ⓘ Free online encyclopedia. Did you know? page 19
                                               

የቴቭኒን እርግጥ

የቴቭኒን እርግጥ የተወሳሰበን የኤሌክትሪክ ዑእት ወደ ቀላል ተመጣጣኝ ዑደት የምንልወጥበት መንገድ ነው። በእርግጡ መሰረት ብዙ ባትሪ ፣ የኤሌክትሪክ ጅረት ምንጮች እና ሁለት ጫፍ ያላቸው ተቃዋሚዎች ያለውን የኤሌክትሪክ ዑደት በአንድ የቮልቴጅ አመንጭና ከርሱ ጋር በተቀጠለ አንድ ተቃዋሚ ዑደት ሊተካ ይችላል ነው። ስለሆነም ውስብስብ የሚመስልን አንድ ዑደት ወደ ቀላል ዑደት በቴቭኒን እርጉጥ ...

                                               

የኖርተን እርግጥ

የኖርተን እርጉጥ የተወሳሰቡ የኤሌክትሪክ ኡደቶችን ለማቃለል የሚረዳ ስሌት ነው። እርግጡ እንደሚለው፣ ማናቸውም የምንጮች፣ ኤኤክትሪክ ጅረት ምንጮች እና ኤሌክትሪክ ተቃውሞወች ጥምረት፣ በተመጣጣኝ ሁኔታ በአንድ የኤሌክትሪክ ጅረት ምንጭ እና ከርሱ ትይዩ ባለ የኤሌክትሪክ ተቃዋሚ ሊተካ ይችላል። በአንድ አይነት ብቻ የሚደጋገም ተለዋዋጭ የኤሌክትሪክ ስርዓት እንዲሁ በኖርተን እርጉጥ መሰረት በ ...

                                               

የአነባብሮ እርግጥ

የአነባብሮ እርግጥ ከአንድ በላይ የሆኑ ራሳቸውን የቻሉ የጅረት ወይንም ቮልቴጅ ምንጮች በአንድ የ ኤሌክትሪክ ዑደት ውስጥ ሲገኙ፣ የሚፈጠረውን የስሌት ውስብስብነት ለመቀነስ የሚረዳ ነው። ምንም እንኳ የአነባብሮ እርግጥ በጣም ጠቃሚ መሳሪያ ቢሆንም፣ የሚተገበርበት የኤሌክትሪክ ዑደት አይነት ከጉብር ትንታኔ ይጠባል። ይሄውም፣ የአነባብሮ እርግጥን ለመጠቀም፣ የሚተነተነው ዑደት ሊኒያር መርብ ...

                                               

የኤሌክትሪክ ፈሳሻዊ ተምሳሌት

በኤሌክትሪክ አስተላላፊ ብረቶች ውስጥ የሚጓዘው ኤሌክትሪክ ጅረት በአይን ስለማይታይ ብዙ ጊዜ ጸባዩን ለማወቅ አስቸጋሪ ይሆናል። የመጀመሪያዎቹ የኤሌክትሪክ ፍሰት ተመራማሪዎች ኤሌክትሪክ ፍሰትን ይረዱት የነበረው በቱቦ ውስጥ በሚፈስ ውሃ ወይም ፈሳሽ ነገር ተምሳሌትነት ነበር። በዚህ ብቻ ሳይበቁ እራሱ ኤሌክትሪክ ፈሳሽ ነገር ነው ይሉ ነበር። በአሁኑ ጊዜ ያ ግንዛቤ ስህተት መሆኑ የተረጋገጠ ...

                                               

ቋጠሮ ድረ ገጽ

ቁጠሮ ድረ ገጽ ከ2001 ጀምሮ ግልጋሎት እየሰጠች የምትገኝ ድረ ገጽ ነች። ግልጋሎት መስጠት በጀመረችበት በመጀመሪያ 5 ዓመታት ውስጥ ሙሉ ትኩረቷ በአማርኛ ስነ ጽሁፍ ዙሪያ ማለትም በሥነ- ግጥም፤ ቅኔ፤ አጫጭር ልቦለዶች እና ከስነ ጽሁፍ ጋር ተያያዥነት ባላቸው የፈጠራ ስራዎች ላይ ነበር። ከ2005 ጀምሮ ግን በተለይ በምርጫው እንቅስቃሴና ከዚያ ጋር በተጎዳኙ ጉዳዮች ላይ ዘገባና ጽሁፎች ...

                                               

አሉምኒ ፖርታል ዶችላንድ

አሉምኒ ፖርታል ዶችላንድ ከትርፍ ነፃ የሆነና በጀርመን አገር ስልጠና ላደረጉ ሰዎች የተዘጋጀ ማህበራዊ ድረ ገፅ ነው። ማንኛውም በጀርመን አገር ጥናት፤ ሪሰርች ያደረገ፤ የስራ ወይም በጀርመን አገርም ሆነ በውጭ አገር ማንኛውንም አይነት የቋንቋም ሆነ ሌላ አይነት ስልጠና ያደረገ አሉምኑስ ሊጠቀምበት የሚችል ድረ ገፅ ነው። ፖርታሉ ለግልም ሆነ ሙያን ላስመለከተ ጉዳይ የተዘጋጀ ነው። ስኮላር ...

