ⓘ Free online encyclopedia. Did you know? page 25
                                               

አሦር (የሴም ልጅ)

አሦር በብሉይ ኪዳን ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 10 መሠረት ከኖኅ ልጆች መካከል የሴም ሁለተኛ ልጅ ነበረ። የጥንታዊ አሦር ሀገርና ሕዝብ አባት መሆኑ ይታመናል። በዘፍጥረት 10፡11 መሠረት ይህ አሦር ከሰናዖር ወጥቶ "ነነዌን፥ የረሆቦትን ከተማ፥ ካለህን፣ በነነዌና በካለህ መካከልም ሬሴንን ሠራ፤ እርስዋም ታላቂቱ ከተማ ናት።" አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ግን ከፊተኛው ቁጥር ከ10፡1 ...

                                               

ሃቢሩ

ሃቢሩ ወይም አፒሩ ከ1600-1150 ዓክልበ. መካከል በከነዓን ዙሪያ የተገኘ በብዙ አገራት መዝገቦች የተጠቀሱት ብሔር ናቸው። ብዙ ጊዜ እንደ ቅጥረኞች ወይም ወታደሮች ይገለጻሉ። 1465 ዓክልበ. ግ. - ፈርዖኑ 3 ቱትሞስ ሦስት ከተሞች በደቡብ ሊባኖስ ይዞ የሐቢሩ ዕደ-ጥበቦች እንዳገኘ ተዘገበ። 1188 ዓክልበ. ግ. - ኡጋሪት ከተማ በ "ባሕር ሕዝቦች" ወረራ ሲጠፋ፣ "ሃቢሩ" የጠቀሰ ...

                                               

አሞራውያን

አሞራውያን በጥንት ከኤፍራጥስ ወንዝ ወደ ምዕራብ የኖረ ሕዝብ ነበረ። "የማርቱ አገር" ከሁሉ ጥንታዊ በሆኑት ሱመራዊ ምንጮች ለምሳሌ በ ኤንመርካርና የአራታ ንጉሥ ወይም በኤብላ ጽላቶች ይጠቀሳል። ለአካድ ነገሥታት ደግሞ ማርቱ በአካድ ዙሪያ ከነበሩት አራት ሩቦች አንዱ ሲሆን ሌሎቹ 3 ሱባርቱ፣ ሱመርና ኤላም ነበሩ። ይህ ስያሜ ወደ ምዕራብ የሆኑት አገራት ሶርያና ከነዓን ይጠቀልል ነበር። ...

                                               

አቢሜሌክ

አቢሜሌክ በኦሪት ዘፍጥረት ዘንድ የፍልስጥኤማውያን ከተማ ጌራራ ንጉሥ ነበር። የስሙ ትርጉም "አባቴ ንጉሥ ነው" እንደ ሆነ ይታሰባል። መጀመርያው የሚጠቀሰው በምዕራፍ ፳ ሲሆን አብርሃም በጌራራ ንጉሥ አቢሜሌክ ግዛት እየኖረ ሚስቱ ሣራ እኅቴ ነች በማለት አቢሚሌክን እንዳታለለ ይወራል። ከዚህ በፊት ተመሳሳይ ታሪክ ስለ ሣራና የግብጽ ፈርዖን አለ። ከዚያ በኋላ በምዕራፍ ፳፮ ይስሐቅ ደግሞ በ ...

                                               

ከነዓን (የካም ልጅ)

ከነዓን በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት የካም ልጅና የኖህ ልጅ-ልጅ ነበረ። በዛሬው እስራኤልና ሊባኖስ ያለው አገር በጥንት ስለ ስሙ ከነዓን ይባል ነበር። የከነዓን በኩር ልጅ ሲዶን ሲሆን ሲዶና ከተማ እንደ ተመሠረተና የፊንቄ አባት እንደ ሆነ ተብሏል። እንዲሁም ኬጢ ወይም ኬጢያውያን፣ አሞራዊው ወይም አሞራውያን የተባሉት ሕዝቦች ከከነዓን ተወለዱ። ከዚህ በላይ ኢያቡሳውያን፣ ጌርጌሳውያን፣ ኤዊያው ...

                                               

ኬጥያውያን (መጽሐፍ ቅዱስ)

ኬጥያውያን ወይም "የኬጢ ልጆች" በመጽሐፍ ቅዱስ በከነዓን ከተገኙ ብሔሮች አንዱ ነበሩ። በአብርሃም ዘመን ኬጢያዊው ኤፍሮን የመቃብር ዋሻ በኬብሮን ለአብርሃም ሸጠ። ኤሳውም ከኬጢያውያን ሚስቶች እንዳገባ ይለናል። በመጽሐፈ ኢያሱ 1:4 "ከምድረ በዳው ከዚህም ከሊባኖስ ጀምሮ እስከ ታላቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ድረስ የኬጥያውያን ምድር ሁሉ እስከ ፀሐይ መግቢያ እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ ዳርቻ ...

