ⓘ Free online encyclopedia. Did you know? page 10
                                               

ፍሬገ

ጎትሎብ ፍሬገ ጀርመናዊ ፈላስፋ፣ ስነ አምክንዮ ተመራማሪ፣ እና ሂሳብ አጥኝ ነበር። ፍሬገ ከጥንቱ ግሪካዊ አሪስጣጣሊስ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውን የአምክንዮ ትምህርት በሙሉ የለወጠና ፕሪዲኬት ካልኩሉስ የተባለውን የአምክንዮ ርዕዮት አለም ያበረከት ነው። በዚህ አዲሱ አምክንዮ ስርዓት የተወሰኑ አባባሎች እንዴት በአምክንዮ እንደሚፈቱና አንድን ማረጋገጫ በርግጥ ትክክል ነው የሚባልበትን ስልት ...

                                               

ኤሌክትሮመግነጢስ ጨረራ

በብርሃን ፍጥነት የሚጓዙ ሞገዶች ኤሌክትሮመግነጢስ ጨረራ ይሰኛሉ። እያንዳንዳቸው ሞገዶች እርስ በርሳቸው ቀጤ ነክ የሆኑና በአንድ ቅድሚያ የሚርገበገቡ የኤሌክትሪክ መስክ እና የመግነጢስ መስክ አላቸው። ሁለቱም መስኮች በተራቸው ሞገዶቹ ለሚጓዝበት አቅጣጫ ቀጤ ነክ ናቸው። የኤሌክትሮመግነጢስ ጨረራ በሚኖረው የሞገድ ድግግሞሽ ይከፈላል። ከዝቅተኛ ድግግሞሽ ተነስቶ ወደ ከፍተኛ ድግግሞሽ ሲዘረዘ ...

                                               

ብርሃን

ብርሃን ነገሮች በዓይን እንዲታዩ የሚያደርግ የተፈጥሮ ሞገድ ነው። የብርሃን ሞገድ ከኤሌክትሪክ እና ከመግነጢስ የተሰራ ስለሆነ ሞገዱ የ ኤሌክትሮመግነጢስ ጨረራ ይባላል። ይሁንና፣ የኤሌክትሮመግነጢስ ጨረራ ብርሃንን ብቻ ሳይሆን የብርሃንን ታናናሽና ታላላቅ ወንድሞች ሳይቀር ያፈልቃል። ከብርሃን ታናናሽ ወንድሞች፣ ሬዲዮ፣ ራዳር እና ታህታይ ቀይ ይገኙበታል። ታላላቅ ወንድሞቹ ቢባል፣ ላዕላይ ...

                                               

የብርሃን መጠላለፍ

የብርሃን መጠላለፍ እንደማንኛውም ሞገድ መጠላለፍ ነው እንጂ ልዩ አይደለም። ለምሳሌ አንድ የረጋ ውሃ ላይ ሁለት ልጆች የተለያየ ቦታ ላይ ጠጠር ቢጥሉ፣ ከጠጠሮቹ እየከበቡ የሚሰፉት ሞገዶች የሚሰሩት መጠላለፍ አንድ ቦታ በሃይል እንዲጎብጡ፣ ሌላ ቦታ እንዲያንሱ እያደረገ ለአይን የሚስብ የመጠላለፍ ቅርጾች በውሃው ገጽታ ላይ ይሰራሉ። ብርሃንም እንዲህ አይነት የመጠላለፍ ባህርይ ያሳያል። ጉዳ ...

                                               

የብርሃን ስብረት

የብርሃን ስብረት እምንለው የብርሃን ጨረር ካንድ ብርሃን አሳላፊ ወደ ሌላ አሳላፊ አካል ሲጓዝ የሚገጥመውን የመጉበጥ ሁናቴ የሚወክል ጽንስ ሃሳብ ነው። ይህ የመጉበጥ ሁናቴ በስኔል ህግ እንዲህ ሲባል በሒሳብ ቋንቋ ይገለጻል፦ n 1 sin ⁡ θ 1 = n 2 sin ⁡ θ 2. {\displaystyle n_{1}\sin \theta _{1}=n_{2}\sin \theta _{2}\.} እዚህ ላይ θ 1 ...

                                               

የብርሃን ነጸብራቅ

ብርሃን አንድ ቁስን ሲመታ የቁሱ አተሞች የተውሰነውን ብርሃን ውጠው የተቀረውን መልሰው በተለያየ አቅጣጫ ወደውጭ ይረጫሉ። ይህ ጉዳይ የብርሃን ነጸብራቅ ይሰኛል። ሆኖም ግን ገጽታቸው ልስልስ የሆኑ አካላት በሚያስነሱት የሞገድ መጠላለፍ ምክንያት አብዛኛው ጨረራ እርስ በርሱ ይጣፋል። በዚህ መጠፋፋት ወቅት ጸንቶ የሚቀረው ብርሃኑ በአረፈበት ማዕዘን ትክክል ያለው የሞገድ ስብስብ ብቻ ነው። በ ...