                                               

ዋርካ (ድረገጽ)

ዋርካ ሳይበር ኢትዮጵያ በመባል የሚታወቀው ድረገጽ የአማርኛ ቋንቋ የውይይት መድረክ ድረ ገጽ ነው። ይህ ድረገጽ ኢትዮጵያውያን በራሳቸው ፊደል መወያየት ይችሉ ዘንድ በሁለት ወንድማማች ኢትዮጵያዊያን በሰኔ 1992ተፈጥሮ ዛሬ ሁሉንም ኢትዮጵያዊያን በስፋት እያገለገለ ያለ ዌብሳይት ሆኖአል። ይሁን እንጂ ድረገጹ እንደሚለው ከግንቦት 1998 ጀምሮ ፥ የኢትዮጵያ መንግሥት ድረገጽን ስለአገደው በ ...

                                               

ውክፔዲያ

ውክፔዲያ የባለ ብዙ ቋንቋ የተሟላ ትክክለኛና ነጻ መዝገበ ዕውቀት ነው። ማንኛውም ሰው ለውክፔዲያ መጻፍ ይችላል። ውክፔዲያ፣ ውክሚዲያ የተባለ ገብረ-ሰናይ ድርጅት ከሚያካሂዳቸው ፕሮግራሞች አንዱ ነው። ወደ 272 በሚጠጉ የተለያዩ ቋንቋዎች ፅሁፎች አሉት። ውክፔዲያ በኢንተርኔት ከሚገኙ ታዋቂ መዛግብተ ዕውቀት አንዱ ነው። ውክፔዲያ ድረ-ገፅን መሰረት ያደረገና ማንም ሰው በቀላሉ እንዲያስተካ ...

                                               

ድረ ገጽ መረብ

የ ድረ ገጽ መረብ በጣም ብዙ የኮምፒዩተር አውታሮችን ያያየዘ የመገናኛ መረብ ነው። በመረቡ ውስጥ ብዙ ድረ ገጽ ይገኛሉ። ከዚያ በላይ በርካታ የመነጋገርና መገናኘት መንገዶች አሉ። ከሁሉ አስቀድሞ የተፈጠረ ክፍለ-ኢንተርኔት "USENET" የሚባለው አገልግሎት ነው። ይህ በ1973 ዓ.ም. 1980 እ.ኤ.አ. አካባቢ ሲጀመር በተለይ ለዩኒቨርሲቴዎችና ኮሌጆች ብቻ የታወቀ መገናኛ ሆኖ ቆየ። ይህ ...

                                               

ሰናንኩያ

ሰናንኩያ በማሊ፣ በጊኔና በጋምቢያ የሚገኝ ኅብረተሠባዊ ባሕርይ ነው፤ ባጠቃላይ በብዙ የምዕራብ አፍሪካ ኅብረተሠቦች ይገኛል። ትርጉሙ እንደ "መቀላለድ ዝምድና" ይመስላል። በተወሰኑ የጎሳ ወይም የሙያ ቡድኖች ውስጥ ካለው ልምድ በላይ፣ "በረዶውን የሰበሩት" ማናቸውም ፈቃደኛ ተሳታፊዎች የሰናንኩያ ግንኙነት ሊመሠረቱ ይችላሉ። በሰናንኩያ ዝምድና ያሉት እርስ በርስ እንደ ቅርብ ዘመድ ሊቀላለዱ ...

                                               

ህግ ተርጓሚ

ህግ ተርጓሚ ወይም ፍርድ ቤት፡ ፍርድ የመስጠት ስልጣን ያለው የመንግስት አካል ነው። ከሶስቱ ከፍተኛ የመንግስት አካላት ማለትም ህግ አውጭ፣ ህግ ተርጓሚ እና ህግ አስፈጻሚ አንዱ። ይህ አካል ህግ ተርጓሚ የሚባለው ነው። የወንጀለኛ መቅጫ ህግ፣ ሲቪል ህግ፣ አስተዳደራዊ ህግ እና ሌሎች ህጎችን በየህግ የበላይነት ላይ መሰረት በማድረግ ይተረጉማል።

                                               

ለዘለቄታዊ የልማት ግብ

‘’’ለዘለቄታዊ የልማት ግብ’’’ ‘’’’ ለወደፊቱ ለሚኖር የአለም የሚተካ ነው፡፡ ኤስ.ዲ.ጂ የሚካሄደው ከ2015 እስከ 2030 ነው፡፡ 17 ግቦች ሲኖሩት ከነዚህም ውስጥ 169 ተለይተው የታወቁ አላማዎች አሉት፡፡ ግቦች ቁጥር በነሀሴ 2015፣ 193 ሀገራት አስራሰባቱን ግቦች ለመከተል ተስማምተዋል፡፡ ቁጥር ድህነት:ከሁሉም ቦታ ድህነትን ማጥፋት፡፡ ቁጥር ረሀብ:ረሀብን ማቆም፣ የምግብ ዋስ ...

