ⓘ Free online encyclopedia. Did you know? page 22
                                               

መሃመድ አማን

መሐመድ አማን በመካከለኛ ርቀት በተለይ በ፰ መቶ ሜትር የሩጫ ውድድር የሚሳተፍ ኢትዮጵያዊ ነው። በሐገራችን አቆጣጠር ጥር ፪ ቀን ፲፱፻፹፮ ዓ.ም በአሰላ ከተማ የተወለደው መሃመድ እ.ኤ.አ በ2009 እና 2011 የአፍሪካ ታዳጊ አትሌቶች ውድድሮች ላይ በ800 ሜትር አሸናፊ መሆን ችሎ ነበር። በለንደን ኦሎምፒክስ ተሳትፎ የነበረው መሃመድ ሁለት ዙር ማጣሪያዎችን አልፎ ለፍጻሜ ውድድር በማለፍ ...

                                               

ሮቤል ተክለማርያም

ሮቤል ተክለማርያም በ1998 በዊንተር ኦሊምፒክስ በስካይ ኢትዮጵያን የወከለ ብቸኛና የመጀመሪያ ሰው ከመሆኑም በላይ በዊንተር ኦሊምፒክስ ጨዋታዎች አፍሪካን የወከለ መጀመርያው ስፖርተኛ ነው። ሮቤል በ9 አመቱ ወደ አሜሪካ ቢመጣም አገሩን በጣም ይወዳል። እስከዛሬ ድረስም አማርኛን አቀላጥፎ ይናገራል፡ ሮቤል በጣሊያኑ ኦሊምፒክ በውጭ አገር የሚኖሩት ኢትዮጵያውያን ባደረጉለት ከፍተኛ ማበረታት ...

                                               

ቀነኒሳ በቀለ

በኦል አፍሪካንስ ጌም የ 1ወርቅ በወርልድ ክሮስ ካንትሪ የ 11ወርቅ የ 1ብር በአፍሪካ ሻምፕዮና የ 2ወርቅ በኦሎምፒክ የ 3ወርቅ የ 1ብር በወርልድ ሻምፕዮን የ 5ወርቅ የ 1ነሃስ በወርልድ የቤት ውስጥ ሻምፕዮን የ 1ወርቅ ሜዳሊያዎች ባለ ክብር

                                               

በላይነህ ዴንሳሞ

አትሌት በላይነህ ዴንሳሞ ሠኔ 28 June ቀን 1965 እ.ኤ.አ. በሲዳሞ ተወለደ። ይህ በኢትዮጵያ የቀድሞው የረጅም ርቀት እና በማራቶን ልዩ ብቃት አትሌት በ1996 እ.ኤ.አ. በተደረገው የበጋ ኦሎምፒክሱ ላይ ሀገሩን ኢትዮጵያን ወክሎ አዲስ የአለም ሪከርድን አስመዝግቧል። ነገር ግን የማራቶን ውድድሩን መጨረስ አልቻለም ነበር። እሱ በማራቶን የሰበረው ሪከርድ ለ10 አመታት ማለትም ከ198 ...

                                               

አበበ ቢቂላ

ሻምበል አበበ ቢቂላ ለኢትዮጵያና ጥቁር አፍሪቃ የመጀመሪያውን የኦሊምፒክ ማራቶን ወርቅን ከዓለም ክብረ ወሰን ጋር ያስገኘ ኢትዮጵያዊ ከመሆኑም ሌላ በሮማ የኦሊምፒክ ውድድር በባዶ እግሩ ሮጦ በማሸነፉ፤ በተከታዩ የቶክዮ ኦሊምፒክ የራሱን የዓለም ክብረ ወሰን በማሻሻል ለሁለተኛ ጊዜ የወርቅ ሜዳይ በመሸለሙ ታሪካዊና ዝነኛ ለመሆን አብቅቶታል።

                                               

ጥሩነሽ ዲባባ

ጥሩነሽ ዲባባ ቀነኔ የተወለደችው ከአባትዋ ከአቶ ዲባባ ቀነኔ እና ከእናትዋ ከወይዘሮ ጉቱ ቶላ በመስከረም 21 ቀን 1978 ዓ.ም. በኢትዮጵያ በአርሲ ክፍለ ሀገር በቼፋ ወረዳ ከኦሮሞ ብሄረሰብ ነው። ጥሩነሽ ለቤተሰብዋ ከአምስት ልጆች ሶስተኛዋ ናት። የጥሩነሽ ዲባባ አስተዳደግ ከሌሎች አትሌቶች ትንሽ ለየት ያለ ነው። ይሀውም ትምህርት ቤት ለመሄድ መሮጥ አልነበረባትም። ምክንያቱም ትምህርት ...

