ⓘ Free online encyclopedia. Did you know? page 9
                                               

አዲስ አበባ

አዲስ ፡ አበባ ወይም ባጭሩ "አዲስ" ፡ ተብላ ፡ የተሠየመችው ፡ እቴጌ ፡ ጣይቱ ፡ ኅዳር ፲፬ ፡ ቀን ፡ ፲፰፻፸፱ 1879 ፡ ዓ.ም. ፡ ፍልውሃ ፡ ፊን-ፊን ፡ ወደሚልበት ፡ መስክ ፡ ወርደው ፡ ሳሉ ፡ ከዚህ ፡ በፊት ፡ አይተዋት ፡ የማያውቋት ፡ አንዲት ፡ ልዩ ፡ አበባ ፡ አይተ ፡ ስለማረከቻቸው ፡ ቦታውን ፡ ‹‹አዲስ ፡ አበባ!›› ፡ አሉ ፡ ይባላል። አዲስ ፡ አበባ ፡ ኣዲስ ኣ ...

                                               

ፍኖተ ሰላም

የፍኖተሰላም ከተማ የምትገኘው በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምዕራብ ጎጃም ዞን ጃቢጠህናን ወረዳ ከአዲስ አበባ በ 387 ኪ.ሜ ከክልሉ ዋና ከተማ ባህርዳር ደግሞ 176 ኪ.ሜ ላይ ነው፡፡ አስትሮኖሚያዊ መገኛ ቦታዋም በ10º 41’ ሰሜን ላቲቲውድ እና 37º 16’ ምስራቅ ሎንግቲውድ ነው፡:1 ፍኖተ ሰላም በኢትዮጵያ ውስጥ በጎጃም እምብርት ላይ የምትገኝ ከተማ ...

                                               

መርካቶ

መርካቶ ገበያ ወይም አዲስ መርካቶ በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ ውስጥ በዋነኛነት አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ እና በአጎራባች አከባቢዎች የተካለለ ሠፊ ገበያ ነው። መርካቶ በአፍሪካ ሠፊው ገላጣ ገበያም ነው። በዚህም በብዙ ካሬ ኪሎሜትር በሚቆጠር መሬት ላይ ከ13.000 በላይ ሠዎችን በ7.100 የሚደርሡ የንግድ ሠቆች ውስጥ የያዘ እንደሆነ ይገመታል። በዚህ ገበያ ውስጥ በአብዛሃኛው ጊዜ ...

                                               

ንግድ

ንግድ በመሰረቱ እጅግ በጣም ጥንታዊ የሰው ልጆች እንቅስቃሴ ነው። ሰው ማንኛውንም የፈለገውን ቁሳቁስ ማሙዋላት የማይችል ስለሆነ የግድ በተሰማራበት ሙያ የሚያገኘውን የስራ ውጤት ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ነገር ግን እሱ ራሱ ማምረት የማይችላቸውን ነገሮች ለማግኘት ሲል የሚያካሄደው የምርቶች ልውውጥ ሂደት ነው። ደግሞ ይዩ፦ ምጣኔ ሀብት

                                               

ፔትሮሊየም

ፔትሮሊየም ወይም ክሩድ ዘይት በተፈጥሮ ከመሬት በታች የሚገኝ የተቀጣጣይነት ጸባይ ያለው ፈሳሽ ነው። የተገነባው ከውስብስብ የሀይድሮካርቦን እና ሌሎች ውህዶች ጥምረት ነው። የ "ክሩድ" እንግሊዝኛ፦ crude ማለት "ጥሬ" ዘይት የድፍድፍ ነዳጅ ዘይት በዓለም ውስጥ በብዛት የሚገዛና የሚሸጥ ፤ ጠቀሜታውም ከሃምሳ በመቶ በላይ የሆነውን በዓለም ላይ የሚገኝ የቤትና የመስሪያ ቤት፣ የፋብሪካና ...

                                               

ህይወት

ሕይወት ወይም ሂወት ሊባል ይችላል፣ ነገሮች ራሳቸውን ችለው እና የህይወት ክንውን አድርገው በራሳቸው እንዲኖሩ የሚያደርግ እና ህይወት ከሌላቸው እንዲለዩ የሚያደርግ ነው። ይህ ሁኔታ ሞት እስከሚከተል ድረስ ወይም ይህንን ሂደት እንዳያደርጉ እክል እስከሚገጥማቸው ድረስ ይቀጥላል። ሥነ-ህይወት የሚባለው የሳይንስ ዘርፍ ስለ ህይወት እና ህይወት ያላቸው ነገሮች የሚያጠና የትምህርት ዘርፍ ነው። ...