                                               

የብርሃን ዋለታ

የብርሃን ሞገድ ልከ አንድን ገመደ ወደላይ ወደታች ስናደርግ እንደምናገኘው ሞገድ ነው። ማለት የሞገዱ ጉዞ ወደፊት ሲሆን ሞገዱ የሚርገበገበው ወደ ላይ-ወደ ታች ነው። ስለሆነም ሞገዱ ወደፊት ሚጓዝ ቢሆንም የሚርገገበው ግን አቅጣጫ ሊቀይር ይችላል፡ ለምሳሌ ወደ ጎንና ወደ ጎን ሊርገበገብ ይችላል። ይህ የብርሃን ባህርይ መዋለታ ይባላል። ጉዳዩን በገሃዱ አለም ማየት ይቻላል። ብዙ የጸሐይ መነ ...

                                               

ኮረንቲ

ኮረንቲ ወይም ኤሌክትሪክ የሚባለው በኮረንቲ አስተላላፊ ቁስ አካል ውስጥ የሚገኙ ኤሌክትሮኖች በኤሌክትሪካዊ ሙል ተሞልተው ወይም በመግነጢሳዊ ኃይል ተገፍተው ካንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ሲንቀሳቀሱ ነው። ኮረንቲ እንግዲህ በተለያዩ ክስተቶች ዘንድ የመገኘት ባህርይ አለው።በስታቲክ ኤሌክትሪሲቲ በመፋተግ፣በሙቀት ልዩነት፣ጨረራ፣ኬሚካላዊ አጸግብሮት፣ኬሚካላዊ ንትበት ለምሳሌ ያልን እንደሆን በመብረቅ ...

                                               

መጠነ እንቅፋት

የኤሌክትሪክ መጠነ እንቅፋት የሚባለው አንድ ኤሌክትሪክ አባል በውስጡ ሊያልፍ የሚሞክር የኤሌክትሪክ ጅረትን የሚያደናቅፍበት መጠን ልኬት ነው። የኤሌክትሪክ መጠነ እንቅፋት ከሰበቃ ጋር ተመሳሳይ ባህርይ አለው። የኤሌክትሪክ መጠነ እንቅፋት የተደረሰበት በ1819 ዓ፣ም በጆርጅ ኦም ሲሆን፤ በዚህ ሰው ጥናት መሰረት የአንድ ነገር ኤሌክትሪካዊ መጠነ እንቅፋት በዚያ ነገር ላይ ያለ የቮልቴጅ ለ ...

                                               

ነፋሳዊ ኤሌክትሪክ ማመንጫ

ንፋሳዊ ኤሌክትሪክ ማመንጫ የንፋስን አቅም ወደ ኤሌክትሪክ አቅም የሚቀይር መሳሪያ ነው። ኤሌክትሪክ ማመንጫው አብዛኛውን ጊዜ ከ4 አበይት ክፍሎች ይዋቀራል። እኒህም #ዘዋሪ ላባ፣ #ጄኔሬተር ቆጥ፣ #መቆጣጠሪያ ስርዓት እና #የነፋሳዊ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ሰገነት ናቸው ። ዘዋሪው ላባ በንፋስ ጉልበት ሲሽከረክረ፣ እርሱ በተራው ዳይናሞውን በመዘወር ኤሌክትሪክ እንዲመነጭ ያደርጋል። የመቆጣጠሪያ ...

                                               

አቃቢነት

አቃቢነት ወይንም ካፓሲታንስ የሚለካው የአንድ ቁስን የኤሌክትሪክ ሙላት የማጠራቀም ችሎታ ነው። የበለጠ ትክክል ለመናገር አንድ ቁስ ላይ በሚያርፍ የቮልቴጅ ጫና ምክንያት ያ ዕቃ ሊያጠራቅመው የሚችለው የኤሌክትሪክ ሙላት መጠን የዚያ ቁስ አቃቢነት ይባላል። ስለሆነም አቃቢነት በአንድ ቁስ ውስጥ የሚገኝ የኤሌክትሪክ ሙላት እዚያ ዕቃ ላይ በተጫን ቮልቴጅ ሲካፈል ይገኛል፡፡ በሒሳብ ቋንቋ፦ C ...

                                               

ሊኑክስ

ሊኑክስ የሚባለው ቴክኖሎጂ የኮምፒውተር ዉስጠ-አካልን የሚቆጣጠር ዩኒክስን የሚመስል ሶፍትዌር ነው። ነገር ግን ብዙ ጊዜ ሰዎች ሊኒክስ ብለው የሚጠሩት ከዩኒክስ የሚባለው ኦፕሬቲንግ ሲስተም የተወለዱትን ኦፕሬቲንግ ሲስተሞችን ነው። ሊኑክስ በነፃ ከሚገኙ ሶፍትዌሮች ግንባር ቀደም ተብሎ ሊጠቀስ የሚችል ነው። የምንጭ ኮድንም ማለትም ሊኑክስ የተጻፈበትን ኮድ ተጠቃሚው ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ሊ ...