                                               

ኲሰርሰቴም

ኲሰርሰቴም በብሉይ ኪዳን መጽሐፈ መሣፍንት 3:1-11 መሠረት ዕብራውያንን ለ8 ዓመት የገዛ የመስጴጦምያ ንጉሥ ነበር። በዚያ እንደሚዘገብ፣ ከኢያሱ ወልደ ነዌ መሪነት ካልተወሰነ ጊዜ በኋላ፣ ከእስራኤል ዙሪያ የቀሩት ሕዝቦች፦ ፍልስጥኤማውያን፣ ሲዶናውያን ፊንቄ እና ሌሎች የተረፉት የከነዓን አሕዛብ ፡ ይፈተኑዋቸው ነበር። ከኬጥያውያን፣ አሞራውያንና ከነዓናውያን ጋር ተጋብተው ወደ ጣኦታቸውም ...

                                               

ዐግ

ዐግ በብሉይ ኪዳን ዘንድ እስራኤላውያን በሙሴ መሪነት በኤድራይ ውጊያ እስካሸነፉት ድረስ የባሳን አገር አሞራዊ ንጉሥ ነበር። መጀመርያ ሲጠቀስ ኦሪት ዘኊልቊ እንደሚገልጽ፣ ይህ ውግያ ሌላውን አሞራዊ የሐሴቦን ንጉስ ሴዎንን ካሸነፉት ቀጥሎ ሆነ። "ተመልሰውም በባሳን መንገድ ወጡ፤ የባሳንም ንጉሥ ዐግ ከሕዝቡ ሁሉ ጋር በኤድራይ ይወጋቸው ዘንድ ወጣ። እግዚአብሔርም ሙሴን፦ እርሱንና ሕዝቡን ሁ ...

                                               

ዔግሎም

ዔግሎም በብሉይ ኪዳን መጽሐፈ መሣፍንት 3:12-30 መሠረት ዕብራውያንን ለ18 ዓመት የገዛ የሞዓብ ንጉሥ ነበር። ይህ በቅደም-ተከተል 1457-1439 ዓክልበ. ነበር። ከፈራጁ ጎቶንያል በኋላ እስራኤላውያን እንደገና ክፉ ስለ ሠሩ እግዚአብሔር ዔግሎምን አበረታባቸው ይላል። ከሞዓብ ጭምር የአሞንና የአማሌቅ ሰዎችን ሰብስቦ ነበር። እነዚህ እንደ ሞዓባውያንና ዕብራውያን ሁሉ ሴማዊ ነገዶች ነበ ...

                                               

የያሚና ልጆች

የያሚና ልጆች ከአሞራውያን ኻና አገር ሁለት ኗሪ ብሔሮች አንዱ ነበር። ሌላውም የስምኣል ልጆች ተባለ። በኒ-ያሚና በማሪ ዙሪያ፣ በበሊኽ ወንዝ ና ወደ ምዕራብ ከአሌፖ ደቡብ እስከ ቃቱ ድረስ ተገኙ። የማሪ ነገስታት ግን ከስምኣል ልጆች ጋር ተዘመዱና ብዙ ጊዜ ከበኒ-ያሚና ጋር ይታገሉ ነበር። በተለይ ነገሥታት ያህዱን-ሊም 1723-1707 ዓክልበ.፣ ያስማሕ-አዳድ 1694-1687 ዓክልበ. እ ...

                                               

2 አጉም

2 አጉም ካክሪሜ እንደሚታሠብ ከካሣውያን ነገሥታት መጀመርያው ባቢሎንን የገዛው ነበር ። ካሣውያን ለብዙ አመታት በቂ መዝገቦች ስላልጻፉ ይህ እርግጥኛ አይደለም። የኬጥያውያን መንግሥት ንጉሥ 1 ሙርሲሊ በ1507 ዓክልበ. ከአናቶሊያ ሐቲ ደርሶ ባቢሎንን በሙሉ አጠፋት፣ የጣዖቷንም የማርዱክን ሐውልት ዘርፎ ወደ ሐቲ ተመለሰ። ከዚህ በኋላ ባቢሎን "ካርዱኒያሽ" ተብላ በካሣውያን ብሔር እንደ ተ ...

                                               

3 ቴልጌልቴልፌልሶር

3 ቴልጌልቴልፌልሶር ከሚያዝያ ወር 753 ዓክልበ. ጀምሮ እስከ 735 ዓክልበ. ድረስ የአሦር ንጉሥ ነበረ። ዙፋኑን በመንፈቅለ መንግሥት ከመያዙ አስቀድሞ፡ ስሙ ፑሉ የተባለ የካልሁ አለቃ ነበረ። ይህም ፑሉ በአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ "ፎሐ" ተጽፎ ይገኛል። በ754 ዓክልበ. የአሦር ቤተ መንግሥት የተገኘበት ሠፈር ካልሁ በአመጽ ተያዘ። በድካሙ ንጉሥ 5 አሹር-ኒራሪ በደረሰው ብሔራዊ ሁከት መካ ...

