ⓘ Free online encyclopedia. Did you know? page 12
                                               

እሌኒ

ንግስት እሌኒ የአጼ ዘርዓ ያዕቆብ ሚስት ስትሆን ከንጉሱ ሞት በኋላ በሌሎች ሶስት ነገስታት ዘመን ከፍተኛ የአስተዳደር ስራ ፈጽማ በ1522 ከዚህ አለም በሞት አርፋለች። የተቀበረችውም በትልቅ ጥበብ ባሰራችው ቤ/ክርስቲያን መርጡለ ማርያም፣ ጎጃም ነው። እሌኒ የሃድያው ንጉስ መሐመድ ልጅ ስትሆን ዘርዓ ያዕቅብን ባገባች ጊዜ ክርስቲያን ሆናልች። አንዳንድ ታሪክ ጸሃፊያን ለምሳሌ ባላዛር ቴሌዝ ...

                                               

እቴጌ ምንትዋብ

እቴጌ ምንትዋብ በዙፋን ስሟ ብርሃን ሞገስ በ1698 ዓ.ም. ከአባቷ ደጅአዝማች መንበር እና እናቷ ልዕልት እንኮይ በቋራ፣ ጎንደር ስትወለድ የክርስትና ስሟ ወለተ ጊዮርጊስ ነበር። እናቷ ልዕልት እንኮይ ከዓፄ ሚናስ ዘር የምትወለድ እንደነበረች ይጠቀሳል። ምንትዋብ በ18ኛው ክፍልዘመን ኢትዮጵያ ላይ ብዙ አሻራ ትታ የለፈች ንቁ፣ ሃይለኛና ተራማጅ መሪ ነበረች። ከባሏ ዓፄ በካፋ ዘመን ጀምሮ ...

                                               

ክሪስታቮ ደጋማ

ክሪስታቮ ደጋማ በኢትዮጵያ የፖርቹጋሎችን ጦር መሪ የነበረ ሲሆን የግራኝ አህመድን ሰራዊት ቁጥሩ በጣም ባነሰ ሰራዊት አራት ጊዜ አሸንፎች በአምስተኛው ጊዜ ተማርኮ ሃይማኖቴን አልቀይርም ሲል የተገደለ አዋጊ ነበር። ሪቻርድ በርተን የተባለ የታሪክ ተመራማሪ ክሪስታቮን በጀግኖች ዘመን የተወለደ ቀደምት ጀግና ነበር ሲል አድንቆታል። በሌላ በኩል ክሪስትቮ የታዋቂው አለም አቀፍ ተጓዥ ቫስኮ ደጋ ...

                                               

ዘመነ መሳፍንት

ዘመነ መሳፍንት በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ከ፲፰ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ጀምሮ እስከ ፲፱ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ድረስ የተከሰተ ጊዜ ሲሆን፣ በወቅቱ የየአካባቢው መሳፍንት ኃይል የገነነበትና እርስ በርሳቸው የሚዋጉበት እንዲሁም ዋናው ንጉስ ሥልጣኑ ከመዳከሙ የተነሳ ከጎንደር ከተማ ውጭ እምብዛም ተሰሚነት ያልነበርበት ወቅት ነበር። ከነበረው አለመረጋጋት የተነሳ ከጎንደር ከተማ ተነስ ...

                                               

የሆር-ለቫል ውል

የሆር ላቫል ውል በ 1935 ታህሣስ ወር ላይ በብሪታንያ የውጪ ጉዳይ ፀሃፊ በነበረው ሣሙኤል ሆር እና በፈረንሣይ ጠቅላይ ሚኒስተር ፒየር ላቫል ተዘጋጅቶ ቀረበ። የዚህ ውል አላማው በጊዜው የነበረውን ኢጣሊዮ-አቢሢኒያ ጦርነት ለመደምደምና በ1896 በተደረገው ጦርነት ተዋርዶ የተሸነፈውን አቢሲንያን በመክፈል ለመቀበል ነበረ። የጣሊያን አምባገነን መሪ የነበረው ቤኒቶ ሙሶሊኒ አላማ የነበረው ...

                                               

የታኅሣሥ ግርግር

የታኅሣሥ ግርግር በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ዓመቱ በገባ በአራተኛው ወር ላይ የተከሰተው የታኅሣሥ ፲፱፻፶፫ቱ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ፤ የአገሪቷ መጭው ዕድሏ ፊቱን ገለጥ ያደረገብት ሁኔታ ነበር። ለምን? ከ፲፱፻፷፮ቱ አብዮት በፊት ዙፋኑን ክፉኛ ያናጋ ተቃውሞ ቢኖር፤ እንዲያውም የአብዮቱ ምሥረታ፣ በኢትዮጵያ" ዘመናዊ” ታሪክ ውስጥ ወሳኝ የሆነ የፖለቲካ ተቃውሞ ምዕራፍ መክፈቻ ሊባል የሚገባው ...

