ⓘ Free online encyclopedia. Did you know? page 15
                                               

ኢድሪሚ

ኢድሪሚ ከ1473 እስከ 1443 ዓም ያህል ድረስ የሙኪሽ አገር ንጉሥ ነበረ። የኢድሪሚ ታሪክ በተለይ ከሐውልቱ አካድኛ ጽሑፍ የሚታወቀው ነው። የሐለብ መጨረሻ ንጉሥ የ1 ኢሊም-ኢሊማ ልጅ ነበር፣ ይህም ሥርወ መንግሥት ቀድሞ የያምኻድ መንግሥት ተብሎ ነበር። በ1480 ዓክልበ. ገደማ የሑራውያን ንጉሥ ባራታርና ሐለብን ወደ ሚታኒ መንግሥት እንደ ጨመረው ይታመናል። ኢድሪሚና ቤትሠቡ ከሐለብ ወ ...

                                               

የሾቶኩ ሕግጋት

የሾቶኩ ሕግጋት ወይም 17 አንቀጽ ያለ ሕገ መንግሥት በ596 ዓ.ም. በጃፓን ልዑል ሾቶኩ የተጻፈ ሕገ መንግሥታዊ ሰነድ ነው። እስከ 1883 ዓ.ም. ድረስ እንደ ጃፓን መንግስት ላዕላይ ሕግ ይቆጠር ነበር። በ1883 ዓ.ም. የጃፓን ንጉሥ አዲስ ዘመናዊ አይነት ሕገ መንግሥት አወጡ። ቢሆንም በግልጽ መቸም ስላልተሰረዘ፣ አንዳንድ የጃፓን ሕግ ጠባቂ የሾቶኩ ሕግጋት እስካሁን ሕጋዊ እንደሚሆኑ ...

                                               

የቻይና ነገሥታት ዝርዝር

ማስታወሻ፦ በቻይና ታሪክ ከ849 ዓመት ከክርስቶስ ልደት በፊት አስቀድሞ የሆኑት አመት ቁጥሮች ሁሉ አጠያያቂ ናቸው። ከ849 ዓክልበ. በኋላ ግን አመቶቹ በብዛት ሊወሰኑ ይቻላል። ከሥነ ቅርስ መጀመርያው የተረጋገጠው ንጉሥ ዉ ዲንግ ነው። ከ1200 ዓክልበ. የሆኑት ንግርተኛ አጥንቶች ጽሑፎች በኤሊ ቅርፊት ወይም በበሬ ትከሻ ላይ የጨረቃ ግርዶሽ ጊዜዎች ስለ ዘገቡ፣ የቻይና አጥኒዎች የዉ ዲ ...

                                               

የአሾካ አዋጆች

የአሾካ አዋጆች በሕንድ ንጉሥ አሾካ በ264 ዓክልበ. የተሰጡት ሕግጋት ናቸው። እነዚህ ሕግጋቱ በድንጋይ ላይ ተቀረጹና በግዛቱ በየቦታው በዐምዶችና በሐውልቶች ተደረጉ፤ ስለዚህ ለሥነ ቅርስ በደንብ ታውቀዋል። የሕገ መንግሥት ታሪክ ውስጥ ናቸው። ሕግጋቱ እንደ ቡዲስም ሃይማኖቱ መርኆች የተመሠረቱ ናቸው። ፬፣ እነዚህ መርኆች እናትን አባትን ማክበር፣ ልግሥና ለባልንጀራ፣ ዘመድ፣ ቄስና ባሕታዊ ...

                                               

የዕብራውያን ታሪክ

እንደ ብሉይና ሐዲስ ኪዳን አቆጣጠር አብርሃም አብራም ለአዳም ፳፩ኛ ትውልድ ነው። የተወለደውም ከአርፋክስድ ወገን በከለዳውያን ከተማ በከላውዴዎን ዑር ነው። ኦሪት ዘፍጥረት 11፡31 እንደሚለው፣ ይህ አብራም ከአባቱ ከታራ ቤተሠብ ጋራ ከዑር ተነሥተው ወደ ከነዓን ይሄዱ ዘንድ በካራን አገር ተቀመጡ። ስለዚህ ዑርና ካራን የተለያዩ ቦታዎች ናቸው። የከለዳውያን ዑር የሚባለው ስፍራ በአርፋክስድ ...

                                               

የጥንት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት

በጥንታዊ ቻይና ከአፈታሪካዊ ዘመን ነገሥታት ጀምሮ በቤተመንግሥታቸው ቸንግ ጁ የተባለ ተቋም እንደ መሠረቱ ይባላል፤ ይህም በልዩ ልዩ ዋና ከተሞችና በልዩ ልዩ ስሞች እስከ 229 ዓክልበ. ድረስ ቆየ። ያስተማሩት ጥናቶች ቀስትን ማስፍንጠር፣ ሠረገላን መንዳት፣ ሙዚቃ፣ ጽሕፈት፣ ሥነ ቁጥር፣ ሥነ ፈለክ ጠቀለሉ። እንዲሁም በአውሮፓ አፈ ታሪክ የኬልቲካ የአሁን ፈረንሳይ ነገሥታት ከ2200 ዓክል ...

