ⓘ Free online encyclopedia. Did you know? page 13
                                               

የምስራቅ አፍሪካ የሃይል ማእከል

ኢትዮጵያ ለኮሜሳ የሃይል አቅርቦት አይነተኛ ሚና አላት። የተፈጥሮ ሀብቷን በጥቅም ላይ በማዋል በአሁኑ ጊዜ ለጅቡቲና ለሱዳን ንፁህ ሀይል እንደምታቀርብ ይታወቃል። የምስራቅ አፍሪካ የሃይል ማእከል ለሙሉ ሲተረጎም ደግሞ፡ የኢትዮጵያ ሀይል ዘጠኝ የምስራቃዊ አፍሪካ አገሮችን ያቆራኛል። እነዚህም ከጅቡቲና ከሱዳን በተጨማሪ፦ ኬንያ፣ ታንዛኒያ፣ ሩዋዳ፣ ዩጋንዳ፣ ቡሩንዲና የኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ረ ...

                                               

የቪዛ መስፈርቶች ለኢትዮጵያ ዜጎች

የቪዛ መስፈርቶች ለኢትዮጵያ ዜጎች በየአገሩ ይለያያሉ። የኢትዮጵያ ዜጎች ወደ ብዙዎቹ አገራት ለመግባት፣ አስቀድሞ ከዚያው አገር ኤምባሲ ወይም ቆንስላ በፓስፖርት ውስጥ የቪዛ ማሕተም ማግኘት አስፈላጊነት ነው። ሆኖም አንዳንድ አገር ያለ ምንም ቪዛ ሂደት ኢትዮጵያውያን ለተወሰነ ጊዜ እንዲጎብኙ ይፈቅዳል፣ እንዲሁም አንዳንድ አገር ኢትዮጵያውያን እዚያ በደረሱበት ጊዜ የመግቢያ ፈቃድ ይሰጣል። ...

                                               

ሴይር

ሴይር ተራራ ከሞት ባሕርና አቃባህ ወሽመጥ መካከል ያለው ተራራማ አገር ነው። ይህ የኤዶምያስ ደቡብ-ምሥራቅ ጠረፍ ከይሁዳህ ጋር ነበረ። ምናልባትም ከዚያ በፊት የግብጽ ጠረፍ በከነዓን ይሆናል። ሴይር ተራራ ስሙን ከ "ሖሪው ሴይር" አገኘ። የሖራውያን ጎሣ መታወቂያ ወይም ተወላጅነት በመጽሐፍ ቅዱስ ባይሰጥም፣ የዚህ ሴይር ልጅ ፅብዖን ደግሞ ኤዊያዊ በመባሉ ዘፍጥ. ፴፮ የከነዓን ዘር ይመስላ ...

                                               

ትርኪ ተራራ

ትርኪ ተራራ በቱልሳ አካባቢ ኦክላሆማ ክፍላገር አሜሪካ ውስጥ ከአርካንሳው ወንዝ አጠገብ የሚገኝ ሲሆን እንዲያውም ተራራ ሳይሆን ትልቅ ኮረብታ ነው። በዚያ ላይ በተገኙት ድንጋዮች ላይ ያሉት ምልክቶች የጥንታዊ አሜሪካ መዝገቦች ተብለዋል። በአንድ ዋሻ ውስጥ የተቀረጹት ስዕሎችና ምልክቶች ከውቅያኖስ ማዶ የመጡት መርከበኞች ሥራ መሆናቸውን አንዳንድ ምሁር ያምናል። በዋሻው የሚታይ አንዱ ምልክ ...

                                               

ፒሬኔ ተራሮች

ዲዮዶሮስ ሲኩሉስ 60 ዓክልበ. ግድም እንደ ጻፈው V. 35 በጥንት ከእረኞች አለመጠንቀቅ የተነሣ አንድ ታላቅ እሳት ዙሪያውን በሙሉ ስላቃጠለ የተራሮቹ ስም ከ "እሳት" ፒር ወይም ፑር በግሪክኛ መጣ። በመቃጠላቸው ምክንያት የብር ፈሳሾች ተገለጡ። የፊንቄ ሰዎች ሲደርሱ ብር እንደ ርካሽ ዕቃ አገኝተውት ከኗሪዎቹ በንግድ ገዝተውት እንደ በለጠጉ ይለናል። በኋላ ግን የሮሜ ደራስያን ሉካን 60 ...