                                               

የመንግሥት ሃይማኖት

የመንግሥት ሃይማኖት በአንድ መንግሥት ዘንድ የተመሠረተ ሃይማኖት ወይም ይፋዊ እምነት ነው። ይህ ሲባል ግን የተመሠረተው ሃይማኖት መሪዎች የመንግሥቱ መሪዎች አይደሉም፤ እንደዚህ ከሆነ ግን ያው መንግስት "Theocracy" ይባል ነበር። የተመሠረተው ሃይማኖት ማለት በመንግሥት የተደገፈው እምነት ወይም ትምህርት የሚመለከት ነው።

                                               

ፍርድ ቤት

ፍርድ ቤት ፍርድ የመስጠት ስልጣን ያለው የ መንግስት አካል ነው። ከሶስቱ ከፍተኛ የመንግስት አካላት ማለትም ህግ አውጭ፣ ህግ ተርጓሚ እና ህግ አስፈጻሚ አንዱ ነው። ይህ አካል ህግ ተርጓሚ የሚባለው ነው። የወንጀለኛ መቅጫ ህግ፣ ሲቪል ህግ፣ አስተዳደራዊ ህግ እና ሌሎች ህጎችን በየህግ የበላይነት ላይ መሰረት በማድረግ ይተረጉማል።

                                               

ስኳር

ስኳር በተለይ በምግብ የሚገኙ ልዩ ጣፋጭ ካርቦሃይድሬት ኣይነቶች ነው። ዋና ንጥል ሶከር አይነቶች ፍሩክቶስ እና ግሉኮስ ናቸው። ግሉኮስ ደግሞ "ዴክስትሮስ" ይባላል። እነዚህ ስኳሮች በተለያዩ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም በማር ይገኛሉ። ዋንኛው ክሌ ሶከር አይነት ሱክሮስ ነው። ይህ የፍሩክቶስና የግሉኮስ ውሑድ ነው። የገበታ ስኳር ባብዛኛው ሱክሮስ ሲሆን ይህ በብዛት ከሸንኮራ ኣገዳ እና ከ ...

                                               

ጨው

ጨው ማለት በጥንተ ንጥር ረገድ በተለይ NaCl ነው። የተሠራው ከሶዲየም እና ክሎሪን ንጥረ ነገሮች ነው። ይህ ማዕደን በምግብ ውስጥ ይበላል። ጣዕም ለመጨመር እንዲሁም የምግብን ኹኔታ ለማስጠበቅ በጣም ይጠቅማል።

                                               

መንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ

የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሕንፃ የመሠረት ድንጋይ ታኅሣሥ ፲፭ ቀን ፲፱፻፳፬ ዓ/ም ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሲያስቀምጡ የእስክንድርያ ኮፕት ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ዮሐንስ እና የሀገር ጳጳሳትም በተገኙበት ልዩ ጸሎት እና ቡራኬ ተሠጥቶ ተመረቀ። ቤተ ክርስቲያኑ ሲታነጽ ቀዳሚ ዓላማው ለአገራቸው ነፃነት ሲታገሉ ለተሰው አርበኞች መካነ መቃብር እንዲሆን ታቅዶ ነው። ...

                                               

ምስካዬ ኅዙናን መድኀኔ ዓለም

ምስካዬ ኅዙናን መድኀኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን፣ አዲስ አበባ የዚህ ቤተ ክርስቲያን ጽላት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አገራችን ኢትዮጵያ በፋሺስት ኢጣልያ በተወረረች ጊዜ በስደት እንግሊዝ አገር ባዝ በተባለ ከተማ ሲኖሩ፣ ጥር ፲፫ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓ/ም በጊዜው በስደት ኢየሩሳሌም ለነበሩት ወደ ብፁዕ እጨጌ ገብረ ጊዮርጊስ በኋላ አቡነ ባስልዮስ አንድ ፅላትና ለአገልግሎት የሚበቁ አምስት መነኮሳትን ወ ...

                                               

እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን

ደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ በንግሥት ዘውዲቱ ዘመነ መንግሥት በ፲፱፻፱ ዓ/ም ተመሠረተ። በዚያን ጊዜም ዘመኑ በፈቀድው መልክ የቤተ ክርስቲያኑ ሕንጻ ተጠናቆ ሲወደስበት ሳለ፤ በጣልያን የወረራ ዘመን፣ በ፲፱፻፴፪ ዓ/ም ባልታወቀ ምክንያት የእሳት አደጋ ደርሶበት ሕንጻው ተቃጠለ። ኢትዮጵያ ከ ፋሺስት የወረራ ቀንበር ከተላቀቀች በኋላ፤ የግንባታው በሥራ ሚኒ ...

