርዝር

የግብጽ ፈርዖኖች ዝርዝር በሥርወ መንግሥታት አከፋፈል እንደ ተለመደ ከማኔጦን የተወረሰ ነው። በተጨማሪ አንዳንድ ሌላ ጥንታዊ ዝርዝር ምንጭ ይታወቃል። ለመሆኑ ለብዙዎች ፈርዖኖች በሥነ ቅርስ የሃይሮግሊፍ መዝገብ በመገኘቱ፣ የስሞቻቸው አጠራር በግብጽኛ አሁን ሊታወቅ ይችላል። ለብዙዎቹም አያሌ ልዩ ስሞች አሏቸው።

                                               

ያኑስ

ያኑስ በሮሜ አረመኔ ሃይማኖት ውስጥ ጣኦት ወይም አምላክ ነበረ። የወሩ ስም ጃንዩዌሪ የመጣ ከሱ ነው። በሮማውያን ትውፊቶች ዘንድ ያኑስ መጀመርያ በጣልያን ላቲዩም ይነግሥ ነበር፤ መንግሥቱንም ከሳቱርን ወይም ካሜሴ ጋር ይይዝ ነበር። ከዚህ በላይ የጄኖቫና ያኒኩሉም ከተሞች መስራች እንደ ነበር የሚል ልማድ አለ። ማርቲን ዘኦፓቫ 1240 ዓ.ም. ገደማ፣ የ ሚራቢሊያ ዑርቢስ ሮማይ ኋለኛ ቅጂዎች፣ እና የጆቫኒ ዲ ማሪንዮላ ክሮኒኮን ቦሄሞሩም 1347 ዓ.ም. ሁላቸው ሲስማሙ፣ ወደ ጣልያን አገር ፈልሶ ሥነ ፈለክን ፈጥሮ ናምሩድንም ያስተማረው የኖህ አራተኛ ወንድ ልጅ ያኑስ ነበረ። ጣልያናዊ መኖኩሴ አኒዩስ ዴ ቪቴርቦ ባሳተመው ዜና መዋዕል ዘንድ 1490 ዓ.ም. የታተመ፣ ያኑስ የኖኅ ልጅ ሳይሆን የኖኅ እራሱ ሌላ ስም ነው። ኖኅ በአራራት ላይ ወይንን ስለ ተከለ፣ የስሙ "ያኑስ" ትርጉም በአራማይስጥ "ወይን" እንደሆነ ይላል። ከናምሩድ መንግሥት ቀጥሎ ያኑስ ከተሞችና ሠፈረኞች እየተከለ በዓለሙ ይዛወር ነበር። በመጨረሻ ያኑስ ካምን ከጣልያን አባ ...

                                               

ዳኛዋቲ

ዳኛዋቲ በጥንታዊ አራካን እና በአፈ ታሪክ የነበረ የከተማ፣ የ፫ ሥርወ መንግሥታትና የሀገር ስም ነበረ። ለነዚሁ ፫ ቅድመ ታሪካዊ ሥርወ መንግሥታት አንዳችም ቅርስ እስካሁን ባለመገኘቱ፣ ከትውፊትና አፈ ታሪክ ብቻ ይታወቃሉ። በአራካን ታሪክ፣ እስከ 1420 ዓም እስከ ምራውክ-ኡ መንግሥት ምንም እርግጠኛ አቆጣጠር ወይም መዝገብ የለም። የእንግላንድ ጸሐፊ አርሰር ፈይር በ1825 ዓም በጻፈው የበርማ ታሪክ አቆጣጠር፣ የልማዳዊ ነገሥታት ዝርዝር ለነዚህ ፫ ዳኛዋቲ ሥርወ መንግሥታት ከ2674 ዓክልበ. ጀምሮ እስከሚከተለው እስከ ዌሻሊ መንግሥት እስከ 780 ዓም ድረስ ቆየ። በእርሱ አከፋፈል ዜና መዋዕሉ እንዲህ ያመልክታል፦ መጀመርያው ዳኛዋቲ መንግሥት፣ 2674-833 ዓክልበ.። ከመሥራቹ ማራ ዩ 2674-2612 ዓክልበ. የገዛ ተብሎ ይጀመራል። ሁለተኛው ዳኛዋቲ መንግሥት፣ 833 ዓክልበ 138 ዓም ሦስተኛው ዳኛዋቲ መንግሥት፣ 138-780 ዓም። በአራካን አፈ ታሪክ፣ በዚህ ፫ኛው መንግሥት መጀመርያ ጎታማ ቡዳ እራሱ አገሩን እንደ ጎበኘ ይባላል። ...