                                               

ምሥራቅ

ምስራቅ የሚለው ቃል ስም፣ የስም ገላጭ ወይም የግሥ ገላጭ ሊሆን ይችላል፣ ከአራቱ ዋና የአቅጣጫ መጠሪያዎች አንዱ ነው። ይህ አቅጣጫ ለምዕራብ ተቃራኒ ሲሆን ለሰሜን እና ለደቡብ ደግሞ ቀጤ ነክ ነው። እንደ ስምምነት ሁኖ የማንኛውም ካርታ ቀኝ ምስራቅ ተደርጎ ይወሰዳል።

                                               

ምዕራብ

ምዕራብ የሚለው ቃል ስም፣ የስም ገላጭ ወይም የግሥ ገላጭ ሊሆን ይችላል፣ ከአራቱ ዋና የአቅጣጫ መጠሪያዎች አንዱ ነው። ይህ አቅጣጫ ለምስራቅ ተቃራኒ ሲሆን ለሰሜን እና ለደቡብ ደግሞ ቀጤ ነክ ነው። እንደ ስምምነት ሁኖ የማንኛውም ካርታ ግራ ምዕራብ ተደርጎ ይወሰዳል።

                                               

ሰሜን

ሰሜን የሚለው ቃል ስም፣ የስም ገላጭ ወይም የግሥ ገላጭ ሊሆን ይችላል፣ ከአራቱ ዋና የአቅጣጫ መጠሪያዎች አንዱ ነው። ይህ አቅጣጫ ለደቡብ ተቃራኒ ሲሆን ለምስራቅ እና ለምዕራብ ደግሞ ቀጤ ነክ ነው። እንደ ስምምነት ሁኖ የማንኛውም ካርታ የላይኛው ክፍል ሰሜን ተደርጎ ይወሰዳል። ደግሞ ይዩ፦ ስሜን ዋልታ

                                               

የስልክ መግቢያ

ሰይንት ኪትስና ኒቨስ - 1-869 ዶሚኒካን ሬፑብሊክ - 1-809 እና 1-829 አንቲጋ እና ባርቡዳ - 1-268 በርሙዳ - 1-441 ካናዳ - 1 ግረኔዳ - 1-473 የብሪታንያ ቭርጂን ደሴቶች - 1-284 ትሪኒዳድና ቶቤጎ - 1-868 ዶሚኒካ - 1-767 አሜሪካ - 1 ሞንትሰራት - 1-664 ሰይንት ሉሻ - 1-758 ቅዱስ ቭንሰንትና ዘ ግረናዲንስ - 1-784 አንጊላ - 1-264 ካይ ...

                                               

ሒሚልኮን

ሒሚልኮን የቀርጣግና መርከበኛና ተጓዥ ነበረ። የግሪክ ጸሐፊ ትልቁ ፕሊኒ እንደሚለን፣ ንጉሥ 2 ሓኖ የአፍሪካን ጠረፍ በተጓዘበት ዘመን ሒሚልኮን ደግሞ ከጋዲር ወጥቶ ወደ ስሜን በመዞር የአውሮጳን ጠረፍ ለመጓዝ ተላከ። ሆኖም ከፕሊኒና ከአዌኑስ ጥቅሶች በቀር፣ ስለ ሒሚልኮን ጉዞ ምንም መረጃ አሁን አይኖርም። አዌኑስ እንደ ጠቀሰው፣ ከ4 ወር አደገኛ የመርከብ ጉዞ በኋላ "ዌስትሩምኒዴስ" ደሴ ...

                                               

ክሪስቶፎር ኮሎምበስ

ክሪስቶፎር ኮሎምበስ በሰሜን ምዕራብ ጣሊያን፣ ጀኖዋ ከተማ በ1451 እ.ኤ.አ. የተወለደ ነጋዴና አገር አሳሽ ነበር። የአረፈውም በ1506 እ.ኤ.አ. በቫላዶሊድ ስፔን ነበር። ኮሎምበስ በ14 አመቱ የባህር ጉዞ እንደጀመረ ዜና መዋዕሉ ያትታል። ይሁንና በአሁኑ ዘመን የሚታወቀው የአሜሪካን አህጉር በ1492 እ.ኤ.አ. ስለደረሰበት ነው። የኮሎምበስ የጉዞ አላማ ቻይናንና ህንድን ከአውሮጳ ጋር ...

                                               

ጋን ዪንግ

ጋን ዪንግ በ89 ዓ.ም. በቻይና አበጋዝ ባን ቻው ወደ ሮማ የተላከ የቻይና ተልእኮ ተወካይ ነበር። ወደ ጳርቴ ምዕራብ ጠረፍ ከገሰገሱት ከባን ቻው ሳባ ሺህ ጭፍሮች አንዱ ነበር። ጋን ዪንግ ምናልባት እስከ ሮማ ከተማ ድረስ መቸም ባይደርስም፣ በታሪካዊው መዝገብ እንደተመለከተው ከቻይናውያን ሁሉ በጥንት ወደ ምዕራብ የተጓዘው እሱ ሲሆኑ የተቻለውን መረጃ ስብስቦ ተጽፎ ነበር። ሆው ሀንሹ በተ ...

                                               

ሉሉቢ

ሉሉቢ ወይም ሉሉቡም በ2400-1900 ዓክልበ. ግድም በዛግሮስ ተራሮች በዛሬው ኩርዲስታን የነበረ ጥንታዊ አገር ነበረ። ከተማቸው ሉሉባን ወይም ሉሉቡና በዘመናዊው ሐለብጄ ሥፍራ እንደ ነበር ይታስባል። ሉጋልባንዳና የአንዙድ ወፍ በተባለው የቀድሞ ሱመርኛ ተውፊት ዘንድ፣ በኡሩክ መጀመርያው ንጉሥ በኤንመርካር ዘመን ሉጋልባንዳ የተባለ አለቃ በ "ሉሉቢ ተራሮች" የአንዙድን ወፍ አገኘ። ይህም ...