                                               

የካ ሚካኤል

የካ ሚካኤል የአለት ውቅር ቤተክርስቲያን ሲሆን ከአዲስ አበባ ወጣ ብሎ በሚገኘው የየካ አምባ ላይ ይገኛል። ቤተክርስቲያኑ የላሊበላ ውቅር ቤተክርስቲያን አይነት ስልት የያዘ ነበር። ምንም እንኳ የህንጻው አወቃቀር ባልታወቀ ምክንያት ሳይጠናቀቅ የቀረ ቢሆንም ስራው ቢገባደድ ኑሮ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት የአለት ውቅር ቤተክርስቲያኖች በትልቅነቱ ሁለተኛ ይሆን እንደነበር ተመራማሪዎች ይዘግባሉ ። ...

                                               

ደብረ ፀሐይ ቍስቋም

ደብረ ፀሐይ ቍስቋም ከጎንደር ከተማ በስተ ስሜን ምዕራብ ወጣ ብሎ በሚገኘው ደብረ ፀሐይ የተባለ ተራራ ላይ የተሰራ የቤተክርስቲያንና ቤተመንግስት ግቢ ነው። ደብረ ፀሓይ ቁስቋም በእቴጌ ምንትዋብ፣ ከ1725 ዓ.ም. እስከ በ1738 ዓ.ም. ተገንብቶ የተጠናቀቀ ሲሆን ዙሪያው በግምብ የታጠረና በ8 እንቁላል ግንቦች የተከበበ ነው። ግቢውን ሰንጥቆ የሚያልፍ ግምብ ደብሩን ለሁለት ሲከፍል አንዱ ...

                                               

ሥርዓት

ሥርዐት አንዱ የሌላ ጥገኛ የኾኑ ነገሮች ተሰብስበው የሚፈጥሩት ዎ ጥ ወይንም ምሉዕ ነገር ማለት ነው። አንድ ሥርዐት የቁስ አካላት ወይንም የሐሳብ/ሐሳቦች ወይንም የኹለቱም ስብስብ ሊኾን ይችላል። ለምሳሌ አንድ ሰው በውስጡ ብዙ ሥርዐትን ይይዛል። ልብ፣ ሳምባ፣ እና የደም ቧምቧዎች ተደጋግፈው የአንድን ሰው የደም ሥርዐት ይፈጥራሉ። ጥርስ፣ ምላስ፣ ጨጓራ.ወዘተ.እነዚህ ተደጋግፈው የምግብ ሥ ...

                                               

በር: ፍልስፍና/የተመረጠ ጽሑፍ/52

ሥርዐት አንዱ የሌላ ጥገኛ የኾኑ ነገሮች ተሰብስበው የሚፈጥሩት ዎ ጥ ወይንም ምሉዕ ነገር ማለት ነው። አንድ ሥርዐት የቁስ አካላት ወይንም የሐሳብ/ሐሳቦች ወይንም የኹለቱም ስብስብ ሊኾን ይችላል። ለምሳሌ አንድ ሰው በውስጡ ብዙ ሥርዐትን ይይዛል። ልብ፣ ሳምባ፣ እና የደም ቧምቧዎች ተደጋግፈው የአንድን ሰው የደም ሥርዐት ይፈጥራሉ። ጥርስ፣ ምላስ፣ ጨጓራ.ወዘተ.እነዚህ ተደጋግፈው የምግብ ሥ ...

                                               

ቅየሳ

ቅየሳ የአንድን የመሬት ገጽ ወይም የግንባታ አካል አቀማጥ ለማወቅ የሚደረግ የልኬት ስራ ነው። የቅየሳ ስራ ለቅየሳ ስራ የሚውሉ እንደ ውሃ ልክ ወይም ቴዎዶላይት ያሉ መሳሪያዎች በመጠቀም በሁለት የልኬት ቦታዎች መካከል ከልኬት ቦታው አንጻር የሚኖረውን የቦታ ልዮነት ለማወቅ የማእዘን ፣ የአግድም ቁመትና የሽቅብ ቁመት ልኬቶችን በመውሰድና የሂሳብ ስሌትን በመጠቀም የመሬት ገጽን ወይም የግን ...