                                               

ባክቴሪያ

ባክቴሪያዎች ቅድመኑክለሳውያን ናቸው። ቅድመኑክለሳውያን ማለትም ፦ ኑክለስና ሌሎች በክርታስ የተሸፈኑ ክፍለ ህዋሳት የሌሏቸው መሆናቸው ከአርኬአዎች ጋር ያመሳስላቸዋል። እንደ ታዮማርጋሪታ ናሚቢየንሲስ እጅግ በጣም ጥቂት ወጣ ያሉ ዝርያዎች በስተቀር ባክቴሪያዎች በሙሉ ያለ ማይክሮስኮፕ የማይታዩ ደቂቅ ዘአካላት ናቸው።

                                               

ወንድ

ወንድ ወይም ተባዕት የአንድ ፍጥረት ጾታ ነው። ጾታ በሚለዩ ፍጥረታት ዘንድ የሴቷን እንቁላል ማዳበር የሚችሉ ሕዋሶችን የሚያመነጭ ፍጥረት ነው። ወንድ ሴት በሌለችበት በራሱ መራባት አይችልም። ወንድ እና ሴት የሚሉት ባሕርያት ለእንስሳት ብቻ ሳይወሰን ለተክሎች እና ለሌሎችም ፍጥረታት ይሠራል። ወንድ

                                               

ዝግመተ ለውጥ

የአንድ ሕይወት ያለው ማህብረሰብ የዘር ውርስ ባህሪይ ከትውልድ ወደትውልድ እየተቀየረ መሄዱ ዝግመተ ለውጥ ይባላል። ቻርለስ ዳርዊን ይህን ኩነት በማስተዋልና በሳይንሳዊ አመክንዮ አሰደግፎ በመተንተኑ የመጀመሪያው ሰው ነው። ዳርዊን በተጨማሪ የተፈጥሮ ምርጫ ባለው ኅልዮቱ ሕይወት ያላቸው ማህበረሰቦች ዝግመተ ለውጥ እሚያካሂዱት ምንም እንኳ በዘፈቀደ ስህተት እየፈጸሙ ቢሆንም፣ ተፈጥሮ እራሷ በ ...

                                               

ደቂቅ ዘአካላት

ደቂቅ ዘ አካላት ወይም በእንግሊዝኛ Microorganisms የሚባሉት በአጉሊ መነጽር ብቻ የሚታዩ ማለትም በባዶ ዓይን የማይታዩ አካላት ናቸው። የነዚህ አካላት ጥናት microbiology ይባላል። ይህም ጥናት የተጀመረው በአንቶን ቫን ሉዊንሁክ ሲሆን በ1675 እ.ኤ.አ. የራሱን የአጉሊ መነጽር ተጠቅሞ የመጀመሪያዎቹን ደቂቅ ዘ አካላት በማግኘቱ ነው። ዋቅላሚ የሚለው ቃል ከተለያዩ ስርወዘራ ...

                                               

ግብረ ስጋ ግንኙነት

ግብረ ስጋ ግንኙነት ወይም ሩካቤ ስጋ ማለት በሴትና በወንድ መካከል ለስሜት እርካታ የሚደረግ ግንኙነት ወይም ፍቅር መሥራት ነው። ይህም ለመባዛት ወይም ለመዋለድ አስፈላጊ ከመሆኑ በላይ የወሲብን እርካታዊ ፍላጎት ለማሟላት ሊሆን ይችላል። በሥነ ሕይወት ዘርፍ ሲታይ ወሲብ፣ የእንስትን ሴትን እና የተባእትን ወንድን ዘር በማዋሃድ ወይንም በማዳቀል፣ የፍጡራን ዝርያ species፣ ከአሮጌ ወደ ...

                                               

ፀጉር

ፀጉር በፕሮቲን የበለጸገ follicles ከተባለ የሰውነት ክፍል ማደግ የሚጀምር አካል ነው። ይህ አካል በተለይም ኬራቲን ከተባለው የፕሮቲን አይነት የተገነባ ነው። በአብዛሃኛው ጊዜ ፀጉር የአጥቢ እንስሳት መለያ ቢሆንም በአንዳንድ ነፍሳት ላይ ይታያል፤ ይህ ግን በሳይንስ ፀጉር አይባልም።

                                               

የሰበክ-ሁ ጽላት

የሰበክ-ኹ ጽላት ከጥንታዊ ግብጽ መካከለኛው መንግሥት ከ3 ሰኑስረት ዘመን በ1893 ዓ.ም. የተገኘ ቅርስ ነው አሁን የሚታየው በማንቸስትር ሙዚየም በኢንግላንድ ነው። ሰበክ-ኹ ወይንም ኹ-ሰበክ ከሰኑስረት ሥራዊት አንዱ መኮንን ወይም መቶ አለቃ እንደ ነበር ይገልጻል። ጽሑፉ ከሰበክ-ኹ መቃብር በአቢዶስ ነው የተገኘው። በጽሑፉ ውስጥ በከነዓን እና በኩሽ መንግሥት ላይ ስለ ተሳተፉባቸው ዘመቻ ...