                                               

ላርሳ

ላርሳ ከ1844 እስከ 1675 ዓክልበ. ድረስ የሜስፖጦምያ ከተማ-ግዛት ነበረ። ከተማው በኤአናቱም ዘመን 2200 አካባቢ መኖሩ ይታወቃል። በ1844 ግን የኢሲን መንግሥት በሱመር ላይኛ ሥልጣን እየሆነ የላርሳ አሞራዊ አለቃ ጉንጉኑም ነጻነቱን ከኢሲን አዋጀ። በ1835 ጉንጉኑም ኡርንም ያዘ። ላርሳና ኢሲን፣ ከ1807 በኋላ ባቢሎንም ተወዳዳሪዎች ነበሩ። በየጊዜ ሦስቱ እርስ በርስ ጦርነት ያድ ...

                                               

ሐማዚ

ሐማዚ ምናልባት በ2420 ዓክልበ. ገዳማ የነበረ መንግሥት ሲሆን በምዕራብ ዛግሮስ ተራሮች ከኤላምና ከአሦር መካከል እንደተገኘ ይታሥባል። ሐማዚ ለሥነ-ቅርስ ጥናት መጀመርያ የታወቀው በዚህ ቦታ ላይ የኪሽ ንጉሥ ኡቱግ ወይም ኡሁብ ድል የሚመዝገብ በጥንታዊ ባለ-ማዕዘን ኩኔይፎርም ጽሕፈት የተጻፈ ጽላት ሲገኝ ነበር። ሌላ ጥንታዊ ጥቅስ ደግሞ ኤንመርካርና የአራታ ንጉስ በተባለ አፈ ታሪክ ተገ ...

                                               

ማርሐሺ

ማርሐሺ በጥንት በኤላም አጠገብ የተገኘ አገር ነበር። በአዳብ ንጉሥ ሉጋል-አኔ-ሙንዱ ግዛት ከ፯ቱ ክፍላገራት ከኤላምና ጉቲዩም መካከል በአንድ መዝገብ ቢቆጠርም፣ ከእላም ምሥራቅ በጂሮፍት አካባቢ እንደ ነበር ይታሥባል። ደግሞ የማርሐሺ አለቃ ሚጊር-ኤንሊል በአመጽ ተነሥቶ ሉጋል-አኔ-ሙንዱ እንደ ተወጋው ይላል። በኋላ የአካድ ንጉሥ ታላቁ ሳርጎን ማሐሺን ያዘ። ሆኖም በሳርጎን ልጅ በሪሙሽ ላ ...

                                               

ምድያም

ምድያም በመጽሐፍ ቅዱስና በቁርዓን የሚጠቀስ አገርና ሕዝብ ነው። በአብዛኛው ሊቃውንት ዘንድ የምድያም ሥፍራ "በስሜን-ምዕራብ አረባዊ ልሳነ ምድር፣ በአቀባ ወሽመጥ ምሥራቅ ዳር፣ በቀይ ባሕር ላይ" ተገኘ። ፕቶሎመይ ደግሞ "ሞዲያና" የተባለ ሠፈር በዚህ አካባቢ አለው። የምድያም ሰዎች ከአብርሃምና ኬጡራ ልጅ ምድያም ተወለዱ ዘፍ. ፳፭፡፪። በዘፍ. ፴፯፡፳፰ የምድያም ልጆች ዮሴፍን በጉድጓድ ...

                                               

ሱመር

ሱመር በጥንታዊ መካከለኛ ምሥራቅ አለም በቅድሚያ ሥልጣኔ የሚባል ኹኔታ የደረሰለት አገር ነበር። ዘመኑ ከታሪካዊ መዝገቦች መነሻ ጀምሮ ይታወቃል። ሱመራዊ ማለት ሱመርኛ የቻሉ ወገኖች ሁሉ ነው። ከጥንታዊ ግብፅ እና ከሕንዶስ ወንዝ ሸለቆ ሥልጣኔ ጋራ ከሁሉ መጀመርያ ሥልጣኔ ካሳዩት አገሮች አንዱ ነው ይባላል።

                                               

ሹቡር

ሹቡር ከሰናዖር ወደ ስሜን በጤግሮስ ወንዝ ላይ የተቀመጠ አገር ነበረ። ይህም ስም በጥንታዊ አማርና ደብዳቤዎችና በኡጋሪት መዝገቦች ሽብር ተጽፎ ተገኝቷል። ከሁሉ ጥንታዊ በሆነ ዘመን፣ ከሰናዖር ሱመር ዙሪያ ሌሎቹ 4 ሩቦች ማርቱ አሞራውያን፣ ሱባርቱ፣ ኤላምና ኡሪ -ኪ አካድ ነበሩ። እንዲሁም ኤንመርካርና የአራታ ንጉስ በተባለው ሱመራዊ አፈ ታሪክ፣ ልሣናት የተደባለቁባቸው አገሮች ሹባር፣ ሐ ...