                                               

ሞዴት

ሞዴት የግዕዝ ቀለም ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኮምፕዩተር የገባበት ቃላት ማተሚያ ነው። ስሙን ያገኘው ሞደርን ኢትዮጵያ የሚሉትን ቃላት ወደ ሞዴት በማሳጠር ነው። በእጅ ጽሑፍና ማተሚያ ቤቶች ብቻ ይታተም የነበረው የግዕዝ ፊደል በማይክሮሶፍት ዲስክ ኦፐሬቲንግ ሥርዓት ለገበያ ዩናይትድ እስቴትስ ውስጥ ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ በኣደረጉት በዶ/ር ኣበራ ሞላ በ፲፱፻፹ ዓ.ም. ቀረበ። ይህ የኢትዮጵያ ኮ ...

                                               

ቤሲክ (BASIC)

በኮምፒውተር ፍርገማ ዘርፍ ቤሲክ የሚሰኘው የከፍተኛ ደረጃ ፍርገማ ቋንቋዎችን የሚያዝል ቤተሰብ ነው። የቃሉም ትርጉም መሰረታዊ ወይም ቀላል ቢሆን የተሰየመው ግን ከእንግሊዝኛው B eginners A ll-purpose S ymbolic I nstruction C ode አኅጽሮተ ቃል ነበረ። ይህም ማለት "የጀማሪዎች ሙሉ-ምክንያት ምልክታዊ ትምህርታዊ ኮድ" የሚያሕል ነው። ቤሲክ መጀመሪያ በ1963 ...

                                               

ኮምፒዩተር

ኮምፕዩተር ማለት ማንኛውንም ኢንፎርሜሽን ፕሮሰስ የሚያደርግ ማሽን ነው። ይህንም የሚያደርገው በተርታ የተቀመጡ ትዕዛዞች በመፈጸም ነው። ለብዙ ሰዎች ኮምፒዩተር ሲባል ዐዕምሯቸው ላይ የሚመጣው የግል ኮምፒዩተር ነው። ነገር ግን ኮምፒዩተር ሲባል በጣም ብዙ ነገሮችን ያጠቃልላል። ላፕቶፕ ፣ ዴስክቶፕ ፣ ማይክሮ-ኮምፒዩተር ፣ ሱፐር-ኮምፒዩተር ፣ ካልኩሌተር ፣ዲጂታል ካሜራ እና ሌሎችንም ያጠቃልላል።

                                               

ጃቫ

ለኢንዶነዥያዊው ደሴት፣ ጃዋን ይዩ ። ጃቫ ስነ ፍርገማ በቅርብ ታዋቂነትንና ተቃባይነትን እያገኘ ከመጡ ፍርገማ ቋንቋዎች አንዱ ነው። ጃቫ ተመራጭ ካደረጉት ዋና ባሀሪዎቹ አንዱ በ ፕላትፎርም አለመወሰኑ ነው። ይሀም ማለት በ ጃቫ የተጻፈ ትግበራ የ ጃቫ ቨርቹአል ማሽን ባለበት ሁሉ መሮጥ መቻሉ ነው። ስለዚህ በ ጃቫ ስራአት የሚጻፍ ኮድ በመጀመሪያ ኮምፓይል ከተደረገ በኋላ ኮምፓይለሩ አዲስ ...

                                               

ግዕዝኤዲት

ነፃ የአማርኛ መክተቢያ የማንንም ፈቃድና ዕርዳታ ሳይጠየቅ ግዕዝን በዊንዶውስ እና ማክ ኮምፕዩተሮች መክተብ ያስችላል። ለምሳሌ ያህል ድረ ገጽ ሄዶ "ግዕዝኤዲት" የሚለውን ቃል ከትቦና ቀድቶ ኮፒ ቃሉን የውክፔዲያ መፈለጊያ ውስጥ በመለጠፍ Paste በዓማርኛ መፈለግ Search ይቻላል። ኣንድ ሌላ ቦታ የተጻፈ የዓማርኛ ጽሑፍ ኮፒ ኣድርጎ የግዕዝኤዲት መክተቢያ ገጽ ላይ በመለጠፍ ጽሑፉን ማረ ...

                                               

የሰው ልጅ

የሠው ልጅ ወይም በአጭሩ ሰው በዝርያ ምደባ ሳይንስ መጠሪያው Homo sapiens እየተባለ የሚጠራው ዘር ሲሆን ከታላቁ የሰብአስትኔ ዘር በ Hominidae ከሚገኙት Homo የሚባሉ ባለ ሁለት እግር ዝርያዎች ንዑስ ቤተሰብ በህይወት የቀረ ወይንም ያልጠፋ ምድርንም ለመግዛት የተዘጋጀው ብቸኛው ዝርያ ነው። ነገር ግን ሠው የሚለው ቃል ለማንኛውም በ Homo ውስጥ ለሚገኝ ዝርያ መጠሪያ ነው።

                                               