                                               

ሳንኮሬ ማድራሣ

ሳንኮሬ ማድራሣ በቲምቡክቱ፣ ማሊ መንግሥት፣ ከ981 እስከ 1585 ዓም ያህል የቆየ የእስልምና መስጊድና ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ወይም ዩኒቨርሲቲ ነበረ። ከቲምቡክቱ ዩኒቨርሲቲ ሦስት ተቋማት መጀመርያው የተመሠረተው ነበር። መስጊዱ የተመሠረተው በ981 ዓም በቲምቡክቱ ዳኛ በአል-ቃዲ አቂብ ነበረ። ከ1100 ዓም ያህል በፊት በአንዲት ሀብታም ማንዲንካ ወይዘሮ እርዳታ፣ ሕንጻው ሰፊ ማድራሣ ተ ...

                                               

ሻንግ ሥያንግ

ሻንግ ሥያንግ በቻይና አፈ ታሪክ ዘንድ በጥንት በቤተ መንግሥት ከተማ የተገኘ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ነበረ። እንኳን ከ "ሻንግሥያንግ" አስቀድሞ፣ በቅድመኞቹ አፈ ታሪካዊ ነገስታት ዘመኖች ከ2350 ዓክልበ. ጀምሮ "ቸንግ ጁ" የተባለ ትምህርት ተቋም በቤተ መንግሥት እንደ ነበር ተጽፏል። ንጉሥ ያው ወይም ንጉሥ ሹን ምናልባት 2060 ዓክልበ. ግድም "ሻንግ ሥያንግ" ላይኛ ወይም ከፍተኛ አ ...

                                               

ታይሥዌ

ታይሥዌ ወይም "የቻይና ቤተመንግሥት ዩኒቨርሲቲ" በቻይና በ6 ዓክልበ. በንጉሥ ፒንግ ሃን የተመሠረተ የጥንት ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ነበረ። ከዚህም በፊት የቤተ-መንግሥታዊ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም በቻይና ይታወቅ እንደ ነበር ይመስላል። በአፈ ታሪክ ትውፊታዊው ንጉሥ ሹን በ2050 ዓክልበ. ገደማ ሻንግ ሥያንግ የተባለውን ተቋም እንደ መሠረተ ተዘግቧል። እንዲሁም በሥያ ሥርወ መንግሥት 200 ...

                                               

ናንጂንግ ዩኒቨርሲቲ

ናንጂንግ ዩኒቨርሲቲ በናንጂንግ፣ ቻይና የሚገኝ ጥንታዊ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ነው። መጀመርያው በ250 ዓም ናንጂንግ ታይሥዌ ተብሎ እንደ ኮንግ-ፉጸ ተቋም ተመሠረተ፣ ስለዚህ ለ1.760 ዓመት ክፍት ሆኗል። ይህ ከ571 ዓም በኋላ ናንጂንግ ዋና ከተማ በሆነባቸው ጊዜዎች ናንጂንግ ጐዝርጅየን ሆነ። ዋና ከተማ ባልሆነባቸው ጊዜዎች ደግሞ ናንጂንግ ሹዩዋን ናንጂንግ አካዳሚ ይባል ነበር። በ18 ...

                                               

አበየጊሪ ቪሃረ

አበየጊሪ ቪሃረ በአኑራደፑረ፣ ስሪ ላንካ የሚገኝ ጥንታዊ የቡዲስም ትልቅ ገዳምና ቤተ መቅደስ ነበር። በ80 ዓክልበ. በንጉስ ቨለገምባ ተመሠረተ። እስከ 1157 ዓም ድረስ ቆመ። የ "ቪሃረ" ትርጉም ከፓሊኛ "ገዳም" ሲሆን ከቡዲስት ገዳም በላይ ለቡዲስም ኅብረተሠብ ተከታዮች እንደ ከፍተኛ ትምህርት ቤት አገልግሎ ነበር። ከእርሱ በፊት ትልቁ የጤራቫዳ ቡዲስም ተቋም አኑራደፑረ መሃቪሃረ ከ24 ...

                                               

አኑራደፑረ መሃቪሃረ

አኑራደፑረ መሃቪሃረ በአኑራደፑረ፣ ስሪ ላንካ የሚገኝ ጥንታዊ የቡዲስም ትልቅ ገዳምና ቤተ መቅደስ ነው። በ244 ዓክልበ. በንጉስ ደቫናምፒያ ቲሣ ተመሠረተ። የ "መሃ ቪሃረ" ትርጉም ከፓሊኛ "ታላቅ ገዳም" ሲሆን ከቡዲስት ገዳም በላይ ለቡዲስም ኅብረተሠብ ተከታዮች እንደ ከፍተኛ ትምህርት ቤት አገልግሏል። ከ244 ዓክልበ. እስካሁን ወይም 2.254 ዓመታት ያህል፣ ይህ አኑራደፑረ መሃቪሃረ ...