                                               

የመዋቅር ትንታኔ

የመዋቅር ትንታኔ የአካላዊ ህጎች ስብስብ ሲሆን በሒሳብ ህጎች ጋር በማጣመር ለመዋቅሮች አሰራር መፍትሄ የሚሰጥ የስሌት አይነት ነው። የዚህ የመዋቅር ስሌት ዋናው ግቡ የሚሰሩት መዋቅሮች ለሚገለገሉበት ድልድይ፣ ሕንፃ፣ አየር ማረፊያ አልያም መኪና በቂ ጥንካሬ እንዳለው ማረጋገጥ ነው። ስሌቱ በዋናነት በሜካኒክስ እና ዳይናሚክስ የትምህርት ዘርፎች ላይ በብዛት ጥቅም ላይ የሚውል ነው። ዋናው ...

                                               

ግድብ

ግድብ ማለት ከመሬት ስር ያለንም ሆነ ከመሬት ላይ የሚፈስን ውሃ ገድቦ ወይንም አንቆ የሚይዝና ሰው ሰራሽ ሃይቅ ለመፍጠር የሚረዳ እንቅፋት ነው። በጐንና በጐን የሚገኙት ሸለቆዎችም የግድቡ አካል ሲሆኑ የሃይቁን የጎንዮሽ ዳርቻዎችን ይወስናሉ። ግድብ የሚለው ቃል የግድብ አካል የሆኑ የግንባታ ክፍሎችን ማለትም እንቅፋት ፈጣሪውን አካል፣ ውሃ የታቆረበትን አካባቢ፣ ውሃውን ለመጠቀም የሚረዱ ግ ...

                                               

ክላውድ ሻነን

ክላውድ ሻነን አሜሪካዊ ሓሳቢ፣ ኤሌክትሮኒክ ኢንጂኔር፣ እና ሥነ ምስጢረኛ የነበር ሲሆን በቅጽል ስሙ የመረጃ ኅልዮት አባት ተብሎ ይታወቃል፡፡ ሻነን በ1940ዓ.ም. በደረሰው አንድ ጽሑፍ የሥነ መረጃ ኅልዮትን እንደመሰረተ ይጠቀሳል፣ ይሄውም በአሁኑ ዘመን ለሚገኘው የኮምፒውተርና ከኮምፒውተር ጋር የተነካኩ ማናቸውም ቴክኖሎጂዎች መነሻ ነው፡፡ በሌላ ጎን ክላውድ ሻነን የዲጂታል ኮምፒውተርና ...

                                               

ኆኅተ እና

ኆኅተ እና መሰረታዊ ከሆኑት ኆኅተ አመክንዮዎች አንዱ ሲሆን ተግባሩም የአመክንዮ እናን ተግባር በተጨባጭ ቁስ መፈጸም ነው። ምንም እንኳ ኆኅተ አመክንዮዎች በተለያዩ ቁሶች ሊሰሩ ቢችሉም፣ በአሁኑ ዘመን እነዚህ ኆኅቶች የሚሰሩት ከኤሌክትሪክ አካላት ስለሆነ አስራሩ ከዚህ አኳያ ይመረምራል። ኆኅተ እና አምክንዮ-እናን በቁስ እንደመግልጹ፣ የዚህ ኆኅት ውጤት ከፍተኛ ቮልቴጅ እሚሆነው ሁለቱም ግ ...

                                               

ዲጂታል ዑደት

የዲጂታል ዑደት እምንለው የ ስታቲክ ዲሲፕሊን ን የሚቀበል ማናቸውም ዓይነት የዑደት አይነትን ነው። የዲጂታል ዑደት ከአናሎግ የኤሌክትሪክ ዑደት እሚለየው በተወሰኑና የአምክንዮ ትርጓሜ ባላቸው ሲግናሎች ብቻ መስራቱ ነው። ይህን እሚፈጽመው ያልተቆራረጡ የአናሎግ ሲግናሎችን በመከፋፈል፣ ለምሳሌ ከተወሰነ ቮልቴጅ በላይ ያሉትን ቮልቴጆች እንደ አምክንዮ እውነት በመውሰድ እና ከተወሰነ ቮልቴጅ በ ...

                                               

ቅዱስ ጊዮርጊስ የእግር ኳስ ቡድን

ቅዱስ ጊዮርጊስ የስፖርት ክ ለ ብ የተመሠረተው ጣሊያን ኢትዮጲያን በወረረችበት ጊዜ፣ ታኅሣሥ ወር ፲፱፻፳፰ ዓ/ም በአዲስ አበባ አራዳ አካባቢ ፣ አየለ አጥናሽ እና ጆርጅ ዱካስ በተባሉ ሁለት ግለሰቦች ነው። የኋላ ኋላ ክለቡ የኢትዮጲያ ምልክት እስከመሆን ደርስዋል።

                                               

መቅደላ

መቅደላ አምባ ለመድረስ ከደሴ ከተማ በስተምዕራብ ፻፳፰ ኪ/ሜ ርቀት ላይ ከምትገኘው የተንታ ከተማ በስተሰሜን ምስራብ ፳፱ ኪ/ሜ መጓዝን ይጠይቃል፡፡ ጥንት ከመቅደላ ደብረ ታቦር ከዚያም ወደጣና ሐይቅ ዳርቻ የሚያዘልቅ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር ጐብኝዎች የሚታወቅ የእግር መንግድ ነበር፡፡ ግን ልክ እንደ ጥንታዊው የላሊበላ ሰቆጣ መንገድ ሁሉ መስመሩ ከተዘጋ ዘመናት ተቆጥረዋል። መቅደ ...