                                               

አራም (ጥንታዊ አገር)

አራም በመጽሀፍ ቅዱስ የሚጠቀስ ጥንታዊ አገር ነው። ይህ አገር በስሜን መስጴጦምያና ከዚያ ምዕራብ በሶርያ ይገኝ ነበር። በጠቅላላ አራማውያን የኖሩባቸው አገሮች ማለት ነው። እነዚህ የሴም ልጅ አራም ዘር መሆናቸውን የሚል ልማድ አለ። በ መጽሐፈ ኩፋሌ 9፡19 መሠረት፣ የኖህ ልጆች ምድሪቱን ሲያከፋፈሉ የአራም ልጆች የወረሱት ርስት ከኤፍራጥስና ከጤግሮስ ወንዞች መካከል ያለው አገር ሁሉ ያጠ ...

                                               

አራታ

አራታ በሱመር አፈ ታሪክ የተገኘ ጥንታዊ መንግስት ነበር። በዚያው መሠረት አራታ ሀብታም፣ ተራራማ፣ በወንዞቹ ምንጭ ያለበት አገር ይባላል። በተለይ የሚታወቀው ከ4 ጥንታዊ ጽሕፈቶች ነው። እነሱም፦ ኤንመርካርና የአራታ ንጉስ - ሉጋልባንዳ እንደገና በኤንመርካር ሠራዊት አለቃ ሆኖ በአራታ ላይ እንደ ዘመተ ይላል። የታሪክ ሊቃውንት ሁሉ ስለ ስፍራው በአንድነት አይስማሙም፤ ብዙዎቹ የአዘርባይጃ ...

                                               

ኢሲን

ኢሲን ከ1900 እስከ 1709 ዓክልበ. ድረስ የሱመር መጨረሻ ከተማ-ግዛት ነበረ። በ1900 ዓክልበ. የኡር መንግሥት ሥልጣን እየደከመ የኢሲን ገዥ እሽቢ-ኤራ ከኡር ነጻነቱን አዋጀ። ከጥቂት አመት በኋላ በ1879 የኤላም ሕዝቦች ኡርን ዘረፉና የኡር መንግሥት ሲወድቅ ኢሲን ያንጊዜ ላዕላይነቱን በሱመር ያዘ። የኢሲን ንጉሶች እጅግ አረመኔ ተከታዮች ነበሩ። በ1844 የላርሳ ከተማ ገዥ ጉንጉኑ ...

                                               

ኢንካ መንግሥት

የኢንካ መንግሥት ከ1430 እስከ 1525 በደቡብ አሜሪካ በተለይም ፔሩ የነበረ መንግሥት ነው። ቀድሞ በአንዴስ ተራሮች የነበሩት መንግሥታት የቲዋናኩ መንግሥት 300-1150 ዓም ግድም እና የዋሪ መንግሥት 600-1100 ዓም ግድም እንደ ተገኙ ታውቋል። ከነዚህ መንግሥታት ውድቀት በኋላ ከተነሡት አነስተኛ ክፍላገራት አንዱ የቁስቁ መንግሥት በ1190 ዓም ግድም ተነሣ። ይህ የቁስቁ መንግሥት ...

                                               

ኤላም

ኤላም ጥንታዊ ሃገር ነበር። ዛሬ ደቡብ-ምዕራብ ፋርስ በሆነ አቅራቢያ ተገኘ። መነሻው በዋና ከተማው በሱስን እና በካሩን ወንዝ ሸለቆ ከታሪክ መዝገብ መጀመርያ ሲሆን እስከ 547 ክ.በ. ድረስ ቆየ። ከሱመር እና ከአካድ ወደ ምስራቅ የሆነ አገር ነበር። የኤላም መንግሥት ለፋርስ ከወደቀ በኋላ ቢሆንም የኤላም ቋንቋ በፋርስ አሐይመንድ መንግሥት በመደብኝነት ቆይቶ ነበር። ይህ ቋንቋ የፋርስኛ ...

                                               

ኤውላጥ

ኤውላጥ ማለት በዕብራይስጥ መጽሐፍ ቅዱስ የሚጠቀስ አገርና ግለሰቦች ነው። በ ኦሪት ዘፍጥረት 2፡10-12 የዔድን ገነት ሲገልጽ፦ "ወንዝም ገነትን ያጠጣ ዘንድ ከዔድን ይወጣ ነበር፤ ከዚያም ለአራት ክፍል ይከፈል ነበር። የአንደኛው ወንዝ ስም ፊሶን ነው፤ እርሱም ወርቅ የሚገኝበትን የኤውላጥ ምድርን ይከብባል፤ የዚያም ምድር ወርቅ ጥሩ ነው፤ ከዚያም ሉልና የከበረ ድንጋይ ይገኛል።" ከዚህ ...

                                               

ኦስሮኤኔ

ኦስሮኤኔ ከ140 ዓክልበ. ጀምሮ እስከ 234 ዓም በስሜን መስጴጦምያ የተገኘ ነፃ አገር ግዛት ነበር። ከዚያ በኋላ እስከ 600 ዓም የሮሜ መንግሥት አውራጃ ሆነ። ዋና ከተማው ኤደሣ ነበረ። በ600 ዓም የፋርስ መንግሥት ያዘው። የሰሌውቅያ መንግሥት እየወደቀ የኦስሮኤኔ መንግሥት በ140 ዓክልበ. ግድም የመሠረተው ሥርወ መንግስት ነባታያውያን ከተባለው አረባዊ ነገድ ነበር። በአንዳንድ ታሪክ ...