                                               

ዳግማዊ ዓፄ ዳዊት

ዳግማዊ ዓፄ ዳዊት ፣ ዙፋን ስም አድባር ሰገድ ፣ ከ1708 እስከ 1713 ዓም ድረስ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ነበሩ። ከዘመኖች በፊት ነግሠው የነበሩት ዓፄ ልብነ ድንግል ደግሞ በይፋ "ዳግማዊ ዳዊት" ስለ ተሰየሙ፤ ይሄው ንጉሠ ነገሥት እንዲሁም ሣልሳዊ ዓፄ ዳዊት ተብለዋል። የቀዳማዊ ዓፄ ኢያሱና የቁባታቸው የቅድሥተ ክርስቶስ ልጅ ነበሩ። በሃይማኖት ረገድ በዚሁ ዘመን ሦስት ትልልቅ ድርጊቶች ተከሠቱ። መጀመርያው የአቡነ 10ኛው ማርቆስ ዕረፍት ነበር። ዳዊት ወደ እስክንድሪያ ልከው ከዓመታት በኋላ አዲሱ አቡነ ክርስቶዶሎስ ደረሱላቸው። ሁለተኛው ድርጊት ሦስት ሮማን ካቶሊክ ካፑቺን ሰባኪዎችና አንድ ልጅ ያለ ፈቃድ ወደ ሀገሩ ሲገቡ ሆነ። አራታቸው ታስረው እንደ ሀረ ጤቆች ተፈረደባቸውና ተገደሉ። ሦስተኛውም ድርጊት አንድ የኢኦተቤ ሲኖዶስ በጎንደር መካሄዱ ነበር። በዚሁ ጉባኤ ላይ ከኤዎስጣጤዎስ ትምህርት ወገንና ከደብረ ሊባኖስ መኖኩሳት መካከል ክርክር ሆነ። አጼ ዳዊት ለኤዎስጣጤዎስ ወገን ደገፉ፤ ስለዚህ የደብረ ሊባኖስ ወገን አቤቱታ አ ...

                                               

ገላውዴዎስ

ዓፄ ገላውዴዎስ ከጥቅምት ፳፯ ቀን ፲፭፻፴፫ ዓ/ም እስከ መጋቢት ፳፯ ቀን ፲፭፻፶፩ ዓ/ም ድረስ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ነበሩ። ግዛታቸው በኢትዮጵያና አዳል ጦርነት ጊዜ ነበር። ዓፄ ገላውዴዎስ የስቅለተ ዓርብ ዕለት በአዋሽ አካባቢ ከአዳሉ አሚር ኑር ጋር በተደረገው ጦርነት ላይ ተወግተው ሞቱ። በዚሁ ጦርነት ላይ የደብረ ሊባኖስ እጨጌ ዮሐንስም ሕይወታቸውን አጥተዋል። የታሪኩ ምሑር ሪቻርድ ፓንክኸርስት፣ አሚር ኑር የንጉሠ ነገሥቱን ጭንቅላት ወደይፋቱ ሡልጣን ሳዳዲን እንደላከው ለመረጃ የሐረርን ዜና መዋዕል ይጠቅሳሉ።

                                               