                                               

የአይሻል ጦርነት

የአይሻል ጦርነት በደጃዝማች ካሳ ሃይሉ እና በራስ አሊ መካከል የተደረገ በደም የጨቀየ ጦርነት ነው። ድሉ ለደጃዝማች ካሳ ሆኖ የዘመነ መሳፍንት እና የየጁ ኃይልን ለመጨረሻ ጊዜ የሰበረ ጦርነት ነበር። ራስ አሊ በወቅቱ የካሳን ጦር ተመልክተው ፦ "መልእክተኛ እንዳንለው በዛ፣ ጦረኛ እንዳንለው አነሰ" ብለው እንደተሳለቁ በታሪክ ይዘገባል።

                                               

የኢትዮጵያ ሶማሊያ ጦርነት

የኦጋዴን ጦርነት እየተባለ የሚታወቀው የ1977 እ.ኤ.አ./1978 እ.ኤ.አ. ጦርነት በኢትዮጵያና በሶማሊያ መንግስታት የተካሄደ ግቡም ኦጋዴን የተባለውን ስፍራ ለመያዝ ነው። በዚህ ጦርነት ሶቪየት ህብረት መጀመሪያ ሶማሊያን ትደግፍ እንጂ በኋላ ላይ ወደ ኢትዮጵያ በማዘንበል ኢትዮጵያን ረድታለች። ኢትዮጵያ በመጀመሪያ ዙር በአሜሪካ ስትረዳ ቆይታ በኋላ ላይ አሜሪካ ሶማሊያን ረድታለች። ጦርነ ...

                                               

የወታደሮች መዝሙር

የወታደሮች መዝሙር የሚባሉት አስራ ሁለት በጥንቱ አማርኛ የተጻፉ ግጥሞችን ነው። ከነዚህ ግጥሞች አራቱ በ1300ወቹ በአጼአምደ ጽዮን ዘመን የተጻፉ ሲሆን ምናልባትም በጣም ቀደመትና እስካሁን ካልጠፉ የአማርኛ ጽሁፎች መካከል ናቸው። እኒህ አራቱ ግጥሞች በኤድዋርድ ኡልንድሮፍ የበለጠ ተጠንተዋል። የመጀመሪያዎቹ ግጥሞች ስለ 15ኛው ክፍለ ዘመን ንጉስ፣ ስለ ቀዳማዊ አፄ ይስሐቅ የተገጠሙ ሲሆን ...

                                               

የጁ ስርወ መንግስት

የየጁ ስርወ መንግስት ከ18ኛው ክፍለዘመን መጨረሻ እስከ 19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ድረስ ተጠናክረው ኢትዮጵያን በእንደራሴነት ሲያገለግሉ የነበሩ ራሶችን የሚገልጽ ነው። በዚህ ዘመን የጎንደር ነገስታት ሃይል እጅግ ከማሽቆልቆሉ የተነሳ እኒ እንደራሴወች የፈለጉትን ከስልጣን የማንሳትና የፈለጉትን የመሾም ሃይሉ ነበራቸው። ስለዚህም የአገሪቱ መሪ ነበሩ ቢባል ማጋነን አይሆንም። ከየጁ ስርወ ...

                                               

የጥንቱ ኢትዮጵያ ገዢ መደብ

የጥንቱ የኢትዮጵያ ገዢ መደብ የምንላቸው በዘውድ ስርዓቱ ውስጥ ስልጣን ኑሮዓቸው አገሪቱን የሚያስተዳድሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ነው። እኒህ ክፍሎች በአራት ዋና ክፍሎች ይከፈላሉ፦- ፩- ንጉሠ ነገሥት ወይንም ዐፄ -- በድሮው ስርዓት፣ ንጉሠ ነገሥት ወይም ዐፄ የስልጣን ፍጽምና ነበረው። ስልዚህም በሁሉ ላይ ሙሉ፣ ይግባኝ የማይባልበት ስልጣን ነበረው። ፪- መሳፍንት -- ከሌሎች መሳፍንት ወ ...

                                               

ደርግ

ደርግ ከሰኔ 21፣ 1966 እስከ 1979 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሰፍኖ የነበር የወታደራዊ አገዛዝ ስርዓት አይነት ነበር። ደርግ የሚለው ቃል ከግዕዝ የተወሰደ ሲሆን ትርጓሜውም ቡድን ወይንም ኮሚቴ ማለት ነው። ይህን ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ ለስርዓቱ መገለጫነት የተጠቀመው ግለሰብ ሻለቃ ናደው ዘካሪያስ ሲባል ይሄውም ሰኔ 21፣ 1966 ዓ.ም. ነበር። በዚህ ወቅት፣ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው የአ ...