                                               

ኦፊር

ኦፊር በዕብራይስጥ መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን የሚጠቀስ አገር ነው። በ ኦሪት ዘፍጥረት 10 የኖህ ልጆች ሲዘረዘሩ ከዮቅጣን ልጆች መካከል አንዱ ኦፊር የሚባል አለ። በ መጽሐፈ ነገሥታት ቀዳማዊ 9፡26-28 መሠረት፣ የእስራኤል ንጉሥ ሰሎሞን መርከበኞች ከዔጽዮንጋብር ወደብ በኤርትራ ባህር ቀይ ባህር በመጓዝ ወደ ኦፊር መጥተው ከዚያ 420 መክሊት ወርቅ ወደ ሰሎሞን አመጡ። በ መጽሐፈ ዜና ...

                                               

ኻና አገር

ኻና አገር በኤፍራጥስ ወንዝ አካባቢ በአሁኑ ሶርያ የነበረ ግዛት ነበር። ዋና ከተማው ተርቃ ነበር። የማሪ ነገሥታት በይፋ "የማሪ፣ የቱቱል እና የኻና ግዛት ንጉሥ" ይባሉ ነበር። የባቢሎን ንጉሥ ሃሙራቢ ማሪን በያዘበት ጊዜ 1673 ዓክልበ. የማሪ መንግሥት ውድቀት ነበር፤ በኋላም በባቢሎን ንጉሥ አቢ-ኤሹህ 1627-1596 ዓክልበ. ዘመን፣ የባቢሎን ኃይል በዚያ አቅራቢያ ደክሞ ኻና ነጻ መ ...

                                               

የቾላ ሥርወ መንግሥት

የቾላ ሥርወ መንግሥት በደቡባዊ ሕንድ አገርና በኋላም በስሪ ላንካ ቢያንስ ከ300 ዓክልበ ጀምሮ እስከ 1271 ዓም የቆየ የታሚል ብሔር መንግሥት ነበረ። በሥነ ሕንጻ፣ በሥነ ጽሑፍ፣ በመርከብ ኃይልም ለሥልጣኔ አንጋፋዎች ሆኑ። ከታሪካዊ መዝገቦች እስከምናውቅ ድረስ ቢያንስ ከ300 ዓክልበ. ጀምሮ ተገኙ ሲባል፣ እንደ ልማዳዊ ታሪካቸው በጥንታዊ ታሚልኛ ሥነ ጽሑፍ ከዚያ በፊት ብዙ አፈ ታሪካ ...

                                               

የአክሬ ሪፐብሊክ

የአክሬ ረፐብሊክ, ወይም የአክሬ ነፃ መንግሥት, የዛኔ የቦሊቪያ ግዛት በነበረችው በአክሬ ክፍላገር ውስጥ የታወጁት ሦስት ተከታታይ ተገንጣይ መንግሥታት ነበሩ። እነዚህም ሦስቱ ተገንጣይ መንግሥታት ከ1891 እስከ 1896 ዓ.ም ድረስ ባሉት ዓመታት ውስጥ የቆሙት ናቸው። በ1896 ዓ.ም. ክፍላገሩ በይፋ ወደ ብራዚል ተጨመረችና እሳካሁን የብራዚል አክሬ ክፍላገር ትባላለች።

                                               

ያምኻድ

ያምኻድ በጥንታዊ ሶርያ የተገኘ መንግሥት ሲሆን ዋና ከተማው በሃላብ ነበር። የያምኻድ መንግሥት በታሪክ መዝገብ መጀመርያ የሚጠቀሰው ከማሪ ንጉሥ ያኽዱን-ሊም ጎረቤቶች መካከል ሲሆን ነው። የያምኻድ ነግሥታት በሥራዊትም ሆነ በዲፕሎማሲ ግዛታቸውን አስፋፉ። ከመመሠረቱ ጀምሮ ያምኻድ ከጠላቶቹ ማሪ፣ ቃትና እና አሦር ይታገል ነበር፤ በንጉሡም 1 ያሪም-ሊም ዘመን ከሁሉ ሃይለኛ መንግሥት በሶርያ ...

                                               

ፑንት

ፑንት ከጥንታዊ ግብጽ ጋራ ንግድ ያካሄድ የነበረ ሀገር ነበር። ግብጻዊ ተጓዦችና መርከበኞች ከዚያ ወርቅ፣ ሙጫ፣ ቆጲ፣ የዝሆን ጥርስ፣ ባርያዎችና አውሬዎች ያመጡ ነበር። ፑንት ደግሞ አንዳንዴ "ታ ነጨር" ይባላል። ፑንት በቀይ ባሕር ዳርቻ ወይም በአፍሪቃ ወገን ወይም በአረቢያ ወገንወይም ምናልባት በሁለቱም እንደ ተገኘ ይታሰባል። በአንዳንድ ዘመናዊ መምህሮች ዘንድ ፑንት ከፉጥ የካም ልጅ ...