ጥንታዊ ግብፅ

በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ከማየ አይኅ ቀጥሎ መጀመሪያ የአፍሪካ ሕዝብ የኖኅ ልጅ የካም ዘሮች ናቸው፤ ይህ አገር ሰናዖር ለሚሉት ቅርብ ስለ ነበር የባብል ግንብ ከተሠራ በኋላ ከዚህ ተነስተው ወደ ግብፅ ወረዱ። የግብጽ ቀድሞ ዘመን መንግሥት ዋና ጥንታዊ ነው፤ የመሠረተውም ፈርዖን ሜኒስ የተባለው ነው። ጸሓፊው ጊዮርጊስ ስንቄሎስ ፰፻ ዓ.ም. አካባቢ የጻፈው ይህ ፈርዖን ሜኒስ በዕውነት የካም ልጅ ምጽራይም እንደ ነበረ ገመተ። ዳሩ ግን አባ አውሳብዮስ በጻፉት ዜና መዋዕል ዘንድ ፫፻፲፯ ዓ.ም. ተጽፎ፣ የድሮ ግብጻዊው ባለታሪክ ማኔጦን ፫ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. ስለ ኋለኞቹ ግብጻውያን ሲጽፍ፣ ይኮሩበት የነበረው የታላቁ ጥንት ዘመን ከማየ አይህ አስቀድሞ እንዳለፈ፣ በኋላም በዚያው አገር ዳግመኛ ከሠፈረበት ከካም ልጅ ምጽራይም በውኑ እንደ ተወለዱ ጽፎ ነበር። ተመሳሳይ ታሪክ በእስላም ጸሐፊዎች በግብጻዊው እብን አብድ ኤል-ሀከም እና በፋርሳውያን አል-ታባሪና ሙሐመድ ቈንዳሚር መጻሕፍት ሲገኝ፣ ፒራሚዶች፣ እስፊንክስ ወዘተ. ሁሉ የተሠሩ ከጥፋ ...

                                               

ፈርዖን

ፈርዖን ማለት የጥንታዊ ግብጽ ንጉሥ ነው። ይህ ከግብጽኛ "ፐር-ዓ" ከ "ፐር" እና "ዓ" ወይም "ታላቁ ቤት" ደረሰ። ፐር-ዓ መጀመርያ ቤተ መንግሥት ለማመልከት ሲሆን፣ ከ1400 ዓክልበ. በኋላ ንጉሡን ፐር-ዓ ይሉት ጀመር። ስለዚህ ከዚያ በፊትም የነገሡት ግብጻዊ ንገሥታት ለምሳሌ በኦሪት ዘፍጥረት በአብርሐም፣ በዮሴፍ ወይም በሙሴ ዘመን የነበሩት ነገሥታት ደግሞ "ፈርዖን" ተብለዋል። ነገር ግን በታሪክ ላይ ፈርዖን የሚለው ማዕረግ ጥቅም ላይ የዋለው በጥንቱ የግብጽ መንግሥት ከ 2691-2625 ሳይሆን አሊያም በመካከለኛው የግብጽ መንግሥት ከ 2050-1710 ሳይሆን በአዲሱ የግብጽ መንግሥት በ 1570 ነው። ቁርኣንም ፈርዖን ማለት የጀመረበት በአዲሱ የግብፅ መንግሥት በሙሴ ዘመን ነው። ደግሞ ይዩ፦ የፈርዖኖች ዝርዝር

                                               