                                               

3 ካሽቲሊያሽ

3 ካሽቲሊያሽ ከ1473 እስከ 1463 ዓክልበ. ግድም ድረስ የባቢሎን ካሣዊ ንጉሥ ነበረ። የ1 ቡርና-ቡርያሽ ልጅና ተከታይ ነበር። ባለፈው ቅርብ ጊዘ ውስጥ 2005 ዓም ግድም "ካሽቲሊያሽ የቡርና-ቡርያሽ ልጅ፣ የአጉምም ልጅ ልጅ" የሚል ጽላት ተገኝቷል። በዚህ ላይ አርእስቱ "የኤንሊል ጣዖት ሻካናክ አገረ ገዥ" ይባላል፤ ቢሆንም የካሣውያን ንጉሥ ሳይሆን አይቀርም። የያሙትባል ሰዎች ለኤን ...

                                               

ሃሙራቢ

ሃሙራቢ ከ1705 እስከ 1662 ዓክልበ. ድረስ የባቢሎን ንጉሥ ነበረ። አባቱ ሲን-ሙባሊት ማዕረጉን ከተወ በኋላ ወራሹ ሃሙራቢ የባቢሎንን መንግሥት ግዛት በሜስፖጦምያ በጦርነት አስፋፋ። ሃሙራቢ በተለይ የሃሙራቢ ሕገ ፍትሕ ስለሚባለው የ1704 ዓክልበ. ሕገ ፍትሕ ይታወቃል። ሕግጋቱ የተቀረጹ ቁመቱ 2.4 ሜትር በሆነ ድንጋይ ሲሆን በ1893 ዓ.ም. ለሥነ ቅርስ ተገኝቷል። ሃሙራቢ እንደ ሕግ ...

                                               

ማናማልቴል

ማናማልቴል የማርቱ ንጉሥ ኪሱራ በሚባል ከተማ-አገር በመስጴጦምያ ሲኖር ምናልባት ከ1836 እስከ 1805 ዓክልበ. አካባቢ ነገሠ። ከሥነ ቅርስ ሰነዶች ጥቂት መረጃ ይታወቃል። ማናማልቴል ለዘመናዊ መምህራን መጀመርያ የታወቀው በ1891 ዓ.ም. በታተመ የሥነ ቅርስ መጣጥፍ ነበር። ከባቢሎን መጀመርያ ነጻ ንጉሥ ከሱሙ-አቡም ዘመን አስቀድሞ በዙሪያው ግዛት እንደ ነበረው ታወቀ። ሊቃውንት በፊት ...

                                               

ሱሙ-አቡም

ሱሙ-አቡም ከ1807 እስከ 1793 ዓክልበ. ድረስ የባቢሎን መጀመርያ ንጉሥ ነበረ። በዚህ ወቅት የኢሲንና የላርሳ መንግሥታት ለሱመርና ለአካድ ላዕላይነት ሲወዳደሩ ብዙ ነጻ ከተማ-አገሮች ወደ ስሜን ተነሡ። ከነዚህ መካከል አንዱ ካዛሉ ሲሆን አሞራዊው ሱሙ-አቡም በ1807 ዓክልበ. ግድም የባቢሎን ነጻነት ከካዛሉ አዋጀ። ከዚህ በኋላ ከዓመት ስሞቹ ኢሊፕ የ "ማናና" መንግሥት ከተማ፣ ኪሽንና ...

                                               

ሳምሱ-ኢሉና

ሳምሱ-ኢሉና ከ1662 እስከ 1624 ዓክልበ. ድረስ የባቢሎን 7ኛ ንጉሥ ነበረ። አባቱን ሃሙራቢን ተከተለው። ለሳምሱ-ኢሉና ዘመን 38 ያህል የዓመት ስሞቹ ታውቀዋል። እንግዲህ በ9ኛው ዓመት 1654 ዓክልበ. ካሳውያንን እንዳሸነፈ ታውቋል። በሚከተለው ዓመት የላርሳ ገዥ 2 ሪም-ሲን በዓመጽ ተነሣ፣ ይህም አመጽ በመላው ሱመርና አካድ ተስፋፋ። ሳምሱ-ኢሉና ግን እስከ 1649 ዓክልበ. ድረስ ...

                                               

ሳምሱ-ዲታና

ሳምሱ-ዲታና ከ1538 እስከ 1507 ዓክልበ. ድረስ የባቢሎን ንጉሥ ነበር። የአሚ-ሳዱቃ ልጅና ወራሽ ሲሆን፣ ሳምሱ-ዲታና የባቢሎን የሃሙራቢ ሥርወ መንግሥት መጨረሻ ንጉሥ ነበረ። የዘመኑ አመት ስሞች ምንም ዘመቻ ስለማይጠቅሱ ሰላማዊ ዘመን ይመስል ነበር፣ ወደ ደቡቡ ግን የባሕር ምድር ሥርወ መንግሥት ንጉሥ ጉልኪሻር ከሳምሱ-ዲታና ጋር እንደ ታገለ በአንድ ታሪክ ጽላት ተቀረጸ። በ1507 ዓ ...

                                               

አሚ-ሳዱቃ

አሚ-ሳዱቃ ከ1559 እስከ 1538 ዓክልበ. ድረስ የባቢሎን ንጉሥ ነበረ። አባቱን አሚ-ዲታናን ተከተለው። ለአሚ-ሳዱቃ ዘመን 21 የዓመት ስሞቹ ታውቀዋል። እነዚህ የዓመት ስሞች ባብዛኛው ስለ አረመኔ መቅደስና ሥርዓት የሚነኩ ናቸው። ምንም ዘመቻ ስለማይጠቅሱ ስላማዊ ዘመን እንደ ሆነ ይመስላል። በ2ኛውና እንደገና በ10ኛው ዓመት የሕዝብ ዕዳዎች እንደ ሠረዘ ይላሉ። ለዚሁም የአዋጅ ሰነዱ ታ ...