                                               

ደብረ ሊባኖስ

በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ገድል መሠረት፣ ይህ ገዳም የተመሰረተው በ1300ዎቹ መጀመሪያ በራሳቸው በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ነበር። ተክለ ሃይማኖት የግራርያን ስዩም የነበረውን ሰሜን ሰገድን ክርስትና እንዲቀበል ካደረጉ በኋላ፣ ይሄው ሹም ለተክለ ሃይማኖት አስቦ ከተባለው ስፍራ መሬት ለክርስትና ግልጋሎት በፈቃድ ስለሰጠ፣ በዚሁ ቦታ ለቅድስት ማሪያም መታወሻ የሚሆን ቤ/ክርስቲያን ተቋቋመ። ይህ ...

                                               

ደብረ ዳሞ

ደብረ ዳሞ በ6ኛው ክፍለ ዘመን የተቆረቆረ ገዳምና ይህ ገዳም የሚኖርበት ተራራ ስም ነው ። ደብረ ዳሞ ከአዲግራት በስተምዕራብ በመካከለኛው ትግራይ ይገኛል። ከተራራው ቀጥ ብሎ ለመውጣት አዳጋችነቱ የተነሳ ወደገዳሙ ለመድረስ ከቆዳ በተሰራ ገምድ ላይ መንጠላጠል ግድ ይላል። ቤተ ክርስቲያኑ በኢትዮጵያ ውስጥ ጥንታዊ የአሰራር ዘዴን ተከተሎ እስካሁን ዘመን ድረስ በመዝለቅ ቀደምትነት ስፍራን ይ ...

                                               

ዳግማዊ ዓፄ ኢያሱ

ዳግማዊ ኢያሱ በዙፋን ስማቸው ዓለም ሰገድ ከመስከረም 19፣ 1730 ጀምሮ እስከ እለተ ህልፈታቸው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት የነበሩ ሲሆን አባታቸው አጼ በካፋ ሲሆኑ እናታቸው እቴጌ ምንትዋብ ነበሩ። የወደፊቱ ዳግማዊ እያሱ ወደ ስልጣን በወጣበት ጊዜ ገና ህጻን ስለነበር እናቱ እቴጌ ምንትዋብ የልጁ እንደራሴ ሆና ተሾመች። ነገር ግን የልጁን መንገስ የሚፎካከሩ አካሎች የፋሲል ግቢን በመክበብ ...

                                               

ግራኝ አህመድ

በተለምዶው ግራኝ አህመድ ተብሎ የሚታወቀው የጦር መሪ ሙሉ ስሙ ኢማም አህመድ ኢብን ኢብራሂም አልጋዚ ሲሆን የኖረውም ከ1507 እስክ ታህሳስ 21፣ 1543 ነበር።) በዘመኑ በእስልምና ሃይማኖት የኢማምነት ደረጃ የደረሰ ሲሆን የአዳል ግዛት ተብሎ ይታወቅ የነበረውን የጥንቱን የኢትዮጵያ ክፍል በመምራት እንዲሁም በዘመኑ የነበሩትን ነገስታት ከመካከለኛው የኢትዮጵያ ክፍል እንዲያፈገፍጉ በማድረ ...

                                               

ግሸን ተራራ

ግሸን ተራራ በአሁኑ ደቡብ ወሎ የሚገኝ ጥንታዊና ታሪካዊ ተራራ ነው። የታሪካዊነቱ ምንጭ የዕርስ በርስ ጦርነትን ለማስወገድ ሲባል እንደ ደብረ ዳሞ እና ወህኒ የነገስታት ወንድ ተገዳዳሪ ዝርያወች በአምባው ላይ ይታሰሩ ስለነበር ነው። አጼ ጅን አሰገድ ወንድሞቻቸውንና ወንድ ልጆቻቸውን በአምባ ግሸን እንዳሳሰሩ በዜና መዋዕላቸው ላይ ሰፍሮ ይገኛል። ሆኖም ግን ይህን ስራ እኒህ ንጉስ ያስጀምሩ ...

                                               

ግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም

ግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም በአሁኑ ወሎ ክፍለ ሃገር፣ አምባሰል ወረዳ ውስጥ ግሸን ተራራ አናት ላይ የምትገኝ ቤ/ክርስቲያን ናት። ለዚች ቤ/ክርስቲያን መግቢያ አንድ መንገድ ብቻ ነው። እንደ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ይች ቤተ ክርስቲያን በየዘመኑ የተለያየ ስያሜን አግኝታለች። በ1446 አጼ ዘርአ ያዕቆብ ግማደ መስቀሉን በዚህ ስፍራ ሲያርፍ ደብረ ነገስት መባሏ ...