                                               

የሻባካ ድንጋይ

የሻባካ ድንጋይ ከግብጽ አዲስ መንግሥት 25ኛ ሥርወ መንግሥት የደረሰ ቅርስ ነው። በዚህ ታላቅ ድንጋይ የተቀረጸው የሃይሮግሊፍ ጽሑፍ በኩሻዊው ንጉሥ ሻባካ ትዕዛዝ ትል ከበላ ከጥንታዊ ብራና እንደ ተቀዳ ይላል። ሻባካ የብራናውን ወረቀት በአንድ የሜምፎስ ቤተ መቅደስ አገኝቶት ቃሉ እንዳይጠፋ እንዲቀረጽ አዘዘ ይላል። ሆኖም በኋለኛ ዘመን ድንጋዩ እንደ ወፍጮ ተጠቅሞ ብዙ ሃይሮግሊፍ ጠፋ፤ ከ ...

                                               

ብራና መቅደስ

ብራና መቅደስ በሙት ባሕር ብራናዎች መኃል አንድ ነው። ይህ ብራና ጥቅል በ1948 ዓ.ም. በዋሻ ቢገኝም እስከ 1959 ዓ.ም. ድረስ በሊቃውንት አልተተረጎመም ነበር። የተጻፈው በዕብራይስጥ ሲሆን ስለቤተ መቅደስ የሚነኩ የእግዚአብሔር ትዕዛዛት ለሙሴ ይከትታል። በነዚህ ትእዛዛት የዘላለማዊ ቤተ መቅደስ ዝርዝሮች፣ ሥርዓቶችና ደንቦች ለሙሴ ይገለጻሉ። ሆኖም በታሪክ የእስራኤል ንጉስ ሰሎሞን ቤ ...

                                               

ናጋርጁነኮርንደ

ናጋርጁነኮርንደ በአሁኑ አንድረ ፕረደሽ፣ ሕንድ ምናልባት ከ90 እስከ 340 ዓም ግድም ድረስ የቆየ ቪሃረ ወይም የቡዲስም ገዳም፣ መቅደስና ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ነበር። ዛሬ የሚታወቀው በተለይ ከሥነ ቅርስ ፍርስራሽ ነው። የስሙ ትርጉም የናጋርጁነ ኮረብታ ቴሉጉኛ፦ ኮርንደ ነው። ናጋርጁነ የመሃያነ ቡዲስም ወገን ዋና ፈላስፋ ነበር። እርሱም በልማድ መሠረት በዚያው ቦታ ምናልባት እስከ 24 ...

                                               

ዘንዶ-ነብር

ዘንዶ-ነብር በጥንታዊ ግብፅ መንግሥት ዘመን በኩል መኳያ ሠሌዳዎች ላይ ብዙ ጊዜ የተቀረጸ የግሩም እንስሳ ነው። እነዚህ የኩል መኳያ ሠሌዳዎች ከፈርዖኖች አስቀድሞ እጅግ በጥንታዊ ታሪክ ዘመን ተሠሩ። ዘንዶ-ነብር ነብርን ይመስላል፤ ነገር ግን እንደ ነብር ያልሆነ በጣም የረዘመ አንገት አለበት። በተቀረጹት ስዕሎች፣ ለግብጻውያን ለመዳ ሆነው ሲያገለግሉ በልባብ ገመድ ሲመሩ ይታያሉ። የቀረጹዋ ...

                                               

የመንደሮቹ መኳያ ሰሌዳ

የመንደሮቹ መኳያ ሰሌዳ ከጥንታዊ ግብጽ የተገኘ ቅርስ ሲሆን፣ ኩልን ወዘተ. ለማደባለቅ ከተጠቀሙት ሠሌዳዎች አንድ ነው። የተሠራበት ዘመን 3100 ዓክልበ. አካባቢ መሆኑ ይታመናል። ይህም በፈርዖኖች ቅድመ-ዘመን ነበረ፤ በአባይ ወንዝ ሸለቆ የነበሩት ሀገራት በአንድ የግብጽ መንግሥት ገና ሳይዋሀዱ ማለት ነው። በሠሌዳው ፊት ላይ፣ በሦስት መስመሮች የሚራመዱ እንስሶች ከብት፣ አህያና ፍየል ይ ...

                                               

የማልታ-ቡረት ሥልጣኔ

የማልታ-ቡረት ሥልጣኔ በባይካል ሐይቅ ዙሪያ በሳይቤሪያ፣ ሩስያ የተገኘ ቅድመ-ታሪካዊ የሥነ ቅርስ ሥልጣኔ ነው። በዚህ ስፍራ በተለይ ከቀንደ መሬት ጥንት የጠፋ የዝሆን ዝርያ በመጣ በዝሆን ጥርስ ብዙ እቃዎችና ቅርጾች ተሠርተው ተገኝተዋል። በጥንት የሥፍራው ኗሪዎች ቀንደ መሬቱን ያደኑት አዳኞች ይሆናሉ። የአውሮፓና ምዕራባውያን ሊቃውንት እንደ ገመቱ ሥፍራው የተሰፈረው ከ22.000 እስከ 1 ...