                                               

ኡላም-ቡርያሽ

ኡላም-ቡርያሽ ከ1463 እስከ 1447 ዓክልበ. ግድም ድረስ የባቢሎን ካሣዊ ንጉሥ ነበረ። የ1 ቡርና-ቡርያሽ ልጅና የወንድሙ የ3 ካሽቲሊያሽ ተከታይ ነበር። "የቀድመኞች ነገሥታት ዜና መዋዕል" ABC 20 በተባለው ሰነድ እንዲህ ይላል፦ ኤዓ-ጋሚል፣ የባሕር ምድር ንጉሥ፣ ወደ ኤላም ሸሸ። ከሄደ በኋላ፣ ኡላም-ቡርያሽ፣ የካሽቲሊያሽ ወንድም፣ ካሣዊው፣ ሥራዊትን ሰብስቦ የባሕር ምድርን ያዘ። ...

                                               

የባሕር ምድር ሥርወ መንግሥት

የባሕር ምድር ሥርወ መንግሥት በቀድሞ ሱመር ከባቢሎኒያ መንግሥት ተለይቶ የተነሣ መንግሥት ነበር። በ1645 ዓክልበ. አካባቢ የኢሲን ከንቲባ ኢሉማ-ኢሊ በሃሙራቢ ልጅ በባቢሎን ንጉሥ ሳምሱ-ኢሉና ላይ በዓመጽ ተነሣና ሥርወ መንግሥቱን መሠረተ። ነገሥታት ሱመራዊ ስሞች ቢወስዱም፣ ያንጊዜ መደበኛ ቋንቋ አካድኛ እንደ ሆነ ይመስላል። በባሕር ምድር ሥርወ መንግሥት ውስጥ የሚከተሉት ነገሥታት ከአ ...

                                               

ሲሉራውያን

ሲሉራውያን በደቡባዊ ዌልስ ቢያንስ ከ30 ዓክልበ. ግድም ጀምሮ የተገኘ የብሪቶናውያን ነገድ ነበሩ። የሮማ ታሪክ ጸሐፊ ታኪቱስ በ90 ዓም እንደ ጻፈው፣ ሲሉራውያን ጥቁር ጥቅል ጽጉር ስላላቸው ትውልዳቸው ከእስጳንያ እንደ ደረሰ መሰለው። ወደ ስሜኑ በካሌዶኒያ ስኮትላንድ የነበሩ ኬልቶች ግን ስለ ቀይ ጽጉራቸው ይታወቁ ነበር። ሮማውያን ከ35 ዓም ጀምሮ ታላቅ ብሪታንያን ደሴት ከደቡብ ወረሩ፤ ...

                                               

የሷሶን ግዛት

የሷሶን ግዛት በስሜን ጋሊያ የተገኘና ከሮሜ መንግሥት ውድቀት በኋላ ትንሽ የቆየ የሮማውያን ግዛት ነበረ። የሷሶን መንግሥት መነሻ የሮሜ ንጉሠ ነገሥት ማዮሪያኑስ በ449 ዓ.ም. አይጊዲዩስን የጋሊያ አውራጃ ዋና አለቃ እንዲሆን በሾሙበት ወቅት ሆነ። በ5ኛው ክፍለ ዘመን የጀርመናውያን ብሔሮች ወደ ሮሜ ግዛት እየፈለሱ ነበር፣ በተለይም ቪዚጎቶች የተባለው ትልቅ ሕዝብ ለሮሜ ሰዎች እንደ ወታደ ...

                                               

ጎጆሰን

ጎጆሰን የጥንታዊ ኮርያ መንግሥት ነበረ። ግዛቱ በተለይ በዛሬው ስሜን ኮርያና ለዛ ቅርብ የሆነው የቻይና ክፍሎች ይጠቀለል ነበር። እስከ 116 ዓክልበ. ድረስ ቆይጦ ነበር። ዋና ከተማው አሳዳል ምናልባት የአሁኑ ፕዮንግያንግ፥ ወይም ሓርቢን በማንቹርያ ነበር። ይህ ለኮርያ የነሐስ ዘመን ነበር፣ መሣርያቸው ሁሉ ከነሐስ የተሰሩ ነበር። በመጀመርያው ንጉሡ ዳንጉን ዋንገም እንደ ተመሠረተ ይታመና ...

                                               

ሰውሃን

ሰውሃን ወይም ዉሰውሃን በኮርያ ልማዳዊ አፈ ታሪክ በጥንታዊ ኮርያ የነገሠ ንጉሥ ወይም "ዳንጉን" ነበር። እርሱ ከዳንጉን ሃንዩል መንግሥት ቀጥሎ ገዛ። በጠቅላላ ለ፰ ዓመታት ምናልባት 1778-1770 ዓክልበ. እንደ ነገሠ ይጻፋል። ከዚያ በኋላ አሱል ተከተለው። በ1903 ዓም. በኮሪይኛ የተዘጋጀው ዜና መዋዕል ኋንዳን ጎጊ ስለዚሁ አፈታሪካዊ ዘመን መረጃ ይሰጣል፤ ሆኖም በብዙ የኮርያ መምህ ...