                                               

ፋሲል ግቢ

ፋሲል ግቢ ወይንም ነገሥታት ግቢ በጎንደር ከተማ የሚገኝ የምሽጎችና የቤተመንግስታት ግምቦች ስብስብ ነው። ግቢው የተመሰረተው በ1628ዓ.ም. በዓፄ ፋሲለደስ ነበር። ማቀባበያ የሚሰኘው የግቢው አጥር 900ሜትር ርዝመት ሲኖረው በውስጡ 70፣000 ስኩየር ሜትር የመሬት ይዞታ ያካልላል። አጼ ፋሲለደስ የመጀመሪያውንና ታላቁን ግንብ ያሰሩ እንጂ፣ ከርሳቸው በኋላ የተነሱት ነገሥታትም ለ220 ዓመ ...

                                               

ቀራንዮ መድኅኔ ዓለም

ደብረ ቀራንዮ መድኃኔአለም ቤተክርስቲያን ደብሩ ለመጀመርያ ጊዜ የተመሠረተው በንጉሥ ሣህለ ሥላሴ በ1826 ዓም ሲሆን ከአዲስ አበባ ቤተክርስቲያኖች በዕድሜ ትልቁ ነው። አሁን ያለውን ቤተክርስቲያን ያሠሩት ደግሞ አፄ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ናቸው።የደብረ ቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተክርስትያን ዳግማዊ ቀራንዮ ዘኢትዮጵያ ከአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት አንዱና ቀዳሚው የሆነው ይህ ደብር የተመሰረተ ...

                                               

መቀሌ አሉላ አባ ነጋ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ

መቀሌ አሉላ አባ ነጋ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በትግራይ ክልል ርዕሰ ከተማ ከመቀሌ በአሥር ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ዘመናዊ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ነው። አየር ማረፊያው በዘመናዊ መልክ የተገነባ እና የተደራጀ ሲሆን ከባሕር ወለል በ ፪ሺ ፪መቶ ፶፯ ሜትር ከፍታ ላይ ይገኛል። ባሁኑ ጊዜ አየር ማረፊያው አንድ ባለ ፫ሺ ፮፻ ሜትር ርዝመት በ፵፫ ሜትር ስፋት ያለው አስፋልት የለበሰ ...

                                               

ባሕር ዳር ግንቦት ሃያ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ

የባሕር-ዳር ግንቦት ሃያ ዓለም አቀፍ ጥያራ ጣቢያ ከባህር ዳር ከተማ በስተ ምዕራብ ስምንት ኪሎ ሜትር ርቀት፣ በ፩ሺ፰መቶ፳፩ ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኝ የአየር ጣቢያ ነው። ጥያራ ጣቢያው አንድ አስፋልት የለበሰ የሦስት ሺ ሜትር ርዝመት በአርባ አምስት ሜትር ስፋት ያለው የኮንክሪት ማኮብኮቢያ ያለው ሲሆን በአሁኑ ጊዜ እንደ ቦይንግ 757 የመሳሰሉ ሦስት የጭነትና አራት ቦምባርዲዬር የመንገደ ...

                                               

ቦሌ ዓለም አቀፍ ጥያራ ጣቢያ

ቦሌ ዓለም አቀፍ የጥያራ ጣቢያ በአዲስ አበባ ከተማ በደቡብ-ምሥራቅ አቅጣጫ ከአራዳ በስምንት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ የአገሪቱ ዋና አድማሳዊ የንግድና የግንኙነት በር ነው። ፕሮፌሶር ዲባቶ መስፍን አረጋ፣ ቦሌ በኦሮምኛ ቋንቋ ትርጉሙ የሚፈረፈር ወይም የሚሰነጣጠቅ መሬት እንደሆነ ይነግሩናል። እውነትም የአካባቢው ገጸ-ምድር ለአየር ማረፊያ አመቺ ሜዳማ ቢሆንም መሬቱ ግን ረግራጋ እና ...

                                               

ባቢሌ የዝሆን መጠለያ

ባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ ከአዲስ አበባ ወደ ጅጅጋ መስመር፣ ፭መቶ ፶ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል። ይህ መጠለያ በቆዳ ስፋት ፮ሺ ፱መቶ ፹፪ ካሬ-ሜትር የሚመዘን ሲሆን፣ ከጠቅላላ ስፋቱም ውስጥ ፸፯ ከመቶ ያህሉ በአሁኑ አጠራር ”በሶማሌያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት” ሥር ሲካለል፤ ቀሪው ፳፫ ከመቶ ያህሉ ደግሞ ”በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት” ሥር ይገኛል። የአካባቢው የኦሮሚያ ብሔር ተ ...