ፑርሽፐጊሪ ቪሃረ

ፑርሽፐጊሪ ቪሃረ በአሁኑ ኦዲሻ፣ ሕንድ ምናልባት ከ250 ዓክልበ. እስከ 1200 ዓም ግድም ድረስ የቆየ ቪሃረ ወይም የቡዲስም ገዳም፣ መቅደስና ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ነበር። ዛሬ የሚታወቀው በተለይ ከሥነ ቅርስ ፍርስራሽ ነው። የ "ፑርሽፐ-ጊሪ" ትርጉም ከሳንስክሪት "ፑርሽፐ" አበባ እና "ጊሪ" ተራራ፣ ኮረብታ ወይም "አበባማ ኮረብታ" ነው። በፑርሽፐጊሪ አጠገብ ባሉት ኮረብቶች ደግሞ ሦስት ሌሎች የተዛመዱ የጥንት ንዑስ ቪሃራዎች ፍርስራሶች በውስጡ አሉ፣ እነርሱም ላሊትጊሪ፣ ኡደየጊሪ፣ ረትናጊሪ ናቸው። ከሥነ ቅርስ የተነሣ ቪሃረው መጀመርያው የመሠረተው ንጉሥ አሾካ 277-240 ዓክልበ. እንደ ነበር ይታስባል። ለሕንድ የቡዲስም ጥናት ማእከል እስከ 1200 ዓም ያህል እንደ ቆየ ከቅርሶቹ ይመስላል፤ ልክ መቼ ወይም በማን ዕጅ እንደ ጠፋ ግን አይታወቅም። በታሪካዊ መዝገቦች ዘንድ ስለ ፑርሽፐጊሪ የሚጠቅሱ ሰነዶች ጥቂትና እርግጠኛ ያልሆኑ ናቸው። በተለይ በ630 ዓም ግድም የጎበኘው የቻይና ተጓዥ ሧንዛንግ አንድ "ፑሴጶቂሊ" የተባለ ተቋ ...

                                               

ፕሩሲያ

ፕሩሲያ ከ1517 እስከ 1939 ዓም ድረስ የጀርመን ድሮ ክፍላገር ነበር። ከዚያ በፊት ጥንታዊ ፕሩሲያ ከ500 ዓም ያህል በትውፊት ዘንድ ጀምሮ እስከ 1216 ዓም ድረስ የተገኘ አረመኔ አገር ሆኖ ነበር። ቋንቋቸው ጥንታዊ ፕሩስኛ የባልቲክ ቋንቋዎች አባል ነበር። ከ1216 እስከ 1275 ዓም ያህል ድረስ፣ ቴውቶኒክ ሥርዓት የተባለው የመስቀለኞች ሥራዊት በጦርነት አሸነፋቸው፣ በክርስትና እንዲጠመቁ አስገደዳቸውና መሬታቸውን ያዙ። አገሩ እስከ 1517 ዓም ድረስ ቴውቶኒክ ግዛት ተባለ። በ1517 ዓም በፕሮቴስታንት ተሃድሶ ንቅናቄ ዘመን፣ የቴውቶኒክ ግዛት አለቃ አልቤርት ዘፕሩሲያ የፕሮቴስታንት ሉተራን ቤተ ክርስቲያን ምዕመን ሆነና ከሮሜ ፓፓ ነጻነት ስለ አዋጀ፣ ግዛቱ ያንጊዜ የፕሩሲያ መስፍንነት ተባለ። ይህ በ "ቅዱስ ሮማዊ መንግሥት" ጀርመን ውስጥ ክፍላገር ነበረ። ፕሮቴስታንቶች ከብዙ አገራት በስደት ወደ ፕሩሲያ ፈለሱ፤ የክፍላገሩም ዋና ቋንቋ ጀርመንኛ ነበር። ጥንታዊ ፕሩስኛ በቀስ እየጠፋ ከ1700 ዓም በኋላ በሙሉ ተረሳ። የፕሩሲያ ...

                                               

1 ሳባ

1 ሳባ በጥንታዊ የኢትዮጵያ ነገሥታት ዝርዝር ዘንድ ከንጉሥ ሆርካም ቀጥሎና ከንጉሥ ሶፋሪድ አስቀድሞ ለ30 ዓመታት የኩሽ መንግሥት ንጉሥ ነበረ። የነገሠበት ዘመን በየምንጩ የሚለያይ ነው፤ ለምሳሌ በተክለጻድቅ መኩሪያ ዝርዝር ከ2375 እስከ 2345 ዓክልበ. ነበረ። በሌላ ቁጠራ ከ2094 እስከ 2064 ዓክልበ. ነገሠ። አለቃ ታዬ እንደ ጻፈው በ15ኛ ዓመቱ በግብጽና በሱዳን ላይ ረሃብ ስለ ጸና ከከነዓን ልጆች የሰማሪዎን ሳምሪ ተወላጅ ዋቶ እና ነገዱ ወይጦ ወደ ኩሽ ገቡ።