የተፈጥሮ ጭማሪ

የተፈጥሮ ጭማሪ በሰው ልጅ ጥናት በኩል ከአንድ አገር ጥሬ ልደት መጠን ቁጥር የዚያው አገር ጥሬ ዕረፍት መጠን ሲቀነስ የሚገኘው የሕዝቡ ጭማሪ መጠን ነው። ይህ መጠን ግን "የተፈጥሮ" በመባሉ የሰው ልጅ ፍልሰቶች ቸል ይላል። የጥሬ ዕረፍት መጠን ከጥሬ ልደት መጠን ይልቅ ሲበዛ፣ ጭማሪ ሳይሆን የተፈጥሮ ቅነሳ አለ። አሁን በተለይ በምሥራቅ አውሮጳና በጃፓን ውስጥ ብዙ ልደቶች ስለሌሉ የተፈጥ ...

                                               

እሳት

እሳት ብርሃንንና ሙቀት የሚሰጥ የጥንተ ንጥሮች አፀግብሮት ነው፣ የውክሰዳ ምሳሌ ነው። የሚነካቸውን ነዳጅ ነገሮች ሁሉን ይበላል፣ ጢስንም ያወጣል፣ አመድ ወይም ቀላጭ ይተርፋል። አስፈላጊ የሆኑት ነገሮች ኦክሲጅን፣ ነዳጅና ሙቀት በሚፈለገው መጠን አንድላይ ሲጋጥሙ፣ እሳት ይከሠታል። የራሱን ሙቀት ከዚያ ይፈጥራል፣ ኦክሲጅን ወይም ነዳጅ እስከሚያልቅ ድረስ ይቃጠላል።

                                               

ቁልፍ

ደግሞ ይዩ ያለቁልፍ ቁልፍ መክፈት ቁልፍ ከእናት ቁልፉ ውስጥ ገብቶ በመሽከርከር እናት ቁልፉን የሚከፍት ማሽን ነው። ከታሪክ አንጻር ቴዎዶር ወልደ ሳሞስ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ6ኛው ክፍለ ዘመን ቁልፍን እንደፈለሰፈ ይጠቀሳል። ቁልፍ የተፈለሰፈ በአቃቂ ብረታብረት ሲሆን የፈለሰፋት ሰዉ ስም ደግሞ አስራአለቃ ጫንጮ ቢሪሞስ አቁ ሲሆኑ የፈለሰፋበት ምክንያት ደግሞ አቧራና የተለያዩ ጠጠሮች ...

                                               

ዓለም ንግድ ሕንጻ

የዓለም ንግድ ሕንጻ በኒው ዮርክ ከተማ የነበሩ ሰባት ሕንጻዎች ነው። ሕንጻዎቹን የነደፈው ጃፓናዊ-አሜሪካዊው ሚኖሩ ያማሳኪ ነው። 110 ፎቅ ላላቸው መንታ ሕንጻዎቹ ይታወቃል። የየካቲት 19 ቀን 1985 ዓ.ም. ጥቃት ቢቋቋምም በመስከረም 1 ቀን 1994 በደረሰበት ጥቃት ፈርሷል።

                                               

ኤሌክትሪክ ዑደት

የ ኤሌክትሪክ ዑደት ማለቱ የኤሌክትሪክ አባላት እርስ በርስ ግንኙነት ነው። የኤሌክትሪክ አባላት ኤሌክትሪክ ተቃዋሚን፣ ኤሌክትሪክ ቃቤን፣ ኤሌክትሪክ አቃቤን፣ ቮልቴጅ ምንጭን፣ ኤሌክትሪክ ጅረት ምንጭን ማብሪያ ማጥፊያንና ሽቦን ይጠቀልላል። በኤሌክትሪክ መረብና በኤሌክትሪክ ዑደት ያለው ልዩነት የኤሌክትሪክ ዑደት ሽቦወች የተዘጋ መንገድ ሲሰሩ የኤሌክትሪክ መረብ ግን ክፍት ሊሆን ይችላል። በ ...

                                               

የጂኦሜትሪክ ዝርዝር

በሒሳብ ጥናት ውስጥ አንድ የቁጥሮች ዝርዝር በቀዳሚና ተከታይ አባሎቹ መካከል ቋሚ ውድር ካለው ያ ዝርዝር የጆሜትሪ ዝርዝር ይባላል። ምሳሌ ፦ 1 2 + 1 4 + 1 8 + 1 16 + ⋯ {\displaystyle {\frac {1}{2}}\,+\,{\frac {1}{4}}\,+\,{\frac {1}{8}}\,+\,{\frac {1}{16}}\,+\,\cdots } እያንዳንዱን ቀጣይ ቁጥር ከፊት ያለውን ቁጥር ...