                                               

የበለዓም ጽሑፍ

የበለዓም ጽሑፍ በሥነ ቅርስ በ1960 ዓ.ም. በዴር አላ፣ ዮርዳኖስ የተገኘ ጽሑፍ ነው። ጽሑፉ አራማያ በሚመስል ቋንቋ ሲሆን የቢዖር ልጅ በለዓም የነበየ ትንቢት ይናገራል። ይህ አረመኔ ነቢይ በመጽሐፍ ቅዱስ በተለይም ኦሪት ዘኊልቊ ምዕ. 22-24 ስለሚጠቀስ፣ በሙሴና በኢያሱ ዘመን እንደ ኖረ ስለሚባል፣ ይህ ጽሑፍ ለሊቃውንቱ ዕጅግ በጣም ቁም ነገር ይሆን ነበር። ይሁንና በብሉይ ኪዳን ከን ...

                                               

የብርሃን ልጆች ጦርነት በጨለማ ልጆች ላይ

"የብርሃን ልጆች ጦርነት በጨለማ ልጆች ላይ" በቁምራን ዋሻ ከተገኙት ከሙት ባሕር ብራናዎች አንዱ ነው። ምናልባት ከ165 ዓክልበ እና 40 ዓ.ም. መካከል ጽሕፈቱን የጻፈው ንቅናቄ አባላት ስለ መጨረሻው ዘመን ጦርነት የሠልፍ ትዕዛዙን እንደሚስጥ ያምኑ ነበር። በመጀመርያ ክፍል፣ የብርሃን ልጆች ከነ ሌዊ፣ ይሁዳና ብንያም ወገኖች በኤዶም፣ ሞዓብ፣ አሞንና በአሦር ኪቲም ላይ ጦርነት ያደርጋሉ ...

                                               

የናርመር መኳያ ሠሌዳ

የናርመር መኳያ ሠሌዳ ከጥንታዊ ግብጽ መጀመርያ ፈርዖን ወይም አምባ ገነን ከናርመር ዘመን የታወቀ ጥንታዊ ኩል መኳያ ቅርስ ነው። የኩል መኳያ ሠሌዳ በጥንታዊ ግብጽ መጀመርያ ኩልን ለዓይን ቆብ ኮስሞቲክ ለማዘጋጀት የጠቀመ እቃ ነበር። የኩል መኳያ ሠሌዶች የሚታወቁ በተለይ ከናርመር ዘመንና ከናርመር ጥቂት አስቀድሞ በሆነው ዘመን ብቻ ነው "ቅድመ-ሥርወ መንግስት" ፣ በንጉሥ ጊንጥ ዘመን ያ ...

                                               

የአክሱም ሐውልት

የአክሱም ሃውልት ወይም Rome Stele እየተባለ በተለምዶ የሚጠራው በኢትዮጲያ በአክሱም ከተማ የሚገኝ የአለማችን ረጅሙ ትክል የድንጋይ ሃውልት ነው። ይህ ሀውልት 1700 ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን የ24 ሜትር ርዝመት አለው። 160 ቶን የሚመዝነው ይኽው ግዙፍ ድንጋይ መሠረቱ አከባቢ ሁለት የሀሠት በር መሣይ ፍልፍሎች አሉት። የዚህ ሀውልት ጌጥ ይህ ብቻም አይደለም በያንዳንዱ ጎን የመስኮ ...

                                               

የጊንጥ ዱላ

የጊንጥ ዱላ የግብጽ ጥንታዊ መንግሥት ቅርስ ሲሆን በነቀን ከተማ የተገኘ ስብብር የዱላ ራስ ነው። ከበሀ ድንጋይ ተሠራ። በትልቁ ክፍል የተቀረጸው ትርዒት ንጉሥ ጊንጥ ስለሚያሳይ፣ ቅርሱ "የጊንጥ ዱላ" ተብሏል። ይህ "ንጉሥ ጊንጥ" ከፈርዖኖች ዘመን አስቀድሞ በግብጽ የነገሠ አለቃ መሆኑ ይታወቃል። ጥንታዊው መንግሥት በ "ሔሩ ወገን" እንደ ተመሠረተ ሁሉ፣ ዱላው በአረመኔው አምላክ በሔሩ ቤ ...

                                               

ማህፈድ

ሳተርን ፡ መሬት በምትገኝበት ማለትም ሚልክ ዌይ ተብሎ በሚጠራው ረጨት ወይም የከዋክብት ስብስብ ውስጥ የሚገኝ ፕላኔት ነው። ይህ ፕላኔት ከፀሐይ ባለው ርቀት 6ኛ ነው። ከበፊቱ ሜርኩሪ፣ ቬነስ፣ መሬት፣ ማርስ እና ጁፒተር የተባሉ ፕላኔቶች ይገኛሉ። ኸበስተኋላው ደግሞ ኡራኑስ፣ ነፕቲዩን እና ፕሉቶ የተባሉት ይገኛሉ።

                                               

ማርስ

ማርስ ወይም ቀይዋ ፈለክ ፡ መሬት በምትገኝበት ማለትም ሚልክ ዌይ ተብሎ በሚጠራው ረጨት ወይም የከዋክብት ስብስብ ውስጥ የሚገኝ ፈለክ ነው። ይህ ፈለክ ከፀሐይ ባለው ርቀት 4ኛ ነው። ከበፊቱ ሜርኩሪ፣ ቬነስ እና መሬት የተባሉ ፈለኮች ይገኛሉ። ኸበስተኋላው ደግሞ ጁፒተር፣ ሳተርን፣ ኡራኑስ፣ ነፕቲዩን እና ፕሉቶ የተባሉት ይገኛሉ። ይህ ፈለክ በዚህ ረጨት ውስጥ ከሚገኙ ፕላኔቶች በግዝፈቱ የ ...