                                               

ዳሪዎስ ሞዲ

ከፐርሺያ የሚሳብ የዘር ግንድ ያላቸው በዜግነት እንግሊዛዊ በትውልድ ሕንዳዊ አባቱና ከኢትዮጵያዊት እናቱ በአዲስ አበባ ከተማ ራስ መኰንን ድልድይ አካባቢ በ1938 ዓ.ም.የተወለደው ዳርዮስ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ያጠናቀቀው በዳግማዊ ምኒልክ ትምህርት ቤት ነበር፡፡ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ትምህርቱን መከታተል ቢጀምርም በወቅቱ በነበረው የተማሪዎች ንቅናቄ ሳቢያ የቅርብ ...

                                               

ማሲንቆ

የመሰንቆን ከየት መጣ በቅጡ ለመረዳት አዳጋች ቢሆንም በአንድአንድ የምዕራብ አፍሪካ እና መካከለኛ ምሥራቅ ሀገራት በድምጽ የሚመሳሰሉ አካላዊ ቅርጻቸው ግን ልዩነት ያላቸው መሣሪያዎች አሉ። መሰንቆ በቤተ መንግሥት መኳንንትን ለማስደሰት፣ ጦርነት የሆነ እንደሆነ ደግሞ ወታደሩን በስሜት ለመቀስቀስ ይጠቀሙበት ነበር። በማዕረግ ደረጃም ሊቀ መኳስ በሚል ስያሜ ሹመት ይሰጣቸው ነበር። ለምሳሌ ያህ ...

                                               

በገና

በገና በተወጠሩ ክሮች የሚሰራ የኢትዮጵያ የሙዚቃ መሳሪያ ነው። በገና ሌላው ስሙ በግዕዝ እንዚራ ተብሎ ይጠራል። ቁመቱ ረዘም ገበታው ሰፋ ያለ ከ 90 ሳንቲ ሜትር እስከ 140 ሳንቲ ሜትር ርዝመት ያለውና 10 ጅማቶች ያሉት ጥንታዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የመንፈሳዊ መሳርያ ነው።

                                               

የኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ መሣሪያዎች

እነዚህ መሣሪያዎች ድምጽ የሚሰጡት በንዝረት ነው። ዱል፡ በጋምቤላ የሚገኝ የጅማት መሣሪያ ነው። በገና፡ መንፈሳዊ ዜማዎችን ለማዜም በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ የሙዚቃ መሣሪያ ነው። ክራር፡ ይህ የጅማት የሙዚቃ መሣሪያ ለአያሌ ዓመታት ለደስታ፣ ለትካዜ፣ ለፍቅርና ለቀረርቶ ስንጠቀምበት የቆየ መሣሪያ ነው። ዲታ፡ በሲዳሞ የሚገኝ የጅማት መሣሪያ ነው። መሰንቆ ማሲንቆ፡ በተለይ በሰሜን ኢትዮጵያ ...

                                               

ገብረ ክርስቶስ

ገብረ ክርስቶስ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ከአለት የተፈለፈ ቤተ ክርስቲያን ነው። ገብረ ክርስቶ በሌላ ስሙ አብዱል መሲህ - የቆንስታቲኖፕሉ ንጉስ ቲወዲሰይስ ልጅ የነበረ ጻድቅ ነው። የዚህ ጻዲቅና መባዓ ጽዮን የተባለው የኢትዮጵያ ጻዲቅ ገድሎች ተከለ ሃይማኖት በተባለ ሃብታምና ሚስቱ ወለተ ጽዮን አነሳሽነት ምክሖ ጊዮርጊስ በተባለ ፀሐፊ በአንድ መጽሃፍ እንዲጻፉ ተደረገ። ይህ መጽሐፍ እጅግ ...

                                               

ለማ ገብረ ሕይወት

ለማ ገ/ሕይወት በ፲፱፻፲፰ ዓመተ ምሕረት በቡልጋ፣ ኮረማሽ ልዩ ስሙ ሰንበሌጥ ማርያም ነው የተወለደው። የቄስ ትምህርቱንም እዚያው ቡልጋ ውስጥ የከሰምን ወንዝ ተሻግሮ መስኖ ማርያምተከታትሏል። በጠላት ወረራ ጊዜ ጥሩ ድምጸኛ በመሆኑና በአካባቢው ሽለላ፣ ቀረርቶ እና ፉከራ የሚችለው እንዳልነበር የሚነገርለት ለማ፣ አርበኞችን እየዘፈነ እየሸለለ ያዝናና እና ያበረታታ እንደነበር ተዘግቧል። ለማ ...

                                               

ሐመልማል አባተ

ሐመልማል ያደገችው አሰበ ተፈሪ ሲሆን ሙያዋን የጀመረችው በቤተ ክርስትያን ዘማሪ ሆና ነው። የመጀመሪያው አልበሟ የወጣው በ፲፱፻፸፮ ዓ.ም. ነው። ሐመልማል አባተ የሁለት ሴት ልጆች እናት ናት። ግንቦት ፲፫ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. በመካኒሳ መንገድ አቦ ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ የሚገኘው የአርቲስት ሐመልማል ቪላ ቤት በእሳት ቃጠሎ የወደመ ሲሆን የቃጠሎው መንስኤ ወደ ቤቱ የሚመጣው የኤሌክትሪክ ...