                                               

የጆሜትሪክ ድርድር

የጂኦሜትሪክ ድርድር የምንለው የቁጥሮች ድርድር ሲሆን እኒህ የተሰለፉ ቁጥሮች የኋለኛው የከፊተኛው ቋሚ ብዜት ውጤት ሲሆን ነው። ይህ ቋሚ ቁጥር የጋራ ውድር በመባል ይታወዋል። ለምሳሌ ይህን ድርድር እንመልከት 2, 6, 18, 54.፣ እያንዳንዱ ተከታይ ቁጥር የፊተኛውን ቁጥር በጋራ ውድሩ ስናበዛ እናገኛለን፣ ስለዚህም የጅኦሜትሪክ ድርድር ይሰኛል። በተመሳሳይ ሁኔታ 10, 5, 2.5, 1.2 ...

                                               

የፎሪየር ሽግግር

የ ፎሪየር ሽግግር አንድን የአቅጣጫ ቁጥር ፈንክሽን ወደ ሌላ አቅጣጫ ቁጥርፈንክሽን ይሚያሻግር የሂሳብ መሳሪያ ነው። በተለይ በሲግናል ዝግጅት ጥናት ፣ የመጀመሪያው ፈንክሽን ግቤት ጊዜ ሲሆን የጊዜ ግዛት ውስጥ ያለ ፈንክሽን ያስብለዋል። የፎሪየር ሽግግሩ እንግዲህ ይህን በጊዜ ግዛት ውስጥ ያለ ፈንክሽን ወደ ድግግሞሽ ግዛት ውስጥ ወዳለ ፈንክሽን በማሻገር አዲሱ ፈንክሽን ግቤቱ ድግግሞሽ እ ...

                                               

የፎሪየር ዝርዝር

በቀላሉ ለመመርምር የማይመቹ ተደጋጋሚ የሆኑ ፈንክሽኖችን ወይም ደግሞ መልዕክቶችን ወደ ቀላል የሳይን እና ኮሳይን ተርገብጋቢ ድምሮች የምንቀይርበት መንገድ ፎሪየር ዝርዝር ይባላል። እነዚህ ድርድሮች ለአለም የተበርከቱት በፈረንሳዊው ዮሴፍ ፎርየር ሲሆን የፈጠራው ምክንያትም "ሙቀት በብረት ምጣድ እንዴት ይተላለፋል?" ብሎ ለጠየቀው ጥያቄ የፎርየር ዝርዝር መልሱን ስላስገኘለት ነበር። ፎሪየር ...

                                               

የዕውነታ ሠንጠረዥ

የዕውነታ ሠንጠረዥ በሥነ አምክንዮ እና ሥነ ኮምፒዩተር ጥናት ከፍተኛ ተጠቃሚነት ያለው የሒሳብ ሠንጠረዥ ነው። ተግባሩም አንድ የአምክንዮ ፈሊጥ ይሰጥና በውስጡ አቅፎ የያዛቸው የአምክንዮ አረፍተነገሮች ግቤት ዋጋዎች ሲቀያየሩ ሊይዟቸው ለሚችሏቸው ማናቸውም ዋጋወች የአጠቃላይ ፈሊጡ ውጤት ምን እንደሆን በአንድ ለማስላት ነው። እያንዳንዱ የሠንጠረዡ ዐምድ የአምክንዮ ፈሊጡ ግቤቶች ሊይዙት የሚ ...

                                               

የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት

የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት የሚለው የኢትዮጵያ "ሕገ ሕዝብ" ተብሎ ቢጠራ መንግስት እሚለውን በሕዝብ በመተካት አመሰራረቱ አሁን ባለው ተኮርጆ የተጻፈ ከምእራባውያን የተቀዳ በተግባር የማይፈጸም በመሆኑ፡ ለወደፊቱ የሀገሪቱ መመርያ ከሕዝቡ የወጣ ከያንዳንዱ ግዛት ከምክትል ወረዳ ጀምሮ እስከ ክፍለ ሀገር፡ ያለባቸውን ችግርና መፍትሔ የሚመሩበት ሕግ በማውጣት፡ ባጠቃላይ ሁሉንም ጎሳዎች ሊያስተናግ ...

                                               

ፍትሐ ነገሥት

ፍትሐ ነገሥት በ1240 አካባቢ በግብጽ አገር ቅብጡ አቡል ፋዳዒል እብን አል-አሣል በአረብኛ የጻፉት ሕገ መንግሥት ነው። እብን አል-አሣል ሕጎቹን የወሰዱት በከፊል ከሃዋርያት ጽህፈቶችና በከፊል ደግሞ ከድሮ ቢዛንታይን ነገስታት ሕጎች ነበር። አንደኛው ክፍል ስለ ቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች ሲሆን የቤተክርስቲያን ስነሥርዐትና ምስጢራትን ይገልጻል። የተለቀሙት መጻሕፍት መጽሐፍ ቅዱስ የአበው ለም ...