                                               

የእስክንድርያ ማስተማርያ ቤት

የእስክንድርያ ማስተማርያ ቤት በእስክንድርያ፣ ግብጽ በጥንት የተገኘ የክርስትና ሥነ መለኮት ትምህርት ተቋም ነበረ። ተቋሙን የመሠረተው የኢየሱስ ሐዋርያ እና መጀመርያው የእስክንድርያ ጳጳስ፣ ቅዱስ ማርቆስ ወንጌላዊ በ54 ዓም እንደ ሆነ ተጽፏል። የተቋሙ መጀመርያው መሪ በኋላ የእስክንድያ ፮ኛው ጳጳስ የሆነው ዩስቱስ እንደ ተሾመ ይታመናል። ተቋሙ ያስተማረው ከሥነ መለኮት፣ መጽሐፍ ቅዱስና ...

                                               

ጄተቨነራመየ

ጄተቨነራመየ በአኑራደፑረ፣ ስሪ ላንካ የሚገኝ ጥንታዊ የቡዲስም ትልቅ ገዳምና ቤተ መቅደስ ነበር። በ270 ዓክልበ. በንጉስ መሃሴነ ተመሠረተ። እስከ 1157 ዓም ድረስ ቆመ። ከእርሱ በፊት ትልቁ የጤራቫዳ ቡዲስም ተቋም አኑራደፑረ መሃቪሃረ ከ244 ዓክልበ. ጀምሮ ይኖር ነበር፤ በ80 ዓክልበ. ግን 300 መኖክሶች ከመሃቪሃረ ተገንጥለው ወደ አዲሱ አበየጊረ ተዛውረው አዲስ የቡዲስም ወገን ጀ ...

                                               

ጎንደሻፑር አካዳሚ

ጎንደሻፑር አካዳሚ በጎንደሻፑር፣ ፋርስ የነበረ የኔስቶራዊ ክርስትና ከፍተኛ ትምህርት ቤት ነበረ። ያቀረባቸው ትምህርቶች በሕክምና፣ ፍልስፍና፣ ስነ መለኮትና ስነ ፍጥረት ነበሩ። መጀመርያ እንደ ኔስቶራዊ ገዳም በ263 ዓም ተመሠረተ። ከ521 ዓም ከፋርስ መንግሥት ንጉስ ኾስራው ጀምሮ ዝነኛ ትምህርት ተቋም ሆነ። ከቢዛንታይን የሸሹት ኔስቶራዊ ስደተኞች የሕክምና፣ ስነ ፈለክ፣ እና የፍልስፍና ...

                                               

ጊዜ

ጊዜ ኩነቶችን ለመደርደር፣ ቆይታቸውን ለማነጻጻር፣ በመካከላቸውም ያለፈውን ቆይታ ለመወሰን በተረፈም የነገሮችን እንቅስቃሴ መጠን ለመለካት የሚያገለግል ነገር ነው። ጊዜ በፍልስፍና፣ ሃይማኖት፣ ሳይንስ ውስጥ ብዙ ጥናት የተካሄደበት ጽንሰ ሃሳብ ቢሆንም ቅሉ እስካሁን ድረስ በሁሉ ቦታ ለሁሉ የሚሰራ ትርጓሜ አልተገኘለትም። የጊዜ መተግበሪያ ትርጉም ለዕለት ተለት ኑሮ ጠቃሚነቱ ስለታመነበት ከዘ ...

                                               

ቅፅበታዊ ምላሽ

ቅፅበታዊ ምላሽ የአንድ ሲስተም ምላሽ ማለት የሲስተም ውጤት ለእያንዳንዱ ፍሪኩዌንሲ ኦፍ ኢንፑቱ ስቴፕ ኢንፑት የሲስተም ውጤት ለኢንፑት ከአንድ ደረጃ ወደ ሌላ እና የሲስተም ውጤት ምን ያህል ስቴብል እንዲሁም ሴትል እስኪያደርግ ያለውን ሁኔታ መለኪያ ኢምፐልስ ኢንፑት የሲስተም ውጤት ለሁሉም ፍሪኩዌንሲ በተመሳሳይ የኢንፑት ማግኒቱድ መጠን የሲስተም ምላሽ ለሆነ ቅፅበታዊ ውጫዊ ኢንተርፊራንስ ...

                                               

የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት

የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት በአውሮፓ አገሮች መኻል ከ ፲፱፻፮ ዓ/ም እስከ ፲፱፻፲፩ ዓ/ም መግቢያ፣ ለአራት ዓመታት የተካሄደ ጦርነት ነው። ይኼ ግጭት የዘመኑ ኃያላን አገራት በሁለት ተቃራኒ ወገን ተሰልፈው ያካሄዱት ግብግብ ሲሆን እስከ ሰባ ሚሊዮን ታጣቂዎች የተካፈሉበትና እስከ አስራ አምስት ሚሊዮን አውሮፓውያን ሕይወታቸውን ያጡበት ትልቅ ጦርነት ነው።

                                               

የባንጯን ውግያ

የባንጯን ውግያ በቻይና ልማዳዊ ታሪክ መሠረት በጥንት የተካሔደ ግጥሚያ ነበረ። በዚህ ጦርነት የኋንግ ዲ ወገን ወይም ዮውሥዮንግ በያንዲ ወገን ወይም ሸንኖንግ ላይ ድል አደረገ። ከዚህ ድል በኋላ ሁለቱ ወገኖች በኋንግ ዲ ሥር ተባብረው አንድላይ ኋሥያ የተባለ ብሔር ፈጠሩ። ይህም ኋሥያ ነገድ የዛሬው ቻይናዊ ዘር አባቶች ነበሩ። በአንድ ልማዳዊ አቆጣጠር ይህ ውግያ 2600 ዓክልበ. ገደማ የ ...