                                               

መሐሙድ አህመድ

ማህሙድ አህመድ እና የሙዚቃ ህይወቱ የተወለደው ሚያዚያ 30, በ1933 ዓ.ም. አዲስ አበባ መርካቶ በአሜሪካን ግቢ አካባቢ ነው፡፡ ሥራንም ሆነ ሕይወትን በራሱ መጋፈጥ የጀመረው ገና በሕፃንነቱ ነው፡፡ አባቱ በሚሠራበት ግሪክ ክለብ አብሮ በመሔድ ቅርጫት ኳስና የቴኒስ ሜዳዎቹ ላይ ይሠራም ነበር፡፡ በስድስት ዓመቱም ሊስትሮ ሆኖ መሥራት ጀመረ፡፡ በትምህርት ቤት ቆይታው ብዙ ጐበዝ እንዳልነበ ...

                                               

መርዓዊ ዮሐንስ

መርዓዊ ዮሐንስ ተወልዶ ያደገው አዲስ አበባ ውስጥ ሲሆን ወደ ሙዚቃ ዓለም የገባው የስምንት ዓመት ልጅ እያለ ነው። ወለጆቹ በትምህርቱ እንዲተጋ በማሰብ በቀድሞው አስፋወሰን ትምህርት ቤት አስገብተውት ነበር። ሆኖም መርዓዊ በዚያን ዘምን ቀደምት የነበሩትን ድምጻውያን በተለይም የጥላሁን ገሠሠን የምኒልክ ወስናቸውንና የግርማ ነጋሽን ድምጽ በሬዲዮ በሚያዳምጥበት ወቅት በስሜት አብሯቸው ይመንን ...

                                               

መስፍን ኃይሌ

መስፍን ኃይሌ ዝነኛ ኢትዮጵያዊ ዘፋኝ ነው። መስፍን ኃይሌ በሐረርጌ ከተማ ተወልዶ ያደገ ሲሆን ከዚያም ወደ ዝቋላ መጥቶ የቄስ ትምህርት ተምሮ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት የክብር ዘበኛ ሠራዊት ባልደረባ በመሆን ከ፲፱፻፵፫ እስከ ፲፱፻፵፱ ዓ.ም. ድረስ እያገለገለ በመጠኑ ያንጎራጉር ነበር። በ፲፱፻፶ ዓ.ም. እንደገና የፖሊስ ባልደረባ በመሆን የቲያትርና የሙዚቃ ክፍል አባል ሆኖ በድምፃዊነቱ ...

                                               

ሙሉቀን መለሰ

ሙሉቀን መለስ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ወርቃማ ዘመን ዘፋኖች መሃል አንዱ ነው። 1960 ና 1970ዎቹ በርካታ ዘመናዊ ዘፋኞች የታዩበት ወቅት ነበር። ሙሉቀን መለስን ለየት የሚያደርው ቢኖር ባሀላዊውን ከዘመናዊው በማዋሃድ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ለማሳደግ ያደረገው ጥረት ነው። ሙሉቀን መለስ ባሁኑ ጊዜ በአሜሪካን አገር በዋሽንግተን ዲሲ ሙሉ ጊዜ የፕሮቴስታንት ሃይማኖት አገልጋይ ሲሆን ያለውን ድንቅ ች ...

                                               

ሚካያ በሀይሉ

ሚካያ ከእናቷ ከወይዘሮ ሙሉ እመቤት ፀጋዬ እና ከአባቷ አቶ በሀይሉ ገለታ ግንቦት ፳፪ ቀን ፲፱፻፷፱ ዓ.ም. አዲስ አበባ ቄራ አካባቢ ተወልዳ ያደገች ስትሆን ከአምስት ልጆች የመጀመሪያ ናት። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቷን በቤተልሄም 1ኛ ደረጃ የህዝብ ት/ቤት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን ደግሞ በአብዮት ቅርስ ት/ቤት ተከታትላለች። ሚካያ ግጥም መድረስ የጀመረችው በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ...

                                               

ሜሪ አርምዴ

ሜሪ አርምዴ ---------------- - ቤተሰቦቿ ያወጡላት ስም ሜሪማ የሚባል እንደነበር ይነገራል፡፡ ኋላ ላይ ዘመናዊነትን ስትነግሥበትና ፒያሳን ስትደምቅበት በራሷ ጊዜ ስሟን ሜሪ ብላ አስተካከለቸው፡፡ - ሜሪ የተወለደችው በ1915 ዓ. ም. በአዲስ አበባ ከተማ ዶሮ ማነቂያ ከሚባለው ሰፈር ነው፡፡ - ቤተሰቦቿ ፈረንሳይኛን የተማሩ ሲሆኑ በፈረንሳይ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ውስጥ ይሰሩ እንደ ...