                                               

ሁኖርና ማጎር

ሁኖርና ማጎር በሀንጋሪ አፈ ታሪክ ዘንድ የሁኖችና የሀንጋራውያን ቅድማያቶች ናቸው። በአንዳንድ መጻሕፍት መሠረት ለምሳሌ የመካከለኛ ዘመን ላቲን ዜና መዋዕል ጌስታ ሁኖሩም ኤት ሁንጋሮሩም፤ መንታ መሳፍንት ሁኖርና ማጎር የታና ልጅ መንሮትና የሚስቱ ኤነሕ ልጆች ነበሩ። ይህ መንሮት 200 አመታት ከማየ አይህ በኋላ በባቢሎን ሥልጣን እንደያዘ ሲባል መታወቂያው ደግሞ የኩሽ ልጅ ናምሩድ መሆኑ ...

                                               

ሉጋልባንዳ

ሉጋልባንዳ "እረኛው" በሱመር ነገሥታት ዝርዝር ዘንድ የኡሩክ ሁለተኛ ንጉሥ ነበረ። 1200 አመታት እንደ ነገሠ ይጨምራል። ስለ ሉጋልባንዳ የሚናገሩ ሁለት የሱመርኛ ትውፊቶች በሸክላ ጽላት ተገኝተዋል፤ እነርሱም በሊቃውንት "ሊጋልባንዳ በተራራ ዋሻ" እና "ሉጋልባንዳና የአንዙድ ወፍ" ይባላሉ። በ "ሊጋልባንዳ በተራራ ዋሻ" ፣ የኡሩክ ንጉሥ ሆኖ የቀደመው ኤንመርካር ሠራዊቱን በአራታ ላይ እ ...

                                               

ሐይክ

በሙሴ ሖሬናዊ ዘንድ ሐይክ የያፌት ልጅ ጋሜር ልጅ የቶርጎም ቴርጋማ ልጅ ነው። ሐይክ ደግሞ የሐይካዙኒ ሥርወ መንግሥት መስራች ይባላል። በታሪክ ጸሐፊው ጇንሸር ዘንድ፣ ሐይክ የሰባት ወንድማማች መስፍን ሆኖ፣ መጀመርያ ዓለሙን በሙሉ እንደ ንጉሥ ለነገሠው ለረጅሙ ሰው ለናምሩድ ያገልግል ነበር። ሐይክ ደግሞ በአርሜንኛ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም የኦሪዮን ከዋክብት ስም ነው። ኢዮብ 38፡31

                                               

መስኪያጝካሸር

መስኪያጝ-ካሸር በሱመራዊ ነገሥታት ዝርዝር ዘንድ የኤንመርካር አባትና የኤአና ንጉሥ ነበር። እንዲህ ሲል፦ "በኤአና መስኪያጝ-ካሸር የኡቱ ልጅ ገዢና ንጉሥ ሆነ፤ ለ324 ወይም 325 አመታት ነገሠ። መስኪያጝ-ካሸር ወደ ባሕር ገብቶ አልታየም። የመስኪያጝ-ካሸር ልጅ ኤንመርካር ኡሩክን ሠርቶ የኡሩክ ንጉሥ ሆነ።" "ኡቱ" ማለት የፀሐይ አምላክ ወይም ጣኦት ሲሆን "ኤ-አና" ማለት የኡሩክ ከተ ...

                                               

ሚስቶች በኖህ መርከብ ላይ

ከማየ አይህ በፊት በነበሩ ዕለታት ስለ ኖሩ በኖህ መርከብ ላይ ስለ ተገኙ ስለ አራቱ ሴቶች ኦሪት ዘፍጥረት ምንም እንኳን ዝም ቢል፣ ከሌላ ምንጭ ስለነዚሁ ሴቶችና በተለይ ስለ ስሞቻቸው የተገኘው አፈ ታሪክ በርካታ ነው። በጥንታውያን እምነት ዘንድ፣ የሴም፣ የካምና የያፌት ሚስቶች ዕጅግ የረዘማቸው ዕድሜ ሲኖራቸው ከመጠን ይልቅ ለብዙ መቶ ዓመታት ኑረው ለያንዳንዱ ትውልድ ትንቢት እየተናገሩ ...

                                               

የሲቢሊን መጻሕፍት

የሲቢሊን መጻሕፍት በግሪክ የተጻፉ የትንቢት ግጥሞች ክምችት ነበሩ። በአፈ ታሪክ የጥንታዊ ሮማ ንጉሥ ታርኲኒዩስ ሱፐርቡስ ከአንዲት ሲቢል ገዝተዋቸው በሮማ መንግሥት ታሪክ ታላቅ አደጋ በተከሠተበት ወቅት እኚህ ትንቢቶች ይማከሩ ነበር። የዛሬው ምሁሮች እኚህ መጻሕፍትና ዛሬ የታወቁት በክርስትና አባቶችም ከ2ኛ ክፍለዘመን እስከ 5ኛ ክፍለዘመን ድረስ በሰፊ የተጠቀሱት የሲቢሊን ራዕዮች አንድ ...