                                               

ማይጨው

ማይጨው በስሜን ኢትዮጵያ ያለች ታሪካዊ ከተማ ናት። ከአዲስ አበባ 665 ኪሎ ሜትር ወደ ስሜን በአዲስ አበባ-መቐለ መንገድ በትግራይ ክልል ደቡባዊ ክፍል ስትገኝ ኬክሮሷና ኬንትሮሷ 12°47′ ሰሜን ኬክሮስ እና 39°32′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ከፍታዋም 2.479 ሜትር ነው። በ1997 ዓ.ም. ከማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ በቀረበው ቁጥር መሠረት የማይጨው ጠቅላላ ሕዝብ ቁጥር 34.379 ሰዎች ...

                                               

ሞጣ

ሞጣ ከተማ የምትገኘው በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ጎጃም ዞን፣ በ ሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ከአዲስ አበባ በ371 ኪሜ ከክልሉ መንግስት መቀመጫ ከሆነችው ባህርዳር ከተማ ደግሞ 120 ኪሜ ርቀት ላይ ከዞኑ መቀመጫ ከሆነችው ከደብረማርቆስ ደግሞ 192 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ነው። አስትሮኖሚያዊ መገኛ ቦታዋ ደግሞ 11º 04’ ምስራቅ ላቲቲዩድ እና በ37º 52’ ሰሜን ሎንጊትዩድ ነው።

                                               

ቆላድባ

ቆላድባ ከተማ የምትገኘው በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር ዞን በደምቢያ ወረዳ ውስጥ ነው ። ከጎንደር ከተማ በስተ ደቡብ 35 ኪ.ሜ ፣ ከጣና ሃይቅ በስተ ሰሜን 30 ኪ.ሜ መካከል ትገኛለች። ቆላድባ የተመሰረተችው በ1930ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ ነው። ቆላድባ ከተማ በአሁኑ ስኣት ማለትም 2005 ዓ.ም. በ2 ሰፋፊ ቄበሌወች የተከፈለች ሲሆን የህዝብ ቁጥሩዋም ወደ 25.000 አካባቢ ነው። ከተማ ...

                                               

ባሕር-ዳር

ባሕር-ዳር በድሮ ስሙ ባሕር ዳር ጊዮርጊስ በሰሜን-ምዕራብ ኢትዮጵያ የምትገኝ ከተማ ስትሆን የአማራ ክልል ዋና ከተማ ናት። ከተማዋ በቀድሞው ጎጃም ክፍለ ሓገር ውስጥ ከጣና ሐይቅ ደቡባዊ ጫፍ ላይ ተቀምጣ ስትገኝ ባህር ዳር እንደ መቀሌና ደሴ የወረዳ ደረጃ ያላት ስፔሻል ዞን ናት። በማዕከላዊ ስታትስቲክ ትመና የ167.261 ህዝብ ከነሱም መሃከል የ86.355 ወንዶችና የ80.906 ሴቶች መ ...

                                               

ቦሩ ሜዳ

ቦሩ ሜዳ በቀድሞ ወሎ የሆነ ትልቅ ገበያ ከተማ ነው። በመጋቢት 18 ቀን 1870 ዓ.ም. በቦሩ ሜዳ ላይ የሸዋ ንጉሥ ምኒልክ ለንጉሠ-ነግስት ዮሐንስ አራተኛ ተገዥ እንደሆኑ ቃላቸውን ገቡ። በምላሽም ዮሐንስ በሸዋ ላይ የምኒልክን ንጉሥነት ተቀበሉ። ዮሐንስ በቦሩ ሜዳ ቤተክርስቲያንን ሠርተው በግንቦት 1870 አንድ ታላቅ የተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስብሰባ ተፈጸመበት። በዚህ ስብሰባ "የጸጋ ልጅ ...