                                               

ቢግ ባንግ

ቢግ ባንግ ወይንም ታላቁ ፍንዳታ በሳይንቲስቶች ዘንድ የመላው ዓለም መነሻ ኩነትን ይገልጻል ተብሎ የሚታመንበት ኅልዮት ነው። አጠቃላይ አንጻራዊነት የተባለውን የአልበርት አይንስታይን ሳይንሳዊ ቀመር በመጠቀም ከአሁን ከአለንበት ጊዜ ወደኋላ ስንምለስ አንድ ወቅት ላይ ዓለም በሙሉ ተጨምቆ፣ አንዲት ትንሽ እኑስ እንደነበር እንረዳለን። ይህ እኑስ በውስጡ ምንም አይነት አቶም፣ መዋቅርም ሆነ ቅ ...

                                               

ነፕቲዩን

ነፕቲዩን ፡ መሬት በምትገኝበት ማለትም ሚልክ ዌይ ተብሎ በሚጠራው ረጨት ወይም የከዋክብት ስብስብ ውስጥ የሚገኝ ፕላኔት ነው። ይህ ፕላኔት ከፀሐይ ባለው ርቀት 8ኛ ነው። ከበፊቱ ኣጣርድ፣ ቬነስ፣ መሬት፣ ማርስ፣ ጁፒተር፣ ሳተርን እና ኡራኑስ የተባሉ ፕላኔቶች ይገኛሉ። ኸበስተኋላው ደግሞ ትንሹ ፕሉቶ ይገኛል።

                                               

ኡራኑስ

ኡራኑስ ፡ መሬት በምትገኝበት ማለትም ሚልክ ዌይ ተብሎ በሚጠራው ረጨት ወይም የከዋክብት ስብስብ ውስጥ የሚገኝ ፕላኔት ነው። ይህ ፕላኔት ከፀሐይ ባለው ርቀት 7ኛ ነው። ከበፊቱ ኣጣርድ፣ ቬነስ፣ መሬት፣ ማርስ፣ ጁፒተር እና ሳተርን የተባሉ ፕላኔቶች ይገኛሉ። ከበስተኋላው ደግሞ ነፕቲዩን እና ትንሹ ፕሉቶ ይገኛሉ።

                                               

ኣጣርድ

ኣጣርድ ወይም ሜርኩሪ ፡ መሬት በምትገኝበት ማለትም ሚልክ ዌይ ተብሎ በሚጠራው ረጨት ወይም የከዋክብት ስብስብ ውስጥ የሚገኝ ፈለክ ነው። ይህ ፈለክ ከፀሐይ ባለው ርቀት ቅርቡ ነው። ከበስተኋላው ዘጠኙም ፈለኮች ማለትም ቬነስ፣ መሬት፣ ማርስ፣ ጁፒተር፣ ሳተርን ኡራኑስ፣ ነፕቲዩን እና ፕሉቶ ይገኛሉ።ሜርኩሪ ጠንካራ ፣ የብረት ሰልፋይድ የውጪውን ንጣፍ ፣ ጥልቀት ያለው ፈሳሽ ንጣፍ እና ጠንካ ...

                                               

ዘሃራ

ዘሃራ ወይም ቬነስ ፡ መሬት በምትገኝበት ማለትም ሚልክ ዌይ ተብሎ በሚጠራው ረጨት ወይም የከዋክብት ስብስብ ውስጥ የሚገኝ ፈለክ ነው። ይህ ፕላኔት ከፀሐይ ባለው ርቀት ሁለተኛ ቅርቡ ነው። ከበስተኋላው ሰባቱ ፈለኮች ማለትም መሬት፣ ማርስ፣ ጁፒተር፣ ሳተርን ኡራኑስ፣ ነፕቲዩን እና ፕሉቶ ይገኛሉ። ከፊቱ የምትገኘው ብቸኛዋ ፈለክ ኣጣርድ ናት። ዘሃራ የሚለው ስም ከአረብኛ "ዙህራ" ሲሆን ይህ ...

                                               

ጁፒተር

ጁፒተር ፡ መሬት በምትገኝበት ማለትም ሚልክ ዌይ ተብሎ በሚጠራው ረጨት ወይም የከዋክብት ስብስብ ውስጥ የሚገኝ ፕላኔት ነው። ይህ ፈለክ ከፀሐይ ባለው ርቀት 5ኛ ነው። ከበፊቱ ሜርኩሪ፣ ቬነስ፣ መሬት እና ማርስ የተባሉ ፈለኮች ይገኛሉ። ኸበስተኋላው ደግሞ ሳተርን፣ ኡራኑስ፣ ነፕቲዩን እና ፕሉቶ የተባሉት ይገኛሉ። ይህ ፈለክ በዚህ ረጨት ውስጥ ከሚገኙ ፈለኮች በግዝፈቱ የመጀመሪያውን ደረጃ ...