                                               

የሲቢሊን ራዕዮች

የሲቢሊን ራዕዮች በግሪክ የተጻፉ በ12 መጻሕፍት ተከፋፍለው የትንቢት ግጥሞች ክምችት ናቸው። እነሱ የሲቢል ሥራ ናቸው ይላሉ። ይሁንና የዛሬ ሊቃውንት እኚህ ትንቢቶች በአይሁዶች ወይም በክርስቲያኖች ተጽፈው ዕውነተኛ የሲቢሊን መጻሕፍት ሊሆኑ አይችሉም ባዮች ናቸው። ትንቢቶቹ የተባሉ ከድርጊቶቹ በኋላ ተነበዩና ከ2ኛው መቶ ዘመን ዓክልበ እስከ 6ኛ መቶ ዘመን ከክርስቶስ በኋላ መጻፍ ነበረባቸ ...

                                               

ቤሪክ

ቤሪክ ወይም ቤሪግ በስዊድን አፈ ታሪክ የጎጣውያን ንጉሥ ነበረ። የጎጣውያን ታሪክ ጸሐፊ ዮርዳኔስ 543 ዓ.ም. በጻፈው ጌቲካ ዘንድ፣ በጥንት ጎጣውያን ከንጉሣቸው ቤሪግ ጋራ ከስካንዲናቪያ ወጡ፤ ባልቲክ ባሕርን ተሻግረው በማዶ የተገኙትን ሕዝብ ኡልመሩጋውያንን አሸነፉና አገሩን ይዘው ሠፈሩበት። ከዚያ በኋላ ጎረቤቶቻቸውንም ቫንዳሎችን አሸነፉ። ቤሪክና ተከታዮቹ ለጥቂት ዓመታት በዚያ አገር ...

                                               

አሙን

አሙን በጥንታዊ ግብጽ አረመኔ እምነት ዘንድ ከነበሩት ዋና አማልክት አንዱ ነበር። ከዚህ በላይ በጥንታዊ ሊቢያ፣ ኩሽ እና ግሪክ አገሮች አረመኔ እምነቶች ከፍተኛ ሚና ያጫወት ነበር። በግብጻውያን ሃይማኖት፣ አሙን ያልተወለደ ያልተፈጠረ ፈጣሪ መሆኑ ይታመን ነበር። ከ1550 ዓክልበ. የገዙት ፈርዖኖች በተለይ ያከብሩት ነበር። በጊዜ ላይ፣ የአሙን እና የፀሐይ ጣኦት ራ መታወቂያዎች አንድ ሆነ ...

                                               

አውራከፕት ና ኔኬስ

አውራከፕት ና ኔከስ በአይርላንድ ሥነ ጽሑፍ ጥንታዊ የሆነ መጽሐፍ ነው። የተቀነባበረው ከ650 እስከ 1050 ዓም ያሕል ይሆናል። መጽሐፉ ስለ አይርላንድኛ ወይም ጋይሊክኛ እና ስለ ኦጋም ጽሕፈት ጸባይና ታሪክ ነው። በአውራከፕት ውስጥ አራት ንዑስ ጽሑፎች ተቀነባብረዋል፤ እነርሱም፦ ፬፤ "የፌኒየስ ጽሑፍ" - በፌኒየስ ፋርሳ፣ ያር ማክ ኔማ እና ጋይደል ማክ ኤጠር እራሳቸው በሙሴ ዘጸአት ዘ ...

                                               

አፅትላን

አፅትላን በሜክሲኮ የሚገኙት የናዋ ብሐሮች አፈታሪካዊ መኖሪያ አገር ቤት ነው። አፅቴክ የሚለው ስያሜ ትርጉም "የአፅትላን ሕዝብ" ነው። በናዋትል ትውፊቶች ዘንድ፣ 7 ጎሣዎች በ7 ዋሻዎች ውስጥ ቺኮሞጽቶክ በተባለ አገር ይኖሩ ነበር። እነርሱም ሾቺሚልካ፣ ትላዊካ፣ አኮልዋ፣ ትላሽካላን፣ ቴፓኔካ፣ ቻልካ እና መሺካ ተባሉ። ከጊዜ በኋላ እነኚህ ጎሣዎች ከዚያ ወጥተው ወደ አጽትላን ፈለሡ። በአን ...

                                               

ኤንመርካርና የአራታ ንጉስ

ኤንመርካርና የአራታ ንጉስ በጣም ጥንታዊ የሱመርኛ ትውፊት ነው። በታሪካዊ ሁኔታ ምናልባት በ3ኛ ሺህ ዘመን ክ.በ. ድርጊቶች ላይ የተመሰረተ ሊሆን ይቻላል። ከኡኑግ-ኩላባ ንጉስ ከኤንመርካርና ስሙ ካልታወቀ ከአራታ ንጉስ መከከል ስለተደረገው ውድድር ከሚገልጹ ሰነዶች አንዱ ነው። በሰነዱ መጀመርያ ክፍል የሚከተለው መረጃ ይሰጣል፦ "በዚያ ጥንታዊ ዘመን፣ ዕድሉ በተወሰነ ጊዜ፣ ታላላቆቹ መሳፍ ...