                                               

ነፋስ መውጫ

ነፋስ መውጫ በደቡብ ጎንደር የሚገኝ፣ የላይ ጋይንት ወረዳ ዋና ከተማ ነው። ከደብረ ታቦር ወደ ወልደያ በሚጓዘው መንገድ ላይ በመገኘቱ፣ እንዲሁም በአካባቢው በሚገኙት ጥንታዊ ገዳሞች ጋይንት ቤተልሔም እና ውቅሮ መድሃኒ አለም ታዋቂነትን ያገኛል።

                                               

አሪንጎ

አሪንጎ ከደብረ ታቦር 10 ኪ.ሜ ሰሜን ምዕራብ፣ እንዲሁ ከጣና ሐይቅ 45 ኪሎ ሜትር በስተምስራቅ የምትገኝ ጥንታዊ ከተማ ናት፡፡ አሪንጎ በታሪክ ጎላ ብላ መታየት የጀመረችው አጼ ፋሲለደስ ዘመን የነበር ሲሆን፣ በዚችው ከተማ የሃይማኖት ጉባኤዎችን በመጥራትና በየክረምቱ እየሄደ ጊዜውን ያሳልፍ እንደነበር ይጠቀሳል። ታላቁ እያሱ አሪንጎን ይወድ እንደነበርና ለዚህ ምክንያቱ የአካባቢው ቀሳውስ ...

                                               

አንኮበር

አንኮበር በ፲፯፻፳ ዓ/ም በሸዋው ነጋሲ በመርድ አዝማች አብዬ የተመሠረተችና በአልጋ ወሪሹ መርድ አዝማች አምኀ ኢየሱስ የተስፋፋች የሸዋ ከተማ ስትሆን ከደብረ ብርሃን ምስራቃዊ አቅጣጫ ፵፫ ኪሎ ሜትር ርቀት የስምጥ ሸለቆው አፋፍ ላይ ትገኛለች። አንኮበር ከዓፄ ይኵኖ አምላክ ፲፪፻፸-፲፪፻፹፭ ዓ/ም ዘመን ጀምሮ ለኢትዮጰያ ነገሥታት በማረፊያነት አገልግላለች። ዓፄ አምደ ጽዮን ፲፫፻፲፬-፲፫፻ ...

                                               

አዋሳ

ከአዋሳ ሃይቅ በታላቁ ሪፍት ቫሌ/ስምጥ ሸለቆ ላይ የሚገኝ ከተማ ነው። የደቡብ ሕዝቦች ክልል ዋና ከተማ ስትሆን በሲዳማ ዞን ተገኛለች። የአዲስ አበባ-ናይሮቢ መንገድ ላይ በላቲቱደና ሎንጁቱድ 7°3′ ሰሜን ኬክሮስ እና 38°28′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ናት። አዋሳ በውበትዋና በትልቅነትዋ ባሁኑ ጊዜ ታላቅ የቱሪስት መስህብ ያላት ነች። በማዕከአዊ ስታቲስቲክ ባለስልጣን ትመና የ119.623 ...

                                               

አዲስ ዘመን (ከተማ)

አዲስ ዘመን በደቡብ ጎንደር የሚገኝ ከተማ ሲሆን ከባሕር ዳር ወደ ጎንደር ከተማ በሚጓዘው መንገድ መካከል ይገኛል። በድሮ ስሙ ደብረ አብርሃም ሲባል፣ በአሁኑ ጊዜ የከምከም ወረዳ አስተዳደር ማዕከል በመሆን ያገለግላል። ከአዲስ ዘመን ከተማ አጠገብ ከሚገኙ ታዋቂ ቦታዎች የደብረ ገላውዲዎስ ገዳም፣ የዋሻ እንድሪያስ፣ ዋሻ ተክለሃይማኖት አብያተ ክርስቲያናት እና አስባ ተራራዎች ይገኛሉ። ታሪካ ...

                                               

አዳማ

ናዝሬት ወዲህ ይመራል። ለእስራኤል ከተማ፣ ናዝሬት፣ እስራኤል ን ይዩ። ኣዳማ በአማርኛ ናዝሬት በኦሮሚያ ክልል ለኦሮሚያ በዋና ከተማነት የሚያገለግል የኢትዮጵያ ከተማ ነው። በምስራቅ ሸዋ ዞን በላቲቱድና ሎንጂቱድ 8.55° N 39.27° E ላይ ከአዲስ አበባ ወደ ደቡብ ምዕራብ 100 ኪሎመትር ላይ ይገኛል። በማዕከላዊ ስታቲስቲስ ባለስልጣን ትመና የአዳማ ከትማ የ228.628 ሰው መኖሪያ ሲ ...

                                               

ኢትቢራ

ኢትቢራ ፦ይህ ቃል ሁለት ጥምር ቃላትን በአንድ ላይ የያዘ ስሆን ስነጣጠል ወይም ኢቶ=ቢራ የሚል ነው። እና ይህ ትርጉሙ ምን ማለት እንደሆነ እና እንዴት እንደተቀየረ እንመልከት። ቦተው የሚገኛው በደቡብ ቤሔር ቤሔረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት በሀድያ ዞን በጊቤ ወረዳ ውስጥ ሲሆን የስሙም ትርጉም ማለት ነው። እውነትም የፍቅር አደባባይ ለመባል ያበቁ ምክኒያቶች አሉት። ስፍረው የፍቅር ...