                                               

ምኒልክ ወስናቸው

በአዲስ አበባ ከተማ ተወልደው ሐረርጌ ያደጉት ምኒልክ ወስናቸው የ፪ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አጋምሰው ለ፭ ዓመታት ያህል በፈረንሣይ ትምህርት ቤት ካጠኑ በኋላ በ፲፰ ዓመት ዕድሜያቸው በቀ.ኃ.ሥ. ቲያትር ቤት በድምፃዊነት ተቀጠሩ። ምኒልክ የመድረክ ላይ ጧፏቸውን "አልማዝ እያሰብኩሽ" በሚል ምርጥ ዜማ ካበሩ በኋላ በአጭር ጊዜ ውስጥ ፋጣን የሆነ የኪነ ጥበብ ሰውነታቸውን በማስመስከር አንቱ ከ ...

                                               

ሰሎሞን ተካልኝ

ሰሎሞን ተካልኝ አቋም የለለው ፖለቲከኛ ዘፋኝ ከመሆኑ በፊት ከተዋጣላቸው ኢትዮጵያዊያን ዘፋኞች አንዱ ነበር። ሰሎሞን በተለይ በ70ዎቹ ውስጥ "ወደድ ወደድ" የተባለው ዘፈኑ ነበር ወደ እውቅና ብቅ ያረገው። ሰሎሞን ኢሕአዴጎች ኢትዮጵያን እንደተቆጣጠሩ በስደት ወደ አሜሪካን አገር ሎሳንጀለስ ከተማ ከመጣ በኋላ "ሁሉም ዜሮ ዜሮ" የሚል ዘፈኑን አውጣና ታዋቂነቱን አተረፈ። ከዚያም ጊዜ ጀምሮ ...

                                               

ሳህሌ ደጋጎ

ኮሎኔል ሣህሌ ደጋጎ ከእናታቸው ከወይዘሮ ደጊቱ ፈይሣ እና ከባላንባራስ ደጋጎ አለቤ አብራክ በ1923 ዓ/ም በምዕራብ ወለጋ ልዩ ስሙ ነጆ ከተባለው ሥፍራ ተወለዱ። እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ በነቀምት አንደኛ ደረጃ እና በአዲስ አበባ ተፈሪ መኮንን ት/ቤት ዘመናዊ ትምህርቱን ከተከታተለ በኋላ በነበረው ልዩ የውትድርና ፍቅር በቀድሞ 1ኛ ክፍለ ጦር በኋላም ማዕከላዊ ዕዝ ተብሎ በተጠራው የ ...

                                               

ባህሩ ቀኜ

ባህሩ ቀኜ የኢትዮጵያ ታዋቂ ዘፋኝ ሲሆኑ ብዙ ባህላዊ የሙዚቃ ስራዎችን በማቅረብ ይታወቃሉ። አርቲስት ባህሩ ቀኜ ኢትዮጵያ ውስጥ በማሲንቆ አገራረፋቸውና በድምፃቸው ቃና ከሚታወቁት አንጋፋ ባለሙያዎች አንዱ ነበሩ። አርቲስት ባህሩ በሀገር ውስጥ በአገር ፍቅር ቲያትርና ከሀገር ውጭም በአፍሪካ፣ በአውሮፓና በሰሜን አሜሪካ ሙያቸውን አቅርበዋል።

                                               

ባህታ ገብረ ሕይወት

ባህታ ገ/ሕይወት ሚያዚያ ፳፯ ቀን ፲፱፻፴፭ ዓ.ም. በትግራይ ክፍለ ሀገር አዲግራት ከተማ ተወለደ። በዚያው ከተማ የቅዳሴ ትምህርቱን አስር ዓመት ሲሞላው አጠናቋል። አባቱ በቅስናው እንዲገፋበት ቢወተውቱትም የእርሱ ምርጫ ግን እንደ አባቱ ሳልነበረ ዘመናዊው የቀለም ትምህርት እስከ ስምንተኛ ክፍል ድረስ በትግራይ ክ/ሀገር ተማረ። ከፍተኛ ትምህርቱን በመከታተል ላይ ነበር። ጎንደር ጤና ኮሌጅ ...

                                               

ብዙነሽ በቀለ

ጭንቅ ጥብብ ችላ አትበለኝ የናት ውለታዋ፣ የፍቅሬ ነበልባል፣ የሚያስለቅስ ፍቅር፣ የምሰረቅ ቢሆን፣ አይወደኝ አላውቅም፣ ደብዳቤ ላክብኝ፣ ድንገት ሳላስበው ፍቅሬ ደህና ሁን፣ ፍቅር ሀብት እኮ ነው ለምን ጊዜም የማልረሳሽ፣ ለሚወዱህ ቀርቶ፣ ለሰው ቢናገሩት፣ ሌላ አሰበ ወይ አዲስ ፍቅር ይዞኛል፣ እርግብግብ አለብኝ ዓይኔ

                                               