                                               

ክሮኖስ

ክሮኖስ በጥንታዊ ግሪክ አፈ ታሪክ በኩል የአረመኔ እምነት አማልክት ኡራኖስና ጋያ ልጆች የሆኑት የቲታኖች መሪ የነበረ አምላክ ወይም ንጉሥ ነበረ። አባቱን ገልብጦ በአፈታሪካዊ ወርቃማ ዘመን ይነግሥ ነበር፤ በኋላ ግን የራሱ ልጆች ዚውስ፣ ሃይዴስና ፖሠይዶን ክሮኖስን ገለበጡ፣ በታርታሮስም አሠሩት። የክሮኖስ ስም በሮማይስጥ "ሳቱርን" ሲሆን በነርሱም እምነት እንደ አምላክ ይቆጠር ነበር። የ ...

                                               

ኸንቲ-አመንቲው

ኸንቲ-አመንቲው በግብጽ ጥንታዊ መንግሥት ዘመን የፈርዖኖች እና አማልክት ማዕረግ ነበረ። ትርጉሙ ከግብጽኛ "የምዕራባውያን ቀዳሚ" ሲሆን በዚህም "ምዕራባውያን" ማለት "ሙታን" ለማለት ነበር። ስለዚህ ማለቱ ደግሞ "የሙታን ቀዳሚ" ሊሆን ይችላል። መጀመርያው "ኸንቲ-አመንቲው" የሆነው የፈርሮኖች ወላጅ ቅድማያት ኦሲሪስ ግብጽኛ፦ አውሣር ይመስላል። በግብጻውያን ትውፊቶች ዘንድ ይህን አውሣርን ...

                                               

የማግ ኢጠ ውግያ

ማግ ኢጠ በአየርላንድ ልማዳዊ አፈ ታሪክ ዘንድ የአይርላንድ መጀመርያው ውግያ ነበረ። ለዚሁ ውግያ ታሪክ ዋና ምንጮች 3 ናቸው፦ የሴጥሩን ኬቲን ታሪክ መጽሐፍ የአይርላንድ ታሪክ 1625 ዓ.ም. ተጻፈ ሌቦር ገባላ ኤረን 1100 ዓ.ም. ግድም የተጻፈ፤ "የአይርላንድ ወረራዎች መጽሐፍ" የአራቱ ሊቃውንት ዜና መዋዕሎች በ1620 ዓ.ም. ግድም የተቀነባበረው ፓርጦሎን በአይርላንድ 10 ዓመት ከደ ...

                                               

የነጩ ቢትወደድ መጽሐፍ

የነጩ ቢትወደድ መጽሐፍ በ1450 ዓም ገደማ በአይርላንድ የተፈጠረ ሥነ-ጽሑፋዊ፣ ሃይማኖታዊ ወይም አፈታሪካዊ ክምችት ነው። በአይርላንድኛ በ "ነጩ ቢትወደድ" ጄምዝ በትለር፣ የኦርሞንድ 4ኛው እርል ሲሆን በርሱ ደጋፍ ነበር የተጻፈው። በክምችቱ ውስጥ "የወንጉስ ሰማዕታት ዝርዝር" በ820 ዓም ያህል እንደተቀነባበረ ይታስባል፤ ሌሎች ክፍሎች ከ1160 ዓም እንደ ሆኑ ይመስላል። በይዞታው መጨ ...

                                               

ዮቅጣን

ዮቅጣን በብሉይ ኪዳን መሠረት ከኤቦር 2 ልጆች ታናሹ ነበረ። ታላቅ ወንድሙ ፋሌክ ነበረ። ልጆቹም ኤልሞዳድ፣ ሣሌፍ፣ ሐስረሞት፣ ያራሕ፣ ሀዶራም፣ አውዛል፣ ደቅላ፣ ዖባል፣ አቢማኤል፣ ሳባ፣ ኦፊር፣ ኤውላጥና ዮባብ ናቸው። የመጽሐፍ ቅዱስ ቅርሶች Biblicarum antiquitatum liber ወይም "ፕሲውዶ-ፊሎ" በተባለው ጽሑፍ ዘንድ 70 ዓ.ም. ያሕል፣ ከኖህ ዘመን በኋላ ዮቅጣን የሴም ...

                                               

ዲዮኒሶስ

ዲዮኒሶስ ወይም ባኩስ በጥንታዊ ግሪክ እና ሮማውያን አረመኔ ሃይማኖቶች ውስጥ የወይንና የስካር አምላክ ነበረ። የዚውስ ልጅ ይባላል። የእናቱ ስም በምንጮቹ ይለያያል፤ ወይም ሴት አምላክ ፐርሰፎኔ፣ ወይም መዋቲ ሴት ሴሜሌ ነበረች። ኒሳ በሚባል ደሴት ወይም ተራራ እንደ ታደገ ይታመን ነበር። በስሙ "ዲዮ-" የሚለው ክፍል ማለት "የዚውስ" እና "-ኒሶስ" ማለት "ከኒሳ" እንደሆነ ይመስላል። ...