                                               

ወልቂጤ

ወልቂጤ በደቡብ ኢትዮጵያ የምትገኝ የንግድ ከተማ ሰትሆን የጉራጌ ዞን ዋና ከተማም ነች። ከተማዋም በአበሽጌ ወረዳ የምትገኝ ሲሆን የከተማዉ አቀማመጥ በ8°17′ ሰሜን ኬክሮስ እና 37°47′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ይገኛል። በኦሮሚያ ክል በሰሜን በኩል ሲዋሰን፣ የደቡብ ክልል መጀመሪያም ነው። ብዙ ብሔረሰቦች በዉስጡ ሲኖሩ፣ በሃይማኖትም እጅግ የተለያዩ ሰዎች አሉበት። በ1998 ማዕከላዊ የስ ...

                                               

ወልወል

ወልወል በምሥራቅ ኢትዮጵያ ፥ በሶማሌ ክልል ውስጥ የምትገኝ ከተማ ነች ። ከተማዋ ከባህር ወለል በአምስት መቶ ሰባ ሜትር ከፍታ ላይ የምትገኝ ስትሆን 7°03′ ሰሜን ኬክሮስ እና 45°24′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ትገኛለች። ኅዳር ፲፬ ቀን ፲፱፻፳፯ ዓ/ም በኦጋዴን ክልል በኢትዮጵያ እና በኢጣሊያዊ ሶማልያ ያለውን ድንበር እንዲያሠምሩ የተላኩት የብሪታንያ እና የኢትዮጵያ ልዑካን በዚሁ ክልል ...

                                               

ወልደያ

ወልደያ ወይንም ወልዲያ ከደሴ ሰሜን 75 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ከላሊበላ ደግሞ በደቡብ ምስራቅ ያለ በኢትዮጵያ የአማራ ክልል ከተማ ሲሆን በሰሜን ወሎና በወልዲያ ወረዳ ይገኛል። ከኢኮኖሚ አንጻር ለሕንጻ ስራ የሚያገለግል የኖራ ምርት በአካባቢው በትንሹ መካሄዱ በታሪክ ይጠቀሳል።

                                               

ደብረ ማርቆስ

ደብረ ማርቆስ በኢትዮጵያ በአማራ ብሔራዊ ክልል የምትገኝ ሲሆን የምስራቅ ጎጃም ዞን ዋና ከተማ ናት። እንዲሁም ከተማዋ የ ጉዛምን ወረዳ አስተዳደር መቀመጫ ናት። በ1998 ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን እንደተመነው የ85.597 ሰው መኖሪያ ሲሆን ከነሱም 43.229 ወንዶችና 42.368 ሴቶች ይገኙበታል። መገኛ የደብረማርቆስ ከተማ የምትገኘው በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ በአማራ ብሔራዊ ...

                                               

ደብረ ብርሃን

ደብረ ብርሃን በሸዋ ክፍለ ሀገር የጅሩ ሸዋ ሜዳ ተጉለትና ቡልጋ አውራጃ ዋና ከተማ ናት። ከተማዋ የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ርዕሰ ከተማ ከመሆኗ ባሻገር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስም ዋና ጽሕፈት ቤት እዚሁ ይገኛል። በ፲፱፻፺፰ ዓ/ም ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን እንደተመነው ደብረ ብርሃን ከተማ የ፷፯ ሺህ ፪፻፵፫ ሰው መኖሪያ ...

                                               

ደብረ ታቦር (ከተማ)

ደብረ ታቦር በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ከጣና ሓይቅ ሰሜናዊ ምስራቅ 50 ኪሎ ሜተር ርቃ የምተገኝ በተራሮች የተከበበች ከተማ ናት። በከተማይቱ ዙሪያ 48 ምንጮች መኖራቸው ለከተማይቱ እድገት ከፍትኛ አስተዋጾ ቢያደርጉም በ20ኛው ክፍለ ዘመን የባህር ዛፍ ተክል በከተማይቱ መሰራጨት ምንጮቹ እንዲደርቁ አድርጓል። የደብረታቦርን መሰረት የጣለው የ14ኛ ክፍለዘመን ንጉስ አጼ ሰይፈ አርድ ነበር። ...

                                               

ዲላ

ዲላ በኢትዮጵያ የደቡብ ብሄር ብሄረስቦችና ሕዝቦች ክልል ከተማ ሲሆን በጌዴኦ ዞን ይገኛል። ዲላ ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ የሚካሄድባት የጌዴኦ ዞን ዋና ከተማ ናት። ከአድስ አበባ በ365 ኪ.ሜ እና ከሃዋሳ 90 ኪ.ሜ በአ.አ ሞያሌ ዋና የንግድ መስመር ላይ ትገኛለች። እንድሁም የብሄር ብሄረሰቦች መኖሪያ ናት። በ1998 ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን እንደተመነው የ61.114 ሰው መኖ ...