ተፈራ ካሣ

ተፈራ ካሣ የዘፈን ስሜት ያደረበት ገና በልጅነቱ በበረሃ እረኛ ሆኖ ከብቶች በሚጠብቅበት ወቅት ነበር። በጓደኞቹ ዘንድ በድምፁ እየተመረጠ ለሆያሆዬ፣ ለጥምቀት፣ ለዘመን መለወጫና ለመሳሰሉት በዓላቶች አውራጅ ነበር። በ፲፱፻፵፭ ዓ.ም. ወደ አዲስ አበባ መጥቶ በክብር ዘበኛ ወታደርነት ተቀጠረ። ከዚያም ወደ ቲያትር ክፍሉ ተዛውሮ ድምፃዊ ለመሆን በቃ። በልጅነቱ ሲዘፍን ወላጆቹ አሰደብከን፣ ዘራ ...

                                               

ታምራት ሞላ

ታምራት ሞላ ታዋቂ ኢትዮጵያዊ ዘፋኝ ሲሆን ብዙ ዘመናዊና ባህላዊ የሙዚቃ ስራወችን በማቅረብ ይታወቃል። በ፳፻ ዓ.ም የካንሰር በሽታ የተገኘበት ድምጻዊ ታምራት በህክምና ከህመሙ በሙሉ እንደ ተሻለው አሳውቆ የነበረ ቢሆንም ህመሙ እንደገና አገርሽቶበት በተወለደ በ፮፱ አመቱ በየካቲት ፬ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። የቀብር ሥነ ሥርዓቱም በዕለቱ በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ...

                                               

ንዋይ ደበበ

ንዋይ ደበበ በጋሞጎፋ ክፍለ ሀገር በገለብና ሀመርባኮ አውራጃ በሀመር ወረዳ በ፲፱፻፶፫ ዓ.ም. ተወለደ። በተወለደበት አካባቢ ትምህርቱን እስከ ፬ኛ ክፍል ከተማረ በኋላ በ፲፱፻፷፫ ዓ.ም. ወደ አሰላ በመሄድ እዚያው እየተማረ ሳለ በአስተማሪውና በት/ቤት ጓደኞቹ ዘንድ አድናቆትን እያገኘ መጣ። በኋላም ላይ ንዋይ በቤተሰቦቹ የሥራ ዝውውር ምክንያት ወደ ሲዳሞ ሄዶ አርባምንጭ ከነማና በወላይታ ...

                                               

አለማየሁ እሸቴ

አለማየሁ እሸቴ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በአርበኞች ት/ቤት ተከታትሎ ባደረበት ጥልቅ የሙዚቃ ስሜትና ባለው ግሩም ተሰጥኦ ተገፋፍቶ ድምጻዊነቱን በፖሊስ ሠራዊት ሙዚቃ ክፍል ጀመረ። ብዙዎቹ የአለማየሁ ዘፈኖች ከስሜት በሚያፈልቃቸው ዜማዎች ዘመናዊነት የሚታይባቸውና ከውጭ ሀገር ዘፈኖች ጋር ይመሳሰላሉ።

                                               

አሊ ቢራ

አሊ ቢራ በመስከረም ፲፭፣ ፲፱፻፵ ዓ.ም September 26, 1947 በድሬዳዋ ከተማ ተወለድ። በህጻንነቱ የተለያዩ የአገር ውስጥ እና አለም አወፍ ሙዚቃዎችን እያደመጠ ያደገው አሊ ቢራ ለትምህርት ቤት ጓደኞቹ እና ለቤተሰቦቹ በማንጎራጎር ነበር የሙዚቃ ህይወቱን የጀመረው። በድሬደዋ ውስጥ ብዙ ቋንቋዎች መኖር ያልገደበው አሊ በአረብኛ፣ ኦሮምኛ፣ ሃደርኛ እና ሶማሊኛ ሙዚቃዎችን ይጫወት ነበ ...

                                               

አስቴር አወቀ

አስቴር የኢትዮጵያ ታዋቂ ዘፋኝ ስትሆን ብዙ የሙዚቃ ስራዎችን ከ70ወቹ ጀምራ በማቅረብ ትታወቃለች። አስቴር ከ13 አመቷ ወደ ሙዚቃ አለም የገባች ሲሆን ከተወለደችበት ጎንደር ወደ አዲስ አበባ በመምጣት በወጣትነቷ ሙዚቃን ኮንቲኔንታል ባንድ፣ ሆቴል ዲአፍሪክ ባንድ፣ አይቤክስ ባንድ እና ሸበሌ ባንዶች ጋር የፐተለያዩ ዝግጅቶችን አቅርባለች። ከእዚያም በዝነኛው አሊ ታንጎ እገዛ ከባንድ ወጥታ ...