                                               

የዥዎሉ ውግያ

የዥዎሉ ውግያ በቻይና ልማዳዊ አፈ ታሪክ ዘንድ በ2331 ዓክልበ. ግድም በዥዎሉ አካባቢ የተደረገ ታልቅ ውግያ ነበረ። ይህ ከባንጯን ውጊያ በኋላ ትቂት ዓመታት በኋላ ይሆናል። በዚሁ ውግያ የኋንግ ዲ ኃያላት የኋሥያ ወገን በቺ ዮው ሠራዊት ላይ ድል አደረጉ። ይህ ቺ ዮው የ81 ጎሣዎች አለቃ ነበር ይባላል። በውግያው ቺ ዮው ጉምን በጥንቆላ ፈጥሮ ኋንግ ዲ "ደቡብ አመልካች ሠረገላ" የተባለ ...

                                               

የ፳፻፫ ዓ.ም. የሊቢያ ሕዝባዊ አብዮት

የ፳፻፫ ዓ.ም. የሊቢያ ሕዝባዊ አብዮት በሊቢያ ውስጥ የተከሰተ እና በሰሜን አፍሪቃ በተከታታይ ከተደረጉ የተለያዩ ሀገራት ፀረ መንግስታዊ አብዮቶች አንዱ ነው። ይህ አብዮት የተጀመረው በእ.አ.አ. 15 ፌብሩዋሪ 2011 ሲሆን በዚሁ ወር መጨረሻ አካባቢ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች ተባብሶ ታይቷል። አብዮቱ በዋናነት የኮለኔል ሞአመር ጋዳፊን የ42 ዓመታት የስልጣን ላይ ቆይታ በመቃወም ነው። ...

                                               

ንሴት

ማባዛት ተደጋጋሚ መደመር እንደሆነ ሁሉ ንሴት በተራው ተደጋጋሚ ብዜት ነው። ንሴት የሚወከለው ከአንድ ቁጥር ጎን በላይ በተቀመጠ ሌላ ቁጥር ነው። ለምሳሌ: x y {\displaystyle x^{y}}. እዚህ ላይ x መሰረት ቁጥር ሲባል y ደግሞ ንሴቱ ይባላል። ትርጓሜውም ፣x ቁጥር y ጊዜ እራሱን ሲያበዛ ማለት ነው። ለምሳሌ 2 3 {\displaystyle 2^{3}}, 2 መሰረት ሲሆን፣ 3 ...

                                               

ጆን ኔፐር

ጆን ኔፐር – ስኮትላንዳዊ ሓሳቢ ፣ የተፈጥሮ ህግጋት ጥናት ተመራማሪ፣ ሥነ ፈለክ አጥኚ እና ኮኮብ ቆጣሪ ነበር። ከሁሉ ስራው በታሪክ ቀደምት ስሙ እሚነሳው ሎጋሪዝምን በመፈልስፉ ነበር። ይህን የሂሳብ መሳሪያ የፈለስፈበት ዋና ምክንያት ከኮምፒውተር እና ካልኩሌተር ርቆ በሚገኘው ዘመን ቁጥሮችን ማባዛት፣ ጊዜ የሚወስድ፣ ለስህተትም የተጋለጠ መሆኑ ነበር። ሎጋሪዝም ማባዛትን ወደ መደመር በመ ...

                                               

ሌዮናርድ ኦይለር

ሌዮናርድ ኦይለር የ18ኛው ክፍለ ዘመን ታላቁ ሂሳብ ተመራማሪ ተብሎ ሲታወቅ ፣ በሂሳብ ጥናት ውስጥ በጣም ሰፊና ሁሉን አቀፍ አዳዲስ ጽሁፎች ሲያቀርብ፣ ባጠቃላይ 886 የሚሆኑ ጥናታዊ ህትመቶችን አበርክቷል። የሚገርመው ከዚህ ካበረከተው ጽሁፍ ውስጥ አብዛኛው የተጻፈው በመጨረሻወቹ ሃያ አመታቱ ሲሆን በዚህ ወቅት አይነ-ስውር ነበር። ኦይለር የተወለደ ባዝል ከተማ ስዊትዘርላንድ ቢሆንም ብዙው ...