                                               

ጋሊልዮ

ጋሊልዮ ጋሊሊ ታህሳስ 15, 1564 – ጥር 8, 1642 የነበረ የጣሊያን ሥነ-ፈለክ አጥኝና ተመራማሪ ነበር። ጋሊልዩ በዘመኑ የራሱን አጉሊ መነጽር በመስራት ጨረቃ ተራራ እንዳላት፣ጁፒተር የተባለው ፈለክ ልክ እንደ መሬት የራሱ የሆኑ 4 ጨረቃወች እንዳሉት፣ ረጨቶች ከከዋክብት ስብስብ እንደተሰሩ፣ ፀሐይ ጥቁር ነጠብጣቦች እንዳሏት፣ ቬነስ ልክ እንደ ጨረቃ የተለያየ ቅርጽ በጥልቁ እንደምትይ ...

                                               

ፀሐይ

ፀሓይ በምድር ሥርዐተ-ፈለክ መኻል ያለች ኮከብ ናት። ምድር ሞላላ ቀለበት በሚመስል የዑደት ምሕዋር እየተጓዘች ፀሓይን ትዞራታለች። ሌሎች ሰማያዊ አካላትም፣ ፈለኮች፣ ፈለክ-አስተኔዎች፣ ጅራታም ከዋክብት እና ኅዋዊ ብናኞች በፀሓይ ዙሪያ ይዞራሉ። ምድር በፀሓይ ዙሪያ የምታደርገውን አንድ ዙር ጉዞ ለመጨረስ አንድ ዓመት ይፈጅባታል፤ ይህን ጉዞ ስታደርግም በገዛ ራሷ ዘንጎ ወይም ምሽዋር ዙሪያ ...

                                               

ሃይል (ፊዚክስ)

"ሃይል" የሚለው አርዕስት ወዲህ ይመራል። ተጨማሪ ትርጉሞችን ለማየት፣ ኃይልን ይመልከቱ። ሃይል በተፈጥሮ ህግጋት ጥናት ሲተረጎም ስራ የሚሰራበት ፍጥነት ማለት ነው። በሌላ አነጋገር ሃይል ማለት አቅም ካንድ ቁስ ወደሌላ የሚተላለፍበት ፍጥነት ወይም ደግሞ አንድ አይነት አቅም ወደ ሌላ አይነት የሚቀየርበት ፍጥነት ማለት ነው። የሃይል መለኪያ መስፈርት ዋት ነው። በሃይልና አቅም ልዩነት አለ ...

                                               

ልዩ አንጻራዊነት

ልዩ አንጻራዊነት በአልበርት አይንስታይን የተጻፈ፣ በ፲፱፻፭ ዓ.ም. ለህትመት የበቃ የተፈጥሮ ህግጋት ጥናት መጽሃፍና ርዕዮተ አለም ነው። ይህን ርዕዮተ አለም እንዲያዳብር እና እንዲያስፋፋ አይንስታይንን ከገፋፋው ዋናው ምክንያት በጊዜው የነበረው አጥጋቢ ያልሆነ የኮረንቲና ማግኔት ማዕብል ጽንሰ ሃሳብ ነበር። በአይንስታይን አስተያያት፣ በጊዜው የነበረው ርዕዮት የኮረንቲና ማግኔት ማዕበሉን ...

                                               

መፈንቅል

መፈንቅል የማይልመጠመጥ ጠንካራ እቃ ሲሆን ከ ደጋፊ ችካል ላይ በመቀመጥ ሸክምን ለማንሳት በሚደረገው ስራ ጉልበትን ለማባዛት ወይም ሸክሙ የሚሄደውን ርቀት ከፍል ለማድረግ የሚጠቅም ቀላል ማሽን ነው። የጥንቱ የግሪክ ሂሳብ ተመራማሪ የነበረው አርክሜድስ፣ የመፈንቅልን ጉልበት የማብዛት ጠባይ በማዳነቅ እንዲህ ብሎ ነበር የምቆምበት ቦታ ስጡኝ እንጂ፣ መሬትን በመፈንቅል አነሳታለሁ ። በጥንቱ ...

                                               

ምዕራፍ

ምዕራፍ ከአንድ መነሻ ነጥብ ተንስቶ መድረሻ ነጥብ ላይ የሚደርስ ከሁሉ መስመር በላይ በጣም አጭሩ ርቀት ነው። ስለሆነም ምዕራፍ፣ ምናባዊ ቀጥተኛ መንገድ ነው። የ ምዕራፍ ጨረር የዚያን ቀጥተኛ መስመር ርዝመትና አቅጣጫ ይወክላል። ብዙ ጊዜ ይህ ጽንስ ሃሳብ በተፈጥሮ ኅግጋት ጥናት ዘርፍ ተጠቃሚነትን ያገኛል። ፍጥነት፣ ፍጥንጥነትን ለማስላት ይህ ጽንሰ ሃሳብ አይነተኛ መሳሪያ ነው። D → = ...