                                               

አበበ ተሰማ

አበበ ተሰማ በ፲፱፻፳፬ ዓ.ም. በሰላሴ አውራጃ ጎሓጽዮን ከተማ አካባቢ ከሚኖር የገበሬ ቤተሰብ ተወለደ። አበበ በአደገበት አካባቢ በእርሻ እና በምንጠራ ስራ ላይ ሲሰማራ ማንጎራጎር ይወድ ነበር። በየምንጠራውም እየሄደ ያንጎራጉር ነበር። በ፲፱፻፵፪ ዓ.ም. ወደ አዲስ አበባ በመምጣት በዕደ ጥበብ ማዕከል ውስጥ በሽመና ስራ ተቀጥሮ ይሠራ ነበር። በ፲፱፻፶፫ ዓ.ም. ወደ ሙዚቃው ዓለም ለመግባት ...

                                               

አያሌው መስፍን

አያሌው መስፍን በ፲፱፻፵፪ ዓ.ም. በወሎ ክፍለ ሀገር በየጁ አውራጃ ተወለደ። አያሌው ገና በልጅነቱ የሙዚቃ /የዘፋኝነት/ ሙያ ፍቅር ስለነበረበት ወላጆቹ ወደ ትምህርት ቤት ሲልኩት እሱ ግን የሚውለው አዝማሪዎች በማሲንቆ በሚጫወቱበት ሥፍራ ነበር። ይህንንም በውስጥ የሚነደውን የሙዚቃ ፍቅር ለማርካት ከወሎ ጠፍቶ በ፲፱፻፶፮ ዓ.ም. ወደ አዲስ አበባ መጣ። አዲስ አበባ እንደመጣም ብሔራዊ ቲያ ...

                                               

እሣቱ ተሰማ

እሣቱ ተሰማ ታዋቂ ኢትዮጵያዊ ዘፋኝ ነው። እሣቱ ተሰማ በ፲፱፻፴፩ ዓ.ም. በሲዳሞ ክፍለ ሀገር ተወለደ። በ፲፱፻፴፬ ዓ.ም. ወደ አዲስ አበባ መጥቶ ዘመድና ረዳት ስላልነበረው በስድስት ኪሎ አካባቢ ጫማ እየጠረገ እራሱን ማስተዳደር ጀመረ። በልጅነት ጊዜው በበዓላትና በሠርግ ላይ በድምፁ ይጫወት ነበር። በ፲፱፻፵፮ ዓ.ም. መባቻ ላይ በቀድሞው የክብር ዘበኛ የሙዚቃ ክፍል ውስጥ የመጀመሪያ ድም ...

                                               

እዮብ መኮንን

እዮብ መኮንን የኢትዮጵያ ታዋቂ ዘፋኝ የነበረ ሲሆን ብዙ ዘመናዊ የሙዚቃ ስራዎችን አቅርቧል። ከነዚህም ዉስጥ ለ ኢትዮጵያ የ ሬጌ ሙዚቃ እድገት ያደረገው አስተዋፆ ስሙ በጉልህ የሚጠራበት ነው።እዮብ መኮንን ባደረበት ድንገተኛ ህመም፣ በናይሮቢ ከተማ ሕክምናውን በሚከታተልበት ሆስፒታል እሁድ ማታ ነሐሴ ፲፪ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. አርፏል።

                                               

ወጋየሁ ደግነቱ

አርቲስት ሻለቃ ወጋየሁ ደግነቱ ከአባቱ ከአቶ ደግነቱ ጅማ ከእናቱ ከወ/ሮ አበራሽ ወዲጆ ጥር 12 ቀን 1940 ዓ/ም. በሀረርጌ ክ/ሀገር በወበራ አውራጃ በጐሮ ጉቱ ወረዳ ልዩ ስሙ መካኒሳ በተባለው ስፍራ ተወለደ። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በሐረር ልዑል ራስ መኮንን አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ተከታትሏል። በነበረው ልዩ የሙዚቃ ፍቅር የተነሳ መጋቢት 1 ቀን 1955 ዓ.ም. በሐረርጌ ክ/ሀገር ...

                                               

ይርጋ ዱባለ

ይርጋ ዱባለ የተወለደው ጎንደር ከተማ አርባያ በምትባል መንደር ግንቦት 16 ቀን 1922 ዓ.ም ነው። አባቱ ከሌላ የወልዷቸው በርካታ ልጆች ቢኖሩም ከአንድ አባት የተወለዱ አንድ ወንድና አንዲት ሴት ግን ነበሩ። እንዳጋጣሚ ግን ሁለቱም አሁን በህይወት የሉም። ይርጋ ዱባለ የ10 ዓመት ልጅ እያለ፣ ታናሽ ወንድሙ ባዘዘው ዱባለ ደግሞ የ 7 ዓመት ልጆች ሆነው ማሲንቋቸውን ይዘው ሲጫወቱ" እኒያ ...