                                               

ማንዴልብሮት

ቤንዋ ማንዴልብሮት ታዋቂ የ20 ና የ21ኛው ክፍለዘመን ሒሳብ ፈልሳፊና ተመራማሪ ነበር። የፍርክስክስ ጂዖሜትሪ አባት ተብሎ የሚታወቀው ይህ ሰው በዚህ በፈጠረው የሂሳብ ጥናት ዘርፍ ቅጥ የለሽና የተፈረካከሱ የጂዖሜትሪ ቅርጾችን ፣ በተለይ ባጎላናቸው ከራሳቸው ጋር ተመሣሣይነት ያላቸውን ክስተቶችን በሂሳብ እኩልዮሽ ለመግለጽ ችሏል።ማንድልብሮት ፖላንድ አገር ተወልዶ በህጻንነቱ ፈራንሳይ አደገ ...

                                               

ረኔ ዴካርት

ሬኔ ደካርት ፈረንሳዊ ሳይንቲስት፣ ሂሳብ ተመራማሪ እና ፈላስፋ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ የዘመናዊ ፍልስፍና አባት በመባል ይታወቃል። ሶስት ምክንያቶች ይጠቀሳሉ። የመጀመሪያዊ፣ ከጥንት ዘመን ጀምሮ ይሰራበት የነበረውን ምሁራዊ አሪስጣጣሊያውነትን ለመጀመሪያ ጊዜ ከአስተሳሰብ ዘዴው ያሰዎገደ ፈላስፋ በመሆኑ። ሁለተኛው ምክንያት የአዕምሮ እና አካል ሁለት እና እማይቀላቀሉ ነገሮች መሆን አስተ ...

                                               

አል ኪንዲ

አቡ ዩሱፍ የዕቁብ ኢብኑ ኢስሃቅ አል-ኪንዲ በ 800 እ.ኤ.አ. አካባቢ በኩፋ ነበር የተወለደው። አባቱ የኸሊፋ ሃሩን አር-ረሺድ ባለሥልጣን ነበር። አል-ኪንዲ በአል- መእሙን፣ አል-ሙእተሲም እና በአል- ሙተወኪል ዘመን የኖረ ሲሆን በዋናነትም በባግዳድ ነው ያደገው። በአል-ሙተወኪል ዘመን ለኸሊፋው ተቀጥሮ በካሊግራፈርነት የእጅ ፅሁፍ ጥበብ ሠርቷል። በፍልስፍና አመለካከቱ የተነሣ የሙስሊሞ ...

                                               

ዩክሊድ

ዩክሊድ ወይንም የእስክንድርያው ዩክሊድ የጥንቱ ዘመን ገናና የሒሳብ ተማሪ ነበር። ዩክሊድ እስክንድርያ፣ ግብፅ አገር በእስክንድርያ ቤተ መጻሕፍት ተቀጥሮ ይሰራ ነበር። ከዘመኑ ርዝመትና ከመዝገብ መጥፋት አንጻር፣ የዩክሊድ ህይወት ታሪክ እምብዛም አይታወቅም።

                                               

ጋውስ

ካርል ፍሪድሪች ጋውስ የጀርመን አገር ዋና ታዋቂ እንዲሁም በብዙወች ዘንድ የአለም አንደኛ ሂሳብ ፈልሳፊ በመባል የሚታወቅ የጎቲጄን ከተማ ዜጋ ነበር። ጋውስ በሂወት ዘመኑ ለብዙ የዕውቀት ዘርፎች አስተዋጾ አበርክቷል ነገር ግን የሱ ዋና ስራወች በሥነ ፈለክ በሥነ ቁጥር ጥናቶች ላይ ነበር። አፈ ታሪክ ይሁን እውነተኛ ታሪክ ስለ ጋውስ የሚነገር ዝና አለ። የአንደኛ ደረጃ ክፍል ተማሪ እያለ ...

                                               

ፓይታጎረስ

ፓይታጎረስ በጥንቱ ግሪክ ስሙ የገነነ ሐሳቢ እና ፈላስፋ ነበር፤ የተወለደው ከክርስቶስ ልደት በፊት በ580 ዓክልበ. ሲሆን የሞተውም በ500 ዓክልበ. ነው። በአሁኑ ዘመን ታዋቂነቱ የሚመነጨው የፓይታጎረስ እርጉጥ የተባለውን የሂሳብ ቀመር በማግኘቱ ነው። በኖረበት ዘመን ፓይታጎሪያንስ የተሰኙ ቁጥር አምላኪ ቡድኖችን በመመስረቱ ይጠቀሳል። ፓይታጎረስ፣ በጥንቱ ዘመን ከነበረው የገነነ ስም አን ...

                                               

ማትሪክስ

ማትሪክስ ማለት በአራት ማዕዘን የተደረደሩ ቁጥሮች ማለት ነው። ማትሪክስ የሚለው ቃል ከላቲኑ "ማተር" የመጣ ሲሆን ትርጉሙም እናት ማለት ነው። እናት የሚለው ቃል ለምን የአራት ማዕዘን ድርድር ቁጥሮች ስም እንደሆነ ወደኋላ እናያለን። ማትሪክሶች አጻጻፋቸው እንዲህ ይመስላል A = {\displaystyle {\begin{bmatrix}10&5&222\\\end{bmatrix}}} ከዚህ ...