1 ስልማናሶር
                                               

1 ስልማናሶር

1 ስልማናሶር ከ1278 እስከ 1249 ዓክልበ. ድረስ ግድም የአሦር ንጉሥ ነበረ። "ስልማናሶር" የሚለው አጻጻፍ በኋላ ዘመን ከብሉይ ኪዳን ስለሚታወቀው ሞክሼ 5 ስልማናሶር ነው። ለዘመኑ 30 የሊሙ ዓመት ስሞች ሁላቸው ከሰነዶች ታውቀዋል።

1 ቱኩልቲ-ኒኑርታ
                                               

1 ቱኩልቲ-ኒኑርታ

1 ቱኩልቲ-ኒኑርታ ከ1249 እስከ 1213 ዓክልበ. ድረስ ያሕል የአሦር ንጉሥ ነበረ። በዘመኑ ምድር ከኬጥያውያን መንግሥት ያዘ፤ ከዚህም በላይ ኡራርቱን፣ ባቢሎንን፣ እንዲሁም እስከ ድልሙን አሁን ባሕረይን ድረስ አሸንፎ ለርሱ ግዛቶች እንደ ያዛቸው በጽሑፎቹ ጽፏል።

2 ሓኖ
                                               

2 ሓኖ

2 ሓኖ ወይም ሓኖ መርከበኛው ከ488 እስከ 448 ዓክልበ. የቀርታግና ንጉሥ ከመሆኑ በላይ ዝነኛ ተጓዥና መርከበኛ ነበረ። ስለ ዘመነ መንግሥታቸው ብዙ መረጃ የለም። ነገር ግን ያለን መረጃ የአፍሪካን ጠረፍ በመርከብ ጉዞ እንደ ዞረ የሚናገር ነው። በ478 ዓክልበ. ግድም ከ60 መርከቦች ጋራ ከጂብራልታር ወሽመጥ ውጭ ወደ አትላንቲክ ውቅያኖስ ገባ። በነዚህ መርከቦች 30.000 ሰዎች ሲኖሩ በአሁኑ ሞሮኮ ውስጥ 7 ቅኝ ከተሞች እንደ መሠረቱ ተጻፈ። ከዚያ አልፎ እስከ ጋቦን ድረስ እንደ ተጓዘ ይታስባል። በዚያ በአንድ ደሴት በግሪክ "ጎሪላይ" የተባለ በፍጹም ጠጉራምና አውሬ ጎሣ እንዳገኘ ጻፈ፤ ቆዳዎችንም ይዘው ወደ ቀርጣግና ተመለሱ። እነኚህ ሰዎች ሳይሆኑ ጦጣዎች እንደ ነበሩ ስለሚታመን፣ የጦጣ ወገን ስም "ጎሪላ" ከዚህ ታሪክ የተወሰደ ነው።

2 ናቡከደነጾር
                                               

2 ናቡከደነጾር

2 ናቡከደነጾር የባቢሎን ንጉሥ ነበረ። ናቡከደነጾር በመጽሐፍ ቅዱስ ተጠቅሶ የሚገኘው ንጉስ ነው። ኢየሩሳሌምን ከባቢሎንሁለት ጊዜ እንደወረረ በዚሁ መጽሐፍ ተጠቅሶ ይገኛል።