                                               

ዳምጠው አየለ

በሃምሌ 23 1944 አ/ም ከእናቱ ወይዘሮ ሸዋየ ተካና ከአባቱ አየለ ካሰኝ በመራቤቴ ሰሜን ሸዋ ተወለደ። ልጅነቱን በእረኝነት፥ በግብርና እንዲሁም በቆሎ ተማሪነት እንዳሳለፈ ይናገራል። እድሜውም ለትምህርት ሲደርስ ባቅራቢያው በሚገኘው መራኛ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ገብቶ ተምሯል።

                                               

ጌታመሳይ አበበ

ጌታመሳይ አበበ ታዋቂ የኢትዮጵያ ባህላዊ ዘፋኝ ሲሆን ያለው የጠለቀ የማሲንቆ ዕውቀትና ችሎታው የማሲንቆው ሊቅ የሚል መጠሪያ አጎናፅፎታል። ጌታመሳይ አበበ በሰሜን አሜሪካ፣ በአውሮፓና በአፍሪቃ በመዟዟር የኢትዮጵያን የባሕል ጨዋታ በተለያዩ አለም አቀፍ መድረኮች ላይ ያንፀባረቀ አንጋፋ የባሕል ተጫዎች ነው።

                                               

ግርማ ነጋሽ

ግርማ ነጋሽ ታዋቂ ኢትዮጵያዊ ድምፃዊ ነው። ግርማ ነጋሽ የተወለደው በ፲፱፻፴፮ ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ አራት ኪሎ አካባቢ ሲሆን ያደገው ከፍልውሃ በላይ ፊት በር ከሚባለው ሠፈር ነው። ግርማ ነጋሽ ወደ ሙዚቃው ዓለም ለመግባት ዋናው ምክንያት የሆነው ሙዚቃን መውደድ ብቻ ሳይሆን ከታዋቂው ጥላሁን ገሠሠ ጋር በአደጉበት አካባቢ በሠፈር ልጅነት መገናኘትና የቅርብ ጓደኛ መሆን ነው። መጀመሪ ...

                                               

ጥላሁን ገሠሠ

ከእናቱ ከወ/ሮ ጌጤ ጉሩሙ እና ከአባቱ ከአቶ ገሠሠ ንጉሤ በአዲስ አበባ ልዩ ስሙ ጠመንጃ ያዢ እየተባለ ከሚጠራው ሰፈር የመስቀል ዕለት ተወለደ። እድሜው - ፲፬ ዓመት እንደሆነ ከአያቱ ጋር እንዲኖር ወደ ወሊሶ ተወሰደ በዚያም በራስ ጎበና በሚባለው አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ትምህርት ጀመረ። ጊዜ እያለፈ ሲሄድ ከፍተኛ የሆነ የሙዚቃ ፍቅር እይሳየ ሄደ ። አያቱ ግን ትኩረቱን በሙሉ በትም ...

                                               

ፀሐይ ዮሐንስ

ፀሐይ ዮሐንስ በ፲፱፻፶፬ ዓ.ም. በኤርትራ ክፍለ ሀገር አሥመራ ከተማ ተወለደ። ፀሐይ ከአባቱ ጋር ወደ አዲስ አበባ መጥቶ ትምህርቱን በሚከታተልበት ወቅት የሙዚቃ ችሎታውን ለማዳበር ቻለ። የ፭ኛ ክፍል ተማሪ እያለ በአብዮቱ ወቅት ፷ ሺህ ተማሪዎች ወደ ገጠሪቱ ኢትዮጵያ ለዕድገት በሕብረት ዘምተው ሳለ "በርታ ዘመዴ ዘማቹ ጓዴ" የተሰኘው የመጀመሪያውን ሙዚቃ ለሕዝብ በማቅረብ በወቅቱ ከፍተኛ ...

                                               

ፅጌ ማርያም ገብሩ ደስታ

እማሆይ ፅጌ ማርያም ገብሩ ደስታ ዝነኛ ኢትዮጵያዊ ሙዚቀኛ ሲሆኑ የኢትዮጵያ ክላሲካል ሙዚቃዎች እናት ተብለው ይጠራሉ። ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ለመጀመሪያ ጊዜ በጀርመን ሀገር በሸክላ እንዳስቀረፁ ሁሉ እማሆይ ፅጌ ማርያምም ከዓመታት በኋላ የኢትዮጵያን ክላሲካል ሙዚቃዎች በሲዲ በማስቀረፅ ለዓለም ሕብረተሰብ ያስተዋወቁ የመጀመሪያዋ እንስት ሆነዋል።

                                               

ፍሬው ኃይሉ

ፍሬው ኃይሉ በ፲፱፻፴፫ ዓ.ም. በትግራይ ክ/ሀገር ተንቤን አውራጃ ተወለደ። ቀደም ሲል በድቁና ሲያገለግል የነበረው ፍሬው በ፲፱፻፵፯ ዓ.ም. ወደ አዲስ አበባ በመምጣት በሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት ተቀጠረ። ፍሬው በአኮርዲዮን አጨዋወት ቅልጥፍናው የሚደነቅ ከመሆኑም ሌላ የሙዚቃ አቀናባሪ፣ የተዋጣለት ተዋናይ፣ የግጥምና ዜማ ደራሲ ነበር።

                                               