                                               

ሥነ ስብስብ

ሥነ ስብስብ የሒሳብ ቅርንጫፍ ሲሆን ትኩረት ሰጥቶ የሚያጠናው ስብስቦችን ነው። ስብስብ ማለቱ ተለይተው ሊታወቁ የሚችሉ ነገሮችን ክምችት ወይም ቡድን ነው። የሥነ ስብስብ ኅልዮት በጣም መሰረታዊ ከመሆኑ የተነሳ ማናቸውንም የሒሳብ ቅርንጫፎች በርሱ ቋንቋ መጻፍና መተርጎም ይቻላል። ከቀላልነቱም አንጻር በመዋዕለ ሕጻናትና በአንደኛ ደረጃ ትምህርትቤቶች ደረጃ ሳይቀር ለህጻናት ቢቀርብ ምንም ጉዳ ...

                                               

ስብስብ

ስብስብ ሲባል ተለይተው ሊዘርዘሩ የሚችሉ ነገሮች ክምችት ማለት ነው። ሥነ ስብስብ የሒሳብ ጥናት መሰረት ከመሆኑ የተነሳ በአሁኑ ወቅት በሁሉም የሂሳብ ዘርፎች ሰርጾ ይገኛል። ስለሆነም ከመዋዕለ ህጻናት እስከ ዩኒቨርስቲወች ድረስ የስብስብ ጥናት እንደ ትምህርት ይሰጣል።

                                               

ታህታይ ስብስብ

ማናቸውም የስብስብ A አባላት የስብስብ B አባላት ከሆኑ፣ A የ B ታህታይ ስብስብ ነው እንላለን። ሲጻፍ A ⊆ B ። በዚህ ትይዩ እንዲህ በለንም መጻፍ እንችላለን B ⊇ A, ሲነበብ B የA ላዕላይ ስብስብ ነው ወይም B ስብስብ Aን ይጠቀልላል ። A የ B ታህታይ ስብስብ ሆኖ ነገር ግን ሁለቱ ስብስቦች እኩል ካልሆኑ, A የ B ደንበኛ ታህታይ ስብስብ ይሰኛል፣ በሒሳብ ምልክት ሲጻፍ A ...

                                               

አስረካቢ

በሒሳብ ጥናት አስረካቢ አንድን ብዘት ከሌላ ብዘት ጋር ያጣምራል። የመጀመሪያው ተጣማሪ ብዘት ግቤት ይባላል፣ ሁለተኛው ውጤት ይሰኛል። አስረካቢ ምንግዜም አንድ ግቤት ወስዶ ለአንድ ብቻ ውጤት ያስረክባል እንጂ ለሁለት ውጤቶች አይሰጥም። ይህ ባህሪው ከሌላ አይነት ዝምድና ይለየዋል። አስረካቢ በአብዛኛው እንዲህ ይጻፋል f ፣ ሲነበብ "ኤፍ ኦፍ ኤክስ" ወይን የ ኤክስ አስረካቢ ይባላል።

                                               

ካርቴዥያዊ ብዜት

እያንዳንዷን የአንድ ስብስብ አባላት ከሌላው ስብስብ አባላት ጋር በማያያዝ አዲስ ስብስብ መፍጠር ይቻላል። የ ስብስብ A እና B ካርቴዥያዊ ብዜት እንዲህ ይወከላል A × B ፤ ትርጓሜውም የቅደም ተከተል ጥንዶች ስብስብ ሆኖ ሲያበቃ፣ a እዚህ ላይ የስብስብ A አባል ሲሆን b ደግሞ የስብስብ B አባል ነው ማለት ነው።ብብ ምሳሌ: {1, 2} × {1, 2} = {1, 1, 1, 2, 2, 1, 2 ...

                                               

ወጋኝ አግላይ መርህ

ዋና መጣጥፍ፦ ወጋኝ አግላይ መርህ ወጋኝና አግላይ መርህ የብዙ ስብስቦችን ውህድ ብዛት ከተዋሃዱት ስብስቦች ቁጥር እና ከጋራ አባላቶቻቸው ብዛት አንጻር የሚያገኝ ነው። ለምሳሌ ሁለት ስብስቦችን A እና B ን ብንወስድ፣ የውህደታቸው ብዛት የእያንዳንዱ ስብስብ A እና B ብዛት ተደምሮ፣ ከዚህ ላይ የጋራ የሆኑት አባላቶች ብዛት ሲቀነስ ማለት ነው። ምክንያቱም የእያንዳንዱ ስብስብ አባላት ሲደ ...

                                               

የመደመር ህግ

አንድን ነገር ለማድረግ a መንገዶች ቢኖሩ እና ሌላ ነገር ለማድረግ b መንገዶች ቢኖሩ፣ ሁልቱን በአንድ ጊዜ ማድረግ ባይቻል፣ ከሁሉ አንድ ነገር ለማድረግ a + b መንገዶች አሉ ማለት ነው። አንድን ነገር ለመምረጥ a መንገዶች ቢኖሩ እና ሌላ ክዚህ ነገር ጋር የማይገናኝ ነገር ለመምረጥ b መንገዶች ቢኖሩ፣ ሁሌቱን አንድ ላይ መምረጥ ባይቻል፣ ከሁልቱ አንዱን ለመምረጥ a + b መንገዶች ...