                                               

ጋሞጐፋ ዞን

አርባ ምንጭ ከተማ ከ1955 እስከ 1993 ዓ.ም ድረስ የጋሞ ጐፋ ጠቅላይ ግዛት፣ የሰሜን ኦሞ አስተዳደር አካባቢና ከዚያም የሰሜን ኦሞ ርዕሰ ከተማ በመሆን ለቀድሞዎቹ የጋሞ፣ የጐፋ፣ የጋርዱላና ሐመር ባኮ አውራጃዎች ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ማዕከል ሆና ያገለገለች ስትሆን ከ1993 ዓ.ም ወዲህ ባሉት ዓመታት ደግሞ አስራ አምስት ወረዳዎችንና ሁለት የከተማ አስተዳደሮችን አቅፎ ለያ ...

                                               

የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ

የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ በኢትዮጵያ መንግሥት በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ስር የሚገኝ ኤጀንሲ ወይም ባለስልጣን ሲሆን ተልዕኮው ለኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ዕድገት አሰሳ የሚያገለግሉ የሕዝብ ቆጠራ፣ የዋጋ መረጃ ማሰባሰብ፣ የቤተሰብ ፍጆታና ወጪን ማጥናትና ሌሎች ተመሳሳይ ተግባሮችን ማከናወን ነው። በተጨማሪም ኤጀንሲው በዘርፉ ባለሙያዎችን የማሰልጠን ኃላፊነት አለበት። በአሁኑ ጊዜ ...

                                               

የሳይንስና ቴክኖሎጂ መረጃ ማዕከል (ኢትዮጵያ)

የሳይንስና ቴክኖሎጂ መረጃ ማዕከል ፣ ኢትዮጵያ የሳይንስና ቴክኖሎጂ መረጃዎችን የመሰብሰብ፣ የመምረጥ፣ የመተንተንና እሴት አክሎ የማሰራጨት ኃላፊነት የተጣለበት የመንግስት ድርጅት ነው። ኢሳይንስ በእያንዳንዱ የሳይንሳዊ ጥናትና ምርምር ገፅታ ላይ ትልቅ ሚና የሚጫወት መስክ ነው። ለማንኛውም አይነት ፈር ቀዳጅ ለሆኑ ሳይንሳዊ ጥናቶችና ግኝቶች ከመጀመሪያ ፅንሰ ሃሳብ ጀምሮ የተለያዩ በስርዓት ...

                                               

የትግራይ ሽግግር መንግሥት

የትግራይ ሽግግር መንግስት በትግራይ ክልል ስልጣን ላይ በነበረበት ጊዜ በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ እና በፌደራል መንግሥት መካከል በተፈጠረው ግጭት ምክኒያት በኢትዮጵያ ፌደሬሽን ም / ቤት በይፋ የታወጀ አስተዳደር ነው። እንደ 28 ህዳር 2020 ፣ ዶ/ር ሙሉ ነጋ የሚመራው አስተዳደር በክልል እና በዞን ደረጃ አዳዲስ አመራሮችን በመምረጥ የወረዳና የቀበሌ አስተዳደሮችን በመጠበቅ የህዝ ...

                                               

የኢትዮጵያ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችና ኤጀንሲዎች

የኢትዮጵያ መንግሥት የሥራ አስፈፃሚ አካል በሚከተሉት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች እና ተጠሪ አካላት የተዋቀረ ነው። የትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስቴር መገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ የመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የኢትዮጵያ ሲቪል ኤቪዬሽን ባለሥልጣን የህዝብ ድርጅቶች ባላደራ ቦርድ የመንግስት ቤቶች ሽያጭ ጽ/ቤት የኢትዮጵያ ካርታ ሥራ ኤ ...

                                               

የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን

የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ውስጥ የሥነምግባር መከታተያ ኮሚሽን ነው። የኮሚሽኑ ተጠሪነት በቀጥታ ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ነው። የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ክቡር አቶ ዓሊ ሱለይማን ሲሆኑ ም/ኮሚሽነሩ ደግሞ ክቡር አቶ ወዶ አጦ ናቸው። ኮሚሽኑ "ሥነምግባር" የተባለ በዓመት አራት ጊዜ የሚታተም መፅሄት እና "መስታወት" የተባለ በዓመት ሁለት ጊዜ የሚ ...

                                               

ልብወለድ ታሪክ ጦቢያ

ጦቢያ ወይም ልብወለድ ታሪክ ጦቢያ በአፈወርቅ ገብረ እየሱስ በ፲፱፻ ዓ.ም. በሮማ የታተመ ሲሆን 90 ገጾች አሉት። በኢትዮጵያ የሥነ ፅሑፍ ታሪክ የመጀመሪያ ልብወለድ መፅሐፍ ለመሆኑ የሚነገርለት ይህ መጽሐፍ በወቅቱ ተነስቶ የነበረውን የአረማውያንንና የክርስቲያኖችን ጦርነት ይተርካል። ደራሲው በመፅሐፉ ውስጥ ስለተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ማለትም ስለደግነትና ክፋት፣ ስለሀይማኖትና ፍቅር በሰ ...