                                               

ቡሩ

በ1903 ዓም. በኮሪይኛ የተዘጋጀው ዜና መዋዕል ኋንዳን ጎጊ ስለዚሁ አፈታሪካዊ ዘመን መረጃ ይሰጣል፤ ሆኖም በብዙ የኮርያ መምህሮች ዘንድ ይህ መጽሐፍ እንደ ትክክለኛ ታሪክ አይሆንም። ቡሩ ካደረጉት ሥራዎች መካከል ዋና ዋናዎቹ እንዲህ ናቸው፦ በ2042 ዓክልበ. ግድም ዳንጉን ዋንገም አልጋ ወራሹን ልዑል ቡሩ በተልእኮ ወደ ዩ ላከው፣ ይህ ምናልባት በኋላ ዳ ዩ የተባለው የኋሥያ ቻይና አለ ...

                                               

ታልሙን

ታልሙን በኮርያ ልማዳዊ አፈ ታሪክ በጥንታዊ ኮርያ የነገሠ ንጉሥ ወይም "ዳንጉን" ነበር። እርሱ ከዳንጉን ጉዕል መንግሥት ቀጥሎ ገዛ። ታልሙን ከጉዕል ፭ ሚኒስትሮች "ዉጋ" የተባለው ነበር። በጠቅላላ ለ፴፮ ዓመታትምናልባት 1865-1830 ዓክልበ. እንደ ነገሠ ይጻፋል። ከዚያ በኋላ ሃንዩል ተከተለው።

                                               

ኖዕል

ኖዕል በኮርያ ልማዳዊ አፈ ታሪክ በጥንታዊ ኮርያ የነገሠ ንጉሥ ወይም "ዳንጉን" ነበር። እርሱ ከዳንጉን አሱል መንግሥት ቀጥሎ ገዛ። በጠቅላላ ለ59 ዓመታት ምናልባት 1735-1676 ዓክልበ. እንደ ነገሠ ይጻፋል። ከዚያ በኋላ ዶሄ ተከተለው። በ1903 ዓም. በኮሪይኛ የተዘጋጀው ዜና መዋዕል ኋንዳን ጎጊ ስለዚሁ አፈታሪካዊ ዘመን መረጃ ይሰጣል፤ ሆኖም በብዙ የኮርያ መምህሮች ዘንድ ይህ መጽ ...

                                               

አሱል

አሱል በኮርያ ልማዳዊ አፈ ታሪክ በጥንታዊ ኮርያ የነገሠ ንጉሥ ወይም "ዳንጉን" ነበር። እርሱ ከዳንጉን ሰውሃን መንግሥት ቀጥሎ ገዛ። በጠቅላላ ለ35 ዓመታት ምናልባት 1770-1735 ዓክልበ. እንደ ነገሠ ይጻፋል። ከዚያ በኋላ ኖዕል ተከተለው። በ1903 ዓም. በኮሪይኛ የተዘጋጀው ዜና መዋዕል ኋንዳን ጎጊ ስለዚሁ አፈታሪካዊ ዘመን መረጃ ይሰጣል፤ ሆኖም በብዙ የኮርያ መምህሮች ዘንድ ይህ ...

                                               

ኦሳጉ

ኦሳጉ ወይም ኦሳ በኮርያ ልማዳዊ አፈ ታሪክ በጥንታዊ ኮርያ የነገሠ ንጉሥ ወይም "ዳንጉን" ነበር። እርሱ ከአባቱ ዳንጉን ካርግ መንግሥት ቀጥሎ ገዛ። በጠቅላላ ለ፴፰ ዓመታት ምናልባት 1919-1881 ዓክልበ. እንደ ነገሠ ይጻፋል። ከዚያ በኋላ ሚኒስትሩ ጉዕል ተከተለው።

                                               

ካርግ

ካርግ በኮርያ ልማዳዊ አፈ ታሪክ በጥንታዊ ኮርያ የነገሠ ንጉሥ ወይም "ዳንጉን" ነበር። እርሱ ከአባቱ ዳንጉን ቡሩ መንግሥት ቀጥሎ ገዛ። በጠቅላላ ለ፵፭ ዓመታትምናልባት 1964-1919 ዓክልበ. እንደ ነገሠ ይጻፋል። ከዚያ በኋላ ልጁ ኦሳጉ ተከተለው።

                                               

ዳንጉን ዋንገም

ዳንጉን ዋንገም በኮርያ ልማዳዊ አፈ ታሪክ በኮሪያ በጥንት የነገሠ ንጉሥ ነበር። እርሱ ከሺንሺ መንግሥት ቀጥሎ የአዲስ መንግሥት መሥራች ሆነ። የዚህ መንግሥት ስም "ጆሰን" ሲሆን፣ በኋላ ዘመን ሌላ "ጆሰን" የተባለ መንግሥት ስለ ኖረ፣ ዳንጉን የመሠረተው መንግሥት አሁን "ጥንታዊ ጆሰን" ወይም "ጎጆሰን" በመባል ይታወቃል። የፔዳል ወገንና የናቱ ወገን "የድብ ጎሣ" በውሕደታቸው የጆሰን ብ ...