                                               

የስብስብ ብዛት

የስብስብ ብዛት የምንለው የአንድ ስብስብ አባላትን ብዛት ነው። ለምሳሌ የስብስብ B ብዛት በሒሳብ ምልክት እንዲህ ይወከላል፡ | B | ። ለምሳሌ፡ ስብስብ B የፈረንሳይ ባንዲራ ቀለሞች ስብስብ ቢሆን፣ የ B ብዛት ሲሰላ | B | = 3 ነው፣ ምክንያቱም የፈረንሳይ ባንዲራ ቀለሞች 3 ናቸውና። ባዶ ስብስብ የምንለው ልዩ ስብስብ በውስጡ ምንም አባላት የሉትም ስለሆነም ብዛቱ ዜሮ ነው እንላለ ...

                                               

የቆጠራ መርሆች

የሥነ ጥምረት ውጤቶችን ለማረጋገጥ የሚረዱ መሰረተ ሃሳቦች የጥምረት መርሆች በመባል ይታወቃሉ። የመደመር ሕግ፣ የማባዛት ሕግ እና ወጋኝና አግላይ መርህ ለቆጠራ የሚያገለግሉ የሥነ ጥምረት መርሆች ናቸው። ሁለት ስብስቦች አንድ አይነት የአባላት ብዛት እንዳላቸው ለማረጋገጥ ደግሞ የተጣምዶ ማረጋገጫ ሚባለው መሰረተ ሃሳብ ይረዳል። የደበኔ ሳጥን መርህ ብዙ ጊዜ ያንድን ነገር መኖር ወይም ደግሞ ...

                                               

የውጭ ስብስብ

ሁለት ስብስቦች ሊቀናነሱ ይችላሉ። A \ B ማለቱ ማናቸውም በ A ውስጥ ኖረው ነገር ግን በ B የማይገኙ አባላት ስብስብ ማለቱ ነው። በአንድ አንድ ስሌቶች ማናቸውም ስብስቦች የአቃፊያቸው አለም አቀፍ ስብስብ አባል እንደሆኑ ተደርገው ሊወሰዱ ይችላሉ። ይህ ሁሉን አቃፊ ስብስብ እንዲህ ይወከላል፡ U ። በዚህ ጊዜ U \ A የ A ውጭ ወይንም የ A ተቃርኖ ይሰኛል። ምሳሌ: {1, 2} \ { ...

                                               

ቁጥር

ቁጥር ፦ ለመቁጠር ወይም ደግሞ ለመለካት የምንጠቀምበት የሂሳብ ቁስ ነው። ቁጥሮች ከዚህ ከሁለቱ ጥቅማቸው ውጭ በአሁኑ ጊዜ ለልዩ ልዩ ጥቅም ይውላሉ። ለምሳሌ፦ አንድን ነገር ለመለየት ፣ ለመደርደር ፣ ኮድ ለማበጀት ከብዙ በጥቂቶቹ ናቸው። አንድንድ ሂደቶች አንድ ወይም ሁለት ቁጥሮችን ወስደው ሌላ ቁጥርን ይሰጡናል። እኒህ ሂደቶች ኦፕሬሽን ይባላሉ። ለምሳሌ ቁጥር ሲስጠን ቀጣዩን ቁጥር የም ...

                                               

የአቅጣጫ ቁጥር

የአቅጣጫ ቁጥር በእንግሊዝኛ Complex Number የሚባል ሲሆን የእንግሊዝኛው ስሙ ግን ስህተት ወይም የሚያምታታ ነው። የአቅጣጫ ቁጥሮች ሲጻፉ ባጠቃላይ መልኩ a+jb ወይም a+ib በሚል ሲገለጹ፣ a ና b የውን ቁጥር ሲሆኑ፣ i ወይም j ደግሞ ንጹህ የአቅጣጫ ቁጥር ናቸው፣ ዋጋቸውም − 1 {\displaystyle {\sqrt {-1}}} ነው።

                                               

ፓይ

ፓይ ወይም በተለምዶ አጻጻፉ π የሚታወቀው ቁጥር የማንኛውም ክብ መጠነ ዙሪያ ለወገብ ርዝመት ሲካፈል የሚገኘው ምንጊዜም የማይቀየረው ቋሚ ቁጥር ነው። የፓይን እርግጠኛ ዋጋ ማወቅ ባይቻለም ከ 3.141593 እንደሚጠጋ ግን በሂሳብ ስሌት የተደረሰበት ጉዳይ ነው። የፈለግነውን ሁለት ሙሉ ቁጥሮች አካፍለን ፓይን ማግኘት ስለማንችል ኢራሽናል ቁጥር ነው ማለት ነው። በዚህ ምክንያት ፓይ በነጥብ ...