                                               

አዋሽ ብሔራዊ የመዝናኛ እና የዱር አራዊት ጥበቃ ክልል

የአዋሽ ብሔራዊ መዝናኛ እና የዱር አራዊት ጥበቃ ክልል በ፲፱፻፶፰ ዓ/ም የተመሠረተ ክልል ሲሆን ከአዲስ አበባ በስተ ምሥራቅ አቅጣጫ በ፪መቶ ፲፩ ኪሎሜትር ርቀት ፤ በአፋርና በኦሮሚያ አዋሳኝ ክልሎች ሥር ይገኛል። ይህ ክልል ሲመሠረት በ ፱፻፮ ካሬ ኪሎሜትር የቆዳ ስፋት የነበረው ቢሆንም፤ ባሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለሥልጣን ማስረጃ እንዳስቀመጠው የክልሉ የቆዳ ...

                                               

የኢትዮጵያ እጽዋት

ሃብሃብ ሆሳዕና ለውዝ ሊሻሊሾ ላሎ ሓረግ ልምጭ ሎሚ ሑንጨ. ሓምሌ ቁልጭ ሓረግ ሓርሞ መርዝ መቅመቆ መተሬ መጭ ሙሽ ሙጃ ሚጥሚጣ ማሽላ ማንጎ. ምስር ምጫምጮ ሩማን ሩዝ ራስ ክምር ሬት ሮቃ ሰለሪ ሰሊጥ ሰሪቲ ሰርዶ ሰናፍጭ ሰንሰል ሰንበሌጥ ሰንዳፋ ሰኮሩ ሰገድ ሱፍ ሳማ. ሳኮዮ ስንደዶ ስንዴ ስኳር ድንች ሶሌ ሸምበቆ ሸንኮራ ኣገዳ ሻይ ሽመል ሽምብራ ሽነት ሽፈራው ሾላ. ቀላዋ ቀረሮ ቀረፋ ...

                                               

ሂና

ሂና Lawsonia inermis ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ነው። የአንዳንድ አገር ሴቶች በዚህ ተክል ለቆዳቸው ምልክት ለማድረግ ቀለም ይሠራሉ። "እንሶስላ" ባብዛኛው ለሌላ ዝርያ Impatiens tinctoria ያጠቁማል።

                                               

ሓረግ

ኣዞ ሓረግ C. hirsuta በቅርብ ይዛመዳል። ከClematis ውጭ ሌሎችም ዝርያዎች ደግሞ "ሓረግ" ተብለዋል፣ በተለይም Peponium vogelii የዱባ አይነት እና የHedera ወገን፤ እንዲሁም ማናቸውም እንደ ወይን ሐረግ ያለው ሓረግ ሊሆን ይችላል።

                                               

ሬት

ደማቅ ቢጫና ቀይ አበቦች አሉት። ብዙ ዝርያዎች አሉ፤ ከሁሉ የታወቀው Aloe vera ወይም "እውነተኛ ሬት" ነው። የሴት ሬት A. pulcherima አልጌ A. macrocarpus ብዙ ጊዜ "ቃጫ" ሲባል፣ ቃጫ በደንብ የሌላው ተክል ስም ነው። ወንድ ሬት A. trichosantha

                                               

ሮቃ

ዘሮቹ ጉንቆል ለማድረግ ለአጭር ጊዜ ሊፈሉ ይቻላል። ከዚያ ደረቅ ቢቆዩ ለጥቂት ወሮችም ረቢ ይሆናሉ። ዛፉ ረጅም ሕይወት አለው፣ በ3 ወይም 4 አመት ውስጥ ያፈራል። ፍሬው ቡናማ ወይም ቀይ-ቡናማ ሲሆን ይመረታል። አንድ ዛፍ ብቻ በየዓመቱ 1.75 ኩንታል ፍሬ ሊሰጥ ይችላል።

                                               

ሽፈራው

የሞሪንጋ ዛፍ በኢትዮጵያ በተለምዶ ሽፈራው በሚል የሚታወቅ ሲሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ13 በላይ ዝርያዎች ያሉትና በሁለገብ ጠቀሜታቸው ከሚታወቁት ዛፎች መካከል አንዱ ነው። በአለም ላይ ካሉት የሞሪንጋ ዛፍ ዝርያዎች ውስጥ ሰባት የሚሆኑት በምስራቅ አፍሪካ በተለይ ደግሞ በኢትዮጵያ፣ በኬንያ፣ በጅቡቲና በሶማሊያ አካባቢዎች ይገኛሉ። ሽፈራው ከሚለው ስያሜ ባሻገር የጎመን ዛፍ ወይም የአፍሪካ ...