                                               

ሞላ

ሞላ ማለት ተለጣጭ መሳሪያ ሲሆን የተንቀሳቃሽ አቅሞችን በማከማቸት ወደ እምቅ አቅም ይቀይራል። ሞላወች ብዙ ጊዜ ከጠነከረ አረብረት ይሰራሉ። በ#የሁክ ህግ መሰረት፣ በሞላ ላይ የሚያርፍ ጉልበትና የሞላው የርዝመት ለውጥ ተመጣጣኝ ናቸው። የዚህ ምጥጥን ውድር የሞላ ቋሚ ቁጥር በመባል ይታወቃል። ማለት የሞላው ቋሚ ቁጥር የሚሰላው በሞላው ላይ በሚያርፈው ጉልበት ሲካፈል በዚህ ጉልበት ምክንያት ...

                                               

ሥራ

ሥራ ፣ በተፈጥሮ ህግጋት ጥናት መሰረት፣ በጉልበት የሚተላለፍ አቅም መጠን ማለት ነው። የሥራ መለኪያ መስፈርቱ ጁል ይባላል። የሥራን ጽንሰ ሃሳብ ያገኘው ፈረንሳዊው ሂሳብ ተመራማሪ ጋስፓርድ ጉስታቭ ሲሆን በሱ ትርጓሜ ሥራ ማለት ጉልበት ሲባዛ በርቀት ነበር። ማለት ሥራ = ጉልበት X ርቀት. ግን ጉልበቱ በርቀቱ አቅጣጫ መሆን አለበት። ከላይ የጻፍነውን አባባል በቀላሉ በሂሳብ ቋንቋ ማስቀመ ...

                                               

ርቀት

የርቀት ሐሳብ ሁለት ዓይነት ስሜት አለው። በምሳሌ ለማየት፦ ሰለሞን ጠዋት ከቤቱ ተነስቶ 3 ኪሎ ሜትር ወደ ሥራ ቦታው ቢጓዝ እና ከሰዓት በኋላ ወደ ቤቱ ቢመለስ ፣ የተጓዘው ርቀት ስንት ነው? አንዱ መልስ፣ ሦስት ወደ ፊት፣ ሦስት ወደ ኋላ፤ በአጠቃላይ ስድስት ኪሎ ሜትር ነው። ይህ ዓይነት የርቀት ትርጓሜ "ርዝመታዊ ርቀት" ሲባል፣ ለዕለት ተለት ንግግር ጠቃሚ ቢሆንም በሥነ እንቅስቃሴ ጥ ...

                                               

ተዳፋት

ተዳፋት ከስድስቱ ቀላል ማሽኖች አንደኛው ሲሆን መጨረሻውና መጀመሪያው በተለያዩ ከፍታወች ከተቀመጠ ጠፍጣፋ ገጽታ ይሰራል። የዚህ ማሽን ዋና ጥቅሙ አንድን ከባድ እቃ በቀጥታ ከማንሳት በአንስተኛ ጉልበት ተመሳሳይ ስራን ለማከናወን በማስቻሉ ነው። እዚህ ላይ መረዳት ያለብን ምንም እንኳ አንስተኛ ጉልበት ብናወጣም ዕቃው የሚጓዝበት ርቀት ግን ቀጥታ ከማንሳት ይበልጣል። ባጠቃላይ መልኩ፣ ተዳፋት ...

                                               

አጠቃላይ አንጻራዊነት

አጠቃላይ አንጻራዊነት በ፲፱፻፲፭ ዓ.ም በአልበርት አንስታይን የታተመ አጠቃላይ የቁስ ግስበትን በጂዖሜትሪ የገለጸ መጽሃፍና ርዕዮት አለም ነው። በርግጥም በአሁኑ ዘመን የሚሰራበት ግስበትን ገላጭ የዘመናዊ ተፈጥሮ ህግጋት ጥናት አካል ነው። አጠቃላይ አንጻራዊነት የኒውተንን የግስበት ህግንና ልዩ አንጻራዊነትን በማዋሃድ የግስበትን አጠቃላይ ባህርይ በኅዋና ጊዜ ጥምር ጂዖሜትሪ የሚገልጽ ነው። ...

                                               

ውሻል

ውሻል ከቦታ ቦታ ይዘውት ሊዞሩ የሚችል ተዳፋት ነው። ዋና ጥቅሙም ሁለት እቃወችን ለመለየት ወይም አንድን እቃ ለመሰንጠቅ፣ ወይም እንደ ታኮ በማገልገል ነገሮች እንዳይንቀሳቀሱ ይረዳል። ለምሳሌ መጥረቢያ የውሻል አይነት ነው፣ ለእንጨት መሰንጠቂያ የሚያገለግሉ ሌሎች እጀታ የሌላቸው ውሻሎች አሉ። ምስማርና ሹካ ማንኪያም እንዲሁ የውሻል ማሽን አይነቶች ናቸው። አንድ ውሻል ቁመቱ አጭርና ውፍረ ...