                                               

ዶሄ

ዶሄ በኮርያ ልማዳዊ አፈ ታሪክ በጥንታዊ ኮርያ የነገሠ ንጉሥ ወይም "ዳንጉን" ነበር። እርሱ ከዳንጉን ኖዕል መንግሥት ቀጥሎ ገዛ። በጠቅላላ ለ57 ዓመታት ምናልባት 1676-1619 ዓክልበ. እንደ ነገሠ ይጻፋል። ከዚያ በኋላ አሃን ተከተለው። በ1903 ዓም. በኮሪይኛ የተዘጋጀው ዜና መዋዕል ኋንዳን ጎጊ ስለዚሁ አፈታሪካዊ ዘመን መረጃ ይሰጣል፤ ሆኖም በብዙ የኮርያ መምህሮች ዘንድ ይህ መጽ ...

                                               

ጉዕል

ጉዕል በኮርያ ልማዳዊ አፈ ታሪክ በጥንታዊ ኮርያ የነገሠ ንጉሥ ወይም "ዳንጉን" ነበር። እርሱ ከዳንጉን ኦሳጉ መንግሥት ቀጥሎ ገዛ። ጉዕል ከኦሳጉ ፭ ሚኒስትሮች "ያንጋ" የተባለው ነበር። በጠቅላላ ለ፲፮ ዓመታትምናልባት 1881-1865 ዓክልበ. እንደ ነገሠ ይጻፋል። ከዚያ በኋላ ታልሙን ተከተለው።

                                               

ሂክሶስ

ሂክሶስ በ1661 ዓክልበ. ግድም ከከነዓን ወጥተው ጥንታዊ ግብጽን የወረሩት አሞራውያን ወይም ከነዓናዊ ወገኖች ነበሩ። በስሜኑ ግብጽ የራሳቸውን 15ኛው ሥርወ መንግሥት እስከ 1548 ዓክልበ. ድረስ ያሕል መሠረቱ። በዚያን ጊዜ የደቡቡ ኗሪ ፈርዖን 1 አህሞስ ከግብጽ አስወጣቸው፤ አህሞስም የ18ኛው ሥርወ መንግሥትና የአዲስ መንግሥት መሥራች ሆነ። የሂክሶስ ስያሜ "ሄቃ ኻሱ" በግብጽኛ ማለት ...

                                               

ምጽራይም

ምጽራይም በ ኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 10 መሠረት ከኖህ ልጆች መካከል የካም ሁለተኛ ልጅ ነበረ። የምጽራይምም ልጆች ሉዲም፣ ዐናሚም፣ ላህቢም፣ ነፍታሌም፣ ፈትሩሲም፣ ከስሉሂምና ቀፍቶሪም ናቸው። የ "ሚጽራዪም" ትርጉም በዕብራይስጥ ደግሞ ግብጽ ምሥር አገር ነው። እንዲሁም በአረብኛ የአገሩ ስም مصر ምጽር ይባላል። ስሙ ዕጅግ የቆየ መሆኑ እርግጠኛ ነው። በአካድኛ መዝገቦች የግብጽ ስም "ሙሱ ...

                                               

ትምህርት ለመሪካሬ

ትምህርት ለመሪካሬ በመካከለኛ ግብጽኛ የተጻፈ ጽሑፍ ሲሆን በጥንታዊ ግብጽ ጨለማ ዘመን የነገሡት የሄራክሌውፖሊስ ፈርዖኖች የአገዛዝ ሰነድ ነው። የፓፒሩስ መጀመርያ ስለ ተቀደደ፤ የሚናግረው ንጉሥ ስም ጠፍቷል፤ "ለልጁ መሪካሬ" ማንበብ ተችሎ የግብጽ ንጉሥ መሪካሬ ከአባቱ የተቀበለው ትምህርት እንደ ሆነ ይመስላል። ይህ የትኛው ፈርዖን እንደ ነበር ለማለት አስቸጋሪ ነው፤ ነገር ግን በይዘቱ ...

                                               

አሌክሳንድር ሄሊዮስ

አሌክሳንድር ሄሊዮስ የግብጽ ንግሥት 7 ክሌዎፓትራና የሮማ መሪ ማርክ አንቶኒ ልጅ ነበረ። በ47 ዓክልበ. በእስክንድሪያ ተወለደ። መንታ እኅቱ 2 ክሌዎፓትራ ሰሌኔ ነበረች፣ የስሞቻቸውም ትርጉም በግሪክ "ፀሐይ" እና "ጨረቃ" ነበሩ። በ41 ዓክልበ. የሄሊዮስ ዕድሜ 5 አመት እየሆነ፣ ወላጆቻቸው አንቶኒና ክሌዎፓትራ በአንድ ታላቅ ሥነ ሥርዓት መንግሥታት ለልጆቻቸው ሰጡ። በዚህ አደራረግ በኩ ...