2ኛው ዓለማዊ ጦርነት
                                               

2ኛው ዓለማዊ ጦርነት

2ኛው ዓለማዊ ጦርነት ከ1932 ዓ.ም. እስከ 1937 ዓ.ም. ድረስ የተደረገ ታላቅ አለም አቀፍ ጦርነት ነበረ። በዚህ ጦርነት መጨረሻ የአክሲስ ሃያላት ማለትም ጀርመን፣ ጣልያንና ጃፓን ተሸነፉ። በጠቅላላ አለም ዙሪያ 70 ሚልዮን ሕዝብ በጦርነቱ ጠፉ። ከጦርነቱም በኋላ አሜሪካና የሶቭየት ኅብረት የዓለም ዋና ኃያላት ሆኑ። በሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት ዋናው ተዋናይ ሂትለር ነበር።

ሆሎኮስት
                                               

ሆሎኮስት

ሆሎኮስት ማለት በ2ኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ የአዶልፍ ሂትለር ወገን ናዚዎች በአይሁድና በሌሎች ያደረጉት እልቂት ነበር። ስያሜው በግሪክኛ /ሆሎካውስቶስ/ ትርጒሙ የተቃጠለ መስዋዕት ነው። ስድስት ሚሊዮን ያህል አይሁዶች ተገደሉ። በተጨማሪ ምናልባት አምስት ሚሊዮን ስላቮች ተገደሉ። በሂትለር ርዕዮተ አለም በመከተል ናዚዎቹ እነዚህን ዘሮች መጥፎዎች እንደ ነበሩ ይሉ ነበርና።

                                               

ሆርካም

ሆርካም በጥንታዊ የኢትዮጵያ ነገሥታት ዝርዝር ዘንድ ከንግሥት ነሕሴት ናይስ ቀጥሎና ከንጉሥ 1 ሳባ አስቀድሞ ለ29 ዓመታት የኩሽ ንጉሥ ነበረ። የነገሠበት ዘመን በየምንጩ የሚለያይ ነው፤ ለምሳሌ በተክለጻድቅ መኩሪያ ዝርዝር ከ2404 እስከ 2375 ዓክልበ. ነበረ። በሌላ ቁጠራ ከ2123 እስከ 2094 ዓክልበ. ነገሠ። አለቃ ታዬ እንደ ጻፈው ንጉሥ ሃር ሲለው በ15ኛ ዓመቱ በከነዓን አገር ላይ ረሃብ ስለ ጸና ከከነዓን ልጆች የአራዴዎን አርዋዲ ልጅ አይነር ወይም አናየር እና ሚስቱ ኤንቴላ ከከነዓን ወደ ኩሽ ገቡ። የቅማንት ብሔር ከነርሱ እንደ ተወለዱ ይተረካል።

                                               

ሉጋይድ ሉዋይግኔ

ሉጋይድ ሉዋይግኔ በአይርላንድ አፈ ታሪክ ከ67 እስከ 52 ዓክልበ. ድረስ የአየርላንድ ከፍተኛ ነጉሥ ነበር። የአይርላንድ ታሪኮች እንዳሉት የሉጋይድ ዘመን ለ፲፭ ዓመታት ቆየ። የላውድ አቆጣጠሮች 1014 ዓም ተቀነባብሮ በመከተል፣ ይህ ከ67 እስከ 52 ዓክልበ. ድረስ ይሆናል። በኋላ የታዩት ታሪኮች ግን ከዚያ በፊት ያደርጉታል።

                                               

ሉጋይድ ላይግዴክ

ሉጋይድ ላይግዴክ በአይርላንድ አፈ ታሪክ ከ510 እስከ 503 ዓክልበ. ግድም ድረስ የአየርላንድ ከፍተኛ ነጉሥ ነበር። አብዛኛው የአይርላንድ ታሪኮች እንዳሉት የሉጋይድ ዘመን ለ7 ዓመታት ቆየ። በተለይ የላውድ አቆጣጠሮች 1014 ዓም ተቀነባብሮ እና የድሮ አቆጣጠር በመከተል፣ ይህ ከ510 እስከ 503 ዓክልበ. ድረስ ይሆናል። በኋላ የታዩት ታሪኮች ግን ከዚያ በፊት ያደርጉታል።