                                               

ጉልበት

ለሥነ አካሉ፣ ጉልበት ሥነ አካል ይዩ። በተፈጥሮ ህግጋት ጥናት፣ ጉልበት ማለት የአንድን ቁስ ፍጥነት ለመቀየር የሚደረግ ማንኛውም ተጽዕኖ ማለት ነው። በቀላሉ ሲተረጎም ጉልበት ማለት ስበት ወይም ግፊት ሲሆን አንድን ነገር አርፎ ከተቀመጠበት የሚያንቀሳቅስ፣ እየተንቀሳቀስም ካለ ፍጥነቱን የሚቀይር ነው። ጉልበት ቬክተር ስለሆነ መጠን እና አቅጣጫ አለው። የጉልበት መለኪያ መስፈርት ኒውተን ነ ...

                                               

ጉብጠት

ጉብጠት አንድ መስመር ወይም ገጽታ ከቀጥተኛ መስመር ወይም ከጠፍጣፋ ጠለል የሚለይበትን መጠን የምንለካበት የሂሳብ ጽንሰ ሃሳብ ነው። ከዚህ አንጻር ጉብጠት ማለት በአንድ መስመር ላይ የሚያጋጥመን የአቅጣጫ ለውጥ በእያንዳንዷ የርዝመት መስፈርት ሲካፈል ማለት ነው። ቀስ ብሎ አቅጣጫው ከቀየረ፣ አንስተኛ ጉብጠት አለው እንላለን። አቅጣጫው በፍጥነት ከቀየረ ከፍተኛ ጉብጠት አለው እንላለን የጉብ ...

                                               

ግዑዝነት

ግዑዝነት ማለት ቁስ ነገሮች የሚገኙበት ፍጥነት እንዳይለወጥ የሚያደርጉት ተቃውሞ ነው። አካላት አርፈው ተቀምጠውም እንደሆነ ባሉበት እንዲሆኑ፣ በቀጥታ እየተጓዙም እንደሆነ፣ አቅጣጫቸውን ሳይቀይሩ ባሉበት ፍጥነት እንዲቀጥሉ ያላቸው ፍላጎት ወይም አዝማሚያ ግዑዝነታቸው ይባላል። ግዑዝነት የቁሶች ወይንም ግዝፈት ያላቸው ነገሮች ሁሉ ዋና መገለጫ ባህሪ ነው።

                                               

ፍጥነት

ፍጥነት በተፈጥሮ ህግጋት ጥናት ሲተረጎም አንድ ነገር ምዕራፉን የሚቀይርበትን መጠን መለኪያ ማለት ነው። በካልኩለስ የአነጋገር ዘይቤ ፍጥነት ማለት የአቀማመጥ ለውጥ ከጊዜ አንጻር ማለት ነው። ፍጥነት ቬክተር ስለሆነ መጠን ብቻ ሳይሆን አቅጣጫም ሊኖረው ይገባል። ከአቅጣጫው የተነጠለ የፍጥነት መጠን ጥድፈት ይባላል፣ የሚለካውም በሜትር/ሰኮንድ ወይም ሜ/ስ ነው። በተግባር እንግዲህ የአንድን ...

                                               

ሰርጌይ ብሪን

ሰርጌይ ሚካይሎቪች ብሪን Михайлович Брин) ሩሲያዊ-አሜሪካዊ ሲሆን ጉግልን በመፍጠሩ ይታወቃል። በሩሲያ የተወለደ ሲሆን፥ ብሪን ከላሪ ፔጅ ጋር ጉግልን ከመጀመሩ በፊት ኮምፒዩተር ሳይንስና ሒሳብ አጥንቷል። ብሪን ባሁኑ ጊዜ የጉግል ቴክኖሎጂ ፕሬዝዳንት በመሆኑ ወደ 14.1 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚገመት ገንዘብ አለው። ይህም ከዓለም 26ኛ እና ከአሜሪካ 12ኛው ሀብታም ሰው ያደ ...

                                               

አይሳክ ኒውተን

ሰር አይሳክ ኒውተን ከጃንዩዌሪ 4 ቀን 1663 እ.ኤ.አ. እስከ ማርች 31 ቀን 1727 እ.ኤ.አ. የኖረ እንግሊዛዊ የፊዚክስ፤ የሒሳብ፤ የስነ ክዋክብት፤ የስነ መለኮት፤ የተፈጥሮአዊ ፍልስፍና እና ጥንት የነበረው የአልኬሚ ምሁር ነበረ። ምናልባትም ኒውተን በጣም ከሚታወቅባቸው ነገሮች ውስጥ ሶስቱ የኒውተን ሥነ-እንቅስቃሴ ህጎች ፤ የኒውተን የግስበት ቀመር፤ ካልኩለስ ለተባለውን የሒሳብ ክ ...