                                               

አንቅቲፊ

አንቅቲፊ በደቡብ ግብጽ በ1ኛው ጨለማ ዘመን የነቀን እና የበህደት ኖሞች ገዢ ነበረ። በዚያው ዘመን ከጤቤስ የራቁት ክፍሎች ወደ ደቡብም ሆነ ወደ ስሜን ከጤቤስ ፈርዖኖች ያመጹ ነበር። ስለዚህ አንቅቲፊ የጤቤስ መንግሥት ተጋጣሚ እና የ "ቀቲዎች" ወገን ደጋፊ ነበር። ይህ ምናልባት በጤቤስ ፈርዖን 1 አንተፍ ዘመን ይሆናል። የአንቅቲፊ ሕይወት ታሪክ በመቃብሩ ግድግዳዎች ስለ ተቀረጸ ይታወቃል ...

                                               

የሀረም ጽሕፈቶች

የሀረም ጽሕፈቶች በጥንታዊ ግብፅ መንግሥት ሀረሞች ውስጥ፣ በውስጣዊ ግድግዳዎች ላይ የተቀረጹ የሃይሮግሊፍ መዝሙሮች ናቸው። እነዚህ አረመኔ መዝሙሮች ከ2845 ዓክልበ. ግ. ጀመሮ ተጽፈው፣ እስከሚታስብ ድረስ ከዓለሙ መጀመርያው ሃይማኖታዊ ሰነዶች እነዚህ ናቸው። ጽሑፉ ሲተረጐም፣ የ "ሔሩ" ተከታዮች ወገን በ "ሴት" ተከታዮች ወገን ላይ የፈጸመውን ጨካኝ የጭራቅነት ሥነ ስርዓት የሚመሠክር ...

                                               

የቶሪኖ ፈርዖኖች ዝርዝር

የቶሪኖ ፈርዖኖች ዝርዝር ወይም በተለመደ የቶሪኖ ቀኖና ምናልባት 1250 ዓክልበ. ያሕል የተቀነባበረ የጥንታዊ ግብጽ ፈርዖኖች ዝርዝር ፓፒሩስ ነው። አሁን በቶሪኖ፣ ጣልያን ሙዚየም ይቆያል። ፓፒሩሱ በግብጽኛ በሂየራቲክ የተያያዘ ግብጽ ሃይሮግሊፍ ጽሕፈት በሌላ ሰነድ ጀርባ ላይ ተጽፈው ነበር። በ1812 ዓም ጣልያናዊ ተጓዥ ቤርናዲኖ ድሮቨቲ ፓፒሩሱን በሉክሶር ጤቤስ አገኘው። ፓፒሩሱ ግን በ ...

                                               

የአቢዶስ ሥርወ መንግሥት

የአቢዶስ ሥወ መንግሥት ምናልባት ከ1646-1596 ዓክልበ. ያሕል በአቢዶስ፣ ጥንታዊ ግብጽ የተመሠረተ መንግሥት ነበረ። ይህ በብዙዎች ዘመናዊ ሊቃውንት አስተሳሰብ ወይም መላ ምት ነው። በዚህ ዘመን ከአቢዶስ የገዙት ታስበው የአንዳንድ ፈርዖኖች ቅርሶች ወይም ጽላቶች ተገኝተዋል። በዚህ ዘመን የሂክሶስ ወይም 15ኛው ሥርወ መንግሥት ወደ ስሜን፣ የጤቤስ ወይም 16ኛው ሥርወ መንግሥት ወደ ደቡ ...

                                               

የግብጽ ሁለተኛ ማዕከለኛ ዘመን

የግብጽ ሁለተኛ ማእከለኛ ዘመን በጥንታዊ ግብጽ ታሪክ ከመካከለኛው መንግስት ቀጥሎና ከአዲሱ መንግሥት በፊት ወይም ከ1819 እስከ 1558 ዓክልበ. ድረስ የነበረው ጊዜ ነበር። በዚሁ ዘመን ግብጻውያን አገራቸውን ለራሳቸው ብቻ የያዙት ብቻ ሳይሆን ብዙ ሴማዊ ሕዝቦች አብረው ይገኙ ነበር። ከዚህ ዘመን በፊት ወይም በኋላ በመነጻጸር በመዝገቦች ጉድለት ምክንያት ዘመኑ ደግሞ ሁለተኛው የግብጽ ጨ ...

                                               

የግብጽ የቀድሞ ዘመነ መንግሥት

የግብጽ የቀድሞ ዘመነ መንግሥት በጥንታዊ ግብጽ ታሪክ በሰፊው እስከ 8ኛው ሥርወ መንግሥት መጨረሻ ድረስ የነበረበት ጊዜ ነው። በተለይ ከ3ኛው ሥርወ መንግስት እስከ 6ኛው ሥርወ መንሥስት መጨረሻ ድረስ ያለው ዘመን ወይም ከፈርዖን ነጨሪኸት እስከ 2 መረንሬ ድረስ በአሁኑ ሊቃውንት ዘንድ ጥንታዊው መንግሥት ወይም ብሉይ መንግሥት ተብሏል። ነገር ግን እነዚህ ሥርወ መንግሥታት አከፋፈል ጸሐፊው ...