                                               

ቅርንፉድ

የቅርንፉድ ዛፍ መጀመርያ መናኸሪያ እስከ 1760 ዓም ድረስ የማሉኩ ደሴቶች ኢንዶኔዥያ ብቻ ነበር። ሆኖም ከነዚህ ደሴቶች የቅርንፉድ ንግድ እስከ ሶርያ በ1730 ዓክልበ. እንደ ደረሰ በሥነ ቅርስ ታውቋል። በ1760 ዓም ግድም አንድ የፈረንሳይ ዜጋ ፒዬር ፗቭር የዛፉን ቡቃያ ሰርቆ በዛንዚባር እንዳስተከለው ይባላል፤ ይህም የደሴቶቹን ምኖፖል አስጨረሰው። አሁንም በተለይ እንደ ሰብለ ገበያ ...

                                               

ቋራ

ቋራ ወይም ኮርች ወይም ጎርጎ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ነው። ይህ ዛፍ የእሳትና የምስጥ ጥቃትን የመቋቋም አቅም አለው። ነጭና ለስላሳ የሆነው ግንዱ ጥሩ ጣውላ የሚወጣው ባይሆንም በቀላሉ ቅርፅ ሊወጣለት የሚችል ዓይነት ነው። በወንዝና ኩሬዎች ዳርቻም ስለሚበቅል ለአፈር ጥበቃና እርከን ሥራ ተመራጭ ነው። ፍሬው መርዛማ ነው። ሆኖም ካልደቀቀ ወይም ካልተፈጨ በስተቀር በቀላሉ አይዋጥም። ...

                                               

በርበሬ

ለወረዳው፣ በርበሬ ወረዳን ይዩ። በርበሬ ኢትዮጵያና ዓለም ውስጥ የሚገኝ የተክል ወገን ነው። እንዲሁም በርበሬ ለረጅም ጊዜያት በኢትዮጵያ የነበረ ባህላዊ ምግብ ነው። ሆኖም የበርበሬ መነሻ በአሜሪካዎች ነበረ፤ ከ1500 ዓም ቀጥሎ በፖርቱጋል ሰዎች ወደ አፍሪቃ የተስፋፋው ነው። ቁንዶ በርበሬ የሚባለው ተክል ከጥንት ጀምሮ በአፍሪካ ቢታወቅ እሱ ግን በፍጹም ሌላ አስተኔ ነው። ሚጥሚጣ የበርበ ...

                                               

ብሳና

ፍሬዎቹና የሥሮቹ መረቅ ለአባለዘር በሽቶች ተጠቅመዋል። የተደቀቀው ልጥ ከኮሶ ወይም መተሬ ጋር ተቅላቅሎ ትልን ያስወጣል። ዘሮቹና ሙጫዎቹ መርዛም ናቸው፣ ለአሣ መርዝ ይጠቀማሉ። የቅጠሎቹ ውጥ ለአናት እከክ ይጠቀማል። ለወፍ በሽታ፦ የብሳና ቡቃያ ቅጠል መረቅ ከሰንሰል ጋር ተቀላቅሎ፣ ቁንዶ በርበሬና ቅቤ ይጨምር ለ፫ ቀን በዳቦ ይበላል፤ በርካታ ወተትም ይጠጣል እንጂ ሥጋ ወይም ዘይታም ምግ ...

                                               

ኑግ

ኑግ በሮማይስጥ Guizotia abyssinica በመባል የታወቀው የእህል ዘር የሚሰጥ ተክል ዝርያ ነው። ኑግ ዩናይትድ አስቴትስ ውሱጥ ተወዳጅ የወፍ ምግብ ነው። ይህን የዘይት እህል በብዛት የሚያመርቱ ኣገሮች ኢትዮጵያና ሕንድ ናቸው ይባላል፣ ሌሎችም አሉ። ወፎች ስለሚወድዱት ብዙ አገሮችም ያስገቡታል። ዘሩ ወደ ሌላ አገር ሳይገባ ግን የአረም ዘሮች ስላሉበት ጉንቆል እንዳይሆኑ ለ15 ደቂቃ ...

                                               

ኣጠፋሪስ

ኣጠፋሪስ ወይም አስተናግርት ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ነው። ስሙ ኣጠፋሪስ ከ "እጸ ፋርስ" ጋር የተዛመደ ይሆናል፣ አሁን ግን "እጸ ፋርስ" በተለመደ ለCannabis sativa ያጠቆማል። ሌላም ዝርያ Nicandra physalodes ደግሞ "አጠፋሪስ" ተብሏል።

                                               

እንዳሁላ

ከአለሙ 125 የእንዳሁላ ዝርያዎች፣ 60 ዝርያዎች በዱር ከማዳጋስካር ናቸው፣ 56 ዝርያዎች ከደቡባዊ ወይም ምሥራቅ አፍሪካ ናቸው፤ አንድ ዝርያ ብቻ ከአሜሪካዎች ነው። ብዙ አይነቶች በኢትዮጵያ አሉ፣ አንዳንድ በደረቅ ድንጋያማ፣ ለሎችም በፈሳሽ ዳር ወይም በጫካ ዳር ይበቅላሉ።