አባይ ወይስ ቬጋስ

አባይ ቨርሰስ ቬጋስ በኢትዮጵያዊያን እና በውጭ ሀገር ዜጎች የተሰራ ፊልም ነው። ይህ ፊልም ከኢትዮጵያ ፊልሞች ለየት የሚያደርገው በተሻለ የፊልም ዕውቀት እና የፊልም መሳሪያዎች በተለይም Red One በተባለው ካሜራ የተቀረጸ ፊልም በመሆኑ ነው። ቀረፃዎች በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ ከተሞች ተደርገዋል። በፊልሙ ላይ ዳይሬክተሩ ቴዎድሮስ ተሾመን ጨምሮ ሌሎች አንጋፋ እና ወጣት ተዋንያን ተሳትፈ ...

                                               

ኦፓኛ

ኦፓኛ በኢትዮጵያ እና በደቡብ ሱዳን የሚነገር የናይሎ ሳህራዊ ቋንቋ ነው። ንኡስ የቋንቋ ቤተሰቡ በስነልሳን ምሁራን ዘንድ ኮማን ሲባል ፥ በዚህ ንኡስ የቋንቋ ቤተሰብ ስር ከኦፖ በተጨማሪ በጋምቤላ እና በቤኒ ሻንጉል ክልልሎች የሚነገረው ኮሞኛ፥ በቤኒ ሻንጉል ክልል እና በደቡብ ሱዳን የሚነገሩት ኡዱክኛ እና ደቡብ ሱዳን ውስጥ ይነገር የነበረ ጉሌ የተባለ የሞተ ቋንቋ ይካተተሉ። በተጨማሪም ...

                                               

አማርኛ

አማርኛ ፡ የኢትዮጵያ ፡ መደበኛ ፡ ቋንቋ ፡ ነው ። ከሴማዊ ፡ ቋንቋዎች ፡ እንደ ፡ ዕብራይስጥ ፡ ወይም ፡ ዓረብኛ ፡ አንዱ ፡ ነው። በአፍሪካ ፡ ውስጥ ፡ ደግሞ ፡ ከምዕራብ ፡ አፍሪካው ፡ ሐውሳና ፡ ከምሥራቅ ፡ አፍሪካው ፡ ስዋሂሊ ፡ ቀጥሎ ፡ 3 ኛውን ፡ ቦታ ፡ የያዘ ፡ ነው። እንዲያውም ፡ 85.6 ፡ ሚሊዮን ፡ ያህል ፡ ተናጋሪዎች ፡ እያሉት ፣ አማርኛ ፡ ከአረብኛ ፡ ቀጥሎ ...

                                               

ሰይፉ በኢቢኤስ

ሰይፉ በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ላይ በየእሑድ ሌሊት ከኢትዮጵያ አዲስ አበባ እስቱዲዮ የሚሠራጭ የሌሊት ውይይት ትርዒት ነው። ከ2006 ዓም ጀምሮ ለዘጠና ደቂቃ ከአስተናጋጁ ሰይፉ ፋንታሁን ይቀርባል። እንደ አሜሪካ አገር የሌሊት-ውይይት ልማድ በመምሰል፣ አስቂኝ ክፍሎች፣ የቀልድ ንግግሮች፣ ሙዚቃዊ ትርዕይቶችና የዝነኛ ቆይታዎችም ያቀርባል። እንደ በርካታ አሜሪካዊ ትዕይንቶች ስልት፣ የተመሠረተውን ...

                                               

አንድምታ

አንድምታ የሚለው ቃል "አንድም" ከሚለው የአማርኛ ቃል የመጣ ሲሆን የአረፍተ ነገሮችን ድብቅ ትርጉም አውጥቶ ለማሳየት የሚረዳ መሳሪያ ነው። አንድምታ exegesis) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ውስጥ የመጽሃፍ ቅዱስን ትርጉም ለማወቅ የሚጠቅም የትርጓሜ ሂደት ነው ። በአንድምታ መጻህፍቶች ውስጥ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት ከሁሉ በላይ ትርጓሜ ያገኘው የዮሐንስ ራዕይ 6፡2 ሲ ...

                                               

ወላይትኛ

ወላይትኛ በኢትዮጵያ በተጠቃሚ ብዛት በ4ኛነት የሚመደብና በደቡብ ኢትዮጵያ ውስጥ በሰፊው የሚነገር ቋንቋ ነው። ይህም ብቻ ሳይሆን የሌሎቹ ተቀራራቢ ቋንቋዎች ምንጭ ነው። ወላይትኛ ከሁሉም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች በፊት የመጀመሪያው የላቲን ፊደል መጽኃፍ ቅዱስ ታትሞበታል። ከወላይትኛ ጋር ዝምድና ያላቸው ሌሎች ቋንቋዎች ጋሞ-ጎፋ-ዳውሮ እና ኩሎና ኮንታ ናቸው። ባሁኑ ጊዜ በሥልጣን ላይ ያለው የ ...