                                               

ጌሤም

ጌሤም በብሉይ ኪዳን መሠረት በታችኛ ግብፅ በአባይ ወንዝ አፍ ሠፈር በዮሴፍ ዘመን የዕብራውያን መኖርያ ክፍላገር ሆነ። ዮሴፍ በኦሪት ዘፍጥረት ፵፭፡፲ የጌሤም ሠፈር ለአባቱ ያዕቆብ ቤተሠብ ሠጠው። ዕብራውያን በዚህ ዘመን በከነዓን ያደሩ ዕረኞች ነበሩ። ታላቁ የ፯ ዓመት ረሃብ በከነዓን በደረሰበት ዘመን የያዕቆብ ልጅ ዮሴፍ በግብጽ የፈርዖን ጥበበኛ ጠቅላይ ሚኒስትር ስለ ሆነ ወደዚያ አገር ...

                                               

የምዕራብ ንጉሥ እናት

"የምዕራብ ንጉሥ እናት" በቻይና አፈ ታሪክ ትገኛለች። በ ቀርከሃ ዜና መዋዕል ዘንድ፣ በንጉሥ ሹን ፱ኛው ዓመት 2052 ዓክልበ. ግድም መልዕክተኞች ከምዕራብ ንጉሥ እናት ሺ ዋንግሙ ወደ ሹን ግቢ መጥተው "የነጭ ድንጋይ ቀለበቶችና የዕንቁ የቀስተኛ ጣት ቤዛዎች" ስጦታ አቀረቡ። በሌላ ምንጭ ሹንዝዕ የሹን ተከታይ ዳ ዩ የሺ ዋንግሙ ተማሪ ነበረ። ከዚህ በኋላ በቻይና አረመኔ ሃይማኖት ሺ ዋ ...

                                               

ጉን

ጉን በቻይና አፈ ታሪክ ከኋሥያ ንጉሥ ያው መኳንንት አንዱ ነበር። ከዚህ ቀድሞ በኋሥያ የነገሠው ዧንሡ የጉን ቅድመ-አያት መሆኑ ይባላል። ያው የቾንግ አገረ ገዥ አደረገው፤ ይህም ቦታ ደብረ ሶንግ እንደ ሆነ ይታመናል። በያው ዘመን የቻይና ታላቅ ጎርፍ በወንዞቹ ጀመረ። ስለዚህ ያው ጉንን ልዩ ሚኒስትር እንዲሆን ሾመው። ግድብ በመሥራት ወንዞቹን እንዲያስተዳድራቸው አዘዘው። ትውፊቶች እንድሚ ...

                                               

ነመድ

ነመድ በአየርላንድ ልማዳዊ አፈ ታሪክ ዘንድ በአየርላንድ በጥንት የሰፈረ ንጉሥ ነበር። የነመድ ዘመድ ፓርጦሎን ወገን በቸነፈር ከሞተ 30 ዓመታት በኋላ የነመድ ወገን ከእስኩቴስ እንደ ደረሰ ይጻፋል። በነመድ ዘመን 4 ሐይቆች ከምድር መነጩ። ነመድ በሮስ ፍሬቃይን ውግያ የፎሞራውያንን አለቆች ጋንና ሰንጋንን ገደላቸው። አምባዎች በራይጥ ቂምባይጥና በራይጥ ቂንደይቅ እንደ ቆፈረ 12ም ሜዳዎች ...

                                               

ፓርጦሎን

ፓርጦሎን በአየርላንድ ልማዳዊ አፈ ታሪክ ዘንድ ከማየ አይኅ ጥቂት ክፍለ ዘመናት ቀጥሎ መጀመርያው በአይርላንድ ደሴት ላይ የደረሱት ሰፈረኞች መሪ ወይም ንጉሥ ነበር። የፓርጦሎን ስም በታሪክ መጻሕፍት መጀመርያው የሚታወቅ በ820 ዓ.ም. አካባቢ በሮማይስጥ በተጻፈው ሂስቶሪያ ብሪቶኑም "የብሪታንያውያን ታሪክ" ሊገኝ ይችላል። በዚሁ ጽሁፍ መሠረት፣ "ፓርጦሎሙስ" ከ1 ሺህ ሠፈረኞች ወንዶችና ...

                                               

ሄርኩሌስ ሊቢኩስ

ሄርኩሌስ ሊቢኩስ ወይም ሊብዩስ ጣልያናዊው መኖኩሴ አኒዩስ ዴ ቪቴርቦ በ1490 ዓ.ም. ባሳተመው ዜና መዋዕል ዘንድ፣ በጣልያን ሀገር የነገሠ ንጉሥ ነበር። በሮሜ አፈ ታሪክ ደግሞ የሄራክሌስ ስም "ሄርኩሌስ" ነበረ። በአኒዩስ ጽሑፍ መሠረት፣ ሄርኩሌስ የኦሲሪስ አፒስ ልጅ ነበር። አባቱ ኦሲሪስ የግብጽ ፈርዖን ሲሆን በ2003 ዓክልበ. ግድም በቲፎን ተገደለ። ልጁ ሄርኩሌስ ግን የአባቱን ቂም ...