                                               

መንግሥትና የሕዝብ አስተዳደር

መንግሥትና የሕዝብ አስተዳደር በቢትወደድ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ ተጽፎ በ፲፱፻፲፮ ዓ.ም. የታተመ መጽሐፍ ነው። ይህ መጽሐፍ ከመስራት የተነሳ የሰው ልጅ እንዴት ከተፈጥሮ ጥገኝነት ተላቅቆ ከኋላ ቀር አኗኗር ወደ ተሻለ ሕይወት እንደሚለወጥ የሚያስረዳ ሲሆን የዓለም ሕዝቦች የዕውቀታቸውና የሀብታቸው ደረጃ ከፍና ዝቅ ያለ መሆኑ ምክንያቱ ከጦርነት የተነሳ ነው ይላል። ጦርነቱንም የሚነሱ ነገሥ ...

                                               

ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት

ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ታኅሣሥ ፳፫ ቀን ፲፱፻፲፯ ዓ/ም በአንዲት" ብርሃንና ሰላም” በተሰኘች አነስተኛ ጋዜጣ ሕትመት ሥራውን ጀመረ። በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው መጻሕፍት ፣ ጋዜጦች ፣ መጽሔቶችና የምስጢራዊ ሕትመት ሥራዎች በተለያዩ ቋንቋዎች እያተመ ይገኛል። ማተሚያ ቤቱ በርካታ የመንግሥት እና የግል ጋዜጦችን የሚያትም ሲሆን ፥ በተጨማሪም በየዓመቱ በርካታ የፈተና ሥራዎችን ...

                                               

አዲስ ዘመን (ጋዜጣ)

አዲስ ዘመን ጋዜጣ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ሥር የምተዳደር ነዉ ፣ በየዕለቱ የሚታተም ብሔራዊ ጋዜጣ ነው። አዲስ ዘመን በአሁኑ ጊዜ ከ ፵ በላይ ጋዜጠኞች ያሉት ሲሆን የጋዜጣው መጠን ‘መካከለኛ’ /በርሊነር) ሆኖ የፊትና ጀርባ ገፆችን በሙሉ ቀለም ያቀርባል። ይህ ጋዜጣ የአገሪቱ ብቸኛው ዕለታዊ ጋዜጣ ሲሆን የመንግሥትን አቋም የሚያንፀባርቅ እና በየዕለቱ የተለያዩ ልማታዊ ዜናዎችን ይዞ ይወጣል።

                                               

እንደወጣች ቀረች

"እንደወጣች ቀረች" 189 ገጾች ያሉትና በ፲፱፻፵፮ ዓ.ም. የተፃፈ ሲሆን በውስጡም ከ፲፱፻፳፰ እስከ ፲፱፻፴፫ ዓ.ም. በኢትዮጵያ ላይ የተፈፀመው የኢጣልያ ወረራና በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ያመጣው አያሌ ቀውሶች በሰፊው ያትታል። በተለይም በህዝቡ መንፈስ ላይ፣ በአገሪቱ ልማድና የኑሮ ባህል ላይ በአጠቃላይ በማህበራዊ ህይወቱ ላይ ታላቅ ቀውስን ያስከተለ መሆኑንም ያብራራል። የነበረውን የጦርነት ...

                                               

የኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር

የኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር ፋሺስት ኢጣሊያ በ፲፱፻፳፱ ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ያደረገውን ጭፍጨፋ ፳፫ኛው ዓመት በሚታሰብበት የካቲት ፲፪ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ.ም.፤ የሀገር ፍቅር ቴአትር አዳራሽ በነበረው ኪነ-ጥበባዊ መሰናዶ ተመሠረተ።

                                               

የዓመፅ ኑዛዜ

የዓመፅ ኑዛዜ በደራሲ አቤ ጉበኛ በ፲፱፻፶፭ ዓ.ም. የተፃፈ ሲሆን 85 ገጾች አሉት። በመፅሐፉም የተገለፀው ታሪክ ሰፊ ሆኖ ደራሲው ባጭሩ ለመግለፅ ቀላልና አጭር በሆነ ዘዴ የፃፈው ነው። ታሪኩም አንድ ራሱን ወዳድ ሰው ታሪክ በኑዛዜ መልክ የሚገለፅበት ሲሆን፣ በአንድ የገጠር መንደር ውስጥ ጥሩ ኑሮ አላቸው ከሚባሉ ቤተሰቦች ውስጥ የወጣው ባለታሪክ ቤተሰቦቹን በድንገተኛ ህመምወያጣል። በድን ...

                                               

ዴርቶጋዳ

ዴርቶጋዳ በ ፪፼፩ዓ.ም.በደራሲ ይስማዕከ ወርቁ የቀረበ ልብ-ወለድ ሲሆን ሳይንሳዊ ዘዉግ ያለዉ የኢትዮጵያን አንድነት የሚስብክ መጽሀፍ ነዉ።መጽሀፉ ለዶ/ር ኢ/ር ቅጣዉ እጅጉ ማስታወሻነት ተበርክቷል።ከብዙ በጥቂቱ ገፀ-ባህሪያቱ ሻጊዝ እጅጉ፣ሚራዥ፣ሲፓራ፣ሜሮዳ፣ዣንጊዳ፣ጌራ፣አባ ፊንህሰ፣አባ ዠንበሩ.። ዴርቶጋዳን የኢትዮጵያን ስነ-ጽሁፍ አንድ እርምጃ ወደፊት ያራመደ ብለዉ ብዙ የኢትዮጵያ ሙህ ...