                                               

እንዶድ

ሥሩ ወይም ቅጠሉ ተደቅቆ በውሃ ለቁርባ ወይም ወፍ በሽታ ይጠጣል። የሥሩ መረቅ ለጨብጡ ያከማል። በአነስተኛ መጠን ካልሆነ ሊገድል ይችላል። የወንድ እንዶድ ሥር ተድቅቆ በውሃ ደግሞ ውሻ በሽታን ለማከም ይጠጣል። ወይም እንዲህ በጤፍ ቂጣ ይበላል። የእንዶድ ቅጠል ጭማቂ ለእከክ መቀባቱ፣ ወይም ለሆድ ትል መጠጣቱ ተዝግቧል። የፍሬውም ለጥፍ ለቁስል ይለጠፋል። ፍሬው ተደርቆ ተድቅቆ ለሳሙና መጠ ...

                                               

እጸ ፋርስ

እጸ ፋርስ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲሁም በመላው ዓለም የሚገኝ ተክል ነው። በአንዳንድ ምንጭ ኣጠፋሪስ ወይም አስተናግርት ደግሞ "እጸ ፋርስ" ተብሏል፤ ይህ በፍጹም ሌላ ዝርያ Datura stramonium ነው። C. sativa ደግሞ ቃጫ ተብሏል፣ ይህም ለሌላ ዝርያ Agave sisalana ይገባል።

                                               

ኮባ

ኮባ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ለምግብነት የሚጠቅም የተክል አይነት ሲሆን ለምግብ የሚያገለግለው ስር እንሰት በመባል ይታወቃል። ብዙ የኮባ አይነቶች በአፍሪካ ደጋማ ክፍሎች ይብቀሉ እንጂ በለማዳ እጽዋትነት እየበቀለ ለምግብነት የሚያገለግለው በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ነው። የኮባ ተክል በጥንቱ የግብጽ ስልጣኔ ይበቅል እንደነበር ማስረጃ አለ። የኮባ ቅጠል ዳቦ ለመጋገርና ቃጫ ለመስራት ሲያገለግል እን ...

                                               

ዋጊኖስ

ዋጊኖስ ወይም የደጋ አባሎ ባለጠጕር፣ ሥሩና ፍሬው ለደም ተቅማጥ መድኀኒት ይኾናል። ቅጠሉም ቀጥቅጦ በውሃ ዘፍዝፎ ብልትንና ዐይንን ፡ እንዳይነካ ተጠንቅቆ ገላን ቢቀቡት ከዕከክ ያድናል ። ሌላ ስሙ ጉፋ ይባላል ። ትንሽ ቍጥቋጦ ዕንጨት የይፋት አባሎ ፍሬው ለቍስል የሚኾን።

                                               

የምድር እምቧይ

የዚህ ኪያር ፍሬው በጣም መርዛም ነው አይበላም። የምድር እምቧይ በውነት እምቧይ አይደለም፤ የኪያር ዘመድ ነው። የሮማይስጥ ስሙ Cucumis prophetarum ማለት "የነቢያት ኪያር" ሲሆን፣ ይህም ከአረብኛው "የኒቢዩ ኪያር" ወይም "የውሻዎች ኪያር" ከመባሉ ነው። ሌላ ተመሳሳይ የኪያር ወገን ዝርያ Cucumis ficifolius ደግሞ "የምድር እምቧይ" ተብሏል። ከዚህም በላይ የምድር ...

                                               

የእንቦጭ አረም

የእንቦጭ አረም በጣም አስቸጋሪ የሆነ፣ በውሃ ላይ የሚበቅል ወራሪ አረም ነው። በጣም ቶሎ ሊስፋፋ ይችላል። ይህ ማለት በየ፪ ሳምንት ውስጥ መጠኑ ሊደረብ ይችላል። ኩሬ ወይም ሃይቅ ሲሸፈን፣ ጸሓይን ወይም ሌሎችን አትክልት፣ አሦችን ይክለክላል፤ ለትንኝ እና ለብዙ ተላላፊ በሽቶች መኖሪያ ይሆናል። ከሌሎቹ በሽቶች በላይ አረሙ እከክ መፍጠር ይችላል። በመጀመርያ ለደቡብ አሜሪካ ኗሪ ነበር። ዛ ...