                                               

ስነ አምክንዮ

አምክንዮ ምንድን ነው? ሥነ - አምክንዩ የምክንያት አሰጣጥ 1 ጥናት ማለት ነው። ምንም እንኳ አምክንዮ ለሁሉም የዕውቀት ዘርፍ አስፈላጊ ቢሆንም፣ ትኩረት ተሰጦት የሚጠናው ግን በ ፍልስፍና ፡ በ ሒሳብ እና በ ኮምፒውተር ሳይንስ የዕውቀት ዘርፎች ዘንድ ነው። አምክንዮ አጠቃላይ የክርክርን ቅርፅ፣ የትኛው የክርክር ቅርፅ ትክክል ነው፣ የትኛው ስህተት ነው የሚሉትን ጥያቄወች ይፈትሻል። በፍ ...

                                               

አጋጣሚ ዕውነት

አጋጣሚ ዕውነት ማለት ውሸት ሊሆን ይችል የነበር፣ ነገር ግን ዕውነት የሆነ ረቂቅ ማለት ነው። በሌላ አነጋገር፣ አሁን ካለው ዓለም ሌላ፣ ሌሎች ዓለማት ቢፈጠሩ ኑሮ ፣ በነዚህ አለሞች ዕውነት ሊሆን፣ ወይም ደግሞ ውሸት ሊሆን ይችል የነበር ረቂቅ ማለት ነው። ለምሳሌ፦ በፀሐይ ዙሪያ ፱ ፈለኮች አሉ። ይሄ ዕውነት ቢሆንም፣ ነገር ግን ውሸት ሊሆን ይችል የነበር ረቂቅ ነው። ለምሳሌ ከአሁን አ ...

                                               

እርግጥ

እርግጥ በሒሳብ ወይም በሥነ-አምክንዮ ሲተረጎም የአምክንዮን ህጎች ተጠቅመን ያረጋገጥነው አረፍተ ነገር ማለት ነው። የምናረጋግጠው እንግዲህ እሙኖችወይም ሌሎች እርግጦችን በአምክንዮ እያጣመርን በማያያዝ ነው። የሂሳብና አምክንዮ አረፍተ ነገሮች ብዙውን ጊዜ የሚረጋገጡት የጥገኛ አምክንዮ ዘዴን በመጠቀም ነው። ለዚህ ምክንያቱ የእርግጡ አረፍተ ነገሮች ከአንድ መነሻ አርፍተነገርና ከዚያ አረፍተ ...

                                               

የተቃርኖ አራት ማዕዘን

የተቃርኖ አራት ማዕዘን በአራቱ የተቃራኒ አይነቶች መካከል ያለውን ዝምድና እና ልዩነት የሚያሳይ የሥነ አመክንዮ ዘዴ ነው። ሁሉም ተቃርኖዎች አንድ አይነት አይደሉም። ለምሳሌ፦ ረቂቅ ፩) ሁሉም ሰው ኬኒያዊ ነው። ረቂቅ ፪) ምንም ሰው ኬኒያዊ ነው። ረቂቅ ፫) አንድ ሰዎች ኬኒያዊ አይደሉም። ረቂቅ ፬) አንድ ሰዎች ኬኒያዊ ናቸው። ረቂቅ ፩ን የሚመስሉ ዓይነት ዓረፍተ ነገሮች ሁለንተናዊ አዎ ...

                                               

የአስተሳሰብ ሕግጋት

የአስተሳሰብ ሕግጋት ማለት ማናቸውም ስሜት የሚሰጡ ሐሳቦች ሊከተሉዋቸው የሚገቡ ሕግጋት ማለት ነው። ይህ ፈላስፎች በዘመናት ላይ ያገኙት አንድ የሥልጣኔ ምርት ነው። እነዚህ ሕግጋት እጅግ መሠረታዊ እና ሁሉም የዕውቀት ዘርፍ ሊከተሏቸው የሚገባ ብቻ ሳይሆን በዕለት ተዕለት ኑሮ ሳይቀር ሊተገበሩ የሚገቡ ናቸው። የሕግጋቱ ብዛት ሦስት ሲሆን እንደሚከተለው ይዘረዘራሉ፦ ሕግ ፩)የተቃርኖ ሕግ ፦ ...

                                               

በር: ፍልስፍና/የተመረጠ ጽሑፍ/29

የአስተሳሰብ ሕግጋት የአስተሳሰብ ሕግጋት ማለት ማናቸውም ስሜት የሚሰጡ ሐሳቦች ሊከተሏቸው የሚገቡ ሕግጋት ማለት ነው። ይህ ፈላስፎች በዘመናት ላይ ያገኙት አንድ የሥልጣኔ ምርት ነው። እነዚህ ሕግጋት እጅግ መሠረታዊ እና ሁሉም የዕውቀት ዘርፍ ሊከተሏቸው የሚገባ ብቻ ሳይሆን በዕለት ተዕለት ኑሮ ሳይቀር ሊተገበሩ የሚገቡ ናቸው። የሕግጋቱ ብዛት ሦስት ሲሆን እንደሚከተለው ይዘረዘራሉ፦ ሕግ ፩ ...