                                               

ሀብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴ

ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴ ዓርብ ታኅሣሥ ፫ ቀን ፲፱፻፲፱ ዓ.ም. አርፈው፣ በአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ተቀበሩ፡፡ በምክር አዋቂነትና በአስተዳደር ፈሊጥ የተመሰገኑ ነበሩ፡፡ ለጃንሆይ አፄ ምኒልክ ታማኝ አሽከር ነበሩና ዕለተ ሞታቸው ከጃንሆይ ዕለተ ሞት ጋራ በትክክል ስለተጋጠመ፣ ሰው ሁሉ እያደነቀ ተናገረ፡፡ አፄ ምኒልክ የሞቱት ዓርብ ታኅሣሥ ፫ ቀን ፲፱፻፮ ዓ.ም. ነበር፡፡ ...

                                               

ሃይሉ ሻውል

ሃይሉ ሻውል የምህንድስና ባለሙያ ናቸው። በፖለቲካ ተሳትፏቸው የመኢአድ አመራርና የቅንጅት ሊቅምንበር በመሆን አገልግለዋል። ቅንጅት ከፈረሰ በኋላ ግን፣ የፖለቲካ ተሳትፏቸውም ቀንሷል። ደሞክራሲ ናፋቂ ነን ይበሉ እንጂ ፊውዳላዊ ዘይቤ እንዳላቸው ይታማሉ።

                                               

ራስ መኮንን

ልዑል ራስ መኮንን ወልደሚካኤል የሸዋ ንጉሥ የነበሩት የሣህለ ሥላሴ ልጅ የልዕልት ተናኘወርቅ እና የደጃዝማች ወልደሚካኤል ልጅ ናቸው። ግንቦት ፩ ቀን ፲፰፻፵፬ ዓ.ም ጎላ ወረዳ ደረፎ ማርያም በሚባል ሥፍራ ተወልደው፤ እስከ ፲፬ ዓመት ዕድሜያቸው ከአባታቸው ጋር ከኖሩ በኋላ ያጐታቸው የንጉሥ ኃይለ መለኮት ልጅ ዳግማዊ ምኒልክ ገና የሸዋ ንጉሥ እንደነበሩ፡ ወደርሳቸው ቤተ መንግሥት መጥተው፡ ...

                                               

ቆምጬ አምባው

እዚህ የጎጃም ክፍለ ሀገር የአንድ ወረዳ ገዢ ነበሩ ። ቆምጬ አስተዳዳሪ ሳሉ የአንበሳ ሰል አሰርተው ከግርጌው "ጎጃም አንበሳ ነው" የሚል ጽሁፍ አሰፈሩበት ። ህዝቡም በዚህ ተደስቶ ሲኖር ሳለ ገበሬው ግብር በጊዜ አላስገባ ብሎ አስቸገራቸው ። ይህእኔ ቆምጬ ገበሬውን ሰብስበው "አሁን ይሄን አምበሳ ላም ላድርገው?" በማለት ግዳጁን እንዲወጣ አደረጉት ይባላል ። አዎን፣ በቆምጬ ስም የሚነገ ...

                                               

ቆምጬ ኣምብው

ቆምጬ አምባው በደርግ ጊዜ የቢቡኝ ወረዳ አስተዳዳሪ የነበሩ ሰው ናቸው ። የቆምጬ አምባው- ቃለ-ምልልስ በአበባየሁ ገበያው24 December 2014 at 14:25 የሶሻሊዝምን ርዕዮተ ዓለም በ1960ዎቹ ማብቂያ ላይ በአገራችን ያስተዋወቁት የደርግ ባለስልጣናት ሶሻሊዝምን የተረዱት የ70 ዓመቱ አዛውንት የጐጃሙ ቆምጬ አምባው በተረዱት መንገድ ቢሆን ኖሮ የኢትዮጵያ ታሪክ አሁን ከምናየው ፍፁ ...

                                               

ብርሃኑ ነጋ

ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ 1958 እ.ኤ.አ. በደብረ ዘይት ከተማ ተወለዱ። እድሜያቸውም 17 ዓመት እንደሞላ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የከፍተኛ ትምህርት መከታተል ጀመሩ። በመጀመሪያ ዓመት የዩኒቨርስቲ ቆይታቸው በወቅቱ ከነበሩ ተማሪዎች ጋር በመሆን ዲሞክራሲና የስብኣዊ መብት ይከበር ሲሉ፡ ይታገሉ ከነበሩ ወጣት የአብዮቱ የበኩር ልጆች ጋር ትግላቸውን ጀመሩ። የኢህአፓ ታጋይ ሆነው ሜዳ ገቡ። ኢህአ ...