                                               

ጋጃ

በወፍራም እጅብታ እስከ 4 ሜትር ድረስ ይበቅላል። እጅብታው ባጋማሽ 70 ሰንቲ ሜትር ይደርሳል። ቅጠሎች 30-60 ሳንቲ ሜትር ረጅም፣ እስከ 3 ሳንቲ ሜትር ሰፊ፣ በለስላሳ ጽጉር ተሸፍነው፣ ባለ ልዩ ነጭ መሃል ጎድን ናቸው። አገዳዎችም ጉልበታም፣ በለስላሳ ጽጉር ተሸፈኑ። ሥሮቹ ከአፈር ገጽታ ሳይጠልቁ ከእጅብታው እስከ አንድ ሜትር ይርቃሉ። ዘሮቹ በጥጣማ V-ቅርጽ ባለ ጫፍ ይገኛሉ

                                               

ጓሳ

እስከ 10 ሜትር ድረስ የሚቆም ቀጭን ዛፍ ነው። ለቅርንጫፎቹ ረጅም፣ ቀጥ ያሉ ዐረንጓዴ እሾሆች በጥምዝምዝ አሉባቸው። ከእሾሆቹ መሠረት ጨለማ-አረንጓዴ ውሁድ ቅጠሎች ይበቅላሉ፣ ውሁዱም ቅጠል ከ፪ ቅጠሊቶች እየሆነ በቅርጽም ሆነ በስፋት ሊለያዩ ይችላሉ። ሽንሽን ግንዱ ግራጫማ-ቡኒ ሻካራ ልጥ አለው፤ ይህም በረገፈበት ቦታ ቢጫ-አረንጓዴ እራፊ ይኖረዋል። ህብረአበባው የጥቂት አበቦች ዘለላ ሲ ...

                                               

ጤና ኣዳም

በባህላዊ መድሃኒት፣ የጤና አዳም ቅጠል ጭማቂ በቡና ኢንፍሉዌንዛን ለማከም እንደሚረዳ ተዘግቧል። እንዲሁም የጤና አዳም ቅጠልና ፍሬ ማኘክ ለመጋኛ ወይም ለሆድ ቁርጠት ማስታገሻነት ያገለግላል። ቅጠሉና ፍሬው ከፌጦ ዘር ጋር ሲበላ ለሆድ ቁርጠት መፍትሄ ይሆናል። ከፌጦ ዘርና ከጠጅ ሳር ሥር ጋር ተቀላቅሎ ደግሞ ለሆድ ቁርጠት፣ ወይም ለከብት ጎሎባ ይሠጣል። በተጨማሪም የጤና አዳም ቅጠልና ፍሬ ...

                                               

ፌጦ

ፌጦ ለተቀመመ ጻዕሙ አለም ዙሪያ በአበሳሰል ውስጥ ይወደዳል። አቶ ሲገንጣለር 1960 እ.ኤ.አ. ለፌጦ የሚከተሉት ጥቅሞች ዘግቧል፦ ዱቄቱም ከማር ተቀላቅሎ ለአሚባ በሽታ ይወሰዳል። ዱቄቱም ከፍትፍት ጋር ተቀላቅሎ ፌጦ ፍትፍት የተባለ ምግብ ይሠራል። ይህ በማለዳ እንደ ሞርሟሪ ይበላል። በበጌምድር ባሕል በዕንቁጣጣሽ ዋዜማ ይበላ ነበር። ባለፉት ዘመናት፣ ጦረኞች በሌሊት ብርድ ለመታገስ ለሙቀ ...

                                               

ቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ

የቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ አዲስ አበባ ላይ በ ፲፱፻፹፫ ዓ/ም የቅድስት ማርያም የቋንቋ ትምህርት ቤት በመባል የተመሠረተ የግል የትምህርት ተቋም ነው። ይኸው የቋንቋ ትምህርት ቤት የተማሪዎቹን የእንግሊዝኛቋንቋ ልምምድ እና ችሎታ በማዳበር የላቀ ሥራው ውጤቶች፣ በተመሠረተ በአራት ዓመት ውስጥ ተሻሽሎ የከተማዋ ዋና የቋንቋ ማዕከል ለመሆን በቅቷል። በ፲፱፻፺ ዓ/ም ላይ ድርጅቱ ዋና ...

                                               

ተስፋ ጎህ ኢትዮጵያ

ተስፋ ጎህ ኢትዮጵያ የኤች አይ ቪ በሽታን ለመከላከል እና ባለበት ደረጃ ለመግታት "ትዉልድ ይዳን በእኛ ይብቃ" በሚል ክቡር አላማ ተነሳስተው ዘውዱ ጌታቸው እና አሥር ከኤችአይቪ ቫይረስ ጋር የሚኖሩ ወገኖቻችን ሰኔ 1990 ዓ.ም የመሰረቱት ማህበር ነው። ይህ ማህበር ለትርፍ ያልቆመ፣ ከማንኛውም የፖለቲካና የሀይማኖት ወገንተኝነት ነፃ የሆነ ማህበር ነው። ተስፋ ጎህ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ...